ብአዴን ከአቶ ሌንጮ ለታ የተቀባይነት ጠብታ ይለምን።

እንኳን ደህና መጡልኝ።

የ80ሺህ ህዝብ ሰቆቃን
ማነው አማጩ? 

„እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዛብሄርን እፈራ ነበር“
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ፲፰ ቁጥር ፲፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie 
19.02.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።


የሚቀድመውን ማወቅ እንዴት ያለ ብልህነት መሰላችሁ ውዶቼ? ግን እንደምን አላችሁልኝ። እኔ እህታችሁ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።

እኔ የሰኔ16ቱም ግብታዊ የድጋፍ እና የምስጋና ሰልፍ፤ የወርሃ ሀምሌ የሰሜን አሜሪካ የጠ/ሚር ጉዞም፤ መጨረሻ ላይ የብአዴን ጉዞን አክሎ ምቾት ያልሰጠኝ ዕጣ ነፍስ ነበርኩኝ። በሰኔ 16ቱ በቅጡ የተደራጀ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን አቅሙ ከታዬ ጠላት እንደ አሸን እንደሚያፈራበት የታለመ ነበር። 

አደጋውንም አሳምሬ ገልጫለሁኝ ወዮለሽ አዲስ አባባ ብዬም። ስልፉ የአዲስ አባባ የመከራ አምራች ስለመሆኑ አስረግጬ ገልጫለሁኝ። አማካሪም፤ አዳምጫም አልነበረም ያው የገበረ ተገብሮ ቀረ። እንደ ሰማዕቷ ሽብሬ ደሰለኝ ወላጆች ሁሉ አካሉን ያጣም አካሉን አጥቶ ቀረ።  የመሸበትም መሽቶበት ቀረ። የዳመነበት ዳምኖበትም ቀረ።

·       ዝበት እና እርቀት።

የሀምሌው የጠ/ሚር እና የሚያርቧቸው ነፍሶች የስሜን አሜሪካ ጉዞ በሚመለከት ከዛ በፊት የስሜን አሜሪካ እስፖርት ፌስቲባል ለመገኘት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ባሳዩት መልካም ፈቃድ ላይ የነበረው ሳንክ፤ የነበረው የጦፈ ውግዘት የነበራችሁበት ነው። 

እኔም ያን ጊዜ የሚጠቅማቸው እንደሆን ይሳካ፤ የማይጠቅማቸው ከሆነ ግን በጥበቡ አማኑኤል የፈቀደውን ይፈጽመው፤ ግን ተቀናቃኞቻቸው የቅናት አማርኛ ነው የሚያራምዱት ሁሉ ብዬ ጽፌ ነበር። 

እንደዛ በ90 ዲግሪ ተገልብጠው ደግሞ አክሮባቲስቶች አድናቂም፤ ዘጋቢም፤ ሪፖርተርም መሬት ላይ ተነጥፈው ሰጊድ ለኪ ሊሉ አይተናል። አሁን ደግሞ የድል አጥቢያ ደጋፊ ሆነዋል። ይጨርስላቸው እንጂ ፍቅር በፍቅር የአፍ መፍቻ ቋንቋ የፊደል ገበታ እስከ መሆን ተደርሷል። ነገን ያዬ … ያ የምርጫ ነገር መጥቶ ጉዳቸውን ያዬ ሰው

 … ምክንያቱም የአዲስ አባባ ህዝብ ለእስርም ለአደባባይ ጭፍጨፋ የተዳረገበት ቁርሾ ያው ፍደኛው ኢትዮጵያዊነት ያመጣበት ጣጣ ነውና … ያ ጎልቶ እንዲወጣ የሚፈለገው የመሪዎችን ሌጋሲ ለማስቀጠል ብቻ ነው። ይህን ብልሃት ልብ ያለው ያለ አይመስልም። ያ ቅምጥ የኢትዮጵያዊነት ሃብት ወደ ሌላ ካጋደለ ተወዳጅም ተደጋፊም አይደለም። ይህን አሁን የቆዬ ሰው ይዬው …

የሆነ ሆኖ የሰሜን አሜሪካው ጉዞ ጠ/ሚር አብይ አህመድና የፈቀዱት እና የተመረጡት የቡድናቸው አባል ብቻ መውጣት ነበረበት፤ ዶር ለማ መገርሳ ግን አይከን ስለሆኑ እዛው ኢትዮጵያ መቅረት ነበረባቸው። የሀምሌው ዝምታ ሳይገለጽ፤ ሳይነገረን፤ እንደተዳፈን ቀረ እንጂ የዛን ጊዜው ክፍትት ነው አሁን ድረስ እዛው ኦሮምያ ላይ ያለው የእናቶች እንባ ሲፈስ የባጀው። ሌላም የተጠቀለለ አመክንዮም የያዘ ነው። ውስጡ ለቄስ እንደማለት …

 በተለያዩ አካባቢዎች የተደራጁ ቀውሶች አና ብለው ሰው በአገሩ፤ ሰው በባዕቱ እንዲህ እዬተፈናቀለ የሚገኘው ያ ጊዜ የተገደፈው አበሳ ያመጣው ነው። ለዛውም ያን ጊዜ ደንቢ ደሎ ምልክት ሰጥቶ ነበር ለጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ለዶር ለማ መገርሳ።

በተጨማሪም ኦፌኮን አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሶ ሄዶ ቀይ መብራት አብርቶ ነበር። በዛ ላይ በዛን ወቅት በትጋት ሊሰራ የሚገባው ተግባር አሁን ከመሸ ባለፈው ሰንበት ላይ እዛው አካባቢ አብርሃም ወአጽብሃም ተገኙ ተብሎ ተዘግቦ አዳማጫለሁኝ። ለእኔ ብርቄ አይደለም። ይህን የአገሬ ሰው „ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኽ“ ይሉታል። ስንት ነገር ነው የተከሰረው? 

እኔ ጽፌ ነበር ደንቢ ዶሎ የምትፈልገው የራሷን ንጉሥ ብቻ ነው በቅጡ ይታይ፤ ይፈተሸ፤ ይመርምር ብዬ ሁሉ … ስለሆነም የሚቀድመው እዛው ሆኖ የሚያረገርገውን ጉዳይ መልክ ማስያዝ ሲገባ ለሰሞናት አበባ ሁለቱም በጥምረት ሰሜን አሜሪካ ወጡ። አንድ ሚሊዮን ህዝብ ተፈናቅሎ ነበር ያን ጊዜ። ወያኔን ያህል ድርጅትም አስቀምጦ ... ሁሉ ባለው በነበረው መልክ እንዳለ ሆኖ ... 

ከዛ ወዲህ ነው ከ70ሺህ በላይ በቤንሻንጉል መፈናቀል፤ በርካቶች ለሞት መዳረግ፤ ለዘረፋ፤ ለተስፋ ማጣት ምክንያቱ ያ ጠንቀኛው የስሜን አሜሪካ ያመጣው ጉዞ ነበር። ወለጋም የጦር አውድማ ሆና ነው የባጀቸው። የራሷን መንግሥት መሥርታ በጉለሌው ዘውድ ስትመራ ነበር የባጀቸው። የልብ መሸፈቱ ነገር አይሰፈርም፤ አይመዘን። ይህ ጦሱ የስሜን አሜሪካ ጉዞ ነበር። ስለምን? ልባም መካሪ የላቸውምና።

በዛ ጥንካሬ በዛ ብርታት፤ በዛ መጠን ባልተሰራለት ድጋፉ ኦህዴድ ተጉዞ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ኦሮምያ ላይ የባጀው ስጋት ሁሉ በቀነሰ ወይንም በተመጣጠነ ነበር። በሌሎች የአገራችን ክፍሎችም ዘግይቶ የተገኘው አንጻራዊ ሰላም ቀድሞ ይኖር ነበር። በአንድ ንግግር እኮ ነበር ከጽንፍ እሰከ ጽንፍ ጸጥ ያለው የነበር። ግን አያያዝ አጠቃቀም ጠፋ። 

ህውሃትም ምሽጉን ማጠናከሩ የመነጨው በዚህው መዝረከርክ ነው። ብዙ ነገር አምልጧል። ማትረፍ የሚቻለውን ያለውን ለውጡ አላተረፈም። መስዋትነቱም ተመጣጣኝ በሆነ ነበር። ሰው እኮ ብቅል የሆነበት አገር ነው የሆነቸው ኢትዮጵያ። ይህ ሁሉ መከራ ደግሞ የሚገርመው ትግራይን አይነካም። የጻድቃን ማደሪያ ... 

ይባስ ብሎ ያን ድጋፍ ያሰገኘው „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው፤ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን“ ተጥሶ፤ ቃሉ ፍሬም ላይ ተቀምጦ ከኢትዮጵያዊነት ጋር በነበረው እልህ ለጉለሌው መንግሥት የተሰጠው መጠን የለሽ ልቅ ዕውቅና እና የሀምሌው ዝምታ ታክሎ አነጋነገው ሁለመናውን። 

አሁን እንደቀደመው ሁሉ ትግራዊነት ኢትዮጵያዊነትን ተጭኖ ለመውጣት የነበረው ግብግብ ሲያከትም ኢትዮጵያዊነት ለማጣፈጫነት በልሳኑ ብቅ እያደረገ የሚጓዘው አዲስ መንፈስም፤ የወጣበት ድርጅት አባላት ከሊቅ እስከ ደቂቅ ኦሮሞነትን አስቀድሞ ያው መከረኛውን እንግልተኛውን ኢትዮጵያዊነት ለመደቆስ በሚያደርገው ጉዞም አቶ ሂደት እንደለመደበት ከንፈሩን ነፋፍቶ ተቀምጧል። ማነው ባለተራ እያለ ... 

ብልህነት ማለት እኮ ፍቅርን በአግባቡ መያዝ እና ማስተዳደር ማለት ነው። ፍቅር ከሜዳ የሚታፈስ የአሸዋ ጠጠር አይደለም፤ ወይንም ከጓሮ የሚሸመጠጥ የቡና ፍሬ … ፍቅር ለሰጪውም ለተቀባዩም የእግዚአብሄር ምርቃት ነው። ምርቃት ካልተወቀበት እንጥፍጣፊ አልቦሽ ይነሳል …የሰጠውን ያለከበረ ማናቸውም አካልን እና ሃይል የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እንደሞቀ አይቀጥልም። ምዕራብውያን ያዘጋጁት መንግሥት እኮ የግንቦት 7 ነበር። ያ አቅም በ አቅሙ ልክ ያልቀጠለበት ምክንያት የሄደበት የመጫን እና የማናህሎኝነት መንፈስ ከ ኢትዮጵያዊነት ጋር ስላላተመው ነበር። 

የመቱ 10ሺህ ነዋሪዎች ለማን አብይን አማራን እንዳትነኩ፤ ብትነኩ ወዮላችሁ ያለውን ያህል ኦነግን ትጥቅ ማስፈታት እንዴት ተብሎ ሌላ ጨዋታ መጣ … ብዙ ፈተና ነበር ኦዴፓ ያሳለፈው አልተናገረውም እንጂ የውሽማ ሞት ሆኖበት። 

ሻሸመኔ ላይ ታሪኩን ጥቅርሻ ያስገባ ያከሰለም፤ ቡራዩ ላይ፤ አዲስ አባባ ላይ የነበረው ዘመን ይቅር የማይለው ግድፈት ምንጩ እና መሰረቱ የሰሜን አሜሪካ ጉዞ የፈጠረው ክፍተት ነበር። የሚገርመኝ አንዱ ድርጅት ሲወድቅ አዲሱ ባለዘመንተኛ ያ ስለምን ወደቀ ብሎ በሩን ዘግቶ አይመክርም፤ አይዘክርም። 

ኦህዴድ/ ኦዴፓ ራሱ በራሱ ባመጣው የጥንቃቄ ጉድለት፤ የሚቀደመውን በመሳት በመጣ ጠበሳ … ነው ዛሬ ላይ ሰው መንፈሱን እያሸፈት የሚገኘው። ቤትን ማጥበቅ ሲገባ ቤትን ወና አድርጎ ተለቃቅሞ አሜሪካ መውጣት ወቅቱም ሁኔታውም ቢፈቅድም እንኳን አደብ የሚጠይቁ ብዙ ጉዳዮች ነበሩበት። 

ኦነጋውያን አደብ በማስያዝ ረገድም ኦዴፓ የሚፈለግው የጫና ዓይነት ይመሰለኛል። አስገድዶ ብዙ ነገር ለማስፈጸም ቀለቤ ያለው አመክንዮ መሆኑን ነው እኔ እሚረዳኝ። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት እና ኦዴፓ እርቀሰላማቸው የት ላይ እንድልን ግድ ይለናል። በዚህ ውስጥ ነገረ አማራም አለበት። ተዳፍኖ የተያዘ ጉዳይ ... አጃቢነቱ ብቻ ይፈለጋል መብቱን ግን በመጫን ይወራረዳል።  

ተመስጋኙም፤ ተሞጋሹም፤ ዕውቅና የሚሰጠውም፤ ቦታ እንዲይዝ የሚፈለገው ጠረኑን ተከትሎ በዝርዝር ሲከድበት እጅግ የሚያስደነግጥ ግብረ ምላሽ ይሰጣል፤ ለዛውም በዛሬ በጮርቃነት ጉዞ ነው ይህ አስደንጋጭ ዜና ያለው፤ ሲደነድን ደግሞ ቻል በለኝ ነው ... አቅም ቢኖር እንኳን እንዲህ ገመናን ዳር ማስጣት የተገባ ባልሆነ ነበር ... ጥበብ ፈልጊ ጥበብን ማድመጥ ግድ ይላል። ተጋላጭነቱ ክንብንብ አልቦሽ እዬሆነ ነው ... 

ከዛ አልፎ ባልተገባ ልክ በሌለው የራስ መተማመን የሚወሰዱ አጋ የለዩ ደምን የመልቀም ሂደትም የምልዕት ፍቅርን የሚያጠወልጉ ገጠመኝ ነው። ውጭም ኑር፤ አገር ውስጥም ኑር አንተ የእኔ ስለሆንክ ንገሥ ተቀደስም ሌላው ጠባሳዊ ጉዞ ነው። ለዛውም የነበሩት ላይ ቢሆን ምንኛ ሚዛን ላይ በተቀመጠ፤ ግን የሆነውም የሚሆነውም በተገለበጠ ካርቦን መሆኑ የሚያሳዝነን ብትል ዜጎች አለን።

·       „ብልሃት የሌለው ቅላት“

የነበረውን መዋቅር እማትነካ ከሆነ፤ በነበረው መዋቅር ለማስቀጠል ከወሰንክ ጥንቃቄ ከተፈጥሮ በላይ ማመሳጠር ይጠይቅ ነበር። እንዲያውም የፈጣሪ በረከት ታግዞበት ነው እንጂ ከዚህም እጅግ የከፋ አደጋ ነበረው። እርጋታ ያስፈልጋል። ሁሉ ነገር ቢጠቅም እንኳን አደብ ገዝቶ በማስተዋል ነገሮችን መምራት ግድ ይላል አገር እንመራለን ካሉ አብርሃም ወ - አጽብሃም። አብሶ ፈርሃ እግዝብሄርን ከሁሉ በላይ ማስቀደምን ይጠይቃል። ፈጣሪ ያዘነ ለታ ማዕቱ ቻይ የለውምና።

ዘመን ሲሰጥ በልክ መያዝ፤ ዘመን ሲነፍግም በልክ መያዝ ይገባል። እጅግ እያዘንኩ ነው እኔ የትናንቱን የጸሐፊ አቶ ምህረቱ ዘገዬን „ሁሉን እዩ የሚበጀውን ያዙ“ የሚለውን ውስጠ አካል ጭብጥ ሳነብ። መሬት / ባዕት ምን እያለች እንደሆነ አስገንዝቦኛል። 

አያቴ እናቴ ስትነገረን አባዬ መሬትን ስንረግጣ እንጠነቅቅላት ዘንድ ያደርግ ነበር። „አትርጋግጧት“ ይለን ነበር ትላለች። አሁንም እኔ ስራመድ ያን ትውፊት ተከትዬ በህይወቴ ሙሉ በር እንኳን አስጩኼ ዘግቼ አላውቅም እንኳንስ እምመለስባትን መሬትን። ልክ ያለፉ ነገሮችን መግራት በውል ያስፈልጋል … ፈጣሪ እንዳይቆጣ፤ ፈጣሪ ማዕት እንዳይልክ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። የፈጣሪ ቅጣት ደግሞ ረቂቅ ነውና … በተደጋጋሚ ደግሞ እዮር ምልክት አሳይቷል።

·       የቅንጅት ወደል ግድፈት።

የስሜን አሜሪካኑ ጉዞ የአማራር ድርጁነት ይጠይቅ ስለነበር ሁለት ጊዜ መንፈስን ከማባተል እና ለሌላ አደጋ በርን ቧ አድርጎ ከመከፍት ይልቅ ከሆነም አቀናጅቶ ከብአዴን ዶር አንባቸውን አክሎ የስሜን አሜሪካውን ጉዞ መምራት ሲቻል ሌላ ተጨማሪ ግድፈት ደግሞ በማግስቱ ተፈጠረ። ያ የስሜን አሜሪካ ጉዞ አተረፈ የምንለውን ካከሰረው ጋር ስንመዝነው በምንም መልኩ የሰው ልጅን ሞት የሚመጥን አመክንዮ ማቅረብ አንችልምና።

እንዲያውም ሌላ ተከታይ ግድፈት ተፈጸመ። የብአዴን ጉዞን በሚመለከት ሰሚ አልተገኘም እንጂ እኔ ተናግሬያለሁኝ ወቅቱም አይደለምም፤ አስፈላጊም አይደለም ብዬ። አይለም ትናንት ዛሬ ማን ሁነኛ አለው አማራ እንኳንስ ውጪ አገር አገር ውስጥ ላለው አማራ። የፖለቲካ ስልጣን አያስፈልገኝም ያለው ብአዴን ከዚህም በላይ ቅጣት ቢወሰንበት ጎሽ ያሰኘዋል ፌድራል መንግሥትን። አረግራጊ ብቻ ነው የሆነው፤ ወይንም የካቦ ባለሙያ …

ለዚህም ነበር እኔ እባካችሁ ጉዞው ይቅር ብዬ አበክሬ የገለጽኩት። ዋንኛው ለህይወታቸው ሰጋሁኝ። ሌላው ግን በክፍተቱ ሌላ ሴራ እንደሚኖር ተገነዘብኩኝ። ለውጡን የማይፈልጉ ብቻ ሳይሆን ለውጡን የሚፈልጉ ግን የጠ/ሚር አብይ አህመድን ወደፊት መምጣት ብቻ ሳይሆን ዕውቅናው መጉላት የአንጎላቸው ቡጀሌ የሆነባቸው ነፍሶች እራሱ ከፍተኛ ውጋት ነበር እዛው ብአዴን ውስጥ። ጠ/ሚር ሆነ ም/ጠሚ ለመሆን ያለመ ነፍስ ነገም ሌላ አለበት። ድንገቴ ይገጥማል። 

ዛሬ ከሁሉም ቦታ የላቀው ላይ አለና። ሚስጢር ነው ማሸነፍ እንጂ ቀልሃ አይደለም ማሸነፍ። ቤትህን ከፍተህ ሰጥተህ ነገም ወገቤ አይቀሬ ነው። አሁን የጠ/ሚር አብይ ቢሮ ማናቸውም ሚስጢር ከጃውርውያን ሥር ነው ያለው። በጥበብ ይህ ተከውኗል። ብአዴን አፈነግጣለሁ ቢል ጉሮቦውን ያነቀ ሌላ ስንቅርም ተተክሎለታል። ጸጥ ለጥ ረጭ ግድ ይላል … ፖለቲካ እንዲህ ነው። አክባሪውን እንጂ ናቂውን ጉዳዩ አይደለምና …

የሆነውም ይኸው ነው። በማንም በምንም ይህ ሊሳበብ አይችልም። በዛ በልረጋ በሚያረገርግ ክልል ስንት መከራ ነው ራሱ የፌድራል መንግሥት ያቃተውን ሁሉ ጉዳይ ሲጭን የባጀው። በራሱ ክልል የማይሞክረውን ኦዴፓ አማራ መሬት ላይ ነው ጫን ተደል የቤት ሥራ ሲከምር የበጃው። ስለምን? ቢባል የስሜን አሜሪካ በፈጠረው ክፈተት ኦዴፓ ክልሉን በቀደመው መልክ ሃንድል ማድረግ ተስኖት እንደነበር የሚታወቅ ነው።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ በፈጣሪ እርዳታ ቢተርፉም የሆነው ነገር በዛ በከሰረው ስትራቴጂ ሌላ መታመስ ነበር የታዬው … እንግዲህ በነዛ በጣት በሚቆጠሩ ቀናት … መለዬት ያን ያህል የፖለቲካ ኪሳራ ከደረሰ በተዘናጋንባቸው በያንዳንዱ ሰከንድ ምን ሊጠፋ፤ ምን ሊታጣ እንደሚችል አንድዬ ነው የሚያውቀው። መባተሉ መጥበቅ ካለበት በር ላይ ማገሩን በወጉ ከላሰናደሉት እንደ ዲያስፖራው ፖለቲካ እያፈሰሱ መልቀም እዬለቀሙ ማፍሰስ መንገድ ተከታይ ይሆናል ለውጡ ራሱ። ካልቻልክ ለእከሌ አስረክብ ቀጭን ትእዛዝ ከሚረዱት አገሮች አይቀሬ ይሆናል። ማለት የነበረውን ለማጽናት ያለው የ አያያዝ ጥበብ እንብዛም ነውና። አሁን አማራ መሬት ላይ የሆነው ሁሉ ነገር በ አንድም በሌላም እዬተነገረ ታቅዶ የተከወነ ጉዳይ ነበር። 

 ጉዳዩ የቅማንት እና የአማራ ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩ ኦሮምያን ልብ ለማሸፈት በስሜን አሜሪካው ጉዞ በፈጠረው ክፍተት የተሄደበትን መንገድ የተከተለ ነው። ይህን በቅጡ ያደራጁ ልባሞች አሁን የት ቦታ፤ በምን ቁልፍ ሃላፊነት ላይ እንደሚገኙ ደግሞ አስቀድሜ ጽፌዋለሁኝ። "ነገር ቢደጋግሙት በአህያ አይጫንም" ይሉታል ጎንደሬዎቹ ...

መሪው መንፈስ ቢባዛም ቢደመርም የጃዋርውያን መንፈስ የልዕልና ደረጃ ላይ እንዳለ እንስተውላልን። ተውት ጃውርውያን የሚሉ አይጠፉም። ጃዋርውያን ተሸንፎ እጁን አጣምሮ የሚቀመጥ መንፈስ አይደለም። ይህን በተደጋጋሚ ጽፌዋለሁኝ በ2008። በተሸነፈው ልክ በእጥፍ ድርብ ቀንዶቹን ስሎ አሹሎ እስከቻለው ድርስ የማሸንፍ እርካቡን የሚያጠናከር መንፈስ ነው ጃዋርውያን ማለት።

አንድ አዶልፍ ሂትለር ነው ያን ያህል ዓለምን ያመሰው ያተራመሰው። የጃዋርውያን መንፈስን አቃሎ፤ አሳንሶ ማዬት ጅልነት ነው። ለምንም ይሁን የተፈጠረበት አንድ ሚስጢር እንዳለ እኔ አስተውላለሁኝ። 

እንዲያውም እኔ እግዚአብሄርን ባገኘው ስለምን እንደፈጠረው እጠይቀው ነበር ብዬ ሁሉ ብያለሁኝ። ግርጫማ ሰብዕና በትራጀዲ እና በኮሚዲ መሃከል „ሲቃ“ የሚባል አንድ አርት መኖሩን ሁሉ ጽፌያለሁኝ። አሁን በመንፈስ ሥልጣን ልዕልና ያለው እሱ ስለመሆኑ ይረዳኛል። አጅሬ ደግሞ አድብቶ የሚያደርጋትን ያስደረጋል። 
  
ለምሳሌ አሁን አንድ ነገር ላንሳ ከአዲስ አበባ የተለዬ ተጠቃሚነት ይልቅ ስልጣናቸው ካደላለደሉ በኋዋላ፤ የነፃነት ሃይል የሚባለውም አቅሙን ስለሰለሉት የአዲስ አባባ የባለቤትነት ስሜት ገኖ ወጥቷል። ይህ ማለት ከአደማ ወደ አዲስ አባባ ርዕሰ መዲናችን ኦሮምያ ይሁን ነው። ዛሬ በአጀብ ላይ ያለው ኦህዴድ በያዘው እርምጃው ከኢትዮጵያዊነት ህዝብ ፍቅር ቢፋቅ አዲስ አባባን ይዞ ይቀራል፤ ሌላው ይሰደዳል ማለት ነው።

ትግራይ አኮ ይህን ዕድል ያለገኘው አመጹ የተነሳው ትግራይ ላይ ስለሆነ ነው። እሩቅ ነው ለአዲስ አባቤነት ለትግራይ ሊሂቃን ይሁን ለህወሃት። የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግን ያለሰበው በለስ ቀንቶት ኦሮምያ የምትባል „አገር“ አለኝ ለማለት መነሻ ሻብያ እና ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰርቶላቸዋል ኦሮምያ ክልል ብሎ። 

አሁን እኮ አማካሪዎች እነ አቶ ሌንጮ ለታ ናቸው። እንደ ቀደመው ሁሉ። ብአዴን በተዘዋዋሪ አመራር የሚያገኘው ከአቶ ሌንጮ ለታ ነው። ቅርጥምጣሚ ለቃሚ ሆኗል ብአዴን። ይህን መራራ ሃቅ ቢጎመዝዘውም መቀበል ግድ ይለዋል አቤቶ ብአዴን። 

ይልቅ በጣም ነፍሳቸው እያሳሰበኝ የመጣው የአቶ ምግባሩ ከበደ ጉዳይ ነው። እሳቸው የማይፈልጉ፤ እንዲወገዱ የሚፈለጉ ሰው ናቸውና። ስለሆነም በአጋጣሚው ለነፍሳቸው ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ አበክሬ እናገራለሁኝ። መሸኜት አማራ ልማዱ ነው፤ ደመከልብነትም ምርቃቱ …

ኦነጋውያን አዲስ አባባ የእኛ ናት ሲሉ ብትፈልግ በዚህ ባትፈልግ ጥርግ በል ነው ጨዋታው። የተደራጀ፤ የለመ ከተማ አስረክቦ ማናቸውም ዜጋ ውልቅ ነው። ጃዋርውያን የሚነግሩን በተረብ ዛሬ ላይ እናዬዋለን። አሁን ከላይ እስከታች በተጠናከረ መዋቅር እዬተገነባ ነው ኦሮማይነት። ከሁለት ሦስት ዓመት በኋዋላ ሁሉ መልክ ይዞ ጸጥ ረጭ ይላል። አፈንግጣለሁ ሲልም ሁሉም ወደየመጣበት ይሸኛል። የሰሞናቱ ወታደራዊ ትዕይንት ይሁን የኛ ብቻ ሁኑ ስሌላው ግድ አይስጣችሁን ይኸው ነው ቅኔው። ይህ አዬር መንገድ ላይም በሰው ቁስል የሆነ አገላለጽ አዳምጬ ነበር።  

ዛሬ መልክ ያለው ሁኔታ ካልተስተካከለ ሁሉም ወደ ባህርዳሩ፤ ወደ ጅጅጋው ወደ ውልቂጤው ያመራል። ኦሮምያ አዲስ አባባን ይዛ ትቀጥላለች። ይህ ቀምር ዛሬ ላይ ላይገባን ይችል ይሆናል። ግን ነገ ይሆናል። ብአዴን ስልጣን አያስፈልገኝም ትርክቱም ባህርዳር ላይ ወሎን መርቆ ቁጭ ይላል። ገባሪ ወንዝ ነው ሲፈጠር …  

አማራ ክልል ተብዬው ከጉያው እሳት አቅፎ መኖሩን አይደለም ትናንት ዛሬም እለባነነም። ሳጅን በረከትን ሸኝቶ ሌላ ሳጅን በርከትን አጨግይቷል። ይህም ሰውር ገመና ነው።  ሁለቱም ክፍተቶች የተፈጠሩት መቅደም ያልነበረበትን ጉዳይ ቅደመኝ በመባሉ ነው። ሽርሽር ምን ያስፈልግ ነበር? ለእኔ ሽርሽር ነው? 2 ሚሊዮን ህዝብ ሜዳ ላይ አፍሰህ? ሃላፊነት ማለት እኮ ለሚያስፈልግህ ነገር አለመፍቀድ ነው። አማራ ከጅጅጋም፤ ከቤንሻንጉልም፤ ከሽዋም ይፈናቀል ባለቤት የለውም። ዛሬ ደግሞ በተቆረመመው መሬቱ ላይ የመከራ ጩኽት... 

·       ልብ።

የምክር አገልግሎት ስስነትን ክፈትት ይሞሉ ዘንድ ነበር ለዚህ ነበር እኔ ኮ/ ጎሹ ወልዴ አገር ሲገቡ በጠ/ሚር አማካሪነት ፈቃዳቸው ተጠይቀው ይመደባሉ ብዬ ሳስብ ራሱን ማቆም ካልቻለ ነፍስ ምክር እንደጎርፍ እዬተቀዳ አሁንም በስርክርክ ላይ የሚገኘው አዬሩ ሁሉ። ይህን አካሄድ ራሱ ሳስበው ይቀፈኛል። 

ኦነግ በ40 ዓመት ዕድሜው የረባ ድህረ ገጽ፤ የረባ ሚዲያ እንኳን መፍጠር አልቻለም። እንኳንስ የፈለቀ ሃሳብ ሊኖረው ቀርቶ፤ ዛሬም ሥሜ በባርነት ተሰጠኝ እያለ ያለቅሳል። ዛሬም ጤፍ ብላ ተብዬ ተገደድኩ ይላል … ማን ከለከለው ሥሙን ለመስቀዬር ይሁን ገንፎና ጭኮ በልቶ ለመኖር። የፈቀደውን፤ የወደደውን የማድረግ መንገዱ ክፍት ነው … ዘመኑ የ እነሱ ነው፤ እንዳሻቸው የሚናገሩ፤ ያሻቸውን ወንጀል ፈጽመው የማይጠዬቁ ይለፍ የተሰጣቸው ምርጥ ዜጎች ናቸው... አይደለም አገር ውስጥ ውጭ ያለው ገና ሲገባ በስንት ፍቅር እንደሆን ልብ አለን። 


በሌላ በኩል በስል የገባው አሁንም የራስ ተሰማ ናደው ሴራ እዬገዘገዘ ይገኛል። አገር እያተራመሰ ነው ያለው። ይልቅ ባለተረኛው የቴሌቪዥን ተዋናይነት እና አራጊ ፈጣሪነት እያዬን ነው ቀድሞ አቶ ልደቱ አያሌው አሁን አሳቸውን ተክተው አቶ የሽዋስ አሰፋ … የሚገርመው ሁለቱም አማራ ክልል ከሚባለው የተፈጠሩ ናቸው። ለዚህ ነው አማራ የሚፈለገው … በፈረቃ ለማገልገል።

ወደ ቀደመው ስመለስ ሚሊዮን ዶላር ቢፈስ ኮ/ ጎሹ ወልዴን የመሰለ አማካሪ አይገኝም። እኒህ ሰው አይከን ናቸው። ራሳቸውም የ አገር መሪ መሆን የሚችሉ ናቸው። ግን የአብይ ለማ ካቢኔ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ሆኖበት ከሆነ ኮሚሽን ላይ በተራ አባልነት ኤም ቢም እንዳይከፋበት መድቦ ዎህ ብሏለኝ። በፕሮቶኮል መበላላጥ እንዳየወነቀስ ከአዲሱ ፍቀረኛው እና ከሚፈራው ሚደያ ጋር የምርቃት ጉርሻ ማግኘት ደግሞ አሰኘው።

ስለሆነም ሁላቸውንም በእጥፍ ድርብ የሚበልጡት አባ ቅንዬም ኮ/ጎሹ ወልዴም ትዝብታቸውን በልባቸው ይዘው የሚሆነው ሁሉ እንደማንኛችን እዬታዘቡ ይገኛሉ። በቅርቡ ፕ/ አሻግሬ ይግለጡ ያቀረቡት ፕሮፖዛል ነበር የሳቸውም ነገር ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አዲሱ የ አሜረካ ባለሙሉ አንባሳደር የኦህዴድ ኩላሊት አቶ ፍጹም አረጋ ነው የሚያውቁት። ግን ፕ/ አሻግሬ ይገለጡ መስፈርቱን የዘመኑን ያሟሉ ይሆን ነው ጭንቁ። ዕውቅና አሰጣጡ ልኬታ ዝንባሌው ወደ ማን ያደላ ስለመሆኑ በአደባባይ ጎምርቶ እያዬሁ ስለሆነ …

ኮ/ጎሹ ወልዴን ኦሮሞ ስለሆኑ የሚል ምልከታ የሚኖረው የኢትዮጵያዊነት ስሜት የነጠፈበት መንፈስ ብቻ ነው። እያወቁበት አለመሆኑን እያስተዋልኩኝ ነው እንጂ አብይም ለማም እኮ ከኦሮም አብራክ የተገኙ ናቸው። አቅም፤ ክህሎት፤ ችሎታ፤ ብቃት እስካላቸው ድረስ ወገኔ ላለ ኢትዮጵያዊ የሚታዘል ሸክም ሳይሆን እረፍት የሚሰጥ የተስፋ መንገድ ነው።

አገር በመምራት ረገድ ማዕከላዊ ላይ ብሄረሰብ መስፈረት ይሁን የሚል ዝብርቅ ዕይታ የለኝም እኔ። አቅሙ ሁሉንም የማቀፍ ሁሉንም የእኔ የማለት ሁሉንም በትህትና ለማገለግል እስከ አሰበ ድረስ። መታበይን አብዝቼ ነው እምጸዬፈው። ውሸታምነትም እንዲሁ። በቃል አለመገኘት ሆነ ሰንበሌጥነትንም እንዲሁ።

አሁን ኦነጋውያን ዶር አብይ አህመድን የሚያስቡት እንደ ኦሮሞ መሪነት ብቻ ነው። እኔ ግን እንደ ኢትዮጵያዊ መሪ ነው እማያቸው። ዝበቱም የትርጓሜው ምንጩ ይኸው ነው። አጠጋባቸው ያሰባሰቧቸው ሰዎችም እሚያስቡት በኦነጋውያን ልክ ነው። 

አዬሩ እራሱ ኦሮሞ በሉ እንጂ እያለ እያንባረቀ እንዳለ ጸሐፊ አቶ ምህረቱ ዘገዬ ነግረውናል። ለዛውም ለስለስ ብሎ ሳይሆን ጩኽት እንዳለም። እኛም ከዚህ ሆነን እግዚኦ እያልን ነው። ስለሆነም ነው ዶር ብርሃነመሰቀል አበበ „አብይ የኦነግ ወራሽ ነው“ የሚሉን። 

ብቻ እጽዋቶች ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ትንግርቱን በትዕይንት ቢያሳዩንም ምኞቴ ነው።  … ትምክህት በሰባዊነት በተፈጥሯዊነት ላይ ቢሆን የሥልጣኔ ደረጃውን ይገልጠው ነበር። የሚታዬው ግን አራባ እና ቆቦ እዬሆነ ነው …

የሆነ ሆኖ ኮ/ጎሹ ወልዴ እንደ አንድ ሊሂቅ ብቻ የሚታዩ አይደሉም። አንድ ሊሂቅም ብቻ አይደሉምና። አንድ ነፍስም አይደሉም። እሳቸው ሚስጢር ናቸው። ግን „ነብይ በአገሩ አይከበር“ ሆኖ እሳቸው እያሉ ይኸው ይህ ሁሉ ትርምስ ይፈጸማል። ወርቅ እያለህ ትቢያ ልመና ስትቧጥጥ ጀንበር ታዘቀዝቃለች … 

ወደ ቀደመው ምልስት ሳደርግ የሚታዬው ዝበት፤ የንግግር ግድፈት፤ የአፍ ወለምታ፤ በሚቀድሙ እና በሚከተሉ ተግባራት አትኩሮት አለመመጣን፤ ስህተትን ለመቀበል አለመቻል፤ ህዝብን በሚያቆስለው ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍ፤ እኔ ሳስተውለው ሁለቱም ክልሎች አማራም ኦሮምያም ፌድራል ላይም የአማካሪ ችግር እንዳለባቸው ነው።

በሌላ በኩል ኦነጋውያን ለድርጅቶች ሆነ ለግለሰቦች የሚሰጡት ዕውቅና ቦታ ውስጣቸውን እዬሸረሸረ አጋድሞ ለመዝለቅ ያሰበ መንፈስ እንዳለ ሁሉ ሊገባቸውም፤ ሊረዱም አልቻሉም ሽንጣችን ገትረን ስንሟገትላቸው የነበሩት መሪዎች። እኔ ግን ከዚህ ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ሆኜ ዝበቱን እያስተዋልኩኝ ነው። 

·       ግዴለሸነት።

አማራ መሬት ላይ የተፈጸመው ነገር ሁሉ ለጠ/ሚር አብይ ካቢኔ ምኑም አይደለም። የሰጠው ገፋዊ ፍቅርም። የአለው ታማኝነትም። አማራ ሌት እና ቀን ለሳቸው ይጸልያል። ይህም ጉዳዬ ያልተባለ ነገር ነው። አማራ ፎታቸውን በውስጡ ይዞ እንደ አዳኝ መስህ ይዞራል። ይህም ከቁጥር ያልገባ ጉዳይ ነው። ይህ በኦፌኮንም ታይቷል። 

„በቀለ ገርባ መሪዬ“ ይሁን ብሎ የወጣን ህዝብ ዛሬ የኦፌኮን አመራሮች አቶ ሙላቱን ጨምሮ ከአረና ጋር ሆነው ስለቅማንት ማንነት አዲስ ተቆርቋሪ ሆነው ብቅ ብለዋል። ፈንጅ እየረገጠ „የኦሮሞ ህዝብ ደሜ ደሜ ነው ያለው“ አማራ እንጂ አረና  ወይንም የትግራይ ህዝብ አልነበረም። እኔ ከዚህ የከውንኩት ልባም የሎቢ ተግባር ተከድኖ ይቀመጥ።

ለኦሮሞ ሊሂቃን የትኛው ማህበረሰብ እንደሚቀርበው እዬታዬ ነው። አማራ ከሆነ ዘር የደም ይፈለግለታል ወይንም ኦሮምያ ክልል ተወልዶ ማደግን ይጠይቃል። ይህ ራስን የገበረ የቅንነት ማህበረሰብ፤ የሁለመና የኔታ ገድል ምኑም ያልሆነ ጉዳይ ግን ነገ እራሱን ያሳጣዋል ኦዴፓን እራሱን። እርግጥ ነው ዛሬ ዓለም አርግዶልናል እያሉን ነው። ለዛ የተከወነው ቢያውቁ ደግሞ ሌላ ትዕይንት ነው … በራስ ጥረት ብቻ ከዚህ አልተደረሰምና።

በጠ/ሚር አብይ አህመድ ምርጫ ብአዴን ድምጹን ባይሰጥ፤ ጣና ኬኛ ጉብኝትን ባይቀበል፤ በሎቢ የተከናወነው ተግባር ይህ ሁሉ እንክህ እንክህ አይታሰብም ነበር። በዚህ ውስጥ ውለታ ቢሱ ህውሃት የሾለከው። ዘመን ተዘመን አዝሎ አሽኮኮ አድርጎ ለወግ ለማዕረግ ያደረሰውን ማህበረሰብ ከድቶ በፈጸመው ግድፉቱ ዛሬ ዘመንም ሁለመናም ላጥ ካለ ገደል አስቀመጠው፤ ከዚህ መማር ገና በጥዋቱ ኦዴፓ ተስኖት እያዬሁ ነው። ያ ቀን እንዴት ይረሳል? ያ ሂደት እንዴት እንደማበሻ ጨርቅ ተወርውሮ የትሜን ይወረዋራል?

አማራ ክልል ስላለው ማናቸውም ሙሉ እና ድርጁ አቅም የጠ/ሚር አብይ ካቢኔ ይሁን የለማ ካቢኔ በቅጡ በአክብሮት እና የእኔ በሚል እሳቤ አልያዘውም። እንዲያውም እነ አቶ ሌንጮ ለታ ናቸው አማካሪ ሆነው ቁጭ ያሉት። ጃዋር የተሻለ መረጃ ያገኛል ከገባሪው ከብአዴን ይልቅ።

ይህ የታሪክ ግድፈት ብቻ ሳይሆን ራሱንም ያሾልከዋል አውራ ፓርቲ ሆኜ ወጥቼ የአፍሪካ ነብርነቴን አረጋግጣለሁ ለላው ለኦዴፓ። ብአዴንን ኦዴፓ አብዝቶ ንቆታል። ምን ያመጣል ብሎታል። እንዳለም አይቆጥረውም። ከእሱ ቢነጠል ምንም አልመሰለውም። 

ሲዳማ እና አቦ ሌንጮን ለታ ሲያገናኝ ኦዴፓ ብአዴን የእንቅልፍ መሪፌ ወግቶ ነው። የጅጅጋው ግንኙነት እና ምኞትም ስኬቱን በቅንነት ኦዴፓ ያዬዋል ብዬ አላስብም። ማዕከሉ ኢትዮጵያዊነት ለሆነ ነፍስ ግን እዬነጠሉ ሳይሆን አዋህዶ መጓዝ ነበር ትርፉም ስኬቱም። አሁንም አማራ ቀይ መስመር ላይ ነው ያለው።

ስለሆነም ነው የስሜን አሜሪካን ጉዞ ከበሮውን እዬደለቀለት እነ አቶ ገዱን የላከው። ምን አተረፉ እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው? አተረፉ ቢባል እንኳን 80 ሺህ ህዝብ ዕንባ በላይ አይሆንም። በዛ ላይ ብዙ የአማራ መንፈስ የጽናት መቋሚያው እዬተነቃነቀ ነው። ሲወድቅ ነው ሁሉም የሚያውቀው። በሌላ በኩል የመከላከያ ሠራዊቱ ጥገኛ ሆኗል። ልክ እንደ ኦዴፓ። ይህ እኩልነት ታልሞ የተከወነ ነው። 

የብአዴን የተሻለ ቁመና ላይ መሆን ነበር የ4ቱም ድርጅቶች ጉባኤ ሳይሆን የብአዴን ጉባኤ በጉጉት እንዲጠበቅ ያደረገው። እኔ እንዲያውም ሥሙን ኢዴፓ ይበለው ሁሉ ብዬ ነበር።
እኔ ለግንቦት 7 በ2008 እ.ኢ.አ ይህን አበክሬ ገልጨላቸው ነበር። አቅምን በ አግባቡ የማስተዳር አቅምን ... ባሊህ የማለት።  

ከዜሮ ነው አሁን ግንቦት 7 የተነሳው። እራሱ አብርዶ ለማሞቅ ያለውን አቅም ሁሉ በዘመቻ ማንቀሳቀስ ግድ ብሎታል። የሰሞናቱ በሁሉም አቅጣጫ ዘመቻውም ይኸው ነው። ስለምን ወቅት የሰጠውን አቅም በማጣጣል፤ በመጨፍለቅ፤ በመርሳት፤ በማግለል፤ በመሳደድ ተጠምዶ ሌላውን ሲንከባከብ እሱ እራሱ ሾልኮ አረፈው እሰከ አማካሪው ድረስ። የአሁኑ እኔ የሳሙና አረፋ ወይንም ጤዛ ነው። 

ማንም የማይነቀንቀው የመንፈስ ሃብቱን ሁሉ ተራቁቷል የግንቦት 7። ለዛውም እዬተለማመጥ ነው ኦዴፓን እንደገና ከአነ አቶ ሌንጮ ለታ፤ ከአነ ዶር ሌንጮ ባቲ፤ ከእነ ዶር ዲማ  ሥር ወድቆ። ይህ ሞቱ ነው ለግንቦት 7 ሆነ በጥዋቱ ሽንጣችን ገትረን ስንከረከርለት ለነበርነው ሁሉ።

የለማ አብይ ካቢኔም በአፍላው አሁን ያለ ሊመስለው ይችላል። የውጩም የውስጡም ሙቀቱ ስላል ቀስ እያለ ሲሄድ ግን ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር መሰደዱን አላውቀውም። አፋቸውን ሞልተው ጀ/ብርሃኑ ጁላ „የዛ አካባቢ የሚታወቀው በሽፍትንት ነው“ ሲሉ ምን ያህል መንፈስ ከአብይ መንፈስ እንደሚርቅ አልተገነዘቡትም። 

ቅጣትም ወቀሳም ቀርቶ „አተፈርጁትም“ አለበት። ይህንኑ ደግመው ነው ዶር ደብረጽዮን ጠለምት ላይ በነበራቸው ውይይት የገለጹት። ስለዚህ የተግባር ቅንጅት በዬትኛው ህዝብ ላይ አለ ብሎ ማሰብ ብልህነት ነበር ለግርባው ብአዴን።

መቼም የ27 ዓመት ሰቆቃ ግንባር ቀደም አስፈጻሚነት በአንድ ጊዜ የሚበን የሚተን ይመስል እኔ ውሽክ አልኩኝ መግለጫውን ሳዳመጥው በመከለከያ ቀን አከባበር „አትፈርጁት፤ መመኪያችን፤ ዋሻችን“ ሲባል። ገንደውአሃ ላይ ንጹሐንን ስለረሸነ … ስጋቴም የሶሻሊዝም ጋር ፍች መቼ ሊፈጽም እንደሚችልም ርቆብኛል። 

ወታደራዊ ትርኢት እኮ ባህሉ የሶሻሊዝም ነው። አስፈላጊ አልነበረም የሠራዊት ቀን ማክበር። ማንን ለመጫን? ማንን ለማስፈራራት? ማንም ለማስበርገግ? ፍች የለሽ እንቆቅልሽ … ያው በተዘዋዋሪ ግንቦት 20 ተከብሮ አይተናል። ዶር ደብረጽዮንም እንደ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን ትግራይ ላይ መሰሉን አስፈጽመዋል። የሆነ ሆኖ ጥገናዊ ለውጥ መሆኑ ጠፍቶኝ አይደለም፤ ግን ሉላዊ ሚዲያ እና መሆን ላይ ደግሞ የሚያፋጥጡ እውነቶች አሉና። ፋቲክን እምወደው በሉላዊነት አከባበር ላይ እንጂ በዚህ መሰል አመክንዮ አይደለም። 

የሰይጣን ጆሮ ይደፈንን እና ትግራይ እና አማራ ውጊያ  ቢያደርጉ ሠራዊቱ ከማን ወገን ቆሞ ሊዋጋ ነው? ገና ብዙ መስራት አለባቸው። የህሊና አጠባ ከራስ ጀምሮ ብዙ ድካም ይጠይቃል። ገና ነው ሠራዊታቸው። ገና ከልቅ አነጋጋር መታቀብ አልቻለም። ትግራይ ላይ ምን ጎንደር ላይ ምን፤ ሞያሌ ላይ ምን እንደሠራ ፊርማው አልደረቀም።

ጥሩዎች መኖራቸው እኮ እናውቃለን። የጠ.ሚር ምርጫ ሰሞን ከሁለት ተከፍለው ጥበቃ ሲያደርጉ የነበሩ ቅኖች እንደነበሩ ፕሮፖጋንዲሶቶች አያስፈልግም ነገር ግን አማራ ጠላትህ ነው ተብሎ የተደራጀ ሠራዊት ውልቅልቅ አድርጎ የህዝብ ወገን ይሆናል የሚለው የሰማይ መላዕክ ስለሌለ አይወጥም። ገና አልተጀመረም።  

ራሱ የ 7 ሚሊዮን ሃብታሙ ኢህዴግ እና ካድሬዎቹ እኮ እንደኛ በሚዲያ በሚሰሙት ብቻ ነው ታዳሚነታቸው፤ አይደለም ወይ? አሁንስ መከለከያ ከፖለቲካ አቋም ውጭ ነውን? አይለም። ሚ/ሯ እኮ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ናቸው። ይህ ሀቅ ነው። ጠ/የጦር አዣዡ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ናቸው። የሰላም ሚኒስተሯ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ናቸው - ለዛውም የዞግ። እና ኢትዮጵያዊነትን በዚህ ውስጥ ለማምጣት እንዲህ ስለፈለገነው የሚሆን አይደለም። ከባድ ጉዳይ ነው።

የሆነ ሆኖ መከላከያ ዝቅ ማለት ነው የሚበጀው የነበረው። ይልቅ የአዬር ሃይሉ አዛዥ ብናጠፋም ቅጡን ያሉት የተገባ አመክንዮ ነው። ትናንት በመታበይ ዛሬም በመታበይ የእኔ መባልን ማግኘት አይቻልም። በጠበንጃ አፈሙዝ ፍቅር አይገኝም። ዝቅ በማለት፤ በትህትና፤ ራስን በማዋረድ እንጂ …

የሆነ ሆኖ በአማራ ክልል የ80ሺህ ነፍስ እንግልት እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀው ከለውጡ ጋር በተያያዝ ያለፉት ወገኖች እናት አላቸው። እናቶቻቸው የት እንዳሉ፤ ምን መጽናናት እንደሚያስፈልጋቸው ባለቤት የላቸውም። የችግሩ ምንጭ ግን የብአዴኖች ቤቱን ከፍፋተው ተጠቃለው ስሜን አሜሪካ ሽርሽር መሄዳቸው የፈጠረው ክፍተት ነው። ተጠያቂውን የዛ ውሳኔ ባለቤት እና ፈቃጁ ይሆናል። ብአዴንን እና ፌድራል መንግሥት።

·       ዶፍ።

በሰተመጨረሻ የምለው አሁን ሌላ ሞት ጎንደር ላይ ተደቅኗል። ህዝቡ ትጥቅ እንዳይዝ ተብሏል። ትውፊትህን ተውም ነው። ለጊዜው ጥሩ ነው። ግን በሌላ በኩል ደግሞ ትግራይ ላይ ጄ/ ብርሃኑ በሰጡን ሥያሜ መነሻነት „ሽፍቶችን ቀርቶ ፌድራልን አንፈራም“ እያሉ ነው። ሌላ ጭፍጫፋም እንዳለ ነው እኔ እማስበው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያለው ጎንደር ላይ ነው እንደለመደበት። አስፈላጊ መሆኑን ባምንበትም። የሁለት ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀደመውም ምክንያቱም ያው የጎንደር ጉዳይ ነው … ጎንደር በዬትኛው ዘመን እረፍት እንደሚኖራት እጅግ ሩቅ ነው። ዙሪያ ገባው የሚያማትረው ጎንደር ላይ ነው የፕ/ መራራ ጉዲና መድረክ ሳይቀር …

ጎንደሬዎች ልብ ቢኖራቸው መካራቸውን ላለማበራከት ራሳቸውን ለመጠበቅ ቢጥሩ መልካም በሆነ። ምክንያቱም የዞግ ውትድርና ወገኔ የእኔ በማለት እረገድ ሌላ ቦታ ሊሰራ ይችላል ሌላ ክልል ማለት ነው።

 አማራ እና መከራው ግን መቼውንም ይቀራል የሚል እምነት የለኝም። አማራነት ግማድ ተሸከሞ መኖር ነውና። አማራ ከራሱ በስተቀር ባሊህ ባይ የለውም። ይህን ደግሞ ለመጫን እንደተለመደው ሚዲያ ከፍትኩ የሚለው ሁሉ አማራ አገልጋይነቱን እና ሎሌነቱን እንዲቀጥል የአብን መሪዎችን እያጠዳፉ ይገኛሉ። ከራሱ ያላወቀ ማህበረሰብ ቢኖር የኔታ አማራ ብቻ ነው።  

አማራ ተፈናቀለ፤ አማራ ሞተ፤ አማራ አካሉ ጎደለ፤ አማራ በፎቅ ተወረወረ፤ አማራ እንዲመክን ተደረገ፤ አማራ ከዩንቨርስቲ ተባረረ፤ አማራ በ900 ድንኳን እየተማረ ነው፤ አማራ መሬት ጠመኔ የለም …  ይደክማል … 

የአማራ ድርጅት ነኝ የሚለው ብአዴን አድሮ ጥጃ መሆኑ፤ ድልድይነት ብቻ መሆኑ፤ ራሱ የእርግማን ነው። ያን የመሰለ አቅም እና ጉልበት የነበረው ድርጅት አሁን ድረሱልኝ አለ። ይህ ነበር የሚፈለገው። አሁንም ድጋሚ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ። ይህ ክብር ሳይሆን ውርዴትም ውርዴም ነው። መምራት ካልቻልክ ስለምን ትቀመጣለህ? የሚፈለገውም የታሪክ ባለድርሻን እንዲደርቅ ነው።

ያን ያህል ፍቅር እና ክብር የተቸረው አመራር ዛሬ ጭላጭም ጅራትም ሆኖ ቁጭ አለ። ለማሟያም አይፈለገም፡፤ ከሌላ ክልል ጋርም ጥብቅ ያለ ግንኙነት እንዲኖረው ፈቃድ የለም። ብአዴን አይተነፍስ፤ አይሞግት፤ እይሟገት። በእሺታ ድግምት የተተኮሰበታት ሚዳቋ ወይንም እንግዳ አውራ ዶሮ ሆኖ ጸጥ ረጭ አለ። ይህ ሁሉ የመጣው በስሜን አሜሪካ ያልተገባ ጉዞ እንዝህላልነት ነው።

በሁሉም ቦታ እየተገፋ እዬተገፋ ጠርዝ ላይ ደርሶ ሙሉ ለሙሉ የፌድራል መንግሥት ጥገኛ ሆኖ አረፈው ለዛውም የአቶ ሌንንጮ ባቲ ጡረተኛ ወይንም ተጠዋሪ ሆኖ አረፈው። መብቱንም እያሸበሸበ አሳልፎ ሰጠ። አሁን በወታደራዊ አማራር ሥር ወደቀ … ብአዴን - ማፈሪያ!

የሚቀድምን ማወቅ ብልህነት ነው።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።