ፍቅር #ተፈጥሮ #ግሎባል #የትምህርት #ካሪክለም #ሊነደፍለት ይገባል።

"የደጋግ ሰወች ልጆች ስሙኝ በረድኤት ታደሱ፤ አበባ በምድረ በዳ ጠል እንዲያብብ እንደሱ አብቡ። (በረድኤት ታደሱ)
ዬሽቶ ማዕዛ ደስ እንደሚያሰኝ ማዓዛ ትምህርታችሁ እንደዚያ ደስ የሚያሰኝ ይሁን።"
 
አሜን ብዬ ልጀምር።

 
ፍቅር ተፈጥሮው ጥልቅ ነው። የዛሬ 7 ዓመት አንድ የጀርመን አውሮፕላን አብራሪ ፈቅዶ ከተራራ ጋር አውሮፕላን አጋጭቶ እሱን ጨምሮ ወደ 150 ሰወች አጠፋ። ፈጀ። 15 ቀን CNN ዘገበው። ሬሳው ከአውሮፕላን ላይ ሰው ተንጠልጥሎ ለቀመው። እጅግ አሰቃቂ ነበር። መተኛት መመገብ አቃተኝ።
ከዛ የሰውልጅ ክፋነትን ከምን አመጣው የሚል ምርምር ቤቴን ዘግቼ ሰራሁኝ። ከማህፀን እና ከአብራክ አለመሆኑን ተረዳሁ። ዬሰው ልጅ ሲፈጠር ንፁህ ሆኖ መፈጠሩን ለራሴ ሙግት መልስ አገኜሁ።
ሁለተኛ ደረጃ አቅጣጫዬ ዬሰው ልጅ ከአብራክም ከማህፀንም ክፋትን ካልተማረ ከዬት ዬሚለው ሆነ ፍለጋዬ። መልሱ ከቤተሰብ፤ ከማህበረሰብ ዬሚል ሆነ።
ለምን ዬሚለውን ሦስተኛው ጉዞዬ አንድ ጭብጥን ሸለመኝ። ዬሰው ልጅ ሲፈጠር ሙሉ ሆኖ ሲኖር አንገቱ ተቆርጦ። ማዘዣ ጣቢያ አልባ። መኖር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞተር ዓልባ። ፕላኔታችን አሳሰበችኝ። ነገ አስጨነቀኝ።
ምክንያቱ ቀላል ግን ትኩረት ያላገኜ። ለክፋ ነገር ማርከሻ አልተሰራለትም። ክፋ ነገር ካለ ዬሚመክት ዬደግነት ትምህርት ቤት ሊኖር ይገባ ነበር። ያ ደግሞ ዬፍቅር ተፈጥር ካሪክለም ተሠርቶለት በመደበኛ ዬዓለም ዜጋ መማር አልቻለም።
ዬፍቅር ተፈጥሮ ኮሌጅ፤ ዩንቨርስቲ፤ ኤክስፐርት፤ ሳይንቲስት፤ ፈላስፋ፤ ሙዚዬሣ።ም፤ ሚዲያ፤ መጋዚን፤ ግሎባል ቀን፤ ዬመንገድ ትርዒት ዬለውም። ዓለም በዘመኗ በፍቅር ተፈጥሮ ህግጋት ላይ አጀንዳ ቀርፃ ተወያይታበት አታውቅም። እና ዓለም ዬስጋት የፍርኃት ሰማይ እና ምድር ሆነች።
እያንዳንዱ ልጅ ዬአገሩን ህገ መንግሥት እና ዓለም ዓቀፋን ዬሰባዕዊ መብት ዬታህሳስ 10/1948ቱን በመደበኛ መመማር ቢችል መብቱንም ግዴታውንም ዬሚያውቅ ዜጋ ይኖር ነበር። ወንጀለኞች በማያውቁት ህግ ነው ወንጀል ሠርተው ዬሚቀጡት። ይህ አገላለፄ ሊከብድ ይችላል።
ብቻ ወደ ፍቅር ተፈጥሮ ሂደት ዓለማችን ምን እንደምትመስል ጎጎልኩት። አንድም ተቋም ዬለም። አንድም ህግ እና ሥርዓት አልተደነገገለትም። እርግጥ አሜሪካ የአሚሽ ማህበረሰብን ለናሙና መውሰድ ይቻላል የራሱ ቅብዓ ቢኖረውም። የራሱም መለያ ቢኖረውም።
ዓለማችን ስንት የጦር መሳሪያ ማምረቻ ፋፍክሪያ፤ የባለሙያ ስልጠና ባጀት አላት???? ስንትስ ጦርነት አስተናገገች? መፍትሄው በጦር መስመር ሰልጥኖ ሥልጣኔን ማውደም ወይስ ስልጣኔን ማሰልጠን።
ይህን ጭብጥ ዬያዘ አቤቱታ ለቀድሞው አባት የተመድ ፀሐፊ እና ለአውሮፓ ህብረት ላኩኝ። ለፍቅር ተፈጥሮ ካሪክለም ይዘጋጅለት። ዓለም አስፈርታኛለች። ዬሰው ለሰው መገናኛው ክፋት ሆነ። በሌላ በኩል የማሽን ትውልድም ዓለምን ያሰጋታል። ስለዚህ ሰውነትን በደግነት ለማነጽ አናፂ ሥርዓት ይዘጋጅ ብዬ ሞገቱኝ።
ሁለቱም በአድራሻዬ መልስ ጣፋልኝ። ተግባር ግን ዬለም። መጨረሻ አስር ስሎጋን ንድፍ ሠርቼ በቢዲዮ እንዲቀረጽ ስጠይቅ ደሃ የማይችለው ሆነ። ከዛ ለምን ለመነሻ የሚሆኑ የቃላት አለርሞችን የምሠራበት ዩቱብቻናል አልከፍትም ብዬ ጀመርኩ። እኔ ስሞት አንድ ሰው ሃሳቡን ሊያስቀጥለው ይችላል።
አንድ ታማሚ ሳህን ሙሉ ታብሌት ላኩልኝ። ለምን ስላቸው እምትሰሪው ነገር ያጽናናኛል አሉኝ። በመሃል ጥልቅ ሃዘን ገጠመኝእና ያን ከበድ ያለ ማሰብን ዬሚጠይቅ ፕሮጀክቴ ቆመ። ንድፋን ማርቆስ ላይ ቀለል አድርጌ ለመጀመር ከሁለት ሰወች ጋር ተስማማሁ። ባጋጣሚ ሁለቱም ታመሙ። እና ቆመ። ማርቆስን የመረጥኩት ዬሰላም ማዕከል ስለሆነ ነበር። የህዝቡም ጥንካሬ ቅኔ ነው።
ዬፍቅር ተፈጥሮ ህግጋት = ዕምነት
ዬፍቅር ተፈጥሮ ህግጋት > ማህበራዊ ሳይንስ
ዬፍቅር ተፈጥሮ ህግጋት > ተፈጥሮ ሳይንስ
ኢትዮጵያ ላይ ያለው ድቀት ዬህሊና መዳኛው ይህ ይመስለኛል። የዓለም ግብግብም እንዲሁ።
የፍቅር ተፈጥሮ ተፈጥሮን አድንቆ መነሳትን ያጠይቃል። የገዘፈ ነው። ተዝቆ ዬማያልቅ የዕውቀት ማዕዶት ነው። ሙያም ፍልስፍናም ዊዝደምም ነው ለእኔ።
አብረን ቆዬን።
እነ ማህበረ ቅንነት መሸቢያ ጊዜ ይሁንላችሁ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/12/2023
ፍቅር ፏ ያለ ጎዳና ነው።
ፍቅር ፍንትው ያለ ዬአብሮነት እልፍኝ ነው።


 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።