የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መኮነን ሜጄ አበበ ተ/ ኃይማኖት ኢትዮኤርትራን በሚመለከት ያነሱት ሃሳብ በሳል ዕይታ ነው።

 

የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መኮነን ሜጄ አበበ ተ/ ኃይማኖት ያነሱት ሃሳብ በሳል ዕይታ ነው። 
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
ማህበረ ቅንነት እንዴት አደራችሁልኝ? እምዬ ኢትዮጵያስ? አባ ቅንዬ አማራስ እንዴት ናችሁ።
ከሪፖርተር ያገኜሁት የህወሃት መራሹ የኢህአዴጉ መኮነን ሜ/ጄ አበበ ተ/ ኃይማኖት ብሄራዊ፤ አህጉራዊ፤ ግሎባል ሁኔታወችን ያገናዘበ #በሳል ዕይታ በሚመለከት በዝምታ ባጅቼ፦ ግን እኔ አስቀድሜ የፃፍኩበት ቢሆንም፤ ሃሳቤን፦ ዕይታዬን የሚያጠናክርልኝ ስለሆነ ለሪፈረንስ ይረዳ ዘንድ ሙሉው መንፈስ ከሥር ይገኛል የሪፖርተር ዘገባ።
 
ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት በሳል ዕይታን፤ አስቀድመው ማዬት የሚችሉ ሊቃናት ያስፈልጓታል። ሰሚ ከተገኜ። እኔ በፌድራሉ እና በህወሃት ጦርነትም ጉዳቱን ከመዘገብ ውጪ ምንም አቅም አላዋጣሁም። ለአማራ ታጋዮችም አታበረታቱ፦ ትርፍ የለውም ብዬ ሞግቻለሁኝ። 
 
የሆነ ሆኖ ከዬትኛውም ዞግ ይሁን መንፈሱ ጤናማ፤ መጪውን ዕድል የሚወስኑ ጉዳዮችን በአሰተውሎት የሚያነብ፤ የሚተረጉም እንዲህ #የሚያመሳጥር አቅም ያለው ዕይታ #ሊደመጥ ይገባል። ለጤነኛ ኃሳብ ድንበር እና ወሰን አበጅቶ ዕቀባ ማድረግ ብልህነት አይደለም።
 
ከቀደመው አሳቤ እማክልበት እኔ ስፈራ የነበረው የኔቶ እና የራሽያ ፍጥጫን ነበር። ሦስተኛ ዓለም ጦርነትን አማጭ ይሆናል ብዬ ስሰጋ የነበርኩት። አሁን ተመስገን ነው። ፍጥጫው ቢኖርም ውጥረቱን ሊያመጣጥን ወይንም ሊመክት የሚችል አቅም አለ። #ትራንፒዝም። በሌላ በኩል ይህ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ መነሻው ወደብ፤ የባህር በር የይገባኛል ጉዳይ ይምሰል እንጂ፦ በውስጡ ብዙ የታመቁ፤ #የታመሉም ፍላጎቶች አሉበት። ይህን የአቶ ሽመልስ አብዲሳን ንግግር በስክነት መመርመር ይገባል። በሌላ በኩልም የኤርትራንም የግብጽን ህልም ከውስጥ አስቀምጦ መፈተሽ ይገባል።
 
ለጊዜው ይህን ልተወው እና የአፍሪካ ቀንዱ ፍጥጫ የሦስተኛው ዓለም ጦርነት አማጭ እንዳይሆን አሁንም እኔ ስጋት አለብኝ። ስለዚህ ነው ተው! እረፋ ብዬ ዝምታዬን ጥሼ የፃፍኩት። በብዙ ጉዳዮች ብተጋም፦ ውጤቱ ከንቱ ሆኖ ስለማገኜው ነው አብዝቼ በማድመጥ ላይ እማተኩረው። ማን ይታመናል - በኢትዮጵያ ፖለቲካ??? አናውቃቸው፤ አያውቁን። 
 
በሌላ በኩል #ከትራንፒዝም መምጣት ጋር ያለውን አዲስ የኃይል አሰላለፍ መንፈስም እንደ ጥርጥር ኩታ ሊሸበሽበው፤ ወይንም እንደ ብርንዶ ጎረድ ጎረድ ሊያደርገው ይችላል። ይህን መሰል ምስቅልቅል የፖለቲካ ሁኔታ ሲገጥም አደብ፤ ጥሞና፤ ትልቅ ጆሮ፤ የተረጋጋ ህሊና፤ ባህራዊ ልቦና ይጠይቃል። 
 
በዓለም ከሚገጥሙ የተፈጥሮ አደጋወች በላይ የጦርነት ባህሬ ተለዋዋጭ በመሆኑ ሁልጊዜም ያሰጋኛል። በጦርነት ቀጠና ውስጥም ስለአደኩኝ መከራውን በእኔም በቤተሰቤ ላይ ያመጣውን አሳር ሕይወቱን ስለማውቀው የጦርነት ፍፁም ደጋፊ ልሆን አልችልም።
 
ጦርነቱ ህገወጥ ይሁን ህጋዊ ጦርነት፤ #ፍትኃዊ ይሁን #ኢ - ፍትኃዊ ጦርነት አዲሱ ትውልድ እነደ ዘመኑ ባለቤትነቱ ትውልዱ ሊያስተናግደው አይገባም የሚል ጽኑ አቋም ነው ያለኝ። እደጃፋ ድረስ ለሄደ አጥቂ ግን እራስን ከጥቃት መከላከል #ወንገላዊም ነው። 
 
የቅዱስ ወንጌል ታሪክ እኮ "#ተጋድሎ" ነው። "ተጋድሎ" እራሱ ቃሉ የወንጌል ነው። ቃለ ሕይወት ነው። የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ሲነሳ በስፋት ጽፌበታለሁኝ። ደጉ ሳተናው ድህረገጽም ፈቅዶ አትሞልኛል። ከበቡሽ ብሎጌ ላይም አለ። 
 
#በሌላ በኩል ደግሞ ……… #አቅላይነት #ዊዝደም የራቀው ምልከታ! #የአደጋ ምልክትም ነው - ለእኔ። 
 
በዬትኛውም የፖለቲካ መስመር፤ የማህበራዊ ህይወት፤ ኃይማኖታዊ ጉዞ፤ ማህበራዊ ፍልስፍና ጠሚር አብይ አህመድ አቅላይ ፖለቲካ ተከታይ ናቸው። " የአፍ ወለምታ ነው ያሉት ትጥቅ አስፈቺም፤ ፈቺ የለም ሲሉ አቶ ዳውድ ኢብሳ" ……… ያ መንፈስ ግን በጥቅሙ ሰፊውን እጅ ተጠቃሚ ሆን ሳለ ምድሪቱ በማህበረ ኦነግ መንፈስ እየተመራች፦ ኦረሙማ አና ብሎ፤ ከተመኙት በላይ በፍጥነት ብዙ በጣም ብዙ ትርፍ ተገኝቶላቸው፦ ግን ምን ያህል መከራ እንዳራባ ደግሞ ይታወቃል። ያ ገራገር የሁልጊዜ የመሞከሪያ ጣቢያ አማራ ነው ግማዱን የተሸከመው፤ ለወደፊቱ የሞት እና የማቅ ጉዞም እጮኛው ትርፈ አልቦሹ የአማራ ማገዶነት የሁሉም እጮኛ ነው። ለመቃጠል። ለመንደድ። ለመማገድ። ማን ይሁነው? እግዚአብሄር እና አላህ ብቻ።
 
ወደ ቀደመው ጉዳዬ ስመለስ ጠሚር አብይ አህመድ ከህወሃት ጋር በነበራቸው ጦርነትም የተሳሳተ ግምት ነበራቸው። #አቅላይነት። ዓለም ፈቅዶ ሥልጣኑን - ባርኮልኛል። ለኖቤልም - አብቅቶኛል። ስለዚህ ለህወሃት ፊት የሚሰጠው አያገኝም በማለት ነበር በልበ - ሙሉነት ወደ ጦርነቱ ጠቅልለው የገቡት። እሳቸው ከኖቤላቸው ጋር በጀርባ ነበሩበት። እንደ ጎረቤት አገር መሪ ሆነው ነበርም ይከታተሉት የነበረው። የስንዴ ማሳቸው ላይ ቆመው ምርት እንጂ ጦርነት አያስፈልግም ሲሉ ሁሉ ነበሩ። 
 
ነገር ግን የዓለም አቋም ጠቅላላ ተለወጠ። አመዛኙ የህወሃት ፍላጎት አራማጅ ነበር። ዲያስፖራው፤ ኤርትራ ራሺያ እና ጥቂት አገሮች ብቻ ናቸው እንጂ ሞተሩ አሜሪካ ሆነ አውሮፓ ህብረት ከህወሃት ጎን ነበር የተሰለፋት። የዛን ጊዜው በተመድ የኢትዮጵያ ባለሙሉ አንባሳደር የነበሩት የዛሬው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንትም ሙግታቸው ጠንካራ ነበር።
 
የሆነ ሆኖ በእግዚአብሄር ቸርነት በአሜሪካ መሪነት ነው ጦርነቱ የቆመው። ስምምነቱንም ወዲያው ነበር የዘገብኩት። ደስተኛ ነበርኩ እና። አንድ ቀን እረፍት ማግኜት ትፍስህት ነው - ለእኔ።
 
እህ። ጠሚር አብይ አህመድ ነገረ አማራን የያዙበት ጉዳይም ከግምት በታች -98% ነው። አቅላይነት። ሙሉ ሁለት ዓመት በአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ፤ በሰማይ እና በምድር እዬተዋጉ ግን ያቀሉታል። ሚዲዮቻቸው "ግጭት" ይሉታል። አይጠቅምም። ፈጽሞ አይጠቅምም። አቅላይነት???? --- #የአደጋ ምልክት ነው ለእኔ። የሰሞናቱ የፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ያልተረዱት ይህን ነበር። አሁን ምልሰት እና ክለሳ እያደረጉ ይመስላል። ያው ፖለቲከኛን ማወቅ አይቻልም - እንጂ። የሌላ አገር መሪወች ግን ቢማሩበት ምርጫዬ ነው።
 
የህወሃት እና የአብይዝም ርቀሰላም አካታች አለመሆን ግን ሌላ ከውስጥ መከፋትን አጬ። ያ ነው እዬተንተከተከ የሚገኜው። ትልቁ የጠሚር አብይ አህመድ የፖለቲካ ምልከታ #አቅላይነት ነው። "#የትም #አይደርስም" የሚል ፈሊጥ ይከተላሉ። ኃይል የሚመግበኝ አንዳች ነገር አለም ብለው ያምናሉ። ዮጋይሁን ሜዲቴሽን እሳቸው ያውቃሉ። ምን አልባት የፒኮክ "አምላክ" ይሆናል። ብቻአቅላይነት የደረጄ ግድፈት ነው። ይህን የሚከተሉ ፖለቲከኞች በፍጥነት ሊያርሙት የሚገባው። ሌሎችም የሳቸው ሞጋቾች እሳቸውን ሲያቃልሉ አዳምጣለሁኝ። #እህ። 
 
ሌላው የህወሃት መራሹ ኢህአዴግ መኮንኑ እንዳነሱት ነገረ #ትራንፒዝምን በእጅጉ በተመስጦም በማስተዋል ማዳመጥ ይገባል። እኔም ጽፌበታለሁኝ። የዓለም የኃይል አሰላለፍ እኮ እዬተናጠ ነው። የፖለቲካው ብቻ እንዳይመስላችሁ። ኤኮኖሚው፤ ፍልስፍናው፤ የሃሳብ ሂደቱ ብቻ ሳይሆን በሌላ አገር የሚካሄዱ የተለመዱ ዓለም ዓቀፍ ሾወችም በአሰራራቸው ከተለመደው ውጪ ሥርነቀል ለውጥ እያሳዩ ነው። በተለይ የትራንፒዝም የወንጌል አስተምህሮን የማስከበር ጉዳይ። 
 
#የትራንፒዝም #አቋም፤ ፍጥነት፤ የውሳኔ አቅጣጫ፤ የእርምጃ አወሳሰድ ቅልጥፍና፦ መገመት፥ መተንበይ የሚቻል አይደለም። ይህ ዓይነት ገጠመኝ የግሎባላይዜሽኑ ፖለቲካ ሲገጥመው ብርቱ ጥንቃቄ ይጠይቃል። ከተናጠል ጉዞ በዙሪያ ያሉ መዋቅሮችን ሁሉ አብረው የሚሠሩበትን አትሞስፌር መምረጥ፤ ቲም ወርክን ማነቃቃት ይገባል። ይህም ብቻ ሳይሆን በግል ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ላይ አትኩሮት ካለ ጫና ሊቃናቱ እንዲሠሩ ሃሳባቸውን በነፃነት እንዲገልጹ ሊደረግ ይገባል። 
 
ከግል ከፍ ብሎ ለመታዬት ከማሰብ ይልቅ የጋራ አመራር ቅንጅታዊ ሁነት በተካ መራመድ ይጠይቃል። የከፋን ፈተና መቋቋም የሚቻለው በዚህ መስመር ይመስለኛል። የደራጄ አቅምን ባማከለ ሁነት ወደ ተግባር ማሸጋገር ይገባል። ከሁሉ ከሥር ያሉ "ላም እረኛ" ምን አለ የሚለውን ማድመጥ ይገባል። #ቴርሞሜትሩ ያለው ከህዝብ ህሊና ውስጥ ነውና። 
 
#ትራንፒዝም ሦስተኛው ዓለም ጦርነትን #አክ! ሃራም! በቃ! ያለ ነው አጀማመሩ። እና አፍሪካ ቀንድ፤ መካከላኛው ምስራቅ አፍሪካን፤ ሲዊዝ ካናልን ጨምሮ ለሚያውክ ቀጠናዊ ጦርነት ትራንፒዝም የሚይዘው አቋም ምን ሊሆን ይችላል? ብሎ በብልህነት መመርመር ይገባል። ጥሞና ጥሞና ጥሞና። እጅግ የቀደመ ጥንቃቄም።
 
እኔ በጦርነት ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ኩነቶችን መፍጠር ቢችልም፦ በ21ኛው ምዕተ ዓመት የህዝብን መሰረታዊ ችግር የበለጠ ከማውሰብሰብ ውጪ፦ ምኞትን ያሳካል የሚል ዕምነት የለኝም። ጦርነት የዘላቂ መፍትሄ አማጭሊሆን ፈጽሞ አይችልም ባይ ነኝ። ለረጅም ጊዜ ደግሜ፤ ደጋግሜ እንደማስገነዝበው ለአወንታዊም ይሁን ለአሉታዊም የፖለቲካ ሁነት ከፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ሌሰን መውሰድ በእጅጉ ይገባል ባይ ነኝ። እንዲያውም ባለፈው እንደፃፍኩት ዘለንስኪዝም የመማሪያ ካሪክለም ሊሆን ይገባል ሁሉ ብዬ ደፍሬ ጽፌያለሁኝ። ሊጠና የሚገባ መሰረታዊ አመክንዮ ስላለበት። 
 
ለእኔ የሚሰጠኝ ግብረ ምላሽ በአውሮፓ #ፑቲንዝም አንበርክኮ የመተካት የውስጥ መሻት እንዳለበት ነው የማዬው። ቅናት ነገር ያለባቸው ይመስለኛል። ለዚህም ነው ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን ማለት አገር መሪ ማለት አይደለም፤ አገር መሪ መሆን ግን ተጽዕኖ ፈጣሪነትን ሊያመጣ ይችላል በማለት ለረጅም ጊዜ የሞገትኩት። በአውዲዮም ሠርቸዋለሁኝ። ይህ ጉዳይ ነው ኢትዮጵያን 7 ዓመት የመከራ ዶፍ ያወረደው። መሰሉ በአገራችን ኢትዮጵያም - ተፈጽሟል። 
 
ፖለቲከኞች ተከድነው ይቀርባሉ። ከዛ ህዝብ ድቅቅ ይላል። የማይተካ የሰው ልጅ እምሽክ ይላል። ወልዶ ያላሳደገ፦ ቤተሰብ የደከመበትን፦ አንድ ፔና ያልገዛ ፖለቲከኛ አዛዥ ናዛዥ ሆኖ ቀንበጥ እና ሸበላ እዬለቀመ አንጋች አድርጎ ይማግደዋል። ከሁሉ በላይ የእናት ሰቆቃ። መሰረተ ልማትም አይሆኑ ሆነው ይነኩታሉ።
 
ትውልድም እንደ #ስንደዶ ይታጨዳል። ብዙውን ጊዜ ለጥቂት የኢጎ አርበኞች ሲባል ይሆናል። መነሻው የህዝብ ዕንባ ይሆንና መዳራሻው የዕንባ አምራች ሆኖ ያልፋል። ሁሉ ነገር እርግፍ ብሎ የጥቂት ሰወች የሰብዕና ግንባታ ወይንም ንደት በኽረ ጉዳዩን #ረግጦ ጊዜ፤ አቅም መዋለ መንፈስ ይባክናል።
 
የኢህአዴጉ ሜ/ ጄ አበበ ተ/ ኃይማኖት አመክንዮ ካነሱት ነጥብ ጋር ብዙም ባይቀራረብ ተጠንቅቆ መነሳት፤ ተጠንቅቆ መራመድ እንደሚያስፈልግ ግን በእጅጉ ያስገነዝባል የመኮንኑ በኽረ ሃሳብ። 
 
በምንም ሁኔታ ከኤርትራ ጋር ሊደረግ የታሰበው ጦርነት በኢትዮጵያ በኩል አዲስ ከተፈጠረው ሁለትዮሽ ( ሱማሌ እና ኢትዮጵያ (የአንካራ ቤተ መንግሥት))፤ በኤርትራ በኩልም ከሦስት (ሱማሌ፤ ኤርትራ እና ግብጽ) ወደ ሁለት (ኤርትራ እና ግብጽ) ያለው ጥምረታዊ ጉዞ አይበጅም። በፍፁም! በቃ ለስሜን ጦርንት የመሰናዶ አታሞ ሆነ የቃላት ውርክብ። የሚተርፈው ቂም፤ በቀል፤ ጥላቻ እና ማቅ ብቻ ነው። ለእነኝህ ስንኩል የክፋ ሃሳብ #ተወሳኮች ምንም አቅም ሊባክን ሊገበርም አይገባም። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሸበላ ቆይታ በኋላ ላይ እመለሳለሁኝ። ልሞግተው እምሻ ሃሳብ አለና።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06/03/2025
 
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
«ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ የቀድሞ ከፍተኛ የጦር አዛዥ ተናገሩ»
«ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ የቀድሞ ከፍተኛ የጦር አዛዥ ተናገሩ»
«የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?