#ኮፒ ራይት የማይጠዬቅበት የተጋድሎ ዘርፍ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ብቻ ነው።
ግንስ አንዳቸውም ከሞት መታደግ፣ ከመፈናቀል ማስቆም፣ ከመታረድ መታደግ አልተቻለም። የ40 ዓመቱ መከራ በአራት እጥፍ ተመንድጓል። ዘመናት መሠረት የያዙ ማናቸውም ትውፊት እና ትሩፋት አይሆኑ ሆኖ ከስሏል።
በዚህ ለመቀጠልም አልተፈቀደለም። የመስተዳድሩ ፕሬዚዳንት ዶር አብይ አህመድ በአዳዲስ ቀውሶች #የሚያርሱት አልበቃ ብሎ ሌላውም ተደርቦ ጥልቅ እያለ መከራውን በእጥፍ ድርብ ያነባብረዋል።
ተግባር ላይ ያሉት ደግሞ ድምጣቸውን አጥፍተው ይተጋሉ። ሌላውወይ ሲወድቅ፣ ወይ ማህበራዊ መሰረቱ ሲሳሳ ሄዶ ይዶላል። እናም ዕዳ ከሜዳ ሆኖ ጠንቅ ሆኖ እንደ አርበኛ አስቻለው ደምሴ አደናው፣ እርሸናው፣ እስሩ እንግልቱ ቀጥሏል።
አላያችሁም ጎንደር ሀምሌ 5/ 2008 አብዮት ሲፈነዳ እነ ዋዋ አርበኛ ጎቤ ያን የመሰለ የተደላደለ ኑሯቸውን ትተው ሲደርሱለት። ያንጊዜ "ኢዜማ፣ ባልደራስ፣ አብን፣ "ብልፅግና፣" ህብር ወይንም ኢኃን" ነበሩን?
አሁን እነሆ ከፖለቲካ ድርጅት ጋር ወስደው ዘፍቀው ተው እያልኩ እዬተናገርኩኝ በግራ በቀኝ እዬታደነ ይገኛል። አዝናለሁኝ። እጅግ አድርጌም እምምምም ብዬ #አምጣለሁኝ።
የአማራ ፖለቲካ ግን ያገኜ በፈለገው ሰዓት፣ በወደደው ወራት እንደ አሻው ይወራኝበታል። ያ ባልከፋ። የሚያሳዝነው ስበቡን ተከትሎ የሚመጣው ማትን መግታት አለመቻሉ ነው።
የዜግነት ነኝ የሚለውም ሌላው ማህበረሰብ አይደለም መነሻውም መድረሻውም ያው መከረኛው #አማራ ነው። ዜግነት በሌለበት አገር አማራ ብቻ ይህን እንዲሸከም ኢትዮጵያዊነትን ብቻ እንዲከበክብ ይገደዳል።
ባይባልም ቢባልምየተገራው የአማራ ህዝብ ልጆቹን የሚያሳድገው በሚስጢሩ ትርጓሜ ልክ ነው፣ ያውም ከበቃ ጨዋነት ጋር።
የሆነ ሆኖ አያልቅ ሥም እዬያዛችሁ እዬመጣችሁ አታባክኑት። ተውት! እባካችሁ ተውት። እባካችሁ ታቀቡ። መሬት እዬደበደባችሁ ማት አውርድለት ብላችሁ አትወኩት። እያሳደናችሁት፣ እያስጨረሳችሁት ነው።
ሰላሙን አውካችሁ ስጋት እና ውጥረት እምታነግሱበት እናንተው ፖለቲከኞች ናችሁ። 30 ዓመት ተሞክሮ በከሸፈ መከራ አሳሩን አታብሉት። ሁሉን ተቀምቶ፣ ሁሉንም ተነጥቆ ዛሬም አንተው ተማገድልን ከወንጀል በላይ ሃጢያት ነው።
ሞጣ የታመሰው የተቀጠቀጠው #በራስሰራሽ መከራ ነው። በኮፒራይት ሽሚያ ስትንደፋደፋ ህዝቡን አስጨረሳችሁት። ነገም ይቀጥላል። ሁሉም ተራውን እዬጠበቀ ነው።
የፋኖ መሪወች ብቻ ሳይሆን በአጋዥነት የሚጠረጠሩት ሁሉ ነገ ይጠበቅ። አንድ ተስፋ ቢኖር እሱንም ቀረመት ላይ ዋለ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/03/2022
"አማራነት ይከበር!"
አማራነት ይለምልም!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ