ዕብደት በዝገት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሙልጭነት።
ዕብደት በዝገት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሙልጭነት።
ውዶቼ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በሚመለከት ከእኔ በላይ የተሟገተላቸው ካለ በብዕር ሊሞግተኝ ይችላል በሩም ክፍት ነው።
ህም።
ዕድሜ ሙሉ በማንነት ቀውስ ድዌ የኖሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በቀላቸውን ሲወጡበት የኖረው የአማራ ህዝብ አምላክ እርቃናቸውን አስቀርቶ፣ ዘነዘናቸውን ሲያወጣው አሁን ደግሞ ብልዝ ዕብደት ይዘው መጥተዋል።
ዝም ሲሏቸው መናቃቸውን ካለማወቅ ይመስላል የለም ያሉት ህዝብን የጀርባ አጥንት ሲሉ ተደምጠዋል። ተምሶ የተቀበረ ዝና አደባባይ ለማውጣት ሌላ መድህን የለም።
እማያውቁት ነገር፣ ያልገባቸው ነገር ሚሊዮን የአማራ ልጅ መንፈስ ለአማራነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዘብ መቆሙን ነው። ከአያት ቅድመ አያቶቻችን በወረስነው ጥሞና፣ እርጋታ፣ ልቅና ውስጥነት ዝምታን ሰንቀን ብንቀመጥም ሞገዱ እሳተ ጎመራ መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።
ይልቅ ቤተሰብ ካላቸው ጎንድ ተክላህይማኖት ወይንም አማኑኤል ያስገቧቸው። ክህደትም አለው አይነት። አንድ የአማራ ልጅ ከመንፈሱ ገዳይ ጋር እሞዳሞዳለሁ ቢል ውርዴቱ ለራሱ ነው። አርዮስ አርዮስ ነው።
የአማራ ልጅ የተፋውን አይናፍቅም። ለቁጥር የሚያታክቱ የአማራ ሊሂቃን አሉት አማራ። ጥግኝነት የሚያስኬደው አንዳችም ነገር የለም። ለዛውም ብሎን የወለቀበት ፍለጋ። አማራ ምን አጥቶ።
የዚህ ሁሉ የ60 ዓመታት ዝብርቅርቅ ተመራማሪ አላገኜም እንጂ ተመራማሪ ቢያገኝ የአማራ ሊሂቃን ከመገለላቸው የመጣ የቁልቁለት ጉዞ ነው። አማራ ሰው ነው። በሰውነቱ ውስጥ ያለው ሚስጢር መታመኑ ለአምላኩ ነው። መቼውንም የአማራ አላህ፣ አምላክ አያንቀላፋም። ልኩን በልኩ ጊዜ ይሰጣል።
አማራነት ከሰውም በላይነት፣ ከሰውም በታችነት ሳይሆን አማራነት ልኩን ያወቀ ማንነት ነው። በአማራ ትክሻ ሁሉም ክብር ዝና አግኝቷል። አማራ ግን ተከድቷል ትናንት። ከእንግዲህ ግን ቀልድ የለም። የአማራ ልጅ አቅሙን ቆጥቦ ለራሱ መንፈስ አክባሪዎች ማዋል መደበኛ ሥራው ይሆናል።
ቢረሳ ቢረሳ የሰኔ 15 2011 ቀን ከኦነጋውያኑ ጋር ደባ ተሰርቶ የአማራ ሊሂቃን በገፍ የተጨፈጨፋበት፣ ለካቴና የተዳረጉበት፣ የተሰወሩበት ያ የመከራ ድባብ ይረሳልን። ለመሆኑ በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል? ፎቶዎትን እንኳን ከፔጄ ለመለጠፍ አቅም የለኝም እንኳንስ ሌላ።
የእስልምናን ብሄራዊ የጀግንነት ተጋድሎ እንዴት አድርገው ትቢያ እንዳለበሱትስ ሊረሳ ይሆን? ቀድሞ ነገር የኢትዮጵውያን ተስፋ ክው ብሎ የደረቀው እኮ እርስዎ ከእስር ተለቀው ከጠሚር አብይ አህመድ ጋር በነበረዎት ቆይታ የቀበሩት መርዝ ስለመሆኑ ልብ ያለን ሰዎች እናውቃለን።
ከዝገት፣ ከውብዬት፣ ከምርተት ዕብደት የሚጠበቅ ትሩፋት የለም። የተቃጠለ ፖይዝን ያደረገ ካርቦን። አማራ ከእንግዲህ ያሻው እንዳሻው የሚጋልበው ሰጋር አይደለም። በቃው እነ አክተር አክሮባቲስቶች። መላ ቢሶች።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
በደል ይረሳል ወይንስ ይለመዳል?
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ