የገዳ ቱቦ ግርባው ብአዴን።


#ዕለተ
ሰኞ #ዕለተ ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በሰብለ ህይወት አዝመራ
በቢሆነኝ ብራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ"
(ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)

 
የገዳ ቱቦ ግርባው ብአዴን።
 
 

 
ግርባው ብአዴን አዲስ ኳኳቴ ይዞ ብቅ ብሏል። በሞት አፋፍ ላይ የሚገኜውን ህወኃትን፣ የኦህዴዱን ኦነግን "ሽኔ" በሚል ልብጥ፣ የቬንሻንጉሉን የጉምዝ አማፂ እታገላለሁ የሚል ቅልጥ ያለ የቧልት እርግጫ። ጭንጫዊነት!
ለኦህዴድ ጭንጫ የገዳ ምርጫ የኮረጆ ማጠራቀሚያ ስልብ እንቶ ፈንቶ።
ባለፈው ሰሞን ከክልሉ ውጪ ያለ አማራ አይመለከተኝም ሲል በልሳኑ ያላገጠው የምድር እንቧዩ ብአዴን ቧልቱን ትቶ እሱ በዓለም የርትህ አደባባይ በዘር ማፅዳት ወንጀል ተባባሪነት በዘመነ ህወሃትም፣ በዘመነ ኦህዴድም አብሮ ተባብሮ - ተፋቅሮ - ተነባብሮ ያስፈፀመውን ጀኖሳይድ ተጠያቂ አይደለሁም ቢል አይችልም።
አመሠራረቱም ለዚያ ነው። ተቀፍድዶ ለግርባነት። አማራ የሚመራው በአንጡራ ጠላቶቹ ነው። የጥቃቱ ውስብስብነትም ምንጩ ይኽው ነው።
ዛሬም ህሊናው የሰከነው ገዳይን - ጨራሽን - ሲከበክብ፣ ሲሸልም፣ የገዳይ አጋፋሪዎችን ሲከበክብ ስንቅ ሲያቀብል፣ ሲደለድል፣ ሲያደላድል ውሎ ያድራል። ውርዴ።
እስኪ ይነገረን አቶ እስክንድር ነጋ አማራ አይደለምን? ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት አማራ አይደሉምን? አቶ ልደቱ አያሌው አማራ አይደሉምን? አቶ ስንታዬሁ ቸኮል አማራ አይደሉምን ወይ?
ኢዴፓ የአማራ ሊቅ የፈጠረው ድርጅት አልነበረምን? ኢኃን የአማራ ብቁ የፈጠረው አልነበርም? ባልደራስ የአማራ ልሁቅ የፈጠረው አልነበረምን?
አብሮነት የኢትዮጵያ ተስፋ አልነበረንም? ሁሉም በአውሬያዊ ትንፋሽ ሲሰረዙ፣ ሲታገቱ፣ መንፈሳቸው ሞት ሲታወጅበት ቀብር ሲሆን የት ነው ይሆን ቱቦው ብአዴን።
አዲስ አበባ ላይ የፋሽዝም የህዝብ ስብጥር ቅዬሳ ዕውን ሲሆን ግርባው ብአዴን ተነነ ወይንስ ወደ እንጦርጦስ ሰረገ?እነ አጅሬ ተግባራቸውን እዬፈፀሙ እሱ ቀፎውን የቁም እንቅልፋን ይለጠልጣል። እንባጮ!
እንደ ፓፓጋይ በል የተባለውን አተላ ሃሳብ ከሚያንቆራቁር ውስጡ ሙጥጥ ብሎ መጠናቀቁን ይወቀው። ጭላጭ ሙጣጭ።
የጀግና እስክንድር ነጋ አዲስ መንገድ ሲታገት፣ ሲንገላት ማዕቀብ ሲጣልበት የፈተል ማህበራቸው የት ነው ያለው?
ከአቶ ሽመልስ አንሶ እንዲህ መናጆ ሲሆን ቀብሩ ስለመሆኑ ለምን አይገባውም። ብአዴን ሲፈጠርም ለአማራ ሞት ዛሬም ለአማራ የጥፋት ዘመን ይተጋል። ከንቱ።
ዕንባን አይዞህ ሳይል የገዳ ወረራን፣ የገዳን መስፋፋት፣ የገዳን አስምሌሽን አማራን መሪ የማሳጣት፣ አማራን ተተኪ እጩ የማሳጣት፣ አማራነትን የማምከን ግሎባል ዘመቻ እንደ ምርቃት አይቶ ሲዳክር እሬሳነቱን ቢያብራራልን እንጂ የመፍትሄ መንገድ እንዳልሆነ እንረዳልን። ዝቃጭ።
በገፍ ከዕለተ ኢንጂነር ስመኜው ህልፈት ጀምሮ አማራ ከሥሩ እዬታጨደ አዲስ ማጭድ አምራች ኩባንያ ስለመሆኑ ይነገረዋል። ግልብልብ።
የአገር ጉማሬ ደንደሱን ሲያደልብ በደም ጨቅይቶ ማፈር፣ መሸማቀቅ ሲገባ ለኮረጆ ቁጥር ልብድ ስልብነቱን ይዞ ከች ሲል ሞት በስንት ጣዕሙ ያሰኛል። ሙጃ!
ለኢትዮጵያ ህልፈት ቀዳሚ ተጠያቂው የምድር እንቧዩ ቅሉ ብአዴን ነው። አማራ እርግማኑ ይህን ዝልቦ አረንዛ የደራጎን ማህበር ተሸከም ብለው ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ያሸከሙት ዕለት ነበር።
ዛሬ የዛን ውርስ ሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሲያስቀጥሉት አሁንም ማህበረ ሬሳ መቃብር ውስጥ ሆኖ ከበሮ ይደልቃል። ያቅራራል፣ ይፎክራል። ገበርዲኑም፣ ከረባቱም ፈርዶበት። ከንቱ!
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
15/03/2021
የከንቱዎች ማህበር የሚያከትምበት ዕለት ይናፍቀኛል።
መናፈቅ ብቻ ሳይሆን ለዛም እተጋለሁ።
የጅል ማህበር ሰልችቶኛል።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።