የእኔ ዕይታ እና የሌሎችም። #የአዳኝ ባተሌ አባት ነፍስ እንደ ዋዛ መንገድ ላይ መቅረት። #መራራ ስንብት። እንደ አልባሌ #ዕውቀት ለባሩድ??? #ልቅና ለበቀል???
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"


ሃኪም ለእኔ #ነብይም #መላእክም ነው። ለምን ሃኪም #በጭካኔ ይገደላል? ሃኪም ሩህሩህ ሰባእዊ እና አዛኝ ፍጥረት ነው። ለምን #አረማዊ ነገር ይፈፀምበታል? ህይወታችን የቀጠለችው እኮ በእነሱ ድካም ነው። ከፈጣሪ በታች እረዳታችን የመኖራችን ጌታወች እኮ እነሱ ኒቸው። በእጅግ አሳዛኝ ዜና ነው። የጉበት፤ የቆሽት እና የሃሞት ከረጢት እስፔሻሊስቱ ዶር አንዱአለም ዳኜ ከአንዱ ሆስፒታል ወደ ሌላ ሆስፒታል ነፍስን የመታደግ ቅዱስ ተግባር እዬባተሉ በነበሩበት ከመኪናቸው አስወርደው እንደተገደሉ ነው ዜናወች የሚያመለክቱት።
#አዳኝ እንዴት ይገደላል? በዬትኛውም አለም ሃኪሞች ቀስ ብለው ሲራመዱ እንኳን አታዮዋቸውም። ሁልጊዜ ጥድፊያ ነው። ሰውን የማትረፍ፤ ለሰው ችግር ፈጥኖ የመድረስ ጥድፊያ።
ለመሆኑ ከዚህ ሙያ ለመድረስ ስንት መዋለ መንፈስ አገርስ፤ ማህበረሰብስ? ቤተሰብስ አፈሰዋል? መምህርም እኮ ናቸው። የብዙኃን #አባ። መዳህኒትም ፈዋሽ ናቸው። ያቺን የጭንቅ ሰዓት እኮ ሁላችንም እናውቃታለን። ሃኪም ባይኖር በህይወት ማን ይቀጥል ነበር። አንድ ጣሊያናዊ ሃኪም በኮረና ዘመን "ነገ ትረሱናለችሁ ብለው ነበር። " ዩቱብ ቻናሌ ላይ በድምጽ ሠርቸዋለሁኝ። መሬት ላይ ተነባብረው እያደሩ ነበር ያን የሲኦል በሽታ ኮረናን ጥቃት የታደጉን።
ፖለቲካ ለሰውካልሆነ ለማን እና ለምን ሊሆን ነው? ሰው መሆን #የተሳነው ስለምን የፖለቲካ ቤተሰብ ይሆናል???? ህሊና የላችሁም? ይህን ስል ያልተማረ ሙያ የሌለው ይገደል እያልኩ አይደለም። ሰው የተፈጠረው ለሰው ነው። ሰው የተፈጠረበት አመክንዮ ለምስጋና ነው። የመፈጠራችን ሚስጢር ነው እዬተቀጠቀጠ የሚገኜው። እራስን የሚገል፤ ሚስጢርን የሚገል አረማዊነት እንደምን ክቡር ሊሆን ይችላል። እራሳችን እያረከስን፤ እያከሰርንም ነው እምንገኜው።
ከጭካኔ፤ ከበቀል፤ ከምቀኝነት፤ ከጥላቻ መቼ ነው እምንፋታው? መቼ???? ግን ሰው ነን? ከሰው ተፈጥረናልን? መፈጠራችን እንዲህ ለጭካኔ ሲገዛ ምን ይሰማናል? እራሳችን በራሳችን ህሊና መድረክ እንጠያዬቅ።
አንጀትን በድርቡ ብጥስጥስ የሚያደሬግ መከራ ነው። ሃዘኑ የሁሉም ሊሆን ይገባል። ጭካኔ ይቁም! ይህን ስላልን አይቆምም። ነገር ግን የህሊና ሰውነት ብቃት ይጠይቃል። መሰልጠን ማለት ለእኔ ሰው ሆኖ መፈጠር ማለት ነው። እኛ ግን ከሥልጣኔውም ሰው ሆኖ ከመፈጠሩም ሚስጢር ተላልፈን አጓጉል፤ የጓጎለ ጉዞ ላይ እንገኛለን። እግዚአብሄር ይማረን። አሜን።
ሰማዕትነትን በሙያቸው ላይ እያሉ ለተቀበሉት ዶር አንዱአለም ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁኝ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። ከሌላ ቤተሰብ ያገኜሁት ነው።
"Life is not to be trusted; it will betray you without a moment's hesitation. Those with cruel hearts will never see the road you've traveled, the purpose that drives you, nor the deep love you hold for your people. They are simply malicious, they will take everything. Dr. Andualem was not just a person; he was a beacon of hope, a beloved, disciplined surgeon, specializing in Hepatobilliary and Pancreatic surgery; a brilliant Gold medalist from Jimma, a star at Bahir Dar University during his Residency in General surgery, and a Best Fellow award recipient from his HBP fellowship in Addis Ababa. His path took him from Jimma University to Bahir Dar to Addis Ababa, then to Bahir Dar again to serve his community. But even a light so bright could not escape the darkness of that cursed day when fate, with a cursed hand and a bullet's cold blade, extinguished his life. This incredible person, who we valued so greatly, was gone in a single second. The mind that eased so many anxieties went silent, and the hands that had held so much promise grew still. An unthinking act of evil cut short a life dedicated to saving others; a day of utter cruelty."
"We had a dream, Andualem, a dream woven from your spirit."
RIP ወንድማለም





ይህ ከአቶ ስመኜው ጌታሁን ያገኜሁት መረጃ ነው።
"ምን ተብሎ እንደሚፃፍ አላዉቅም 

"ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ትናንት ምሽት ከሆስፒታል ስራ ቆይቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ በጥይት ተደብድቦ ህይወቱ ማለፉን ሰማን

ሀኪም ነበር ቢባል ሀኪም ብቻ እንዳይመስላችሁ ፤ እጅግ የተለየ እና የተጨበጨበለት ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም ነው። የመጀመሪያ ዲግሪዉን ፣ ስፔሻላይዝድ ሲያደርግ እንዲሁም ሰብ ስፔሻላይዝ ሲያደርግ ሶስት ጊዜ የወርቅ ዋንጫ የወሰዶ እንቁ ሀኪም ነበር። በቀዶ ህክምና ክህሎቱ በትህትናዉ በፀባዬ የተለዬ ሰው ነበር። ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጥበበ ግዮን ሆስፒታል አራት አመት አብሮ የመስራት እድል ነበረኝ። የማይተካ ሰው አጣን 





ነብስህ በገነት ትረፍ!!"" አሜን።
በህይወት እያሉ የተለዋወጡት መልዕክት።
የቀድሞዉ የአማራ ክልል ም/ጤና ቢሮ ሀላፊ
በሰላም እረፍ!
"በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ጠብቀው በትናትናው እለት በአብይ አህመድ የብልፅግና ሰራዊት በግፍ ተገድሏል። ይህ ለ50 ሆስፒታሎች ፣509 ጤና ጣቢያወች፣ 1850 ጤና ኬላወች: ከ350 በላይ አንቡላሶች: 338 የጤና መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች መዘረፍ፣ስራ ማቆም እና መቋረት ምክንያት የሆነዉ የጥቁር ናዚ ስርዓት ዛሬም እንደ ትናነቱ የህክምና ባለሙያወች ላይ የአካል እና የስነ-ልቦና ጉድት አድርሷል ፤ህይወታቸውን ቀጥፏል ፤እንዲሁም ብዙ የህክምና ባለሙያዎችን ፋኖን አክማችሗል በማለት በየማጎሪያ ቤቱ አስሮ ቶርች እያደረጋቸው ይገኛል።
እንደ ሲዲሲ ፣ ሱዛና ቲ በፈት ፋዉንዴሽን፣ ሜሊንዳ ጌትስ ፋዉንዴሽን ፣ ግሎባል ፈንድ እና ከመሳሰሉ አለም አቀፍ ተቋማት የሚያገኘዉን የጤና ፕሮግራም የፋይናንስ ድጋፍ ከታለመዉ አላማ ዉጭ ለሚኒሻ፣ አድማ ብተናና የመረጃ ሰራተኞች ደሞዝ እና የዉሎ አበል እያፈሰሰ የሚገኘዉ ይህ ስርዓት ፤ለጤናዉ ስርዓት መጠናከር የጀርባ አጥንት የሆነዉን የፋይናን ሀብትና እና የተማረ የሰሰዉ ሀይል ለብልሹ አሰራር፣ለእስር፣ለግድያና ለስደት በመዳረግ የክልሉን የጤና አገልግሎት እያዳከመዉ ይገኛል።
Rest in peace!
"Dr. Andualem Dagne, a surgeon and a liver, pancreas and bile duct sub-specialist at Bahir Dar University College of Medicine and Health Sciences, was brutally murdered by Abiy Ahmed’s Prosperity Army on the night before. Ahmed's prosperity army has led to the looting, shutdown and interruption of 50 hospitals, 509 health centers, 1850 health posts, more than 350 ambulances, and 338 health infrastructure projects in the Amhara region of Ethiopia. This 'Black Nazi Regime,' which has caused physical and psychological harm to thousands of medical professionals, has taken their lives and is also imprisoning many medical professionals in concentration camps, claiming that they have treated injured Fano Freedom Fighters.
This regime, which is spending the foreign financial support of the health programs received from organizations such as the CDC, Susan T Buffet Foundation, Melinda Gates Foundation, and the Global Fund on salaries and allowances of militia and intelligence personnel, is weakening the delivery of the health services in the region by mismanaging financial resources and deporting the educated and skilled workforce that is the backbone of the health system.
Dr Kindu Gashu"
In Memoriam: Dr. Andualem Dagne (1988-2025)
==============================================
The medical and academic community mourns the loss of Dr. Andualem Dagne, a brilliant and dedicated surgeon, scholar, and emerging leader who made significant contributions to the field of medicine in Ethiopia. Dr. Andualem's untimely passing on February 2, 2025, at the age of 37, has left a void in the lives of his family, friends, colleagues, and patients.
This tribute honors Dr. Andualem's life, legacy, and achievements, and reflects on the profound impact he had on the medical and academic community and beyond. We celebrate his remarkable journey, from his early days as an outstanding medical student to his rise as a leading expert in hepatobiliary surgery, and remember his unwavering commitment to delivering exceptional patient care, advancing medical knowledge, and inspiring future generations of healthcare professionals.
"Let your light shine before others, that they may see your good deeds and glorify your Father in heaven." - Matthew 5:16
This biblical quote captures the essence of Dr. Andualem's life and legacy, as he embodied the values of compassion, empathy, and kindness in his personal and professional life.
Dr. Andualem was an academic giant, with a string of impressive achievements that marked his journey. He completed his Doctor of Medicine at Jimma University with the highest grade among his batch, and was awarded a gold medal for his outstanding academic performance. He then pursued his training in General Surgery at Bahir Dar University, where he again excelled, completing his training with the highest grade among his batch.
His thirst for knowledge and excellence drove him to pursue further specialized training, and he completed his fellowship in Hepatobiliary Surgery at Addis Ababa University. To further enhance his skills, he also underwent additional practical training in India and South Africa, demonstrating his commitment to staying at the forefront of his field.
But his academic pursuits didn't stop there. He also pursued advanced leadership training at the College of Medicine and Health Sciences, Bahir Dar University, earning a postgraduate certificate that equipped him with the skills and knowledge to lead and transform the healthcare and higher education sectors in Ethiopia.
His academic success was matched only by his professional achievements. He served as Director of Operation Services at Tibebe Ghion Specialized Hospital at Bahir Dar University, where he demonstrated exceptional leadership and management skills.
As a surgeon, Dr. Andualem was renowned for his exceptional skill, compassion, and dedication to his patients. He was a true servant-leader, always putting the needs of others before his own. His passion for his work was evident in everything he did, from the meticulous care he provided to his patients to the countless hours he spent teaching and mentoring young medical professionals.
One of the most notable moments in his career was when he performed the first surgery at Tibebe Ghion Specialized Hospital (TGSH )in 2018 and become part of TGSH history. At that time, the hospital was still in its infancy, and the facilities were far from luxurious. Yet, Dr. Andualem had the audacity to take charge of this historic surgery, filling the operating room with excitement and anticipation. The then Chief Executive Director of the college and the leadership team of the hospital were present in the operating room to witness this momentous occasion from start to finish.
But what inspired Dr. Andualem most was his dream of establishing an advanced cancer surgical center in Ethiopia, where he could provide maximum quality and humane services to those unfortunate ones suffering from cancer. He envisioned a center that would not only provide state-of-the-art treatment but also offer hope, comfort, and dignity to patients and their families. His dream was to revolutionize cancer treatment in Ethiopia and make a lasting impact on the lives of countless people.
Throughout his life and career, Dr. Andualem was a paragon of professionalism and ethical behavior. He held himself to the highest standards, and his deep spiritual life shaped his moral values and guiding principles. The values of compassion, empathy, and kindness that he inherited from his parents, community, and society at large guided his every decision and action.
As we reflect on Dr. Andualem's life, we are reminded of the importance of living with purpose, passion, and principle. We are inspired by his humility, servant-leadership, and commitment to making a positive difference in the community, academic and healthcare institutions and the world.
So, what can we learn from the life of Dr. Andualem Dagne? What principles should govern our temporary life on Earth?
1. Live with purpose and passion.
Dr. Andualem lived a life of purpose, driven by his passion for his work and his commitment to making a positive difference in the world.
2. Put the needs of others before your own.
Dr. Andualem was a true servant-leader, always putting the needs of others before his own.
3. Stand up for what is right, even in the face of adversity.
Dr. Andualem was a champion of equity and healthcare value, advocating for the rights and dignity of patients for high quality and affordable healthcare.
4. Live with integrity and principle.
Dr. Andualem was a man of great principle and integrity, guided by a strong sense of morality and ethics.
5. The power of humility and servant-leadership.
Dr. Andualem's humility and servant-leadership inspired countless people in his circle and beyond.
6. The importance of spiritual life and moral values.
Dr.Andualem's deep spiritual life shaped his moral values and guiding principles.
7. The value of perseverance and resilience.
Dr. Andualem, as citizen born in a countryside of a developing nation, faced many challenges throughout his life, but he persevered and remained committed to his wildly important goals and big pictures.
8. The power of dreams and vision. Dr. Andualem's dream of establishing an advanced cancer surgical center in Ethiopia inspired his colleagues, friends and mentors.
9. The importance of community and family.
Dr. Andualem's commitment to his community and family was unwavering. He was a devoted husband and father of three young children, who were the center of his universe.
10. The legacy of a life well-lived.
Dr. Andualem's life was a testament to the impact one person can have on the people and the world at large.
In conclusion, the life of Dr. Andualem Dagne is a powerful reminder of the impact one person can have on the world. His legacy continues to inspire and motivate us to live our lives with purpose, passion, and principle. As we reflect on his life, we are reminded of the importance of living with integrity, standing up for what is right, putting the needs of others before our own, and pursuing our passions with dedication and perseverance.
May Dr. Andualem's life be a blessing to us all, and may we strive to live our lives in a way that honors his memory and legacy.
As we say goodbye to this remarkable individual, we take comfort in the knowledge that his legacy will live on through the countless lives he touched. We will remember him as a brilliant surgeon, a dedicated scholar, and a compassionate servant-leader.
But most of all, we will remember him as a man of great principle and integrity, who lived his life with purpose, passion, and conviction. May we all strive to follow in his footsteps, and may his legacy continue to inspire and motivate us to make a positive difference in the world.
Our thoughts and prayers are with Dr. Andualem's family, particularly his three young children, who will deeply miss their loving father. May they find comfort in the knowledge that their father's life and legacy will continue to inspire and motivate us all.
Rest in peace, Dr. Andualem Dagne. Your life, legacy, and memory will never be forgotten.
As we close this tribute, we invite you to join us in honoring Dr. Andualem's memory by continuing his legacy of service, compassion, and excellence. Let us strive to make a positive difference in the world, just as he did.
We would like to extend our deepest condolences to Dr. Andualem's family, friends, students, patients, the University community and loved ones. May you find comfort in the knowledge that his life and legacy will continue to inspire and motivate us all.
Thank you for joining us in this tribute to Dr. Andualem Dagne. May his life and legacy be a blessing to us all."
Sincerely,
Yeshigeta Gelaw, M.D, M.Med
Chief Executive Director
College of Medicine and Health Sciences/Tibebe Ghion Specialized Hospital, Bahir Dar University
Bahir Dar, Ethiopian Ayele Seyfe
ባህርዳር ዩንቨርስቲ።
"የዶ/ር አንዷለም ዳኜ ጠብቀው አጭር የህይወት ታሪክ"
========================
[“ሕያው ሁኖ የሚኖር፣ ሞትንስ የማያይ ሰው ማን ነው?" መዝሙር 89:48]
"ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ከአባታቸው ከአቶ ዳኜ ጠብቀው እና ከወ/ሮ ደጌ ጥጉ ግንቦት 5 ቀን 1980 ዓ•ም• በምዕራብ ጎጃም ዞን ጓጉሳ ወንበርማ ወረዳ ቡራፈር ቀበሌ ተወለዱ። በወላጆቻቸው እንክብካቤ አድገው ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በቡራፈር የመጀመሪያ ደርጃ ት/ቤት፣ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሽንዲ ከተማ ሽንዲ ት/ቤት ተከታትለዋል።
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርታቸውን በቡሬ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተምረዋል። ከዚያም የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሁሉንም የትምህርት ዓይነት <<A>> በማምጣት በከፍተኛ ነጥብ አልፈዋል። ከዚያም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የላቀ ውጤት በማምጣት አጠቃላይ ከት/ቤቱ አንደኛ በመሆን አጠናቀዋል።
ከዚያም በ2000 ዓ•ም• ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ በውስን የህክምና ተማሪዎች የተያዘውን ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በ2005 ዓ•ም• የመጀመሪያ የህክምና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ የወርቅ ሜዳሊያና በዩኒቨርሲቲ ደርጃ የዋንጫ ተሸላሚ ሁነዋል።
በመቀጠልም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሌክቸረርነት ማዕረግ ተቀጥረው ከማስተማሩ እና ከምርምሩ ጎን ለጎን የሚውዱትን የህክምና ሙያ በመተግበር እያሉ ለላቅ ብቃት ደግሞ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቀዶ ህክምና ት/ት ክፍል ውስጥ በመማር በ2011 ዓ•ም• ተመርቀው ታዋቂ የቀዶ ህክምና ሀኪም ለመሆን በቅተዋል። በተጨማሪም በበጎ አድራጎት ህክምና በተለያዩ ሆስፒታሎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ለማህበረሰባቸው ሰጥተዋል።
ወጣትና ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ከነበራቸው የዕውቀት መሻት እና ከተገነዘቡት ከፍተኛ የወገን ችግር በመነሳት የጉበት፣ የሀሞት ከረጢት እና የቆሽት ሰብ ስፔሻላይዜሽን ት/ት በአ•አ• ዩኒቨርሲቲ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተከታትለው በ2016 ዓ•ም• አጠናቀው ዕንቁ ባለሙያ ለመሆን ችለው ነበር።
ዶ/ር አንዷለም ዳኜ በተለያዩ የት/ት እርከን ሲያልፉ በተለያዩ የውጭ ሀገራት ማለትም በጀርመን፣ በእንግሊዝ፣ በህንድ፣ በደ/አፍሪካ እና በቱርክ የተለያዩ ስልጠናዎችን የወሰዱና በዚህም ከፍተኛ ከበሬታን እንዳተረፉ የሙያ አጋሮቻቸው፣ መምህሮቻቸው፣ ተማሪዎቻቸው እና ታካሚዎቻቸው ይመሰክራሉ።
በስራቸውም ደከመኝ ሰለቸኝ የማያውቁ ቅን ፣ ትሁት፣ ሰው አክባሪ አዛኝና ሩህሩህ ሐኪም ነበሩ:: ለዚህም ብዙ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ተቋማት ለቅጥር ሲያጯቸው <<የማስቀድመው፣ እየተቸገረ ያስተማረኝ ማህበረሰብ አለ>> በማለት ለሚቀርብላቸው አጓጊ ገንዘብ እና ክብር አልተንበረከኩም::
ዶ/ር አንዱዓለም ዳኜ ህዝባቸውን ለማገልገል ካላቸው ከፍተኛ ፍቅር የተነሳ የሚሰጣቸውን ኃላፊነት ሁሉ በቅንነት ፈጽመዋል:: ዶ/ር አንዱዓለም ዳኜ ሀይማኖተኛ፣ ለሰው ሁሉ መልካም አሳቢ፣ ታጋሽ፣ ደግ፣ አንደበተ ርቱዕ ነበሩ::
የቤተሰባቸውን ሁኔታ በተመለከተ ጋብቻቸውን በስርዓተ ተክሊል በታላቁ ደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም በ2006 ዓ•ም• የፈጸሙ ሲሆን ከውድ ባለቤታቸው ከወ/ሮ ቤዛየ ግርማ የስምንት ዓመትና የአምስት ወር ዕድሜ ያላቸው ሁለት ሴቶችና የአምስት ዓመት ዕድሜ ያለው አንድ ወንድ ልጅ አፍርተዋል። ለቤተሰባቸውም ፍቅር የሚሰጡ፣ እጅግ የሚናፈቁ ተወዳጅ አባት ነበሩ::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወጣቱ ሐኪም፣መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር አንዱዓለም ዳኜ ሩቅ አስበው ስራ ውለው ወደ ቤታቸው ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው መኪናቸውን እያሽከረከሩ እያለ በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ጥር 24/2017 ዓ• ም• በተወለዱ በ 37 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል::
ሥርዓተ ቀብራቸውም ቤተሰቦቻቸው፣ የሥራ ባል ደረቦቻቸው፣ ተማሪዎቻቸው፣ታካሚዎቻቸው እና ወዳጆቻቸው በተገኙበት ጥር 25 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ7:00 በባህር ዳር ከተማ በድባንቄ መካነ-ህያዋን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን እየተመኘን ፤ ነፍሳቸውን በአባቶቻችን በአብርሃም፣ በይስሀቅ እና በያዕቆብ ቦታ በአጸደ ገነት ያሳርፍልን።
የሀዘን እንጉርጉሮ
==========
በክፉ በደጉ ከፊት የሚቀድም ፣
አንዷለም አንዷለም አንዱ እንቋችን የለም።
ለጆሮ ይከብዳል ውስጥን ለማሳመን ፣
ይኸንን ሞት መስማት እንደምን ያሳዝን።
ስንቱ እየለመነህ ስንቱ እያማተረ፣
ዕንቁ ጭንቅላትህ ቆሼ ላይ አደረ፣
የወዳጅ ዘመድህ ልቡ ተሰበረ።
ሜዳሊያ ያንተ ነው ሞራልና ወርቁ፣
አንተን የሚመሰል አይገኝም ዕንቁ።
አሜሪካ አማትራህ ለምኖህ አውሮፓ፣
ለወገንህ ፍቅር በገንዘብ ሳትለካ፣
ሌት ተቀን ስትለፋ ነበር የምትረካ።
ጉበቱና ጣፊያው ቆሽቱ ተቃጠለ፣
አንተ እምታክመው ለአንተ ሲል ቀለለ፣
ሀዘኑ ቅጥ አጣ <<ምን ልበል>> እያለ።"
በዶር አለማየሁ ባየ
«የሕክምና ማኅበረሰቡን ያስደነገጠው የዶ/ር አንዱዓለም ዳኜ ግድያ» BBC.
3 ሰአት በፊት
«ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በጥይት ተደብድበው የተገደሉት የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ዶ/ር አንዱዓለም ዳኜ ግድያቸው የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎችን እና የህክምናውን ማኅበረሰብ አስደንግጧል።
"በስንት ዘመን አንዴ የሚፈጠር ልጅ ነው" ሲሉ ዶ/ር አንዱዓለምን የሚገልፆቸው አብሮ አደጋቸው እና የሙያ አጋራቸው፤ ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ሦስት ዩኒቨርስቲዎችን ባዳረሰው የሕክምና ትምህርታቸው ተሸላሚ እንደነበሩ ያነሳሉ።
"በዘመን እና በጊዜ መሀል ብቅ ከሚሉ ዓለም አቀፍ ጭንቅላቶች አንዱ ነው" ሲሉ የሚገልፆቸው ሌላ የቅርብ ጓደኛቸው፤ ምድር ላይ ከኖሩበት 37 ዓመታት 26ቱን ትምህርት ላይ ማሳለፋቸውን ገልፀዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው የዶ/ር አንዱዓለም ወዳጆች እና ባልደረቦች ከግላዊ ሰብዕናቸው ጀምሮ አንቱታን ያተረፉ ሐኪም እንደሆኑ ይመሰክራሉ።
"ሕክምና ማንን ይመስላል ከተባለ ዶ/ር አንዱዓለምን ነው የሚመስለው" ሲሉም የሙያቸው ቁንጮ እንደሆኑ የሚያሰምሩ አንድ አብሮ አደጋቸው እና የሙያ አጋራቸው፤ በሁሉም ዘርፍ የተካኑ ነበር ይላሉ።
"ክፉ የማይወጣው፤ ታካሚዎቹን በሙሉ በእንክብካቤ የሚያክም" ሲሉ ሰብዓዊነታቸውን የሚገልፁት ወዳጃቸው "ታካሚዎችን በመንከባከብ፤ በማከም ብቻ ሳይሆን አንድ ሐኪም ከዕውቀት ባለፈ ታካሚዎችን የሚይዝበት መንገድ ምን ይመስላል ከተባለ ዶ/ር አንዱዓለምን ነው የሚመስለው" ብለዋል።
"ካለው ሰብዕና፣ ከሚሰጠው አገልግሎት እና ካለው ተቀባይነት አንፃር" ግድያው እንደረበሻቸው ያልደበቁ ሌላ ባልደረባቸው፤ ግድያውን "የሙያን ድንበር የጣሰ" ብለውታል።
"ከባህሪ እስከ እውቀት" ተክነዋል የተባሉት ሐኪም ቅዳሜ ጥር 24/2017 ዓ.ም. ከባሕር ዳር ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቆሼ በተባለ አካባቢ ደረታቸውን በጥይት ተመተው ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ ግድያው ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሯል።
"[ሞትን] እሱ ላይ የምጠብቀው አልነበረም። ምናልባት ብዙዎቻችን ካለቅን በኋላ፤ መጨረሻ ላይ ለሞት ይታጫል ብለን የምናስበው ሰው በእንደዚህ ዓይነት አደጋ መሞቱ. . ." አስደንጋጭ መሆኑን ተናግረዋል።»
ዶ/ር አንዱዓለም በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ስር የሚገኘው ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጉበት፣ የቆሽት ሰብ እና የሃሞት ከረጢት ስፔሻሊት ሐኪም፣ ተመራማሪ እንዲሁም መምህር ነበሩ።
በዩኒቨርስቲው ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር አንዷለም ዳኜ የጉበት፣ የሀሞት ከረጢት እና የቆሽት ሰብ ስፔሻላይዜሽን ትምሕርታቸውን ባለፈው ዓመት ነበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቁት።
በባሕር ዳር ከተማ በትርፍ ሰዓት ከሚሠሩበት አፊላስ ሆስፒታል ሥራቸውን ጨርሰው ከከተማ 10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው (የሆስፒታሉ ባለሞያዎች መኖሪያ) እየተመለሱ ሳለ ነበር አመሻሽ 12፡30 አካባቢ የተገደሉት።
ዶ/ር አንዱዓለም ከመገደላቸው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ሌላ ሐኪም ተመሳሳይ ጥቃት ተፈጽሞባቸው ማምለጣቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የታጠቀ እና "ሲቪል" የለበሰ ግለሰብ ወደ መንገድ ገብቶ ሐኪሙን ሊያስቆማቸው ሲሞክር በድንጋጤ ማምለጣቸውን አንድ የሙያ አጋራቸው ተናግረዋል።
"አንገቱን ቀርቅሮ ነዳጁን ተጭኖ መኪናዋን ነዳት። መኪናዋ በሦስት ጥይት ተመታች። እንደ አጋጣሚ ሆኖ [ሐኪሙ] አልተመታም። እንደዚያ ሆኖ አመለጠ" ብለዋል።
ይህ በሆነ በደቂቃዎች ልዩነት አካባቢው ላይ የደረሱት ዶ/ር አንዱዓለም ማንነታው ባልታወቁ ታጣቂዎች እንደተገደሉ የልጅነት ጓደኛቸው እና የሥራ ባልደረባቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል።
"የቤት መኪና ይዞ የሚንቀሳቀስ ማንም የለም። በዚያች መስመር የቤት መኪና ይዘው የሚሄዱት ሐኪሞች ናቸው" የሚሉት ግለሰቡ፤ ጥቃቱ ግን ዝርፊያ እንዳልነበር ተናግረዋል።
"የተወሰደ ነገር የለም። ስልኩም እዚያው ነው የተገኘው። ምንም የተዘረፈ ነገር የለም" ያሉት የሟች ጓደኛ፤ ጥቃቱ ዶ/ር አንዱዓለም ላይ ያነጣጠረ ነው ለማለት እንደሚቸገሩ ጠቁመዋል።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ ሥራ ኃላፊ ዶ/ር አንዱዓለም ያሽከረክሩት የነበረው መኪና እና ንብረታቸው ባለመዘረፉ ጥቃቱ እሳቸው ላይ ያነጣጠረ ነው ብለው እንደሚያምኑ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
'ግድያው የተቀነባበረ ነው' ብለው የሚያምኑት የሥራ ኃላፊው "ቀጥታ ረሽነውት ነው የሄዱት። ሞባይሉ አልተነካ፤ መኪናው አልተነካ፤ ጥለውት ነው የሄዱት" በማለት ግድያው ተራ ግድያ አይደለም ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
ቢቢሲ ከዚህ ቀደም የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ላይ በሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶች፣ ዝርፊያ እና ዛቻ "የደኅንነት ዋስትና" በመጠየቅ ለቀናት ሥራ እንዳቆሙ መዘገቡ ይታወሳል።
ከሳምንታት በፊትም የሆስፒታሉ የጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ ሆስፒታሉ ውስጥ መገደላቸውን ባለሙያዎቹ ተናግረዋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የሆነው በዶ/ር አንዱዓለም ላይ የተፈጸመው ግድያ በሕክምና ማኅበረሰቡ ከፍተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ እንደፈጠረ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
"የሚችል ሰው ጓዙን ጠቅልሎ ከዚያ ጊቢ ለመውጣት እያሰበ ነው። ለመሥራት ምንም አይነት ዋስትና የለም። የሆነ ነገር ሲፈፀምም የሚደርስ አካል የለም። ከተፈጸመ በኋላም አጣርቶ ፍትሕ የሚሰጥ የለም። በመሀል የሕክምና ባለሙያው ነው እየተጎዳ ያለው" በማለት አንድ ሐኪም ድባቡን ተናግረዋል።
ሌላ የዩኒቨርስቲው ሠራተኛ በበኩላቸው "ተረጋግተው የሕክምና አገልግሎት እንዳይሰጡ እየተደረገ ነው" ሲሉ በሆስፒታሉ ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ጥቃት ውጤት ተናግረዋል።
በአማራ ክልል ያለው ግጭት እና የፀጥታ ሁኔታ ዳፋ ተደርጎ የታው የዶ/ር አንዱዓለም ግድያ፤ የክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ለሕክምና ባለሙያዎች መጠቃት "ክፍተት" እንደፈጠረ አንድ ሐኪም ጠቁመዋል።
ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት የሆኑት ዶ/ር አንዱዓለም ዳኜ የቀብር ሥነ ሥርዓት እሁድ ጥር 25/2017 ዓ.ም. በባሕር ዳር መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል።
እስካሁን ከዶክተሩ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረም ሆነ የተያዘ ሰው የለም። የባሕር ዳር ከተማ ፖሊስ ግድያው "ባልታወቁ ኃይሎች" እንደተፈፀመ በመግለጽ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን አሳውቋል።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/02/2025
በቃችሁ ይበለን ፈጣሪያችን። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ