ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ +

 

ከታሪክ ማህደር።
ብሎጌ ላይ እለጥፈዋለሁኝ።
ከሽዋረገድ ከምወደው ሥም የተገኜ።
~ መጋቢት 7 | #_ጻድቁ_ንጉሥ_ቴዎድሮስ መታሰቢያው ነው፨
 

 
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፨
👑 + ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ + 👑
በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል። በርግጥ በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን (1845-1860) ነው::
በበጎ ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ የምናስበው ቀዳማዊው ነው።
ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ ዳዊት (ጒንደ መስቀሉን ያመጡት) እና የተባረከችው ሚስታቸው የፅዮን ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም ነው።
በኢትዮጵያ ለ3 ዓመታት (ከ1396-1399) ብቻ ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን፦
● ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል ፍርድ እንዳይጓደል ይታትር የነበር፣
● ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር፣
● ወገገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ፣
● ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር።
ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር። በነገሠ በ3 ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል። ከመቃብሩም ላይ ጸበል ፈልቋል::

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።