የአገር መከላከያ ሚ/ር ለማ መገርሳ ራሳቸውን ሾሙ ነው መባል ያለበት።


እንኳን ደህና መጡልኝ
የአገር መከላከያ
 ሚ/ር ለማ መገርሳ ራሳቸውን ሾሙ ነው
 መባል ያለበት።
„ባለጠግነትን አትስጠኝ፤ ነገር ግን የሚአስፈልገኝን
 እንጀራ ስጠኝ እንዳልጠግብ እንዳልክድህም።“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፴ ከቁጥር ፰ እስከ ፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18.04.2019
ከመነኩሲያዋ ሲወዘርላንድ።


እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? የኢህአዴግን ማዕከላዊ ምክር ቤት ስብሰባ እንዴት አዬሽው የሚል መልእክት ደርሶኛል። እንደተለመደው ነው እኔ ያዬሁት።
እንዲያውም የሳጅን በረከት ዳግሚያ ተንሳኤ ብለው ይሻላል። ጠረኑ ሙሉ ለሙሉ ሳጅን በረከት በረከት ነው የሚለው። መድከም አያስፈልግም።

በሌላ በኩል ደግሞ በመስከረሙ ጉባኤም መሰሉን አዳምጠናል፤ መሃል ላይ ደግሞ በህወሃት አሳሳቢነት አንድ ስብሰባ ነበራቸው፤ ያው መግለጫ ወጥቶ ነበር። እንዲህ ተገናኝተው መግለጫ ያወጣሉ። የሚተገበረው ግን በዶር ለማ መገርሳ ምህንድስና ብቻ ነው። ያ የግብር ይውጣ ነው። ወደፊትም በዚህው ይቀጥላል።

ይልቅ አንድ ፖስተር ላይ „ዶር አብይ አህመድ አቶ ለማ መገርሳን ሾሙ“ የሚል ሚዲያ ላይ ተለጥፎ አይሁኝ። ይህ ግዙፍ ግድፈት ስለሆነ ይታረም ዘንድ ነው ይህችን ቆራጣ ጡሁፍ ያሰናዳሁት፤ እንጂ በዬሳምንቱ ለሚናድ ሹመት እና ሽረት ጉዳይ ማድረግ የተገባ አይመሰለኝም። 

„ማን ፈቺ ማን አስፈቺ“ አሉ አቶ ዳውድ ኢብሳ እኔ ደግሞ እንዲህም እላለሁኝ። ማን ሿሚ ማን ተሾሚ ሆኖ ነው? ሾሚውም፤ ሻሪውም ዶር ለማ መገርሳ እራሳቸው ናቸው። እራሳቸውን ይፋዊ ነው የሾሙት፤ ራሳቸው ናቸው ፌድራል ላይ ደግሞ አሰኛቸውና በቋሚነት መቀመጥ አለብኝ ያሉት። ሁሉ በእጅ ሁሉ በደጅ ነው … ዕድሜ ለግርባው ብአዴን …

·     ምኑ ይሆን አዲስ ነገሩ?

የመከላከያ 7ኛ ዓመት ሲከበር እኮ እሳቸው ተናጋሪ ነበሩ ረሳችሁት ወይ? እሳቸው ምን ሲገዳቸው ሲያሻቸው ደግሞ ውጭ ጉዳይን ወክለው ሚኒሶታ ተገኝተው ቆንሲላ ጽ/ቤት መርቀው ይከፍታሉ።

የትግራይ እና የአማራ ሊሂቃን ግብግብ መስመር ለማሳያዝ አባቶች ወደ ተልዕኳቸው ከመሄዳቸው በፊትም ዶር ለማ መገርሳ ነበር ቃለ ምህዳን የሰጡት።
ይህም ብቻ አይደለም የተፎካካሪ/ የተቀናቃኝ/ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ እሳቸው ነበሩ። ዋናው ጠቅላይ እሳቸው በመሆናቸው። ዶር ገዱ አንዳርጋቸውም ዶር. ደብረጽዮን ገ/ሚኪኤን አላየኋዋቸውም። ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚልንም እንዲሁ አላዬሁም።

ከመጋቢት እስከ መጋቢት የጠ/ሚር ባዕለ ሹመት መዘከር ላይም እሳቸው ሚሊዬነም አዳራሽ ላይ ንግግር አድርገው ነበር።


የስሜን አሜሪካውም ጉዞ እሳቸውም ነበሩበት። እሳቸው እኮ ቅመም ናቸው። መጽዳጃ ቤቱ ላይ እንጂ ..

እሳቸው ይልቅ አንድ ጥሩ ነገር በዛው ሰሞን ነገረውን ነበር። ለዛ ሲተጉበት ለባጁት የ አገርን ዴሞግራፊ ምህንድስና ማስተባባዬ ቢጤ … ከጉሮሮ ጠብ ለማይል …  ያው ለዚኽ ሶሞነኛ ይፋዊ ፌድራላዊ ሹመት ሥራ ማስኬጃ መሆኑ ነው … የህሊና ብወዛ …

እንጃ ከጎንደሬዎች ጋር ተጎራብተው እንደነበር አላውቅም „እኔ ብቻ ነኝ ወይ አራጊ ፈጣሪ?“ ብለው ነበር። ይህች ቃል በጎንደር የተለመደች ናት። ከአራጊ ፈጣሪም በላይ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ በመዳፋቸው ነው የለው ምድራዊ አምላክ ማለት ነው። ለዚህም ነው በስንት ጥበቃ የሚንቀሳቀሱት።

ስለዚህ እሳቸው ጠ/ሚር/ መከላከያ ሚ/ር/ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር የሰላም ሚ/ር ናቸው።

ከሁሉም … ደግሞ ፌድራሏን ይወዷታል። ድካሙም ገደሏቸዋል እቴ … አንድ ጊዜ ናዝሬት ሌላ ጊዜ አዲስ አበባ መባከኑ።

እንደ ድሮው ቢሆን ብርቄ ይሆን ነበር የውነት። ሐሤቴም ልክ አይወጣለትም ነበር። አሁን ግን አልሞቀኝም አልቀዘቀዘኝም። እንዲያውም ብርድ ብርድ ነው ያለኝ .. የ ህዝብ ሰፈራ ብወዛ? እና ለብሄራዊ ሃላፊነት ለሉዕላዊነት?!

ያው ኩዴታ ቢጤ ከመጣም ለማገት ነው። ሁሉንም ካልጠቀለሉ እንሱ ይጨንቃቸዋል። ለአፋር መከላከያ ሚ/ርነት? እም ቀድሞም ለግብር ይውጣ ነው። ያው እንደተባለው ሊሚዲያ ፍጆታ።

እነሱ ማንንም አያምኑም። ሌላው ግን የተጀመረው የዴሞግራፊ ፍልስፍና በመከላከያ ያለው የሥራ ድልድል ከቀደመው በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በተከታታይ እና በትጋት ይሠራበታል። 

ሌላው ግን አሁንም መንፈሳቸው ከኦሮምያ አይነቀልም ያንንም በወፍ በረር ከቸች ይሉበታል። ይልቅ „አንሟሟትበታለን“ ያሉትን ቤተ መንግሥት ከሁለት ተከፍሎ እሳቸውም እዛ ቢጠቃለሉ ጥሩ ነበር።  

ወይ የመንጌን ወይ የጃንሆይን አንዱን ርስት ቢያደርጉት መንፈሳቸውም፤ ህሊናቸውም፤ አቅላቸውም ርፍ ይላል … ልምምድ እያደረጉ ለመቆዬትም ወሸኔ ነው።

 … አዋና! … ይፋዊ ጠ/ሚር ቦታው እሳቸውን ስለሚጠበቅ ማለት ነው … የውነት እንዲህ ከሚባትሉም … ከሚሟሟቱበት፤ ማለቴ ሞት ሳይመጣበት ቀድመው መድምደው ገዢ መሬቱን እዛው ሆነው ቢቆጣጠሩ ይሻላቸዋል።

የዶር ገዱ አንዳርጋቸው ጉዳይ ያው ሚዛን ለማስጠበቅ ነው ብዙም ይሰነብታል ብዬም አላስብም … ለምን አትጠይቁኝ ዝምብሎ መንፈሴ ነው እንዲህ የሚለኝ … ስለጤናቸውም እንዲሁ …

ለነገሩ ወንዱ አስቀድመው ከሥር መንፈሶቻቸውን ድርደራ እንደጀመሩ አንድ ዘሃበሻ ላይ ያገኘሁትን ላጋራ  … ዝም ብሎ የሚለቀቅ የለማ ምህንድስና የለም።


ቀንበር አዝለህ ወይንም ተሸከምህ ነው። መታመን በከንፈር በሳቸው ቤት የለም። ከሥር ጉዝጓዝ አለው አንድ ዓይነት ቀለም። እንዲህ …

„የሃገር መከላከያው ሴክተር ላይ ተደረገ የተባለውሪፎርም” – ወንድይራድ ሀይለገብርኤል
April 15, 2019
ሌላም አለ!!!!!
————-
*** የመከላከያንና የገቢዎች ሚንስቴር መስሬያቤትን ያየ በውጭ ጉዳይ የሚንስቴር መስሪያቤት አይቀልድምና ትኩረት ወደውጭ ጉዳይ የሚንስቴር መስሪያቤቱ በአስቸዃይ እንዲደረግ ለመጠቆም እንወዳለን።
===
እንደተባለው ቦታው ለአዴፓ ተሰጥቶ ከሆነ የኦዴፓ/ኦነግ መስሪያቤቱን ማመስ ለምን አስፈለገ? አቶ ለማ መገርሳ የኦቢኤን ስራአስኪያጅ የነበረውን ግለሰብ ጨምሮ ቁጥራቸው ከሀያ በላይ ለሆኑ በኦ/ / / ውስጥ በተለያዩ ሀላፊነቶች ተመድበው ሲያገለግሉ የነበሩ ግለሰቦችን በጅምላ ወደውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያቤት ሊልዃቸው እንደሆነ መረጃ ደርሶናል። አዴፓ ፍተሻ ቢያደርግ መልካም ነው።
===
የምንታገለው ወርድና ቁመታችንን ለሚመጥን ፍህታዊ የስልጣን ክፍፍል መሆኑን መዘንጋት ዋጋ ያስከፍለናል።
ይታሰብበት ለማለት ነው!!!“
ለእኔ ምንም አዲስ ነገር የለውም በሁሉም ቦታ እሳቸው መንፈስ ናቸውና አሉበት ከትግራይ በስተቀር … ይልቅ ዶር. ደብረጽዮን ገ/ሚኬኤል ዛሬ ሽኝታ ላይ ተገኝተው „አካም፤ አካም፤ አካም“ ብለዋል … ወንዳታ¡መሸብለሉን ስታውቁበት … አቤት ምድር ስንቱን ጉድ ተሸከመችው ይሆን?  

የሆነ ሆኖ ከመንፈስ የመከላከያ ሚኒስተርነት ወደ አካላዊ ሽግግር ተደረገ ይባል። ይፋዊ መሆኑ ብቻ ነው የአሁኑ …

ልባቸውም ርግት ይላል። እንደ ቅል ተንጠልጥሎ ነው የባጀው። ቀለሙ ወጥ መሆን ስላልቻለ። ያው ዘር እዬተቆጠረ ከውጭም ከአገር ውስጥም ብቁ ናቸው የሚሏቸውን ሊሂቃኖቻቸውን ወገኖቻቸውን ቦታ የማስያዝ ተልዕኮቸውን አሳምረው ይከውኑበታል ይህ ቦታ ሳሳ ብሎ ከሆነ፤ …

ብአዴን ወንበሩን ከመረከቡ በፊት ሁሉም ነገር መልክ ይዞ ይጠብቃል። ራሱ ቢሮው ውስጥ የደህንነት ስልጡን መሳሪያዎችም ሊኖሩ ይችላል ውጭ ጉዳይ ሚ/ር። የፌስ ቡክን ቲም ኢትዮጵያ ድረስ የጋበዘ መንግሥት … እም! ቆሞስ አንጂነር ስመኘው በቀለ ከመሸኘቱ በፊት የስተዲዮሙ ካሜራ መነቀሉንም እሰቡት። ዋዛ ፈዛዛ የለም በእነ አጅሬ ቤት።

 … ለብአዴን የተሰጠው ቦታም ቢሆን በዓይነ ቁራኛ የሚጠበቅ ነው የሚሆነው … ለማለት። አሁን ም/ጠሚሩን እሰቧቸው? ምን አለ? 

በዚህ ሹመት አዲስ ፍችም ይኖራል ብዬ አሰባለሁኝ። ደጅጥናቱ „ውሃ የበላው ቅል የሆነበት“ ያልተሳክቶም ነፍስ እንዳለመደበት አሁንም "አሞራው በረረ ቅሉ ተሰበረ" ሆኗለኝ።  "ሁለት ያጣ ጎመን፡ ይሉታል ጎንደሬዎች።… „እንትንን ያመነ ጉም የዘገነ“ እንዲሉ …

ያው መከላከያ ቅጠልያ ክፍሉ ነው ብዬ ነው ከጠበለ ጣዲቁ ብራናዬም ትንሽዬ ብዬ ዛሬ እንዲህ ያስኬድኩት … ይብቃኝ … መሰል።

እ … አንድ ነገር እረስቼ ፕሮፌሰር መስፍን እንባዬ „አቀረረ ለማ ሲናገር“ ብለውናል ለካንስ! በዚኽው መልስ ልስጥ እኔ „ለተራበ ትቼ ለጠገበ እዘናለሁ“ የጌዴኦ፤ የቡራዩ፤ የአዲስ አበባ፤ የለገጣፎ እናት፤ ለቀጣዩ ዕንባም ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የተስፋ ቀንበር፤ ለቅርስ ውርስ ቅብረት ዕንባ ያዘለ መከራም ይለቀስ ልቡ ከኖረ … ህሊናው ከቦታው ካለ፤ ለጨፈገገበት አዲስ አበባም …  ይባልለት …

·    ክወና።

ድግስ ላይ የባጀው የአብይወለማ ናዝሬት ላይ እንዲህ እና እንዲህ ይዘናከታል … ከላይ እንደጠቀስኩት ትግራይም ንግግር እያደረገች ነው … ከጎንህ ነን ዓይነት አቤት ማስመሰሉን እንዴት ሰልጥውበታል …

Ethiopia: ሰበር ዜና - ለማ መከላከያ /ር፤ ገዱ ውጭ ጉዳይ / ሆኑ |
በሹመታቸው ላይ በፓርላማው የተነሳውን ተቃውሞ ይመልከቱ
Published on Apr 18, 2019

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በአቶ

ለማ መገርሳ የሽኝት ፕሮግራም ላይ ያደረጉት ንግግር።


ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።