ልጥፎች

የሰማይ ቤት ሸንጎ አፈ ጉባኤያዊት።

ምስል
      አሽካካች።                                    ከሥርጉተ ሥላሴ 14.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዝዬ)                 „አቤቱ በመከራቸው ጊዜ ፈለግሁ፣ በገሰጽሠጽሃቸው ጊዜ ልመናቸውን ወደ አንተ አፈሰሱ።                                             (ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፮ ቁጥር ፲፮“) ጨረሯ ብቻ ደረሰኝ። ምን ደረሰኝ ብቻ አዳረሰኝ። እሷ ግን አትታይም። ስብሰባ ትሆንን ? ወይንስ ሰማያዊ አልጋዋ ላይ ተኝታ … ወይንስ ጫጉላ ጊዜ ላይ ትሆን ወይንስ ከባዘቶማዋ ፍራሽ ተኮፍሳ ? ክብር ሲወድላት -- ደግሞም ሲያምርባትም   የለችም። ብቻ የለችም። ግን አለች ትንፋሿ አገር ያዳርሳል። መንፈሷ ይሆን የሌለው ?  ይሆናል።   ምን ይሆናል ነው እንጂ። ግን ለምን ? … እእ … ለምን …. እ … ለምን …? ጠብቅኳት አልመጣችም። ለእኔ ለእራሱ የላከችው ለብ ያለ ጉድ ነው። ልም ነገር። ስትገርም። ለእናንተስ ይሄው የእኔ ዕጣ ፈንታ ደረሳችሁ ይሆን ? … አላውቅም። ቀና ብዬ ፈራ ተባ እያልኩ ተመለከትኳት …    „ ነገ ሌላ ቀን ነው “    አሃ ! ብላ ጽፋለች። ቀና ብዬ ስመለከት ደግ „ ይህም ያልፋል “   ብላ ጽፋለች ? ጎሽ ! አልኩና ተረጋጋሁ። ግን ለምን ? አላውቅም። ለመሆኑ ያነብበኩትን እርግጠኛ ነውን ? „ ነገ ሌላ ቀን ነው „ ብላ ስለመጻፏ እንደ ገና አዎን እንደ ገና አሻቅቤና ሻቅዬ   ሳዬው ተለውጦ … „ የማይቻለውንም መከራ ቢሆን በትእግስት ቻይው “ ብላ ጽፋልኛለች። ወይ ጉ