ልጥፎች

በትምህርት እገታ የተደራጀ ዲስክርምኔሽት 4 ዓመት ሙሉ ተከውኗል። ባሊህ ያለው አልነበረም።

ምስል
በትምህርት እገታ የተደራጀ ዲስክርምኔሽት 4 ዓመት ሙሉ ተከውኗል። ባሊህ ያለው አልነበረም። እኔ ብዙ ፅፌበታለሁኝ። ቦታው እራሱ ትምህርት ሚኒስተር የግርባው ብአዴን ነበር። ተቀምቶ ለመንጣሪው ተሰጥቷትል። ~~~~~~\\\\~~~~~ የሆነ ሆኖ …… አቶ ደግሰው አላምረው እንደ ዘገቡት። ይድረስ ውጤት ለቀረባችሁ የአማራ ልጆች፣ ሼር ፖስት አድርጉት "ይህ የምትመለከቱት አማኑኤል የተባለ ልጅ ከመርጦ ለማርያም ፣ እንዲህ በትግል ውጤቱ ድጋሜ እንዲታይ አድርጎ የሆነውን እዩ።" "አላለፍኩም ብለህ እቤትህ እጅህን አጣጥፈህ አትቀመጥ ፣ አንተም ጠይቅ ፣ የሆነውና የተደረገው ሆን ተብሎ ነው። ሰብሰብ ብለህ በየወረዳህ መብትህን በራስህ ተደራጅተህ እስከጥግ አስከብር።" እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17/03/2022 #በቃ ሆይ! መቼ ትመጣለህ!  

በእውቀትም #ግዞተኛው አማራ ዬደንቢ ደሎ ትራጀዲ መቀጣጫ ነበር።

ምስል
በእውቀትም #ግዞተኛው አማራ ዬደንቢ ደሎ ትራጀዲ መቀጣጫ ነበር።   #ውጤቱን አንቀበልም የሚል ሰላማዊ ንቅናቄ ይጠይቃል። ይህ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የበቀል ዋንጫኛሞችን ተዋናይ ማድረግ የምጠብቀው ስለሆነ አይደንቀኝም። አማራ ጆኖሳይድ በሁሉም ዘርፍ ይታይ ዘንድ ስጽፍ ባጅቻለሁ። የአማራ እጩ ሙህራን እገታ ጆኖሳይድ ነው ለእኔ። የትምህርት ውጤት በረጅም ጊዜ ነው የሚታዬው። አራት ዓመት ሙሉ አማራ ከዕውቀት ውጪ በግዞት ላይ ይገኛል። ይቀጥላልም። ይህን የገዳኦዳ ሥርዓት አናቱን በጥብጦ የሚንደው ካልተገኜ በስተቀር። ለዚህ ነው እኔ #HR 6600 ከውስጤ እምደግፈው። ናልኝ እምለው። ውስጤ ነህ የምለው። ~~~~~\\\~~~~~~ ከአቶ አዲሱ እንጎቻው። " #የትምህርት ሚኒስቴር ጉድ በድንጋጤ ኩም ሊያደርገኝ ነው:!" ____+____ "በምስራቅ ጎጃም ዞን መርጦለማሪያም ከተማ የሚገኘው አብርሃዋፅብሃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰደው አማኑኤል ፅሀይ ወንድም የተባለ የተፈጥሮ ሳይንሰ ተማሪ ከ700 አጠቃላይ ድምር ውጤት 164 አምጥተሃል ተባለ:ከዚያም ልጁ ጎበዝና በሀገርአቀፍ ደረጃም ሰቃይ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ በመሆኑ በውጤቱ ተደናግጦ online ቅሬታ አቀረበ:ቶሎ ሊሰተካከልለት ባለመቻሉ ፈተናዎች ኤጀንሲ በአካል ቀርቦ ሲያሰመረምር ትክክለኛ ውጤቱ *647*ሆኖ ልክ እንደተገመተው ከፍተኛውን ነጥብ ማሰመዝገቡን አረጋገጠ::" ___ "በምዕራብ ጎጃም ቲሊሊ ከተማ 140 አምጥተሃል ተብሎ የነበረ ተማሪ ቅሬታ አቅርቦ ሲመረመር 601:እንደዚሁም አዴት ከተማ 160 የነበረ ውጤት 618 ሆኖ ተገኝቷል:ሦሰቱ ጎበዝ ተማሪዎች ቅሬታቸውን በአካል በማቅረባቸው ውጤታቸው ተሰተካከለ:ምናልባት መምጣት ባይችሉ ኖሮ

የአማራን ህዝብ በጥበብ የማራቆት ጆኖሳይድ።

ምስል
  የአማራን ህዝብ በጥበብ የማራቆት ጆኖሳይድ።     #ኢዜማ እንደ ድርጅት ይህን የአለቃውን ሁነት ያወግዛዋል ወይንስ እያንቆረቆረ ፁዑም ብሎ ይጨልጠዋል? እኔ ፕሮፌሰር ብርኃኑነገ ይህ ቦታ ሲሰጣቸው በሌላ የሚኒስተር መ/ቤትቢሆንፍላጎቴ ነበር። ጠቅላይ ሚር አብይአህመድ በቀላቸውን የሚወጣላቸው ልካቸውን መርጠው የሰጡት ቦታ ስለመሆኑ ጽፌያለሁ። እርግጥ ለወቀሳ አልደፈርኩም። በሂደት መታዬት ይገባው ስለነበር። ተግባሩን ሳይረከቡ መወንጀሉን አልፈቀድኩትም ነበርና። ~~~~\\\~~~~~~ "አቶ ምትኩ ምንካሰው እንደዘገቡት የጠበቃ ኡስረስ ዳምጤ መልዕክት። የዘንድሮ የ12 ክፍል የማትሪክ ውጤት እና የመግቢያ ነጥብ እንደገና መከለስ ያለበት ነው። አብርሃ ወአፅብሃ መሰናዶ ት/ቤት (መርጡለ ማርያም) 162 አምጥተሃል የተባለው አማኑኤል ፀሐይ በቅሬታ ሲታይ 647 በማምጣቱ የሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል። አዴት መሰናዶ 150 አምጥተሃል የተባለው ተማሪ ውጤት እንደገና ተመርምሮ 618 ሁኖ ተገኝቷል። ቲሊሊ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 140 አምጥተሃል የተባለው ተማሪ ውጤት በድጋሚ ሲመረመር 601 ሆኖ ተገኝቷል። ደቡብ ወሎ ልጓማ ትምህርት ቤት 140 አምጥተሃል ተብሎ ውጤቱ በድጋሚ ሲታይ 601 ሆኖ ተገኝቷል። ውጤታቸው በድጋሚ ባይመረመርም ታናሽ ወንድሜን ጨምሮ በርካታ የደረጃ ተማሪወች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አላመጡም። ------ በጦርነት ቀጠና ውስጥ ለቆዩ የአማራ ተማሪወች ልዩ ድጋፍ መስጠት ሲገባ እንዲህ ዓይነት አሳፋሪ ስራ መሰራቱ በአጋጣሚ የተፈጠረ ችግር እንደማይሆን ይገመታል። ነገሩ የተማሪወቻችንን ስነ-ልቦና በእጅጉ የጎዳ እና ትውልድን የመግደል ውጤት ያለው ነው። በእርግጥ ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በ"North-Sou

አሉታዊው ስስት እና ገፈፋ ጠንቅ ነው። ድዌም

ምስል
አሉታዊው ስስት እና ገፈፋ ጠንቅ ነው። ድዌም።   #ፖርሳ ዬሰከነ መስከንን በእጃችን እንሥራው። ስስት ሰፊ ትርጉም አለው። እኔ አሉታዊ ስስት ላይ ነው ማተኮር እምሻው። "ለመብል ሁሉ አትሰስት ላዬኽውም እህል ሁሉ አትሰስት፤ ብዙ መብላት ደዌ ይሆናልና ስስትም ጓታን ያበዛዋል እና አትሰስት፤ ስስት የገደላቸው ሰወች ብዙ ናቸው፤ መጥኖ ዬሚበላ ግንሰውነቱ ጤና ነው።" ስስታም ዓይኑ ጠባብ ነው። ይቅበዘበዛል። ጎላ ብሎ በወጣው ላይ አንቴናውን ይዘረጋል። የእህል ስስት ለቁንጣን ይዳርጋል። የሥልጣን ስስት ደግሞ ለፋሺዝም። ስስት የህሊና ቀውስም ያስከትላል። ቀውሱ #ማናንሼ እለዋለሁኝ እኔው። የማንነት ቀውስ ያለበት ሰብዕና ውስጡ ሰላም የለውም። ይናደፋል። ይቦጭራል። ሁልጊዜ ግስላ፤ አራስ ነበር ነው። ሥልጣን ኖረውም አልኖረው ቅምጥ ፍላጎቱን ለማስቀጥል ሩጫው አጋጣሚውን በመጠቀም ይሆናል። አድብቶ ይጠብቃል። ብቅ ብሎ ይሰወራል። አረሳስቶም ጠቀራውን ያንዶለዱለዋል። እሳቱን ጫጭሮም ዞር ይላል። ገባ ወጣ ነው። ለምዱ እስቲገለጥ። አክ እስኪባል። መነገጃው ግን ያው የፈረደበት ኢትዮጵያዊነት ነው። እያከሰለ በምራቁ ቀለም ቀቢነት ያጎሳቁለዋል። እርግጥ ጠንቀኛውን ዬአንድ ለአንድ አጋበስባሽ ስስቱን አምቀው የያዙ ጊዜ ራዲዮሎጂ ሆኖ እስኪያጋልጣቸው ብዙ ማገዶ ይጠይቃል። ሰብዕናቸው #ግራጫ #በሲቃ ነው። አካሄዳቸው #ተርገብጋቢ እና #ገርበብ ያለ ነው። አልፎ አልፎ ፍንጭ ቢሰጡም ለሰከኑ ዬሰብዕና አጥኝወች ካልሆነ በስተቀር ተሎ ለማዬት ያስቸግራሉ። የሆነ ሆኖ አቅም፤ አቅል፤ ብቃት፤ ታሪክ ላለው ማህበረሰብ ስስታም ግለሰቦችም፤ ስስታም ተቋማትም የትውልድ ጠንቅ ናቸው። ካንፓቸው እና ካንፓሳቸው #ጥላቻ ነው። ምርታቸው ዲዲቲ ነው። ከሚጠሉት ዘለግ ብሎ የሚወጣ

ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ +

ምስል
  ከታሪክ ማህደር። ብሎጌ ላይ እለጥፈዋለሁኝ። ከሽዋረገድ ከምወደው ሥም የተገኜ። ~ መጋቢት 7 | #_ጻድቁ_ንጉሥ_ቴዎድሮስ መታሰቢያው ነው፨     አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፨ + ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ + በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል። በርግጥ በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን (1845-1860) ነው:: በበጎ ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ የምናስበው ቀዳማዊው ነው። ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ ዳዊት (ጒንደ መስቀሉን ያመጡት) እና የተባረከችው ሚስታቸው የፅዮን ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም ነው። በኢትዮጵያ ለ3 ዓመታት (ከ1396-1399) ብቻ ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን፦ ● ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል ፍርድ እንዳይጓደል ይታትር የነበር፣ ● ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር፣ ● ወገገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ፣ ● ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር። ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር። በነገሠ በ3 ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል። ከመቃብሩም ላይ ጸበል ፈልቋል::

ዬተከበሩ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሚር ክቡር አንቶኒ ብሊንከን በአቀባበሉ እጅግ ሰውነቴ እስኪርድ ድረስ ደንግጫለሁኝ። የኦነግ ልቅነት ሱናሜ ……… ዘፈንብን።

ምስል
  በአቀባበሉ እጅግ ሰውነቴ እስኪርድ ድረስ ደንግጫለሁኝ። የኦነግ ልቅነት ሱናሜ ……… ዘፈንብን። እግዚኦ። ህግ የማያውቁ፤ ህግ የማያውቃቸው ገደሎች። በዬጊዜው አገርን ክብሯን ይቀጣሉ። እንዲህ። "አቤቱ በቁጣህ አትቅሰፈኝ በመዓትህም አትገስፀኝ።" (መዝሙር ፴፯ ቁ ፩)     ካልልኩ የተሰፋ ሽብሽቦ ወይ ይወጥራል፤ ወይ ያስዋኛል። የኦነግ ፖለቲካ ኢትዮጵያን በተመኛት በስንት ዘመኑ በራሳችን የማስተዋል እርቃን እንሆ እራሳችነን መለመልነው። በጥንት ዘመን ሊጋባ፤ በዛሬው ዘመን ፕሮቶኮል ይባላል። ፕሮቶኮሉንም፤ ሊጋባውንም አክ ያለው ገዳወኦዳ ሥርዕወ እንዲህ አገራችን እና ክብሯን በዲፕሎማሲው ህግ ፊት አዋረዳት። ዬተቀበሉትን እኔ ሥማቸውን ሰምቼ አላውቀውም፦ እንኳንስ የዓለም ማህበረስብ ቀርቶ። ዬንቀትም ልክ አለው። የመለጠጥም ልክ አለው። የመንጠራራትም ልክ አለው፣ እንደምን አቻ ካልሆነ ጋር ዬአሜሪካ የኃያሏ አገር የውጭ ጉዳይ ሚር አቀበባል እንዲህ ዛቅጦ እንዲታይ ተደረገ??? ኢትዮጵያን ለማዋረድ ከደረጃዋ ለማውረድ ዬሚኳትነው፤ በበታችነት ስሜት ዬሚባዝነው አገዛዝ አሳዛኝ ትራጀዲ ነው። በውነት ዕንቅልፍ አልወሰደኝም። እኛ ትቢያ ላይ ያለን ዜጎች አረማመዳችን፤ አነጋገራችን፤ አኗኗራችን አርመን፤ አስገድመን እምንጓዘው የታላቅ አገር ልጆች ስለሆን ነው። በእኛ ጉድፍ እናታችን እንዳናስነሳ ብርቱ በጣም ብርቱ ጥንቃቄ እናደርጋለን። እንኳንስ አገር እመራለሁ የሚል በፓርክ እና በአበባ ወረፋ ከፍ እና ዝቅ ውሎ የሚያድር ጉድ። እዮቤል ቤተ መንግሥት እሰራለሁ ብሎ ብድግ ቁጭ የሚልበት እኮ በኃያላኑ፤ በዲታ አገሮች ብድር እና ችሮታ ነው። እናውቃለን እኮ ጠቅላዩ ሹፌር ሆነው ሲቀበሉ። ዬሚገርመው ከአዋረዱ፤ ከቀጡ፤ ከተበቀሉ በኋላ ደግሞ ሌላ ውዝዋዜ፤ ሌላ አጀብ ይከ

ቅኔያዊቷ፣ ተደሟዊቷ፣ ዕድምታዊቷ፣ እዮባዊቷ እንደተናፈቀች ……… ቀጠለች።

ምስል
ቅኔያዊቷ፣ ተደሟዊቷ፣ ዕድምታዊቷ፣ እዮባዊቷ እንደተናፈቀች ……… ቀጠለች። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።" EOTC እንደ ዘገበው።     "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናችን የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 3 የሕግ ድንጋጌ መሠረት አስቸኳይ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ በማድረግ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና አስተዳደራዊ ጥሰት በመፈጸም ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሰዶ ዳጩ ወረዳ በሀሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሕገ-ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ሕገ-ወጥ አድራጐት መሆኑን አጽንኦት በመስጠት በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ፡- 1. ሕገ-ወጥ ሹመቱ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፤ 2. ሕገ-ወጥ ሹመቱን ያከናወኑት 3ቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ተሹመናል ባዮችን 25 ግለሰቦች ከዲቁና ጀምሮ ያላቸውን ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር እና ከቤተ ክርስቲያኒቱ አባልነት በማውገዝ መለየቱ ፤ 3. ምንም እንኳን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሁሉንም አውግዞ የለየ ቢሆንም እናት ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ለሰላም በሯ ክፍት እንደመሆኑ መጠን የተወገዙት ግለሰቦች የቤተ ክርስቲያኒቱን የሰላም ጥሪ ተቀብለውና የተከናወነው ድርጊት ሕገ-ወጥ መሆኑን አምነው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ለፈጸሙት ሕገ-ወጥ አድራጐት የሚሰጣቸውን ቀኖና ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ

ዬአማራ ህዝብ ያሳዝነኛል።

ምስል
#ዕለተ ሰኞ ዕለተ #ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በሰብለ ህይወት አዝመራ በቢሆነኝ ብራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) ዬአማራ ህዝብ ያሳዝነኛል።    ለወሰንከው ውሳኔ ታማኝ መሆን ከተሳነህ ያሸነፍከው ደራጎን መልሶ ያጠቃሃል። ህወሃት 40 ዓመት ሙሉ አማራን ጨፈጨፈ፣ አፈናቀለ፣ ዘሩን አመከነ፣ አገለለ፣ አስጠላ በአማራ ጥንካሬ እና ብርታት ተወገደ። ግን ህጋዊ መሠረት ያለው ዓለም አቀፍ ቁምነገር ስላልተከወነ አማራ ተጨፍጭፎም በዓለም አደባባይ ተጠያቂ ሆነ። ይህ የመንፈስ ቁርጥማት የማይጠዘጥዘው ሰውኛው መንፈስ አለሁ አይበል። ብዙ የተደከመባቸው ዕውነቶች ግሎባል ዕውቅና አግኝተው በቅጡ ስላልተቋጩ እንሆ ዛሬም መኖሩን የተቀማ ህዝብ በአገርም በውጭም ተወጋዥ ሆነ። ጃልመሮ ባቅሙ አማራን ከሳሽ ሆኗል። በምን ቀመር በምን ሁነት የአማራ ልዩ ኃይል ወለጋ ላይ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል? የሚገርመው ሁለገብ ሸፍጡ አማራን በግሎባል ደረጃ ማስወገዝ ነው። ለዚህም ነበር እኔ አቅም ያላቸው ወገኖች ከአማራ ሊቃናት እና ልዩ ኃይል ጭፍጨፋ ማግሥት ጠንከር ያለ ተቋም ፈጥረው እንደ እስራኤሎች ይታገሉ ዘንድ፣ ዓለም አቀፋን ማህበረሰብ ከጎን ያሰልፋ ዘንድ የተማጠንኩት። አልሆነም። #አማራነት አልታወቀም። የታቀደበት ማዕትም አልተረዳነውም። አማራነትን እራሱ አልገባንም። መጪውን ጊዜ ቀርቶ ዛሬ አማራን ሊቀበል የሚችል መንፈስ ኢሚንት ነው። አማራነት ወንጀል ሆኖ ታቅዶ እዬተሠራበት አማራው ደግሞ የሌላ አጀንዳ ተሸካሚ ሆኖ ይባትላል። ያሳዝናል። ይህ የተገፋ፣ ባለቤት አልባ ህዝብ። ዕንባውን የሚያደምጥለት የፆም ውኃ የሆነበት ህዝብ። የሚያሳዝነው መከራህን ተሸክመህ ለገዳ ወረራ፣ ለገዳ መስፋፋት፣ ለ

የገዳ ቱቦ ግርባው ብአዴን።

ምስል
#ዕለተ ሰኞ #ዕለተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በሰብለ ህይወት አዝመራ በቢሆነኝ ብራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ" (ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)   የገዳ ቱቦ ግርባው ብአዴን።       ግርባው ብአዴን አዲስ ኳኳቴ ይዞ ብቅ ብሏል። በሞት አፋፍ ላይ የሚገኜውን ህወኃትን፣ የኦህዴዱን ኦነግን "ሽኔ" በሚል ልብጥ፣ የቬንሻንጉሉን የጉምዝ አማፂ እታገላለሁ የሚል ቅልጥ ያለ የቧልት እርግጫ። ጭንጫዊነት! ለኦህዴድ ጭንጫ የገዳ ምርጫ የኮረጆ ማጠራቀሚያ ስልብ እንቶ ፈንቶ። ባለፈው ሰሞን ከክልሉ ውጪ ያለ አማራ አይመለከተኝም ሲል በልሳኑ ያላገጠው የምድር እንቧዩ ብአዴን ቧልቱን ትቶ እሱ በዓለም የርትህ አደባባይ በዘር ማፅዳት ወንጀል ተባባሪነት በዘመነ ህወሃትም፣ በዘመነ ኦህዴድም አብሮ ተባብሮ - ተፋቅሮ - ተነባብሮ ያስፈፀመውን ጀኖሳይድ ተጠያቂ አይደለሁም ቢል አይችልም። አመሠራረቱም ለዚያ ነው። ተቀፍድዶ ለግርባነት። አማራ የሚመራው በአንጡራ ጠላቶቹ ነው። የጥቃቱ ውስብስብነትም ምንጩ ይኽው ነው። ዛሬም ህሊናው የሰከነው ገዳይን - ጨራሽን - ሲከበክብ፣ ሲሸልም፣ የገዳይ አጋፋሪዎችን ሲከበክብ ስንቅ ሲያቀብል፣ ሲደለድል፣ ሲያደላድል ውሎ ያድራል። ውርዴ። እስኪ ይነገረን አቶ እስክንድር ነጋ አማራ አይደለምን? ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት አማራ አይደሉምን? አቶ ልደቱ አያሌው አማራ አይደሉምን? አቶ ስንታዬሁ ቸኮል አማራ አይደሉምን ወይ? ኢዴፓ የአማራ ሊቅ የፈጠረው ድርጅት አልነበረምን? ኢኃን የአማራ ብቁ የፈጠረው አልነበርም? ባልደራስ የአማራ ልሁቅ የፈጠረው አልነበረምን? አብሮነት የኢትዮጵያ ተስፋ አልነበረንም? ሁሉም በአውሬያዊ ትንፋሽ ሲሰረዙ፣ ሲታገቱ፣ መንፈሳቸው ሞት ሲታወጅበት ቀብር ሲሆ

ቀጨር መጨር። የዕብለት ታንቡር ስልችት አለኝ። ቋቅ!

ምስል
ዕለተ ሰኞ ዕለተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በሰብለ ህይወት ብራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)   ቀጨር መጨር። የዕብለት ታንቡር ስልችት አለኝ። ቋቅ! የአርዮስ ልሳንም ቋቅ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 15/03/2021 ይህን አንቡላ ስብከት የማልሰማበት ጊዜ ናፈቀኝ።  

ዕብደት በዝገት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሙልጭነት።

ምስል
  ዕ ብደት በዝገት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሙልጭነት። "የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ"     ውዶቼ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በሚመለከት ከእኔ በላይ የተሟገተላቸው ካለ በብዕር ሊሞግተኝ ይችላል በሩም ክፍት ነው። መቼም በህይወቴ ሙሉ እንደ እሳቸው የሰብዕና ሙልጭልጭነት የቀፈፈኝ፣ በዝምታ እና በሆደ ሰፊነትም ለመታገስ ከራሴ ጋር የታገልኩለት ሰብዕና የለም። ለልጆቻቸው ስል። ስንት ጊዜ ይሰቃዩ በማለት። ይህም ሆኖ መቻልን አላስቀምጠው ስላሉ ውስጤ እንሆ። ህም። ዕድሜ ሙሉ በማንነት ቀውስ ድዌ የኖሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በቀላቸውን ሲወጡበት የኖረው የአማራ ህዝብ አምላክ እርቃናቸውን አስቀርቶ፣ ዘነዘናቸውን ሲያወጣው አሁን ደግሞ ብልዝ ዕብደት ይዘው መጥተዋል። ዝም ሲሏቸው መናቃቸውን ካለማወቅ ይመስላል የለም ያሉት ህዝብን የጀርባ አጥንት ሲሉ ተደምጠዋል። ተምሶ የተቀበረ ዝና አደባባይ ለማውጣት ሌላ መድህን የለም። እማያውቁት ነገር፣ ያልገባቸው ነገር ሚሊዮን የአማራ ልጅ መንፈስ ለአማራነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዘብ መቆሙን ነው። ከአያት ቅድመ አያቶቻችን በወረስነው ጥሞና፣ እርጋታ፣ ልቅና ውስጥነት ዝምታን ሰንቀን ብንቀመጥም ሞገዱ እሳተ ጎመራ መሆኑን ሊያውቁት ይገባል። ይልቅ ቤተሰብ ካላቸው ጎንድ ተክላህይማኖት ወይንም አማኑኤል ያስገቧቸው። ክህደትም አለው አይነት። አንድ የአማራ ልጅ ከመንፈሱ ገዳይ ጋር እሞዳሞዳለሁ ቢል ውርዴቱ ለራሱ ነው። አርዮስ አርዮስ ነው። የአማራ ልጅ የተፋውን አይናፍቅም። ለቁጥር የሚያታክቱ የአማራ ሊሂቃን አሉት አማራ። ጥግኝነት የሚያስኬደው አንዳችም ነገር የለም። ለዛውም ብሎን የወለቀበት ፍለጋ። አማራ ምን አጥቶ። የዚህ ሁሉ የ60 ዓመታት ዝብርቅርቅ ተመራማሪ አላገኜም እንጂ ተመራማሪ ቢያገኝ የአማራ ሊሂቃን ከመገለላቸ

#ዝልቦ #ፖለቲካ።

ምስል
  #ዝልቦ #ፖለቲካ ።     የምዕራፍ ፰ መክፈቻ አቀባበል ድውለተ ብዕር። "ጥበብስ በቀደሙ ሰወች ዘንድ ተመረመረች።"       #ጠብታ ። እጅግ እያዘንኩ ነው እምጽፈው። ግን zክብረቶቼ ዝልቦ ታውቃላችሁ? ዝልቦ የጎንደር ባህላዊ ወጥ ነው። ቆስጣ በዝልዝል ሥጋ ተዝለብልቦ የሚሠራ። ዝልብልብ ያልኩት ቆስጣውን ነው። መረቁ ዘለል ያለ ነው። ቤት ከመጣችሁ ሠርቼ አሞናሙናችኋለሁ። ለእኔ እንግዳ ንግሥቴም ንጉሤም ነው። ለሁለት ሰዓት የመጣ ይውላታል// ትውላታለች// ያመሻታል/// ታመሻለች። አዳር ባይፈቀድም። ስንት ነገር እንደ ደቀቀ ማውጫ ዬለኝም። ብዙ ጊዜ ዝምታዬም ይኽው ነው። ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለተሠማሩበት መስክ እንጂ ለአገር መሪነት ከንቱ ነው። ዘመናችን ተቋም ተከፍቶለታል። ክቡር ኮሜዲ ፕሬዚዳንት፤ ዬዓመቱ ምርጥ ሰው አቶ ዘለንስኪ። እሰቡት የዓመቱ ምርጥ ሰው ከልዕልት ዶር አንጌላ ሜርክል ጋር መሳ ለመሳ ሆነው ነው የምርጥ ሰውነት ዲግሪያቸውን ያስከነዱት፤ ኦስካር ቢሆን ድንቅ ነበር በአገር መሪነት ግን እኔ እንጃ? ብቻ በተደሞ አስሉት። አድማጬ ክብርት ዶር አንጌላ ሜርክል የአውሮፓ ብሌን ነበሩ። ኖቬል እንዴት እንደ አለፋቸው አላውቅም። የተመድ ቀጣይ መሪ ቢሆኑ ምርጫዬ ነው። ተደሟዊት መራኂት። #እፍታ ። መከራው ወዘተረፈ። መከራው ሥር ዬሰደደ። መከራው ሁለገብ። መከራው አይምሬ። መከራው ትውልድ መታሪ። መከራው ተከታታይ። ግን አይደለም ለመፍትሄው ለመከራው ዕውቅና አቅም የለሽ ነው የኢትዮጵያው ዝልቦው ፖለቲካ። የሰው እልቂት፤ የሰው ፍልሰት ሽግግር ላይ ይገጥማል ብሎ ካልኩሌሽን ይቀምርልኃል። ከፍልሰቱ፤ ከሞቱ መታቀብ እንዲችል ነው ለውጡ ዬተፈለገው። #ውስጠት ። ዬሚገርመኝ ዝላዩ ነው። ዝላዩ መቀሌ ሲለቀቅ የተሰጠውን ማብራሪያ አስታክኬ የፌንጣ

ህግ አምላክ! እባከወት ይሁኑ በልከወት። "#ብሉ እዬተባለ ነው ያለና?" ከኡራኖስ የባጁት ቀዳማይ እመቤት ……

ምስል
በህግ አምላክ! እባከወት ይሁኑ በልከወት። " #ብሉ እዬተባለ ነው ያለና?" ከኡራኖስ የባጁት ቀዳማይ እመቤት …… ምን ብሉ?? ባሩድ? ጭንቅ? ጭፍለቃ? መፍረስ። መናድ? እራስን ማጣት። ብልኃት ዬሌለው ቅላት ትል ነበር እሚታዬ ጽግሽ። በተጓዙ ቁጥር ጎንደር አዲስ ከንቲባ ይጠብቀወታል። አሁን 6/7 ኛው ከንቲባ ይሆናሉ። ለምን ብለው አጤወትን ጠይቀው አያውቁንም? ከ2015 ዓም ጥምቀት ማግስት ደግሞ አዲስ ከንቲባ ተመድበዋል ከብልጽግና ወንጌል። ወይ ጠቅልለው አባጠቅላዩ በሪሙት ኮንትሮል ከንቲባ ቢሆኑ ይሻላል። ሰርክ ከንቲባ ምርጫ??????? "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ" እንሆ ………   ቤተ - ዬሻሸመኔ ዬእግዚአብሔር ዓውደ ምህረት በደም በጨቀዬ ፴ቀን ሳይሞላው ዬድፍረት ኃጢያት አዳመጥኩኝ። "አቤቱ የድፍረት ኃጢያትን እንዳልሠራ ባሪያህን ጠብቅ።" አሜን ንግግር አያስፈልግምፖ። #ሪባን መቁረጡ በቂ ነው። ቤተ - መቅደስ ተከርችሞ በዕለተ ሰንበት በመዲናዋ ሥርዓተ - ቅዳሴ፤ ሥርዓተ - ፍትኃት፤ ሥርዓተ - ተክሊል፤ ሥርዓተ - ቁርባን፤ ሥርዓተ - ማህሌት በጦር ኃይል ታግቶ መስቀል እዬተረሸነ፤ ለመሆኑ አዲስ አበባ ዬማን ናት አሁን? በትውስት እንደሚኖሩባትስ ያውቁ ይሆን??? ፦፦፦፦ ነገ በኤሌትሪክ እጥረት፤ በውሃ አቅርቦት፤ በቀረጥ ጫና ለሚዘጋ ዕለታዊ ነገር ያለልክ እና ያለ ደረጃ በልቁ እና ዝልግልጉ የኦነግወኦህዴድ የቀውስ ፖለቲካ ተማምኖ ካለ ችሎታም፤ ካለ ክህሎትም እንዲህ ዘው ብሎ #ከመበለሻሸት #ዝምታ በስንት ጣዕሙ። ሲሆን ሲሆን መናገር ዬማይችል ሰው አፅፎ ማንበብ። በስተቀር ከመቀስ ጋር ተዋውሎ በዝምታ እንደ ተከደኑ ይሻል ነበር። ትምህርት ቤት ዳቦ ቤት እዬሠሩ ማስመረቅ ይበቃወታል። እላፊ እባከወትን አይሂ