#ዝልቦ #ፖለቲካ።

 

የምዕራፍ ፰ መክፈቻ አቀባበል ድውለተ ብዕር።
"ጥበብስ በቀደሙ ሰወች ዘንድ ተመረመረች።"
 
 

 
እጅግ እያዘንኩ ነው እምጽፈው። ግን zክብረቶቼ ዝልቦ ታውቃላችሁ? ዝልቦ የጎንደር ባህላዊ ወጥ ነው። ቆስጣ በዝልዝል ሥጋ ተዝለብልቦ የሚሠራ። ዝልብልብ ያልኩት ቆስጣውን ነው። መረቁ ዘለል ያለ ነው። ቤት ከመጣችሁ ሠርቼ አሞናሙናችኋለሁ። ለእኔ እንግዳ ንግሥቴም ንጉሤም ነው። ለሁለት ሰዓት የመጣ ይውላታል// ትውላታለች// ያመሻታል/// ታመሻለች። አዳር ባይፈቀድም።
ስንት ነገር እንደ ደቀቀ ማውጫ ዬለኝም። ብዙ ጊዜ ዝምታዬም ይኽው ነው። ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለተሠማሩበት መስክ እንጂ ለአገር መሪነት ከንቱ ነው። ዘመናችን ተቋም ተከፍቶለታል። ክቡር ኮሜዲ ፕሬዚዳንት፤ ዬዓመቱ ምርጥ ሰው አቶ ዘለንስኪ። እሰቡት የዓመቱ ምርጥ ሰው ከልዕልት ዶር አንጌላ ሜርክል ጋር መሳ ለመሳ ሆነው ነው የምርጥ ሰውነት ዲግሪያቸውን ያስከነዱት፤ ኦስካር ቢሆን ድንቅ ነበር በአገር መሪነት ግን እኔ እንጃ? ብቻ በተደሞ አስሉት። አድማጬ ክብርት ዶር አንጌላ ሜርክል የአውሮፓ ብሌን ነበሩ። ኖቬል እንዴት እንደ አለፋቸው አላውቅም። የተመድ ቀጣይ መሪ ቢሆኑ ምርጫዬ ነው። ተደሟዊት መራኂት።
መከራው ወዘተረፈ። መከራው ሥር ዬሰደደ። መከራው ሁለገብ። መከራው አይምሬ። መከራው ትውልድ መታሪ። መከራው ተከታታይ። ግን አይደለም ለመፍትሄው ለመከራው ዕውቅና አቅም የለሽ ነው የኢትዮጵያው ዝልቦው ፖለቲካ። የሰው እልቂት፤ የሰው ፍልሰት ሽግግር ላይ ይገጥማል ብሎ ካልኩሌሽን ይቀምርልኃል። ከፍልሰቱ፤ ከሞቱ መታቀብ እንዲችል ነው ለውጡ ዬተፈለገው።
ዬሚገርመኝ ዝላዩ ነው። ዝላዩ መቀሌ ሲለቀቅ የተሰጠውን ማብራሪያ አስታክኬ የፌንጣ ፖለቲካ ስል በወቅቱ ሞግቸዋለሁኝ። ፍላጎት አልቦሽ፤ ራዕይ አልቦሽ ተጋድሎ መሰብሰቢያ ያጣ፤ ማሰሪያ ልጥ አልቦሽ ጉዞ።
ቢያንስ አሁን ከምርኮም፤ ከድለቃም፤ ከግብረ ሰላምም መልስ ሁሉም ጥሞና ወስዶ ስህተቱ ዬት ላይ ነው ብሎ ለማድመጥ ፈቃዱ ቢኖር እንኳን ያጽናናል። አሁንም ግልቢያ። ወደ ዬት? ምን ለማግኜት? የቱን ነቅሎ ዬቱን ለመትከል መ /// መልስ ዬለም። ሲፈርስ ሲሰራ፤ ሲተረተር ሲሰበሰብ መሽቶ የሚነጋለት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዘመናቸውን ሁሉ በጥላቻ ምቸት ለተንተከተኩ ሃሳቦች ሁሉን አስረክቦ ሙት መሬት ላይ ምላዕቱን ያስማቅቃል።
አምስት ዓመት እጅግ ብዙ ነው። መሻገሩ ቀርቶ መስመጡ በቀረ። አፋፍ ላፋፍ መቧጠጥ። ዓዋቂውም የእኔ ቢጤ ያልተማረውም። ዬእስራኤሉች ተመክሮ ተቋም ነው። እሱም ይቅር የእዮባዊቷ ደርባባ ዬዊዝደም ጉዞ ምን አለ ዬፊደል ገበታ ቢሆን። ባይገርማችሁ እዮባዊቷ ላም እረኛ ምን አለ መርኋ መሆኑን አረጋገጥኩኝ።
እኔ የአንከር ሚዲያ አባ ትምህርትን ብፁዑ አቡነ ጴጥሮስን ጋር ዬነበረው የጥያቄ ፍሰት ስላልተመቸኝ ሞገትኩት። ከዛ አልተደገመም። አልተሰለሰም። ቀጥ አለ። ለምን ቅድስቷ ሰማችኝ። ብፁዑነታቸውም ፍንክች አላሉም ነበር። በፀዳ ዬመንፈስ ቅዱስ አቅም ያን ተርገብጋቢ ቃለ ምልልስ አስክነው ነበር ያጠናቀቁት።
እያንዳንዱን ነገር እዬተከታተልኩ እሞግታለሁ። ተውም እላለሁኝ። ላም እረኛ ምን አለን የናቀ ዬሃሳብ ሂደት ሁሉ ተያይዞ ነኮተ። ቢያንስ ማድመጥ እንዴት ይሳንኃል። ፖለቲካ አክቲቢዝም አይደለም። ፖለቲካም የመሄድ ፖርሳ አይደለም። ሰክኖ መቀመጥን ይጠይቃል። ረጅም ጊዜ ቁጭ ብሎ መስራትን። ፋክክሩ ተግባሩ እንጂ ፎቶ ወይንም የቃል ጅራፍ ሊሆን ባልተገባ። ልምራ ያለ ሁሉ ሁሉ አይሰጠውም። የተደራጀ ሃሰብ ለተደራጀ ህሊና ነው ሊሸለም ይገባ ዬነበረው። ሁሉንም አንኩረው አፈሰሱት ከምል ደፋት።
ሌላው የውጭ አገር ተቋማትን፤ መንግሥታትን አቃሎ ማዬት ሌላው ቁስለት ነው። በዘርፋም ዬተሰበሰበ ተከታታይ ተግባራት???
አሁንም ዕውቀት፤ ልምድ፤ ተመክሮ፤ ስክነት ቅንነት ይመራ ዘንድ መርህ እና ዕውነት ይፈቀድላቸው። ላም እረኛ ምን አለም ይደመጥ። ወቅታዊነት ቋት አይገፋም። እንደ ፌንጣ ዝላይም አያስፈልግም። እርጋታ፤ በግለሰቦች መጠለልም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አክ ሊባል ይገባል። ሲከስሉ መክሰል፤ ሲከሱ መክሳት ሰቀቀን። ሃሳብ ምርኩዝ ፒላር ማገር እና ወጋግራ ይሁን። ትእዛዝ አይደለም። ኧረ እኔ ምን በወጣኝ። አወንታዊ ዕይታ ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።