የኢትዮጵያ ህይወት።

ጥሩ ሰው ሰፊ ስብዕና።
ከሥርጉተ ሥላሴ 18.06.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ)

ዳዊትም፣--- ሥራውን ሁሉ ምሳሌ አውቅ ዘንድ ይህ ሁሉ በእግዚአብሄር እጅ ተጽፎ መጣልኝ አለ።
(መጽሐፈ ዜና መዋእለ ምዕራፍ ፳፰ ቁጥር ፲፱)


የታደለ ማህጸን። የታደለ አብራክ። የታደለ እትብት። የታደለች መሬት። ኢትዮጵያ ብርሃን ወጣላት። ኢትዮጵያ ፈጣሪ አምላክ በቃሽ አላት። በቃ ራስ እግሩ ቅንነት። ራስ እግሩ ፍቅር። ራስ እግሩ መሆን። ራስ እግሩ ቁም ነገር። እራስ እግሩ ምህረት። ራስ እግሩ ማቀራረብ። ራስ እግሩ ማግስታዊነት። ራስ እግሩ ሰዋዊነት። ራስ እግሩ ተፈጥሯዊነት። እንዲህ ዓይነት የተባረከ የተቀደስ ብቁ መንፈስ የሰጠን አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አሜን! ይህ ማለት ግን በሁሉም ሃሳብ ተሰማምቻለሁ ማለት አይደለም።

የልዩነት ሃሳብ ያለው እንኳን ቢሆን በፍቅር አስማምቶ፤ አዋዶ ህሊና በጎ እንዲያስብ፤ ህሊና መልካምነትን እንዲያመርት፤ ህሊና ንጹህ የታጠበ እንዲሆን፤ የሚመክር - የጎበጠን ለማቃናት የሚያግዝ ግን ኮስታራ፤ ግን ወንዳ ወንድ፤ ግን ሃሞት ያለው፤ ግን የቆረጠ እናቱን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን አንድ ለማድረግ የሩቅ ህልመኛ።

የአፍሪካ ህዝብ ደስ ብሎት፤ ስቆ አድሮ መዋል እንዲችል እጅ ለእጅ ለማያያዝ የሚተጋ ጥሩ ሰው ሰፊ ልቦና፤ መጠነ ሰፊ ራዕይ ያለው። ሰፊ ሆድ፤ ሰፊ ስብዕና ያለው። ኧረ ከዓይን ያውጣህ መዳህኒተ ዓለም አባቴ የሚያሰኝ። 

የሰው ልጅ የማይመች ሃሳብም ቢሆን ደስ ብሎት ለመቀበል የሚያስችል ባለ አቅም። ሃሳቡን ባትሸምቱትም ግን የማትወዱት ሆኖ ግን እንደ አንድ የሃሳብ አጋር በፍቅር የምታዩት ተደርጎ ሲቀርብ ወይ ይህቺ ኢትዮጵያ እንዴት እድለኛ ሆነች በመጨረሻው ሰዓት ያሰኛል።

እስቲ እንኝህ ቁምነገሮች ይደመጡ … እኔ በአንድ ሃሳብ ብቻ አልተሰማማሁም። 

ትግራይን በሚመለከት ምንም ተጠቃሚ አይደለም የሚለው ሃሳብ አስደንግጦኛል። አንጻራዊ ለመሆን አልቻለም ዕይታው። ግን ይህም ነጻነት ነው። ሁሉም ይቅር በሥነ - ልቦና የበላይነት የነበረው ገዢ መንፈስ የት ይውደቅ። የትግራይን ገበሬውን በሚመለከት እኔም እቦታው ሄጄ ካላዬሁት መወሰን ይቸግረኛል። ተጠቅሟል አልተጠቀመም ለማለት፤ በጥቅሉ ግን ገበሬ በባህሪው ንጹህ መሆኑን አውቃለሁኝ። ስለዚህ አማካኝ የሆነ አቋም መያዝ እችላለሁኝ በባህሪ ደረጃ።

ብቻ ይህም ቢሆን እንደሌለው ሊሂቅ ከራራ ሆኖ ስላልቀረበ ባልሸምተውም ግን አቅርቤ እንደመረምረው አድርጎኛል። ጥቅል ጭብጡን ግን እኔ ብቻ ሳይሆን መሬት ላይም ያለው ሚሊዮን ህዝብ የሚሸምተው አይደለም። እንዲያውም በመንፈስ ሊያሸፍተው ይችላል። ከ4 ሚሊዮን ህዝብ 1 ሚሊዮን ተጠቃሚ ከሆነ በአምስት ሲባዛ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ይሆናል። 

ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ብቻውን ስለማይበላ። የሆነ ሆኖ እንደ መሪ ሊሆን የሚገባው የዲፕሎማሲያዊ ንግግር ነው ተብሎ ቢታለፍም፤ ህዝብ ግን እንደ ወረደ ይቀበለዋል ተብሎ አይታሰብም - አይመስለኝም። መከራውን ጥጥት አድርጎት 27 ዓመት ኖሯል። ጋንቤላ ላይ „ደም የጠጣች መሬት፤ በደም የበቀለ ሰብል ያነን የበላ ህዝብ“ ሲሉ ያለ ምክንያት አይደለም። ተጠቃሚ ካልሆነ የትግራይ ህዝብ ስለምን አብሮ ይደልቃል? አብሮ እኮ ነው ህጻናትን ከፎቅ የወረወረው አደራውን የበላ ህዝብ ነው። ታማኝነቱን የሳተ። ካህናቱ እንኳን።

የተዘረፈው መሬት መሬቴ ነው የሚለውስ ... ምኑ ተዘርዝሮ ያልቃል። ሌብነት ጀብዱ ነው። ወረራም ጀግንት ነው። መስዋዕትነት ለሚባለው ወሎም ጎንደርም ኤርትራም ደቋዋል። በጦርነቱ ደግሞ ሙሉው የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ ተፋልሟል። ብቻቸውን የደረሰባቸው ምንም ነገር የለም። ለዚህም ተቃሚዎቹ እነሱ እንጂ ወሎ እና ጎንደርማ እዬታዬ ነው። 

መተንፈሻ ቧንቧቸው ተዘግቶ ቡቃያቸው አካላቸው ጎሎ … እስር ቤቱ ይፍረደው … ጥሬ እቃ አቅራቢ … ግፍ ይሆናል … ይህ እነሱንም አይጠቅምም። እውነቱ ተነግሯቸው ከተንጠለጠሉበት ቢወርዱ ነው መቀራረብ የሚቻለው። ፍቅር በአዋጅ አይሆንም። ምህረት ደግሞ ከይቅርታ ነው የሚገኘው። ያ ደግሞ ከውስጥ የሚቀበሉት ዕውነቱ እውነት ነው ብሎ ህዝብ እንዲቀበል ሲሆን ብቻ ነው … ይህ የአደባባይ ሚስጢር ስለሆነ ምንም ማለት አልችልም። ህዝቡ እዬኖረው ስለሆነ።

 … በዚህ ሙግት እንኳን ባለቅኔው ጠ/ ሚር ሊያሸንፉን አይችሉም። በደል ስላለ፤ የተበደለም መሬት ላይ ስላለ … ነገር ግን እንደ መሪ ቅራኒዎችን ለማለዘብ ይህን መንገድ መምረጥ የፈቃጁ ጉዳይ ነው  … ስለምን? አሁን እንኳን ባዶ ስድስት ያሉ መከረኞች ማስፈታት አልቻለም ቅኑ የትግራይ ህዝብ? የሆነ ሆኖ ከዚህ ሃሳብ በስተቀር ሌላው ግን ውስጧን የእናትን ባለፈም የአፍሪካንም ያጠና ስለሆነ ቅንነቱ የበዛ ወደ ፍቅራዊነት የሚወስድ መንገድ ነው።

የኢኮኖሚ የበላይነት፤ የወታደራዊ የበላይነት፤ የደህንነቱ የባለይነት፤ ቴሌኮሙ፤ አዬር መንገዱ ኢፈርት ምን የቀረ ክፍት ነገር ኑሮ ነው ቀድሞ ነገር። እንድ ሰው 16 ቦታ በሚሾምበት አገር … ኢትዮጵያዊው ውሃ የሚጠጠኝ ዘውጋዊ ነው ሳይል ይቀራልን? ጥበብ እራሷ እኮ በጎሳ አንጂ በመክሊት እኮ ከቀረ ስንት ዘመን አለው … የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋነቱ ከልኩ ከመጠኑ ያለፈ ስለመሆነ ክብር ለዛ ጨዋ እና ምስጉን ህዝብ እንጂ አንድ ዘርም ባልተረፈ ነበር።

ቀድሞ ነገር እኛ እንጂ ስለነ የትግራይ ህጻናት የምናስበው ለመሆኑ ስለነገ አስበውት ያውቃሉን? እነሱማ አሁንም ቀርቶብናል ባዮች ናቸው … ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማለት የትግሬ ድርጅት ማለት ነው። በቃ ገዳዩም፤ አራጁም፤ ዘራፊውም፤ ሌባውም ደብዳቢውም፤ ያው ከዚህ ከትግርይ የወጣ ነው። ይሄ እኮ ፋክት ነው። ፋክት አይፈለጥ አይለበጥ። ፊፋ እኮ በአደባባይ ነው የተደበደበው። ከጥጋቡ ከመታበዩ ብዛት እክሌ ተከሌ ማለት አይቻልም። ቋንቋ መቻል በራሱ ይለፍ ነው …

ለዘመናዮች ጥሩ የህሊና ስንቅ ነው፤ ለተበዳዩ ህዝብ ደግሞ ቁስሉን ያመረቅዛል … ከትግራይ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የሚያምረው እነሱ የበደሉትን ህዝብ ድንጋይ ተሸከመው ይቅርታ ሲጠይቁ ብቻ እና ብቻ ነው። አሁንስ የሚያጋድሉት እነሱ አይደሉንም? መልካምነት እኮ የአንድ ወገን ብቻ ከሆነ ወንዝ አያሻግርም። የመታፈን ነገር ሊኖር ይችላል … ለመሆኑ ከትግራይ ህዝብ የተገኜ አንድ የሰባዕዊ መብት ተሟጋች አለን?

የታፈነ ህዝብ እኮ መድፍ እዬረገጠ ተጨፍጭፏል። እነሱም ማድረግ የነበረባቸው የሄውን ነበር .. ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን የገበያ ግርግር እያሉ ከሚያባጭሉ … የሽንት ሽቶ በኮዳ ሞልተው ወልደያ ህዝብ ላይ ከሚያርከፈክፉ … አይደለም ከዛ ውጪ ባሉ VOA // DW ሪፖርተራቸው ሳይቀሩ ሰራተኞች እነሱ አይደሉንም? ምን ስለሆኑ ነው ትግራይ ላይ ልዩ ሪፖርተር የተቀመጠው? ለዚህ ምንም ዓይነት ሸፋን አይሰጠውም። የሞተ አስነስቶ ዲሞ ስለሚያስወጣ። 

ፈጣሪም ዕውነተኛው ዳኛ ስላለ። አይደለም እኛ ውጪዎቹም ያውቁታል። እውነት ስለሆነ። እንዲህ ዓይነት ነገር ሰልችቶናል። ከዚህ ጋር የማያነካኩ ነገሮች ቢነሱ መልካም ነው። በዚህ ውስጥ ያለው ተማህጽኖ ከእነሱ ቢመጣ ነው የሚሻለው። እኛ አብይን በአብይነቱ እንጂ በወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ አፍረቃሪነት ስላልሆን ከልባችን የተቀበልነው። እኛም እንዳንጎዳ ቢታሰብበት መልካም ነው። እንጎዳለን። ብዙ ነገራችን አጥተናል እና። ሚዛናዊ መሆን ያስፈልጋል። "ምን አደረገ ጎንደር" እኮ ከባድ ጥያቄ ነው። "ስለም ያሳድዱናልን? " ከበድ አምክንዮ ነው ... ብቻ ልጅ ካወጣ፤ የልጅ ልጅ ካወጣ የእዬር ጉዳይ ይሆናል።

ሰው ከሚችለው በላይ ነው። አቅም የለንም። ሌላው ግን ሙሉ ህዝብ ለማለት የሚከብዱ ነገሮች ይኖሩሉ የባዶ ስድስት ሰለባዎች ጎንደሬው ብቻ አይደሉም የትግራይ ታሪክ አዋቂ አዛውንትም ተገብረዋል፤ የኢትዮጵያ የቀድሞው የሠራዊት፤ የፖሊስ፤ የደህነነት፤ የኢሠፓ አባሎችም አሉ፤ ቀጥተኛም ተጠቂ ናቸው እንደ ማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ። ለምሳሌ ወዲ ሻንበልን ማንሳት ይቻላል።

በጥቅሉ ሲታይ ስለምን ይሆን የአማራ የህልውና ተጋድሎ እና የኦሮሞ ፕሮቴስት አብዮቶች የተነሱት? ስለዚህም እኮ ነው አዲስ ጸሐይ ኢትዮጵያ ላይ የወጣው። የትግራይ ዘመነ መሳፍንት አክትሞ ኢትዮጵያዊ መሪ ኢትዮጵያ ስለገኘች። በተረፈ ከዚህ ሃሳብ በስተቀር ሌላው ልብ የሚሸለመው፤ እጅግም በሳል፤ ጥንቁቅ፤ ብልህም ነው እንደ ቀደመው ሁሉ … 

  • ·       ምርኩዝ።

የኔወቹ በእኔ ዕይታ በዚህ ውስጥ ከዚህ ከትግራይ የአልተጠቀመም ጉዳይ ባሻገር … ሌሎች ሃሳቦች ግን ገንቢ እና ማግስትን በውል የሚያደራጁ፤ የሚመሩም ናቸው። ወግ ደርሶን የፓርላማ ውይይትን ለማድመጥ መፍቀድ በእኔ ህይወት ራሱ አዲስ ምዕራፍ ነው። ኢትዮጵያ መንግሥትም መሪም አላት ብዬ ስላመንኩኝ ለሁለተኛ ጊዜ ነው እንዲህ ሙሉውን የተከታተልኩት። ተመስገንም ብያለሁ። አሁን ፈጽሞ አልባክንም። ዕለት ዕለት እምከታተለው የኢትዮጵያን ቸር ወሬ የእኔ ብዬ አስጠግቼ ነው። ጤናዬንም አግኝቻለሁኝ። ተመስገንም ብያለሁኝ።

Ethiopia: [መደመጥ ያለበት] ስለ ትግራይ ህዝብ / አብይ ያቀረቡት ከፍተኛ ጥሪ | “ ከፍተኛ ችግር ያለው ትግራይ ውስጥ ነው!!”

Ethiopia: "እኛ ስንዋደድ አለም ያከብረናል" "...ኢትዮጵያዊያን ከጥላቻ ያተረፍነው ነገር መናቅን ነው ባህር ውስጥ መጣልን ነው...”

Ethiopia: “በብሄር እና በደም አይደለም ሰው የሚወነጀለው/ አብይ

Ethiopia: “መግረፍ ጨለማ ቤት ማስቀመጥ፣ አካል ማጉዳል የኛ የአሸባሪነት ተግባር ነው/ አብይ

Ethiopia: / አብይ ስለ ኤርትራ የተናገሩት እስካሁን ያልተሰማ አስገራሚ ሚስጥር | “...አሰብን ስንሰጥ መቼ ተወያየን?"

Ethiopia: / አብይ አሕመድ ለፓርላማ አባላት ስለ ፕራይቬታይዜሽን ያደረጉት ጥልቅ ትንታኔ

የኔዎቹ እኒህ አዲስ ብርሃን እኮ አጣደፉን … አንዱን ሳንጨርስ ሌላውን እያከታተሉ …

  • ሙሉውን ለምትፈለጉ ወገኖቼ 
https://www.youtube.com/watch?v=wJnC2aX4jP8
PM Dr. Abiy Ahmed Speech in Parliament - FULL

 

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

 

የኔዎቹ ቅኖቹ እጅግ አድርጌ አመስግናችሁ አለሁኝ ለዚህ ሙሉ ትእግስት።

መሸቢያ ጊዜ።  

 





አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።