#ህፃናትን ወደ እርጅና የቀዬረ ገመናዊ ዘመን። ሎቱ!
#በዚህ ውስጥ አለን ወይንስ የለንም?
የማይበወዝ፣ የማይቀረፍ፣ የማይሰነጠቅ፣ የማይዘረፍ፣ የማይናወጥ ምን ነገር ሲኖር ገዳ እና ጽልመት ተፈጥሯዊ ናቸውና። የአናርኪዚም መናህሬያ ቀውስ ባጀቱ እራቱ።
ማህበረ ቅንነት እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? አባ ቅንዬ አቶ ሰለሞን ኃይሌን አላዬሁም። ዕልፍኛችን ብርድ ብርድ ይለዋል፣ እሳቸው ከሌሉ። ባሉበት ደህና ታድርግልን ድንግልዬ። አሜን።
ነገረ ድርቅ ጉጂ፣ ሱማሌ፣ ነገሌ ቦረና፣ ዋግ ህምራ እንደምን እዬሆኑ ይሆን? ዋግ ህምራ? በግራ በቅኝ እዬተቀጠቀጠ ነው።
#አፋር እና አማራ ትንፋሻቸው እንዴት እዬሆነ ነው።
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲም ቁንጣን ያላስቻላቸው እያተራመሱት ነው። ማን ይሆን ተባራሪው?
ግን እናንተስ የገዳወኦዳ ኢንፓዬር የወሩራ ጽንፍ እንዴት ይኳችኋል? አስምሌሽኑ፣ ዲስክርምኔሹን ገና ጫፍጫፋን ነው። ወደ ዋናው ምዕራፍ አልተገባም። ጥናት መቀነቱን ለሁላችን ይስጠን አሜን።
ግን የትኛው የፖለቲካ አቅም ይህን ሁለገብ የገዳኦዳ ወረራ፣ መስፋፋት፣ አስምሌሽን፣ ዲስክርምኔሽን መቋቋም ይችለው ይሆን? በብትን ትርትር ጉዞ?
#መጥኔ ለኢትዮጵያ!
#መጥኔ በዬዘመኑ ዕድሜውን በግፍ ለሚነጠቅ የአገሬ ወጣት፣
#መጥኔ ለእኛ ዘመን ለዘመን ከውድቀት ወደ ውድቀት ለሚንከባለለው ፖለቲካ አብረን ለምንዳክር።
አይዞን። ፈጣሪ ብቻ እንማጠነው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/03/2022
እንበርታ! አንዛል!
ህፃናትን ወደ እርጅና የቀዬረ ገመና!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ