የአማራን ህዝብ በጥበብ የማራቆት ጆኖሳይድ።

 

የአማራን ህዝብ በጥበብ የማራቆት ጆኖሳይድ።
 

 
#ኢዜማ እንደ ድርጅት ይህን የአለቃውን ሁነት ያወግዛዋል ወይንስ እያንቆረቆረ ፁዑም ብሎ ይጨልጠዋል?
እኔ ፕሮፌሰር ብርኃኑነገ ይህ ቦታ ሲሰጣቸው በሌላ የሚኒስተር መ/ቤትቢሆንፍላጎቴ ነበር። ጠቅላይ ሚር አብይአህመድ በቀላቸውን የሚወጣላቸው ልካቸውን መርጠው የሰጡት ቦታ ስለመሆኑ ጽፌያለሁ።
እርግጥ ለወቀሳ አልደፈርኩም። በሂደት መታዬት ይገባው ስለነበር። ተግባሩን ሳይረከቡ መወንጀሉን አልፈቀድኩትም ነበርና።
~~~~\\\~~~~~~
"አቶ ምትኩ ምንካሰው እንደዘገቡት የጠበቃ ኡስረስ ዳምጤ መልዕክት።
የዘንድሮ የ12 ክፍል የማትሪክ ውጤት እና የመግቢያ ነጥብ እንደገና መከለስ ያለበት ነው።
👉🏿 አብርሃ ወአፅብሃ መሰናዶ ት/ቤት (መርጡለ ማርያም) 162 አምጥተሃል የተባለው አማኑኤል ፀሐይ በቅሬታ ሲታይ 647 በማምጣቱ የሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል።
👉🏿 አዴት መሰናዶ 150 አምጥተሃል የተባለው ተማሪ ውጤት እንደገና ተመርምሮ 618 ሁኖ ተገኝቷል።
👉🏿 ቲሊሊ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 140 አምጥተሃል የተባለው ተማሪ ውጤት በድጋሚ ሲመረመር 601 ሆኖ ተገኝቷል።
👉🏿 ደቡብ ወሎ ልጓማ ትምህርት ቤት 140 አምጥተሃል ተብሎ ውጤቱ በድጋሚ ሲታይ 601 ሆኖ ተገኝቷል።
👉🏿 ውጤታቸው በድጋሚ ባይመረመርም ታናሽ ወንድሜን ጨምሮ በርካታ የደረጃ ተማሪወች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አላመጡም።
------
በጦርነት ቀጠና ውስጥ ለቆዩ የአማራ ተማሪወች ልዩ ድጋፍ መስጠት ሲገባ እንዲህ ዓይነት አሳፋሪ ስራ መሰራቱ በአጋጣሚ የተፈጠረ ችግር እንደማይሆን ይገመታል። ነገሩ የተማሪወቻችንን ስነ-ልቦና በእጅጉ የጎዳ እና ትውልድን የመግደል ውጤት ያለው ነው።
በእርግጥ ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በ"North-South" ቅኝት ለሚመለከት እንደ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ዓይነት ሰዎች ይህ ነገር "የተዛባ ግንኙነትን የማረም ፕሮጀክቱ" አካል ሊሆን ይችላል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ማተቤ ታፈረን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ችግሩ እንዲስተካከል በመታገል "ትውልድ ከማምከኑ ወንጀል" ራሳቸውን ያነፃሉ ብለን እንጠብቃለን።
አስረስ ማረ ዳምጤ ( ጠበቃ)"
~~~~~\\\~~~~~~~
*** ፎቶው የጸሐፊው ነው። በተለይ የሁለት ሰብዕናወች ፎቶ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/02/2022
#ካህዲን የመሸከም ትክሻ በቃን ይጠጣ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።