ዬአማራ ህዝብ ያሳዝነኛል።

#ዕለተ ሰኞ ዕለተ #ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በሰብለ ህይወት አዝመራ
በቢሆነኝ ብራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
ዬአማራ ህዝብ ያሳዝነኛል። 

 
ለወሰንከው ውሳኔ ታማኝ መሆን ከተሳነህ ያሸነፍከው ደራጎን መልሶ ያጠቃሃል። ህወሃት 40 ዓመት ሙሉ አማራን ጨፈጨፈ፣ አፈናቀለ፣ ዘሩን አመከነ፣ አገለለ፣ አስጠላ በአማራ ጥንካሬ እና ብርታት ተወገደ።
ግን ህጋዊ መሠረት ያለው ዓለም አቀፍ ቁምነገር ስላልተከወነ አማራ ተጨፍጭፎም በዓለም አደባባይ ተጠያቂ ሆነ። ይህ የመንፈስ ቁርጥማት የማይጠዘጥዘው ሰውኛው መንፈስ አለሁ አይበል።
ብዙ የተደከመባቸው ዕውነቶች ግሎባል ዕውቅና አግኝተው በቅጡ ስላልተቋጩ እንሆ ዛሬም መኖሩን የተቀማ ህዝብ በአገርም በውጭም ተወጋዥ ሆነ።
ጃልመሮ ባቅሙ አማራን ከሳሽ ሆኗል። በምን ቀመር በምን ሁነት የአማራ ልዩ ኃይል ወለጋ ላይ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል? የሚገርመው ሁለገብ ሸፍጡ አማራን በግሎባል ደረጃ ማስወገዝ ነው።
ለዚህም ነበር እኔ አቅም ያላቸው ወገኖች ከአማራ ሊቃናት እና ልዩ ኃይል ጭፍጨፋ ማግሥት ጠንከር ያለ ተቋም ፈጥረው እንደ እስራኤሎች ይታገሉ ዘንድ፣ ዓለም አቀፋን ማህበረሰብ ከጎን ያሰልፋ ዘንድ የተማጠንኩት። አልሆነም።
#አማራነት አልታወቀም።
የታቀደበት ማዕትም አልተረዳነውም። አማራነትን እራሱ አልገባንም። መጪውን ጊዜ ቀርቶ ዛሬ አማራን ሊቀበል የሚችል መንፈስ ኢሚንት ነው።
አማራነት ወንጀል ሆኖ ታቅዶ እዬተሠራበት አማራው ደግሞ የሌላ አጀንዳ ተሸካሚ ሆኖ ይባትላል። ያሳዝናል። ይህ የተገፋ፣ ባለቤት አልባ ህዝብ። ዕንባውን የሚያደምጥለት የፆም ውኃ የሆነበት ህዝብ።
የሚያሳዝነው መከራህን ተሸክመህ ለገዳ ወረራ፣ ለገዳ መስፋፋት፣ ለገዳ አስምሌሽን፣ ለገዳ ዲስክርምኔሽን፣ ለገዳ ጥምቀት ሁነኛ ሁንለት ብሎ ማረግረግ ዕብንነት ነው። ከአለመኖር ያልተሻለ ጅልነት።
ለገዳይ ማጭድ ያመርት ዘንድ ነዳጅ ሁንለት ማለት ያሳፍራል። አንድ ተዓማኒ ተቋማዊ ሁነት አለመኖሩ ዕውነት እርቃኑን ሆኖ እናዬው ዘንድ ግድ ይላል።
ህወሃትም ማህበረ ኦነግም ምንጫቸውም ዋንጫቸውም አንድ ነው። ፀረ አማራነት። አሁን ተሳክቶላቸዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ። ከአማራ ጎን ለማስቆም የተደረገው ተጋድሎም ተኗል። በኗል።
በወለጋ እንኳንስ የአማራ ልዩ ኃይል ጠቅላዩ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በዛ የጦር ቀጠና ትውር ማለት አይችሉም። ነቀምት ላይ ኳስ ለመጫወት ካልሆነ በስተቀር።
ኦሮምያ እኮ ድፍን ሦስት ዓመት ኳራንቲ ውስጥ ነው። አንድም መልካም ጠረን ይለፍ የማይሰጥበት የሰው ልጅ መኖር የሚቀቀልበት የደም መሬት። ሲኦል።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
15/03/2021
ጅልነት ህልውናን አያስቀጥልም።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።