እናት የእውነት ቤት።

                                                    

                                                                   
                                                                        ሙሉዑነት
ደግነት         የዋህነት
ገርነት                      ፅናት
ትሁትነት                          ታዛዥነት
ትዕግስት                                         አሳቢነት
ቅንነት                                                   ብልህነት
                               አደራጅነት                                                 ሰብሳቢነት
  ጥላነት                         እናት                         ከለላነት
                              ፍቅርነት                     የእውነት ቤት!                   ፋናነት
ታማኝነት                                                ግልጽነት
ሚሥጢርነት                                         ረቂቅነት
ፍካት                                           ንጋት
አዲስነት                                   ተጋሪነት
ሰባዊነት                             ርግብነት
ባሻነት                      አዛኝነት
መሪነት               ዋቢነት
                                                                        ታማኝነት
  
ሥጦታ ... ለእናት!
·       ሰኔ 3 ቀን 2001 ዓ.ም ሄርሽን ሆቴል ሲዊዘርላንድ።

·       ማስታወሻ።
እንዴት ዋላችሁልኝ የኔዎቹ። ይህ የምታዩት ግጥም ውል ከሚለው ለህትምት ከበቃው የግጥም መጸሐፌ ውስጥ ያለ ነው። ቁጥር አንድ ግጥም ነው። ውል መጸሐፍ ሥጦታው ለቅኒያዊት እናቴ ለእብዬ ነው። እኔ ከምናገረው የጎንደር ከተማ ነዋሪ ይስመስክረው ስለ እሷ ሰብዕና።

በሥርጉተ ፍልስፍና እናት ዓለም ናት። እናትም ለሁሉም ነባቢተ - ማዕዘን ናት ለዚህም ነው ግጥሙን ሥሠራ የእኔ ዓለሜ እናቴ የሁሉም ማዕዘን አውታር ምህዋር መሆኗን ለመግለጽ በዚህ መልክ የሠራሁት።

የውል መጸሐፉ ለእናቴ ሥጦታ ይሁን አንጂ „እናት የእውነት ቤት“ ግጥም ስጦታው ግን ለእናቶች በሙሉ ነው። ይህ ማለት እንደ እናት ሆነው ሌሎች የወለዷቸውን ልጆች በጉዲፊቻ ይሁን እንደ እኔ ሁለመናቸውን ገብራው እህት እና ወንድሞቻቸውን የወላጆችን ሃላፊነትን ወስደው በህሊናም፤ በመንፈስም ብቁ አድርገው ላሳደጉትም ጭምር ነው።

እንደ እነዚህ ዓይነት ራሳቸውን የሚረሱ ቅኖች፣ ቸሮች፣ ደጎች የእናትነት ጸጋ ባይሰጣቸው እንዲህ ዓለማቸውን ለሌሎች ኑሮ ፈቅደው እና ወደው የሚገብሩ ንጹሃን ባልሆኑ ነበር።

ስለ ሰው ቀጣይ ህይወት፤ ስለቀታዩ ትውልድ ግንባታ የእኔ የማለት የቅንነታቸውን ዲካ ለመለካት ሃላፊነቱን ወስደው የመከራ ቀንብሩን ተሸክመው ያሻግራሉ። በኋዋላም  ልጆች ለወላጆቻቸው አገልጋይ እና ተቆርቋሪ እንደሚሆኑ እያወቁም ነው ይህን ገድ የሆነ ተግባር የሚፈጽሙት።

እናትን አባትን በጣምራነት ተክቶ ማሳደግ እጅግ ግዙፍ ፈተና ነው። ቀንበር ነው። ያን ቀንብር ተሸክሞ ያለወለዱትን ልጅ ተንከባክቦ ማሳደግ ለፍቅር ተፈጥሮ የሚከፈል ዋጋ ነው። እናትነት ከሃለፊነቶች ሁሉ የገዘፈ ነው። እናትነት ቁሳዊነት አይደለም። እናትነት የህሊናን መሰናዶ ይጠይቃል። አብሶ የሰው ልጅ ሲያሳድጉ ድካሙ አስተዋሽ አጥቶ፤ ያ የመከራ ዘመን ተረስቶ ከንቱ ቢቀር የሚመጣውን ሰቀቀንም አስቀድሞ ተጸጻች ላለመሆን ስለመወስኑ መቁረጥ በእጅጉ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ቢሆን ተብሎ ካልታሰብ ነፍስን ከሁለት ይሰነጥቃልና።

„እንሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል። ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጓልና ስሙም ቅዱስ ነው። ምህረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።“
( የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ከቁጥር ፵፱ እስከ ፶፩)
ሥርጉተ© ሥላሴ 










አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።