ጥማት።
ጥማት!!
„እግዚአብሄርም እንዲህ ይላል፤ ---
በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፤ በመድሃኒቴም ቀን ረድቼህ አለሁ፤
እጠብቅሃ አለሁም፤ ምድርንም ታቀና ዘንድ፣ ውድማ
የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ፤ የተጋዙትንም
ውጪ በጨለማም የተቀመጡትን ተገለጡ
ትል ዘንድ ቃል
ኪዳን አድርጌ ለህዝቡ
ሰጥቼአለሁ።“
ትንቢተ ኢሳያስ ፵፰ ከቁጥር ፰ እስከ ፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18.12.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
የለማ የዴሞክራሲ ጀግንነት እንዲህ ነው በአፍሪካ ፊደል ያሰቆጠረው
ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? አጀንዳችን ባለቀው የወያኔ ሃርነት
ትግራይ ማንፌስቶ አብሮ ደመር በመቀመጥ ሳይሆን በ27 ዓመት ውስጥ በጠፉን፤ በሾሎኩን ወደፊትም መጥፋቱም ሆነ መሽሎኩን ለመገደብ
ወሳኙን ግንዱ ላይ ማተኮር የተገባ ነው ብዬ አስባለሁኝ። ግንዱ ደግሞ አዲሱ ትውልድ ነው። ከ7 እስከ 18 ዓመት ያለው። ያን ነው
አንጸን ነፍስ ባለው የዜግነት ትሩፋት አንጸን መገንባት ያለብን። ያ ነው የዛሬው የቤት ሥራችን ሊሆን የሚገባው እንደ ሥርጉተ ሥላሴ። እንደ ሥርጉተ ሥላሴ እኛም ማስቲካ የሆን ይመስለኛል።
ያለቀ አሮጌ ቆርቆሮ
ለምን አፈሰስክ፤ ስለምን የወዬበው ግድግዳህ ወረዛ፤ ስለምንስ መቆም የተሰነው ምርጊትህ ፍርክርክ ብሎ ህልምህ እንዲህ እና እንዲያ
ሆነ እያለን የምናባክነው ጊዜ የተገባ አይመስለኝም።
ይልቁኑ በቆሰለው፤ በተጎዳው፤ በደማው የማግስት ድልድይ ላይ እያንዳንዳችን ልናደርግ ስለሚገባው
ብናተኮር እና ብንሥራ መልካም ይመስለኛል። አሁንም ቅድምም ያን ገዳይ፤ ያን ተስፋን ቀሚ፤ ያን መኖርን ነጣቂ ዘመን እያነሳን ከምንጥል
እና በዛ ከምንገሸገሽ በተጨማሪም ውስጣችን ከምናቆስለው … የኖርንበት ለአንጀት በሸታ የተደረግንበትን ዘመን ድገመኝ ሰለልሰኝ አሁንም
በመንፈስ ምልስቶሽ ሥነ - ልቦናዬን ቆስስቁስና ውቃኝ ደቁሰኝ ከምንል …
ቀደመው ባለው ጊዜ የተገባ ነበር፤ በማር የተጠቀለለ የመርዝ ሥርዓት አራማጆች ብቻ ሳይሆኑ ፈላስማዎችም
በመሆናቸው እነ ቤተ አቦይ ቤተሰቦች። አሁን እኔ ዛሬ ላይ ተሁኖ ግን ስለ አቦይ በረከት ይሁን ስለ ሳጅን በረከት ስምዖን ኑዛዜ
ቤተኛ መሆን የምንሥራው የማጣት ያህል ሆኖ ይመስለኛል።
መለመላውን ለቆመ፤ ጭልጥ ባለ በርሃ ጭራሮው ተንጨፍርሮ አለመኖሩ እያባተተው በዬሰከንዱ ከሚያሰበረግገው ነፍስ ጋር እሰጣ
ገባ መግባቱ ተፈላጊም አይደለም።
አሁን እኮ እነሱ የሚፈለጉት አስለቃሽ
እና ምሾ ደርዳሪ እንጂ በአምክንዮ ሞጋችን አይደለም። ሆድ ብሷቸዋል፤ ባባት ይዞቿዋል፤ መጠላት
እኮ መከራ እኮ ነው። ከራሳቸው ከታጋሩ ነፍሶች በሰተቀር ቅንጣት እራፊ የመንፈስ ማሳ
የላቸውም። አወዳደቁ የከፋ ነው የሆነው የወያኔ ሃርነት የ100 ህልም እና ትልም። እንኩትኩቱ ነው የወጣው።
ከአፈርኩ አይመልሰኝ እኮ ነው
ይህ ሁሉ ኳኳታ እና እንድርቺ እንድርቺ። የታላቋን ኢትዮጵያን በታላቋ ትግራይ የመተካት ህልም መራራ ስንብት አደርጓል። አሁን ደመነፍሱን
ሆኖ ኑዛዜ ላይ ያለው። አሁን አይደለም እኔ ይህን በፃፍኩበት አቦይ ኑዛዜ ላይ የነበሩት በ18.11.2018 ነበር ባለፈው ዓመት።
ብቻ ኑዛዜውን ርቱ የሚል ጠፍቶ ነው እንጂ …
የሳጅን
በረከት ስምዖን ቀለሃም ባዶነት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደፊት ሲመጡ እብደት ካሰኘው አንዱ ዘነግ ነበር። እናም እንዲህ ተብሎ ተኮልሞ ነበር … ግራ ቀኙን በሚመለከት፤ አሁን ግን ሥራችን ባይሆኑ ምርጫዬ
ነው። መንግሥት ነን እኮ ነው የሚሉት፤ ፍልሚያቸው ሁለት ዙር ከታጠቀ ሥልጡን አቅም ጋር ስለሆነ ፍልሚያው ባለቤት አለው … በጥበብ እንዴት እንደናዱት
ገድል ነው የተፈጸመው።
የአቦይ ስብሃት ኑዛዜ - ተናውዞ - ወርዞ።
የአቦይ ስብሃት ኑዛዜ በደመመን ጫና ናውዞ …
ከሥርጉተ ሥላሴ 18.11.2017 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)
የ አንቡላ ቃርሚያ
ግብዕቱ አይቀሬ
· ልባዊነት ከተለገሰን።
ልንጣደፍበት፤ ልንቸኩልበት የሚገባ ብዙ ተግባራት አሉን። አሮጌ ቆርቆሮ ጩኽቱ የትዬሌለ ነው።
መጩኹ ደግሞ የማሸነፍ ሳይሆን የመሸነፍ ምልክት ነው። ከሽንፈታቸውን በለቅሶ ቢያወጡት ቢፈቀድላቸውስ ምን አለበት።
የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ብቻ ሳይሆን የግራ ፖለቲካ አፋኝ መንፈስም ከኢትዮጵያ የሚወገድበት ደልዳለ ሁኔታ ላይ ነው የምንገኘው
- ዛሬ። ገፃቸው እኮ ከስሏል ወይ ደግሞ ደምኗል ወይ ደግሞ ገርጥቷል።
ቁጭ እንዳሉ የዘላለም ህንጣቸው በላያቸው ላይ እዬፈረሰ ነው … ትምክህታቸው ጥሏቸው ከሸፈተ
ቆዬ፤ ወጋግራውን ደገፍ ብሎ በጋድሞሽ በስንጥር የቆመ ወኪላቸውም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው … "ልክን ማወቅ ከልክ ስለሚያደርስ"ትር ብትን የሚሉትም የልካቸውን
ያገኛሉ ወይ ይጠቃላሉ፤ „ወደሽን ቆማጤ ንጉሥ ትምረቂ“ ነውና … ጠቅላዩም የፍትህ አደባባይ ነው፤ ተጥቃላዩ ደግሞ
ብልዘት የሚጨፍርበት ቦዞግኝነት መርዝ የተጠቀለለው የግራ ፖለቲካ ይሆናል …
ኢትዮጵያ ዘመን አድሏት፤ ፈጣሪም እረድቷት ሰውኛ፤ ተፈጥሮኛ የሆነ ጠረን
እዬቀረባት ያለበት ወቅት ነው። ይህ ለጨካኞች፤ ይህ ለአረመኔዎች፤ ይህ ለመኖር ቀማኞች አይገባቸውም። በውስጡ አልኖሩበትም እና።
ዴሞክራሲ ስለሚባለው ከሀ እስከ ፐ፤ ከኤ እስከ ዜድ ተፎካካሪ/
ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ የሚባለውም ያልነበረበት ስለመሆኑ መሪዎቹ ሁሉ በምን ሁኔታ መሪ እንደሆኑ እና ያስቆጠሩትን ዘመን በመለካት ራሱ
ከፊታቸው የሚቀድመው መጠሪያቸው መለያ ንቅንቅ ሳይል 40 ዘመን ማስቆጠሩ ምስክር ነው።
ዴሞክራሲ ማለት እስከ ዕለት ሞት ድርስ እንደ ድንጋይ መተከል ማለት ነው በኢትዮጵያኛ ቋንቋ ሲተረጎም። ሌላውንም ህዝብ በቃህ! ስለምን ተተኪ አላመጣህም ብሎ ቢጠይቃቸው እኛ እነ አቦይን እንደምንጠይቅ
ሁሉ መልስ የላቸውም የኛዎቹ የነፃነት፤ የዲሞክራሲ አታጋዮቻችን፤ ተስፋ ጥለንባቸው የነበረው ሁሉም እከሌ ተከሌ ሳይባል። ዴሞክራሲ
የኖረው በእኛ ዘመን በዳማ አጫዋችነት ነው። ለጨዋታ ማሟያ ብቻ።
ልዩነቱ እነ አቦይ የግጦሽ መከዳቸው አይሆኑ ሆኖ መቀበሩ ሲሆን ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ
የሚባሉት ደግሞ በሃላፊነት የሚጠይቁበት ነገር ዕድሉን የመግዛት ሥልጣኑን ስላለገኙ፤ በለ ሙሉ ገዢ ስላልነበሩ ውስን ከመሆኑ ላይ ነው።
ህዝብ ግን በዬጊዜው በሚነሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ገብሮበታል ልጁን፤ ትዳሩን አፍርሶበታል፤ ኑሮውን
አመሳቅሎበታል፤ ሁለመናውን አጥቶበታል። ወይ አይዘልቁ ወይ አያዘልቁ … አሁንም እነሱው ናቸው አለን የሚሉትም።
ደካማ ነህ ውረድ፤ አልቻልክበትም ልቀቅ ሲመጣ ደግሞ ሁሉም ከራሱ ሲደርስ ከሦስት ከአራት ነው
የሚከፈለው፤ አንጋፋውን ኢህአፓን ማዬት ይቻላል ከስንት እንደ ተረተረ። አዲስ ፓርቲ የሚፈጥረው እኮ ዝቅ ብዬ አልመራም ነው እኮ ሌላ ቃናም ሌላ ቃልም የለውም።
እነ አቦይን እነ ሳጅንን ሥልጣን ወይንም ሞት ማለታቸው ጸያፍ መሆኑን ስንናገር ከልጅነት እስከ እውቀት ሊቀመንበር እዬተባለ
ከፊት የተለጠፈው የ40/ 50 የራስ ሹመኛም ራሱን መጠዬቅ ያስፈልገዋል። ከወያኔ ሃርነት ትግራይ የተነጠለው የዶር አረጋይ በርሄን
ፓርቲን ጨምሮ፤ ዛሬም እሳቸው ተፎከካሪ ናቸው። ቧልቱ እንዲህ ነው …
በቅንጅት ከታዬው የህዝብ ምርጫ በፊትም ሆነ በኋዋላ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የመጣ ሊሂቅ ታይቶም
ታሰምቶም አይታወቅም። ተሿሚውም ተሸላሚውም ራሱን በራሱ የሚሰጠው አዲስ የፖለቲካ ድርጅት እምሠርታለሁ ያለው ዓላማ እና ግብ ቀርፆ
በተነሳ መሥራቹ ነፍስ ነው። ለእድሜ ልክ። ይህ
የማይደፈር የማይነካ የተከለከለ መንገድ ነበር።
አሁን የወጣቶች የተባለለት ሰማያዊን እንውሰደው። ስለምን ሁለት መሆን አስፈለጋቸው? ስለ ኢትዮጵያ ከሆነ ትግሉ? የተሰዋው ደግሞ ትግሉን አደራ ብሎ ተሰውቶ ቀርቷል። እናትም ባዶ ጉልቻዋን ታቅፋ ..
የቀደሙት
የፖለቲካ ድርጅቶች የሚመሠረቱት ለዝና እና ለውዳሴ ለሥም ስለሆነ፤ የግራ ፍልስፋና አራማጆች ስለሆኑ ነው ብንል ወጣቶች የመሠረቱትስ ከቶ ምን
ሊባል ነው? በዘመናችን ይህን በሰማያዊ ፓርቲ አይተናል።
አንድነት ላይ የነበረው መከራም ይኸው ነበር። ወጣት ሴት አትመራንም ብቻ ሳይሆን „ዝም አንልም“
አዲስ ንቅናቄ የተፈጠረው በዚኸው አግባብ ነበር። ያ ያፈነገጠ አንጃ ነበር፤
በሃሳብ ተሟግቶ ማሸነፍ ሳይችል ሲቀር ዓርማ፤ ደንብ ፕሮግራም ቀርፆ አዲስ ሥያሜ ይዞ ከች ነው።
ዓርማ ደንብ ፕሮግራም ደግሞ የአንድ ቀን ሥራ ነው። ደንብ ፕሮግራም ዓርማ መቅረጽ ሥራ ሆኖ? ለዚህ ነው መሰረት እና ዘላቂ ዓላማን
በውስጡ ባላሰደረ ድርጅት፤ ውህደት፤ ጥምረት፤ እዬተባለ ትውለልድ በዬዘመኑ ሲታጨድ የኖረው።
ተስፋ ሆነ ተብሎ ሙሴ ለሌለው የለውጥ መንፈስ ጀግኖቹ እነ ሺብሬ ደሳለኝ፤ እነ ሰማዕቱ አሰፈፋ
ማሩ ነፍሳቸውን የሰጡለት። ሊቀመንበር መባል ብቻ ነው የሚፈለገው። ቢያንስ መከራን በወል ለመጋራት ባለመፍቀድ በተበተነ ሁኔታ አዳዲስ
ጉልቻ መጎለት?
እኔ በዚህ ዘመን እራሳቸውን አሸንፈው ያየኋኋቸው በቅርብ ቀን ከሰጡት ቃለ ምልልስ እና ከወሰዱት
ደፋር እርምጃ አንጻር አቶ ሌንጮ ለታ እና በቀደመ ሁኔታ ዶር ነገደ ጎበዜ ናቸው። ኦዴግ እና መኢሶን፤ አቶ ሌንጮ ለታ ዶር አብይ አህመድ ይመርኝ ብለው ወሰኑ ተዋህዱ፤ ዶር ነገደ ጎበዜ ደግሞ ዴሞክራሲ ምርጫ ከኖረ አብይን እመረጠዋለሁ አሉ። የራሳቸው ፓርቲ እያለ። ይህን ማለታቸው
እሳቸው አይወዳደሩም ማለት ነው።
ዶር ነገደ ጎበዜ ጠ/ሚር አብይን ሲገልጡ ብቁነታቸውን አደባባይ ወጥተው ሲመሰከሩ በፊትም በጀርባም
በኋዋላም በቀኝም በግራም ሸፍጥ አልነበረበትም። ይህ የዴሞክራሲ ተቋም ነው ለሚያውቀው ለሚገባው። ዴሞክራሲ እንዲህ ነው የሚመጣው።
ዴሞክራሲ ከቅንጣቱ እሰከ ጉዙፉ ሃሳብ ራስን አሸንፎ በሚመጣ ምህንድስና ነው ዴሞክራሲ ሊመጣ
የሚችለው። ዴሞክራሲ አጥቂ ተከለካይ ጎል ጠበቂን አሳምሮ የመደልደል ልባም የፖለቲካ ሳይንቲስትን ይፈልጋል እንደ ዶር ለማ መገረሳ ያለ ደፋር ነፍስን ይጠይቃል። ዶር ለማ መግርሳ ስለ ዴሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብ አተገባበር ቢነግሩን
ቢያስተምሩን እናደምጣቸዋለን።
ያን ጊዜ የ አሁኗ የገቢዎች ሚ/ር ሚር የዛኔዋ የኦህዴድ የምክር ቤት አባል ወ/ሮ አደናች አቤቤ
ዶር ለማ መገርሳ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ዶር አብይ አህመድን የ =ኦህዴድ ሊቀመንበር ሲያደርጉ በሰጡት ቃለ ምልልስ ዴሞክራሲን ጀመርነው
ነበር ያሉት። እኔም የምለው ይኽንኑ ነው። ከዛች ዕለት ጀምሮ የዴሞክራሲ መሰረት ተጥሏል በ ኢትዮጵያ ምደር ተወጠነ ብዬ አምናለሁኝ።
አሁን እራሳቸው የሆኑበትን ተቋም ለመገንባት ዶር ለማ መገርሳ አያቅማሙም ሁነውበታል እና። ሌላውን
ልውቀስ ቢሉም ያምርባቸዋል እራሳቸውን አሸንፈው ተገኝተዋልና፤ ዴሞክራሲ ከንድፍ ወደ ተግባር ተሸጋገረ ቢባል ዶር ለማ መገርሳን
የሚያክል ታምር የሠራ ምድር አልፈጠረችም፤ ከሳቸው ቀድም ባላው ጊዜ የመድህን ፓርቲ መስራች ኮ/ ጎሹ ወልዴ ይህን አድርገዋል።
የሁለቱ አፈጻጻም ራሱ ልዩነት አለው። ሂደት እና መባቻ ላይነት …
የሆነ ሆኖ ከላይ ጠቅስኳቸው የተፎካካሪ ልላቸው እችላለሁ ተቃዋሚም ተቃናቃኝ የሚለው ሥያሜ ስላማይመለከታቸው
መኢሶንን እና ኦዴግን ከሁለቱን ውጪ እኔ ዶሞክራት ለመሆን ተሰናድጃለሁኝ ብሎ የሚነግረን፤ የሚሞግተን፤ ሊሂቅ፤ ሚዲያ ይሁን የፖለቲካ
ድርጅት ካለ ይምጣ እና እንፋለም። ዴሞክራሲ እኮ የግድ ከፖለቲካ ድርጅት ላይ ብቻ አይደለም ዕውን የሚሆነው። ሁሉ በመዳፉ ካለው
መጀመር ይኖርበታል።
አሳታፊነቱ፤ አቃፊነቱ፤ አድማጭነቱ፤ ተራጋጭ አለመሆኑ፤ የሚሰጠው የነፃነት ልክ ሳያጨናንቅ፤
ሳይወጣጥር ወይንም ሳይዘነጣጥል ማድረግ ይቻለው ነበር። ይህን ግን አለዬንም አለሰማነም።
ለራሱ እንኳን ዴሞክራሲ የሰጠ ድርጅት ይሁን ሚዲያ አለዬንም ሳተናውን እንደ ናሙና እኔ ከማዬው
በስተቀር እሱም ጫና አልነበረበትም ማለት አልችልም። ሲዋከብ እንደ ነበረ ወፊቱ ሹክ ትላለች።
ትግሎ ራዕዩ ለዴሞክራሲ ቢሆንማ ኑሮ ብስል ከቀሊል፤ የክት እና የዘወትር፤ ወርቅ እና ነሃስ፤
ልጅ እና እንጀራ ልጅ፤ ምርጥ ዜጋ እና ተርታ ዜጋ ተብሎ ባልተለዬ ነበር። ከሞት እንኳን ሰው የሚለይበት እረግረግ ላይ ነው የነበረው
ፖለቲካችን። አቅም የሚባለው ነገር እራሱ ባለቤት አልነበረውም በውልም በግልም አጀንዳ አልነበረም። አቅም መሰለኝ ማሸነፍ የሚያስችለው? አቅም ላይ ሳይሆን ምርኩዝ ላይ ነበር ቀልብ የነበረው፤ ምርኩዝ ደግሞ ቀን ሲጥለው ዋቢ መሆን አይችል። ስለምን ካለቀዬው ስለማይሆን?
መረጃ ሰጠን አታገልን ግንባር ቀደም ነበርን ለሚባለው የፊቱ የኋላ እዬሆነ ነው እንጂ የቀደሙ
ነበሩ። ይህም ቢሆን ለሚባለው የድርጊተኝነት ገድል ለማን ድልዳልነት፤ ስለምን እንደ ነበረ „ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ“ እንዲሉ ልብ ያለን ሰዎች እናውቀዋለን።
ብቻ ዘመን ነው ያ ሞገድ ላይ የተንሰራፋው አገር ምድሩን ያካለለው ለሌላ መንፈስ ታስቦ የተሰናዳው
የመንፈስ ድልዳል፤ የመንፈስ ጥሪት የልዩ ኮረቻ መሰናዶ ሳይታሰብ ብልሆች እነ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር ገዱ አንዳርጋቸው በቆረጣ
ገብተው አደላድለው ዓለምን ትንግርት ያሰኜ አዲስ ዘመን የብርሃን ጮራ የሆኑት። ብልጭታው ደግሞ ተዳርሷል ሙቀቱ ለሁሉም ተርፏል።
ለዚህም ነበር የዛሬ ዓመት ይህን ሰሞን በተደራጀ እና በታቀደ ሁኔታ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ
ከታጋላቸው በላይ የነፃነት ታጋዮችም እልፊ ሄደው ብዙ መንፈስ ለመበትን የተጉት። ገዳይም ተብለው ነበር ዶር ለማ መገርሳ ይሁኑ
ዶር ገዱ አንዳርጋቸው። ሌላም ሌላም … „ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል“ ከጡጦ ያልወጣ መንፈስ ጠብቁትም እሱ ታቱ ዥግራውን ተፍጣሚ እስቲያደርስም ሞቶም ነበር፤ ሌላው ጥብቆ የግዞት
መንገድ።
ብቻ ብልሆች የብልህነት አዲስ ፍልስፍና ነድፈዋል በአገረ ኢትዮጵያ ማለት ያስችለኛል። ለዚህም
የረዳቸው የእኔ የሚሉት ሃሳብ ያላቸው፤ የሌላ ባለድል ሃሳብ ተቀራማች ወይንም ተለጣፊ ወይንም ጥገኛ ሳይሆን ሃሳብን እንደ ፏፏቴ
በማያልቅ ብቃት የማፍለቅ አቅሙ ስላላቸው መንፈሳችን ገዙት።
ልቅና በብትህና!
ሚሊዮኖችን አሰለፉ፤ ምንም ፕሮፖጋንዲስት ቀስቃሽ ሳያስፈለጋቸው፤ ሜዞ
ሳያወጡ ወጀቡን ጥሰው ሁሉንም ነፃ አወጡት ትብትቡን፤ ሴራውን፤ ሸሩን ሳይቀር፤ በ4 ማዕዘን በሚናጥ የሃሳብ ወጀብ ሳይረቱ፤ ሳይዘናጉ
በተረጋጋ፤ በፍጹም ሁኔታ በሰከነ ዝልቅ ልዑቅ መንፈስ ማግስትን በመልካም ጥሪኝ በኮለመ ብጡል ክህሎት ዛሬን እዚህ አደርሰዋል በጀግንነት።
አላቸዋ የተግባርም የሃሳብም ተጠማኝ አይደሉምና።
ዴሞክራሲን ዶር ለማ መገርሳ፤ ዴሞክራሲን አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዴሞክራሲን በቅርቡ ባሳዩን ትጋት
ደግሞ በወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል ቢነግሩን ይገባናል።
ከራሳችን ይልቅ ኢትዮጵያ ያለባትን ችግር፤ ከእሷም ባለፈ አፍሪካ ያለባትን ችግር ማሻገር የሚችል
ፈታናን ረቺ ጽኑ ሁለገብ አቅምንና ክህሎትን መፍቀድ ከራስ በላይ አልፈው ተርፈው የፓን አፍሪካን ቀደመት ተልዕኮ ጥቅም ለማስጠበቅ
መትጋት ነው ዴሞክራትነት። ትርፉ ማስበሉ ነው ነገን በተረገጥ በተስፋ እንድንጠበቅ መንሹ የሆነልን።
· ቅጥ።
አስተያዬት ሞጋች ሰብእና የማናስተናግድ፤ ጠንከር ያለ ጹሑፍ ከድህረገጽ እንዲነሳ በዬደህረ ገፆች
ደጅ ስንጠና ውለን የምናድር፤ ሲያስፈለግም በተጫን መንፈስ ለማስፈራራት የሚቃጣን፤ በድርጀት ህቡዑ ስብሰባ አንድ ቀንጣ ወጣት አክቲቢስት
ከቁጥር ገብቶ እንደ አጀንዳ የሚያርበተብተን አባሎቻችን ሰብሰብን በዛ ላይ ጊዜ የምናቃጥል፤ በግል እና በጋራ ሞጋቾችን ለማጥቃት
ሠራዊት በገፍ የምናሰለፍ በዛም የምንኩራራ፤ ሞጋች ሃሳብ ያላቸውን የምናርቅ፤ ሥም በማጥፋት እና በማዋከብ ሰብዕዊ መብትን እምንዳፈር
እኛ ስለ ዴሞክራሲ የተሻልን ነን ማለት ያሰተዛዝባል። ጥሪት የለንም እና።
ሚዲያችን እኮ አገር መሪ ከመሆናቸው በፊት ተጻራሪ
ሞጋች ሃሳቦችን ለማስተናገድ „ሀን“ አልጀመሩትም። ኑረን አይተናዋል እና። በተመሳሳይ መንፈስ ተመሳሳይ በወጥ ህሊና ዴሞክራሲ አይታሰብም፤
አያድግም፤ አይጎለምስም፤ አያስብልም…
ከማድመጥ ውጪ ማን ተፈቅዶለት ነው ሃሳቡን ለማቅረብ፤ ቅሬታውን ለመግለጽ የሚችለው። በሞፈር
ዘመት ብዕር ከተናገረች የዘለዓለም ጠላት ነው/ ናት ያቺ ነፍስ። የእድሜ ልክ ግርዶሽ፤ የዕድሜ ልክ ውግዘት ነው የሚደርሰው። ቂመኝነቱ
እራሱ የበከተ እኮ ነው። ቂመኝቱ አይፈቃም። ተቋጠሮ እንደ መልካም ነገር በዶሴ ተቀምጧል።
ዕውነት የሆነ ነገር ስለምን ተነሳ ነው መከራው የነበረው። ፊርማው እኮ አልደረቀም የጠነዘለው ዘመን ሁላችንም
የኖርንበት። ለዛውም እንዲህ መንገድ ላይ ለሚቀረው ጉዳይ ነበር ስነዋከብ የነበረው፤ ስንት እቅም መክኖ ባክኖ ተሰውሮ ቀርቷል?
ቤት ይቁጥረው …
ዴሞክራሲን ሳናውቀው ለዴሞክራሲ ትግል ተጋድሎ አደረገን ማለቱ በዚህ ዘመን፤ ታዛቢ ባለበት በሚታይ
በሚጨበጥ እውነት ላይ ሆነን ባናነሳው ነው የሚሻለው። ቅርሻ ስለሆነ።
የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ እኮ መሠረቱ የግራ ርዕዮት ነው። ልዩነቱ ይህን ግራ ርዕዮት
ላይ ዞጋዊነትን ጨመረበት እና ተቅለሽላሽ
አደረገው። በዚህ ምክንያት በእጥፍ ድርብ እጅግ የከፋ መስመር ተከተለ እንጂ የትኛውም የግራ ርዕዮት አራማጅ ዕድሉን ቢያገኝ ዞገኝነቱ
ቢቀር ይህ ለዘላለም የመግዛት ጥማት፤ እኔን ብቻ አድምጡኝ የማለት ግለኝነት፤ የተለዩ ሃሳቦችን የማሳደድ ሆና ከምድረ ገጽ የማጥፋት
ሆነ ሁሉን ልጠቅልል ባይነቱ ከርዕዮቱ አፈጣጠር የሚመነጭ መከራ ነው።
ለዚህ ነው እኔ ለወጣቶች ያልጠቀመውን መሰመር እትመኙት፤ ለዛም አትትጉለት ስል የነበረው። ግራ
ርዕዮት ሰብዕዊ ተፈጥሮን ራሱ ይቀይራል። ደጎቹ ጨካኝ ይሆናሉ። ሩህሩሆዎቹ ታባይ ይሆናሉ። እኔ የተወለዱበትን ቀን እና ወራት
ይዤ አጠቃላይ ባህሪያትን አስልቼ የመሪነቱን ክህሎት ሳስተያዬው ካለተፈጥሮ የሚገራ፤ የሚነዳም ፍልስፍና መሆኑን የግራ ርዕዮት ተረድቻለሁኝ።
ያልመሰለን፤ ያልተግባባን የመጥላት፤ የማግለል፤ በዘመቻ የማሳደድ፤ የማስወገድ፤ ያፈነገጠውን
ማህበራዊ መሰረቱን አናግቶ ለጭንቅት በሽታ
መዳረግ እኮ ያው ጭካኔ ነው። ለዛውም ረቀቅ። ይግደለህ ይማርህ የማይባል። የሰብዕዊ መብት ረገጣም ነው ይህም።
ከርቼሌ ከዚህ ውጭ አገር ቢኖር ደግሞ ቀሪም ተራፊም አይኖርም ነበር። ሁላችንም የዕድሜ ልክ
ታሳሪዎች እንሆን ነበር። ለነገሩ እራህብን ለማያውቀው እራህብ ምንድን ነው ተብሎ ቢጠዬቅ „ራህብ ምንድ ነው“ ብሎ መልሶ ይጠይቃል፤
የማያውቀውን ከዬት ያመጣዋል?
ለቤተ መንግሥት ሰዎችም ሆነ ለደጋፊዎቻቸው ቁስለታችን አይገባቸውም። የወያኔ ሃርነት ገመና አሁን ሲነገር ሁሉም ይደነግጣል፤ ሌላውም በሌላው አግባብ
ያልተገባ ጭቆና ማድረጉ ግን እሰተዛሬዋ ድረስ አሰተዋይ አላገኘም።
ቀድሞ ነገር የሰማይ አምላክ የሰጠን ቸሩን መክሊትን መጋፋት እኮ ተፈጥሮን መቃረን ነው። ለዛውም
የሴት በስንት የጉም ጢስ አልፋ ነው ሴት የፖለቲካ ተጋድሎ የምትጀመረው። በጥቅሉ በሸታም ነው የግራ ፍልስፍና ባይረስ። ጨካኝ አረመኔ
ብጣቂ ርህርህና ሆነ ይሉኝታ ያልፈጠረለት።
አሁን ተመስገን ነው ብናግዛቸው፤ የቻልነውም ብናዋጣ የለመለመ ተስፋ ትውልዱን ይጠብቃዋል። የእኛውስ
አይሆኑ ሆኖ እንደታከትን እናልፋለን፤ ቀሪው ጊዜ አጭር ነውና። ትውልዱ ግን አሁን ባለው ገጭ ገውም ሳይደናገጥ፤ ሳይርበተበት፤ ያ የጣር መሆኑን
በመገንዘብ ከለውጡ ጎን መሰለፍ ይኖርበታል።
አማራጭ ስለጠፋ አይደለም እጹብ ድንቅ መንገድ ስለሆነ ነው። በግልጥም በስውርም ያለው መታመስ የግራ ፍልስፍና መንፈሱ ሞት አፋፍ
ላይ ስላለ አጀንዳ አልባ መሆኑ የፈጠረው መደናበር ወይንም መንቀዥቀዥ ነው። እዬዋለ ሲያደር ግራዎች
ሬሳ ሃሳባቸውን እንደታቀፉ ትንፋሽ ትቋራጣለች።
· ትንፋሽ።
ትውልድ ይቀጥል ከተባለ የትውልድ
መተንፈሻ ቧንቧው ብቻ ሳይሆን ዘመኑ የትውልዱ ስለሆነ ለትውልዱ ዘመኑን መልቀቅ ግድ ይላል። ሁሉም
የራሱን ዘመን ጨርሶ፤ አባክኖ፤ ብቄት አሰጥቶ ነው አሁን ባለው ትውልድ ደግሞ እንደ ለመደበት ጢባ ጢቦሽ ልጫወት፤ እኔ ነኝ አባወራው
እያለ የሚገማሸረው። አሁን ይህ አገላለጽ ራሱ ዴሞክራሲን እንደ ታብሌት ለዋጠ ማር ሲሆን፤ ዴሞክራሲን አልይህ አልስማህ ለሚል ሰብዕና
ግን አሰንጋላ እንቆቆ ነው።
በዬዘመኑ ዕድሉን ያገኜ ሁሉ አልተጠቀመበትም። እነኝህ ፍሬዎች ግን ዘመኑን ለመጠቀም በቂ መሰናዶን
አሟልተዋል። ይህም በደራሽነት ሳይሆን በቀደመ ሁኔታ ትጠቃቸውን ጠበቅ አድርገው በሁለመና ብቃት ላይ ብሄራዊ ፍላጎትን በብቁ ጽኑ
መንፈስ የጋራ ራዕይን ስለጀመሩት ተደማጭ እና አጓጊ ሆነዋል።
ተደማጭ እና አጓጊነታቸው ደግሞ ለእኛ ብቻ አይደለም ሉላዊውም ነው ተወደደም ተጠላም። በጣም በሚገርም ሁኔታ ነው ነገረ ኢትዮጵያን
የዓለም ማህበረሰብ በተደሞ፤ በእድምታ፤ በአክብሮት፤ በአንክሮ እዬተከታተለው ነው - የእኔ ብሎ፤ ያልተወለዱን፤ ያልተዛመዱን በደም
በሥጋ የማይገናኙን ግን መንገዱ የምህንድስናው መሰጧቸዋል። ሰው ከሚለው ማዕክላዊ አውታር ስለሚነሱ። የሃሳብ ስልጡኖችም
ስለሆኑ።
ሁላችንም በዴሞክራሲ በቃሉ እንጂ
በጽንሰ ሃሳቡ አስገዳጅ ህግጋት ውስጥ አልነበርነም፤ ኑረንም አናውቅም። ህግ ተላላፊዎች ስለመሆናችን ቢመርም አጣጥሞ መዋጥ ይገባል። ሰው ነን
መላዕኮችም አይደለንም።
ስለዚህ ዶሞክራሲ ከንድፉ ጀምሮ
ለሁሉም አዲስ ነው። እህአዴግም እራሱ እንደ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁሉ አብሮ እኩል ነው የሚጀመረው። ስለዚህ በላጭም
ተበላጭም የለም። እኩል መጀመር ደግሞ መልካም ነው። እንዲያውም ሁሎችም በአንድ ላይ ስለ ዴሞክራሲ ፍልስፍና የጋራ ተከታታይ ሰሚናር
ያስፈልጋቸዋል ባይ ነኝም። መራራንም ቀምሶ ነው መራራ ማለት የሚቻለው እና።
የሁሉ ጀማሪነት ደግሞ የሥልጣን መንበር አታካች ናፍቆት ለማይንጠው የእኔ ቢጤ ባለቤት አልቦሽ
ባተሌ መልካም አጋጣሚ ነው። አጀማመር ላይ አኩል ይኮናል ማራቶኑን ፈጥኖ ተግባራዊ በማድረግ እና ባለማድረግ ማህል ያለውን ፍፃሜ
ደግሞ ማጠሪያ ማንዘርዘሪያ የህዝብ ህሊና ስላለ ሁሉም አንዳለጠውም
አቀበቱን ተወጣውም፤ ተቋርጦም እንደተለመደውም ቀረ ይታያል። ፈተናው ለሁሉም እኩል ነው። ወይ ማለፈ ወይ ደግሞ ዘጭ።
ልባሙ ጉዳይ እኛም እንደ ወትሮው በአገር ምድሩን ገዦዎቻችን ተቋርጣን ስለማንቀር፤ ተገደበን
ስለማንቀር፤ እንዲህ ለመደበኛ ቅን ታዳሚዎቻችን በተከታታይ ሙግቱን በተለመደው ድፈረት እና እርግጠኝነት እንቀጥላለን …
እንዲያም ሲል በዘንካታው ልሳን በድምጽ ከች እናላለን ማን ጌታ ሲኖርብን እድሜ ለግሎባል ዘመን።
ሁሉም እኩል ባለሚዲያ ነው፤ በማይቻልበት ዘመንም ቢሆን አንደበታችን ታስሮ አልቀረም ቀድመንም ነው የጀመረነው፤ እንኳንስ አሁንና …
· የፈሪነት ወረርሽኝ።
የዲሞክራሲን አፈፃፀም በመሚለከት
ሁሉም ፈሪ ነው። ስለዚህ ከፍርሃት ቆፈን ተወጥቶ ደፋር ሙግቶችን ለማስተናገድ መወሰን በራሱ የመጀመሪያው የዴሞክራሲ
ምስረታ ረድፈኛ ፈተና ነው።
እኔ ተንጠፋጥፎ ባለቀው የሶሻሊዝም የግራ ፖለቲካ ፍልስፍና ላይ ለቅሶ ተቀባይ እና አንጎራጓሪ
ሳንሆን፤ ወይንም ምሾ ደርዳሪ ድንኳነኛ ሳንሆን እያንዳንዱ እራሱን ለማሸነፍ ስንዱነቱን ማሳዬት ይኖርበታል ባይ ነኝ። ተሽሎ መገኘት።
የፈሪነት ወረርሽኝ ስላለብን ግን ዳ እና ቃ የተለመደ ነው። የዝና የሥም የከንቱ ውዳሴ አዝማቾችን መንፈስ ሁሉ ብክል ያደረገ ግራ
ነውና ሥልጣን የሚሉት ጥም ጋር በወጉ አለመዛመዱ ይበጃል - ለጤና።
እያንዳንዱ ከጋብቻ፤ ከሥጋ ዝምድና፤ ከዞግ፤ ከማንፌሰቶ ውግንና እና ትስስር ወጥቶ እንደ ዜጋ
ሁሉን በመንፈሱ የሚቀበልበት፤ ዜጋዬ ነው የማለት እርምጃ ነው ነገን የሚያመጣው ብቻ ሳይሆን የሚያሰነበተውም። ዜግነታችን በ እርቦ እና በሲሶ ተሸንሽኖ እንደባጀው በዛ መጪ ከሆነ ግን አሁንም ግጥ ነው የሚሆነው፤
በሌላ እና በላነበረ ነገር አንዱ ተቺ ሌላው ተተቺ፤ አንዱ ወቃሽ ሌልኛው ተወቃሽ ሊሆን አይገባም
በዴሞክራሲ አፈፃጸም አግባብ ሆነ ነፃነትን ሳይስቱ ለህዝብ ለመስጠት በነበረው ፍላጎት አንጻር። ድርቅ የማተው ወና ነው የነበረው።
ሰብሰባዎች እኮ በተለመዱ ሰዎች ብቻ ድምጽ ነበር ተጀምረው የሚጠናቀቁት። ማድመጥ ብቻ ነው የሚፈቀደው። ይህ መቼም አሊ አይባልም።
ጊዜው አራሱ ትክት ብሎት፤ ስልችት ብሎት ነበር፤ እድሜ ለአማራ ይህልውና
ተጋድሎና የኦሮሞ ንቅናቄ ገላገለን እንዲህ። ያን ችኮ መንቻኮ ጠቀራማ ዘመን።
ጥሪው ለማድመጥ ብቻ ቢሆንም ባልከፋ ነበር፤ መሄድም እስከ ርግጫው ድረስ ማወራረድ ግድ ይል
ነበር። ለማንፌስቶ ማህበር አባል ላልሆኑት፤ ልብ እንዲገጠምላቸው ለማይፈቅዱት እንደ እትጌ ፈንጋጣዋ ሥርጉትሻ ላሉ የቀን ተሌት
ባተሌዎች፤ ፍጥጫውም አለ በተጨማሪነት።
ይህ ደግሞ በሥማ በለው ሳይሆን እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ስለኖርኩበት ማንም ሊያስተረጉምልኝ፤
ማንምም ሊያመሳጥርልኝ ከቶ አይችልም። በዚህ ስሌት የዴሞክራሲ ስሌት የነፃነት ተጋድሎ ግብ ፉርሽ ነው …
ዴሞክራሲ ከቃል ውጪ ማንኛችንም ባደራጀነው የፖለቲካ ድርጅት፤ በምንቆጣጠረው ሚዲያ ሆነ ተቋም
አልነበረም፤ መላጣ ነው ሁሉም
ነገር። ዕድሉን ብናገኝም እኛም ከዛው መዘፈቃችን ትናንት የነበረንበትን የመከራ ዝልቦ፤ ያልሞትን ያልታመመን ሰዎች ሁሉንም
በማዕከል ስንታዘብ የነበርን ተጠቂም የሆን ዜጎች አለንና።
ቀደሞ ነገር ለማስተዋል ደፋርም የለም። ቅንነትም አልፈጠረልንም። ርህራሄ ብሎ ነገር፤
እንግዳ በፍቅር ማስተናገድ ብሎ ነገር አልሰራልንም። ለቅልውጥ እንደተሄደ ገንዘብ ተከፍሎ የሰው ፊት ገርፎን ነበር የምንሳታፈው፤ በቃን ብለን አይዋ ስብሰባን በምህላ እስከ ተሰናበተው እስከ 2015 ጥቅምት ድረስ።
በሌላ በኩል ደግሞ ከብፁዕን የወረደልን በል የተባለን በማለት አይደለም ዴሞክራሲ የሚታጨው፤ የሚታዬውን የሚጨበጠውን ለመወሰን እንኳን አቅም የለም፤ አልነበረም። እውነትን ለመናገር
ድፈረቱም ወኔውም አልነበረም። የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ ለማለት እንኳን አልተቻለም። ዛሬ እጬጌው ዘመን ሁሉን ቁጭ አድርጎ
ገራልኝ እንጂ። ዴሞክራሲ አልነበርንበትም።
ራሱ ዴሞክራሲን ለመመኘት ምኞቱን ለራስ ለመቀለብም እንኳን ፈቃደኞች አልነበርንም። ባልነበረ
ነገር ነበርን ተብሎ የተረብ አዲስ መጸሐፍ ተጽፎ እንደ ሳጅን በረከት ስምዖን መርቁልኝ ካልተባለ በስተቀር።
አሁን አብረን እንጀምረዋለን ያግባባናል፤ ለዛውም ያደቀቅነውን የስደተኛ ወገን መንፈስ ይቅርታ ጠይቃን። በአድሎ
ያጨቀዬነውን የግለት ፖለቲካ ማረን ብለን፤ ተንበርክከን ይቅርታ ጠይቃን፤ በሌለንበት አለን እያልን ወላዶችን መሃን ያደረግንበትን
ኢ- ሰብዕዊ የመንፈስ ድቀት ንስሃ
ገብተንበት ተደብቀንም ቢሆን በተጠረገ ልቦና ‚ሀ‘ ብሎ ዴሞክራሲን ቃሏን መጀመር ይቻላል። መራራውንም ለመጎንጨት መሰናዳት።
ሰብዕዊነት
ከብዙ ነገሮች ጋር የተሳሳረ ነው። ሰብዕዊነት ድንበር የለውም። ሰብዕዊነት በግርድፍ እሰጣ ገባ ወይንም በግብር ይውጣ ግርዶሽ አይለካም
አይመዘነም።
ሰብዐዊነት እኮ የሰውን መብት ተረግጦ አለማያዝ ነው። ሌላው የሚወቀስበት የሚነቀስበት የመብት
አያያዝ እኔም ፈጽሜው ነበር ማለትን ይጠይቃል። አውራነት ለሰብዕዊ መብት ረገጣ ስለመሆኑ እዚህም ሆነን አይተናል፤ ኑረንበታልም።
ብዙ መንፈሶች ደቃዋል፤ ከማህበረሰቡ ማዕቀፍ ተገለዋል። እነ ዶር ታዬ ወልደሰማዕት ከቶ በምን
ይሆን ሥማቸውን ያነሳ ወዮ የሚባልበት፤ ያን ጊዜ አገር ምድሩ ወያኔን
ደግፎ አንጣፊ እና ጎዝጓዥ በነበረበት ጊዜ ፊት ለፊት ወጥተው ሞግተው ዛሬን የሰጡን እኒያ የግንባር ሥጋ ዛሬ
የት ናቸው? ለመሆኑ ሥማቸውንስ ማንሳት ይቻላልን?
በሃሳብ መነጠል እኮ የዲሞክራሲ አንዱ ፍሬ ነገር ነው። ያሰምረዋል ማሳውን እንዲያውም። ይማርካል
ይስባልም። የተነጠለን ሃሳብ አክብሮ መሸነፍም፤ ማሸነፍም የብልጦች ሳይሆን የበሳል ፖለቲካ ሊሂቃን መሪዎች ተግባር ነው። ይህን መቀበል ነው
ዴሞክራትነት …
ውዶቼ „ከበሮ በሰው እጅ“ ሆኖ እንዲህ እና እንዲያ የሚወራጩት መንፈሶች እንዳሻቸው መጪ እንዳይሉ
ማህለቅ ስለሚያስፈልጋቸው ያልነውን ብለናል እኔ ብራናዬ ብዕሬ ሦስቱሽ … ማለፊያ ጊዜ ኑሩልኝ።
ማስተዋል ማለት ራስን መኮፈስ ሳይሆን ዕውነትን መኮፈስ ነው!
አራት ዓይናማው መንገዳችን የአብይ ሌጋሲ ብቻ ነው!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ