#ውስጤን በስሱ።
እንዴት አደራችሁ ክብሮቼ። ውስጤን ብጥብጥ ያደረገው ግፋዊ እርምጃ ስከታተል አንድ ጹሁፍ አገኜሁኝ። ሰማዕቱ አልፏል። ነገስ ነው ጥያቄው። በስሱ ሁለት ዓመት ሊቃረበው ያለው ትግል እና ሂደቱን እስኪ እንቃኜው። ብዙ ቻልኩ፤ ብብዙም ታገስኩኝ።
ዘጋቢው አቶ ይክበር ይመስገን በ6 ወር ብቻ 87 #ንጹኃን ተገድለዋል ባይ ናቸው። የገዳዮችን ግምታቸውንም አስቀምጠዋል። ጦርነት ውስጥ #በቀል #ቂም ምግቡ ነው። እናም የአማራ እናት ተሰቃዬች። ይህ ባህርዳር ብቻ ሳይሆን ከወሎ ደሴ ሃይቅ - ኮንበልቻ - ወልድያ ከተሞች ውጪ ያሉ የአማራ ከተሞች ማርቆስ፤ ዳንግላ፤ ፍኖተሰላም፤ ደብረታቦር፤ ጋይንት፤ አዲስ ዘመን፤ ዳባት፤ ደባርቅ፥ አዲስዘመን፤ ወረታ፤ አይከል፤ ጎንደር ከተማም በመሰሉ ከተሞችም ግፍ ይፈፀማል። ፌድራሉ ከህወሃት ጋር በደቡብ አፍሪካ ስምምነት ሲያደርግ ደስታዬ ወደር አልነበረውም። አፈሙዝ ፀጥ ሲል የከተማ ነዋሪወች እረፍት ታዬኝ።
የሆነ ሆነኖ የፋኖ ንቅናቄው የተጀመረው #ከተማ ላይ ነበር። ግራ ነበር የተጋባሁት። ቀደም ብሎ ከዚህም ከዚያም እንድሳተፍ ያወያዩኝ ነበሩ። የማይታሰብ ነገር። በህይወቴ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የድርጅት አባል የሆንኩት። ድርጅቴ ሲፈርስ በቃ። መለካለክ ከሌላ ጋር ሰብዕናዬ አይፈቅድም። በምን ቋንቋስ ልንግባባ??? ወደፊትም የዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባልም አካልም አልሆንም። ፈጽሞ።
ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ የሽምቅ ውጊያ እኔ በታሪኬ ከተማ ውስጥ ከመደበኛ ሰራዊት ጋር ፊት ለፊት ሲገጥም ያዬሁት አሁን ነው። ከተማ ላይ ሽምቅ መሪወቹ እነ ሻለቃ ዳዊትየተገኜውን ድል ዘገባ ሲያቀርቡ ሰምቻለሁ። 4ኪሎም በቅርቡ ሲሉ አዳምጫለሁኝ። እዬገረመኝ።
መከራውን የተሸከመው ግን የአማራ ህዝብ ነው። ለምን ይህ መሰል ስልት እንደ ተጀመረ አላውቅም። ቀድሞ ነገር ገና ከእስር ባልደራሶች ሲፈቱ አቶ እስክንድር ነጋን #ፋኖን እመራለሁ እንዳትል ብዬ ጽፌያለሁኝ። ምክንያቱም ባልደራስን እዬመራ ኢትዮጵንያዝም፤ ከተሞችን፤ የአማራ ተጋድሎን፤ ተዋህዶን የመምራት ዝንባሌ እንደነበረው አስተውል ነበር። ሃሳቡ መልካም ቢሆንም የፖለቲካ አደረጃጀት መርሁ ግን ያግደዋል። ባልደራስ የከተማ የፖለቲካ ድርጅት ነው። ለዛውም የአፍሪካ መናህሪያ የአዲስ አበባ። ትልቅ ተልእኮ የገዘፈ ብቃት የሚጠይቅ።
የባልደራስ የአደረጃጀት ባህሬ በፍፁም ደንበር ተሻግሮ ስለማይፈቅድ ነበር አስቀድሜ የፃፍኩት። በሌላ በኩል "እስክንድር #መሪዬ ነው" ብሎ ዘሜ ሲናገርም የአዲስ አበባ ነዋሪ ሳትሆን በምን መርህ ነው እስኬው መሪህ ሊሆን የሚችለው፦ ይቅርታ ጠይቅ ወይ ኃላፊነትህን አስረክብ ብዬ ጽፌያለሁኝ። በዚህው ፔጅ ላይ። ማደራጀት እኮ ሙያዬ ነው። ባልደራስ ገና ሲወጠን ይህ ስህተት እንዳይመጣ ሰፊ ጹሁፍ አዘጋጅቼ ደጉ ሳተናው ላይ ተለጥፎም ነበር። ለመማር በመርህ ለመመራት ለፈቀደ። የፖለቲካ ድርጅት አቋራጭ መንገድ የለውም። ገዢው መርህ ብቻ ነው። መተዳደሪያ ደንቡ እና ፕሮግራሙ ብቻ ናቸው ጎዳናው።
የአደረጃጀት መርሁ ስለማይፈቅድ ነበር ዘሜን እርማት እንዲያደርግ የፂፍኩለት። ከመርህ ውጪ አንድ ድርጅት ከሆነ #አናርኪዝም ይመጣል። አናርኪዝምን #ማኔጅ ማድረግ ፈጽሞ አይቻልም። የሆነው ሁሉ በዚህ ውስጥ ማለፍ ግድ ነው። ለዚህም ነው እኔ በጥንቃቄ፤ በጥሞና ጉዳዩን ስከታተለው የቆዬሁት።
የቤታችን ብዙ ትንታጎች የሉም። ጦርነቱ በልቷቸዋል። አስቸኳይ ጊዜ ከታወጄ በኋላ የት እንደገቡ አላውቅም። ወሎ ግን ከተማ ላይ ፋኖ ብዙም አክቲብ ስላልነበረ ብዙ ድቀት ውድመት እንዲህ መራራ መለያዬት አልደረሰም። ወልድያ በአንድ ወንድማችን ከደረሰው ውጪ። ለዚህ ነው እነ ዋርካው ምሬን አዘውትሬ እማመሰግነው። ጠንቃቃ ሰው ያስፈልጋል።
#አድነዋለሁ ለምትለው ህዝብ እና መንፈስ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ብዙ ተግባር ነው የቆመው። ብዙ ትጋታችን ነው የተስተጓጎለው። ይህን የሚያውቅ የለም። ረቂቅ ህዝብ ጠቀም ተግባሮች ቀጥ ብለዋል። ግብሩ የሰው ነው ለዛውም በገፍ። ድርጅቱ ደግሞ #የማይበረክት። #የተጎዳ #ተጎዳ። የአማራ ክልልም ድቅቅቅቅ አለ። ብዙ ሰውም ኑሮውን አደላድሎበታል። ዛሬ እንዲህ ሊረሳ።
ግንባር - ኃይል - ድርጅት የስሙ #ብዛት የመስዋዕትነቱ ክብደት ልክ የለውም። አያንዳንዱ #የራሱን #ልጅ #ትዳር #ቤተሰብ ዋስትናው ወደ ተጠበቀበት ያዘዋውራል። የሌላው እንዲማገድ ግን #ርህርህና የለም። ሰሞኑን #ስለማኒፌስቶ አዳምጣለሁኝ። ማን ሊሠራበት? ማንስ ሊያነበው???? ምንስ ተመክሮ ምንስ ልምድ አለና???
ያው ለተጨማሪ የአማራ እናት ማህፀን፤ ለአማራ አባት ማገዶነት። ለዛውም ለአማራ ህዝብ ትፍስት አይደለም። መከረኛ አማራ የ120 ሚሊዮን እንደ ትናንቱ ዛሬም #ቤዛ ሁን፤ "አንተ ለጫንክበት የባህል ተጽዕኖ የጫንከውን ለማንሳት ተገበር ነው። " ግፋ እኮ ጫንተደል ነው። ሁልጊዜ ቀራኒዮ የሚታዘዝለት መከረኛ ህዝብ። "በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበታል።" አማራ ክልል በዚህ አመት ብቻ 5 ሚሊዮን ተማሪወች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው።
ታስታውሱ እንደሆነ 12983 ተማሪወች ከማትሪክ ውጭ ነበሩ። ቤተሰቡ በ5 ሲሰላ ወደ 64000 ይሆናል። ይህ ሁሉ ተስፋው እንዲመንን ሆኗል። ተምሮ በዲግሪ ተመርቆ ትዳር ይዞ ለወለደ ታጋይ ይፈታልን በሚል። በኋላ እኮ ዘሜ ተፈታ። ዕድሉ ግን አመለጠ። ወጣቶቹ ተፈትነው ይደርስ ነበር እኮ። በቀል የሚሹ ነበሩ ተሳካላቸው። እኔም አንጀቴ ቁርጥ አለ። ምርቃታችን ስለተነሳ ነው ጥበብ የጎደለን። ስንቱን ትብትብ ያሸነፋ ጀግኖች ደግሞ እንዲህ እንደ ማይተካው ዶር አንዱአለም ዳኜ መንገድ ላይ ይቀራል። የአማራን መማር መላቅ ተፈልጎ ይመስላችኋልን? አይፈለግም። ያ ነው ማዳበሪያ ያገኜው። ብልህ ሰው ጠፍቶ።
ጎጃም እኮ የዕውቀት #አንከር እኮ ነው። በስራ ይሁን በማህበራዊ ህይወት የማገኛቸው የተለዩ ናቸው። ትምህርት ለቅኔው ጎጃም ፀጋው ነው። ያ ፀጋ ነው እዬስተጓጎለ የሚገኜው። ያ ሁሉ ነው ድፍንፍን ያለው። ግራ ነው የሚገባው። "በሞኝ ክንድ ጉድጓድ ይለካበታል ነው።"
ሁሉንም ነገር ገላልጬ መፃፍ ጠፍቶኝ አይደለም። መኖሬን የሰጠሁለት ትግል እንዲህ መላ ቅጡ ሲጠፋው ዝም ያልኩት። ዝምታም መልስ ከሆነ፤ ቆርጠው ዱር ቤቴ ላሉትም ክብር ስል ብቻ ነው። ከጅምሩ፦ ከአካሄዱ ከአስተሳሰቡ፦ ብዙ የተፋለሱ፦ በውስጡ ያልጠሩ መስመሮች ነበሩበት።
ጎልጉል ላይ አቶ ግርማ ካሳ የፃፋትን ሳነብ ይህ ሁሉ ሆኗልን ነው ያልኩት። መቼም እሳቸው እማይገቡበት የለም። በሁለቱም አያቶቼ ኦሮሞ ነኝ ብለውን ነበር ከመሼ፤ ለምን አሁን ደግሞ አራጊ ፈጣሪ ሆነው እንደተገኙ ባላውቅም #እግዚኦ ነው ያልኩት። መቼ እሳቸው ለጥሞና ጊዜ እንደሚኖራቸውም አላውቅም። በዚህ ሁሉ ውድመት የትውልድ ድቀት ተጠያቂነቱን መውሰድም ግድ ይላል።
እኔማ እግዚአብሄርንም አመስግኜለሁኝ። በዚህ ሁሉ ድቀት፤ በዚህ ሁሉ ውድመት፦ ተመን ሊወጣለት በማይችለው የህዝብ ሰቆቃ ማህበርተኛ ባለመሆኔ። በሎቢ ስንት ተግባር መፈፀም ይቻላል ነበር። ህወሃትን ያህል በሁለመናው የገዘፈ ድርጅት ፈቅዶ ከስልጣኑ የለቀቀው በዊዝደማዊ ጉዞ ብቻ ነበር። የአማራ ህዝብ የዝብሪት ቤት ሳይዘጋ ያድራል እንደሚባለው ዘመን ከዘመን እንዲህ ማገዶነቱ እንደ አንድ የአማራ ልጅ፤ እንደ አንድ ዘወትር ቅን እና ቀና በርህርህና ዓላማዋን እንደምትመራ ባተሌ ማህፀኔ እንደ ዱባ ይቀረደዳል። አዛኙ ከፈጣሪው ከአላህ በስተቀር አባ ቅንዬ አማራ የለውም።
ይህን የመሰለ ብልህ፤ ርጉ፤ ፈዋሽ፤ ልዑቅ፤ ቅኔ፤ ግሥ፤ ሰዋሰው የሆነ ወንድም ማጣት ቀላል አይደለም። ሃዘኑ ሃዘኔ ነው። አንጀቴ ቁርጥ ብሏል። ወደፊትስ መጨረሻው ምን ይሆን? ምከሩበት። ከዋርካው ምሬም ተማሩ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ቸር ዋሉልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
04/02/2025
በቃችሁ ይበለን አላሃችን፤ አምላካችን አሜን።
Yikber Yimesgen Almaw
"የአማራ ክልል የገዳይ መዋቅር !"
"የዶ/ር አንዷለም ታዋቂነት ጉዳዮን በሚዲያ ለብዙ ሰው እንዲደርስ አደረገው እንጅ በ6 ወር ውስጥ በባህር ዳር ከተማ ብቻ 87 ንፁህ ሰዎች ተረሽ*ነዋል፤ በርካቶችም እየታገቱ አካውንታቸው እንዲገለበጥ ተደርጎ የደረሱበት ጠፍቷል። ዶ/ር አንዷለም ደግሞ 7ኛው ዶክተር ነው።
በዋናነት ይሄን የሚመሩት እድሜ ዘመናቸውን ጎንደርን በእገታ እና በግድያ ሲሰቀዩ የኖሩ እና ይሄን መዋቅራቸውን በተደራጄ መንገድ ወደ ባህርዳር የዘረጉ ናቸው ቡድኖች መሆናቸውን በተደጋጋሚ በተጨባጭ መረጃ ስንናገር ነበር፤ እየተናገርንም ነው።"
"ባህር ዳር ከተማ ውስጥ እንደዚህ አይነት ግድያዎችና አስሮ መሰዎር የተጀመረው እኮ እነዚህ ሰዎች ወደ ክልሉ ከገቡ በኋላ ነው።
አሁንም ይኸው ነው :-
1ኛ - በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አሥተባባሪ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው
2ኛ - የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን
3ኛ - የአማራ አድማ ብተና አዛዥ ኮሚሽነር ዋኘው አዘዘው
4ኛ - ኮማንደር መሰረት
እነዚህ ሰዎች የሚመሩት ገዳይና ዘራፊ ቡድን ሰንሰለት ካልተበጠሰ ብዙ ዋጋ እንከፍላለን። ይኸነው የሸበሉ ፡በምስሉ ላይ የምታዩት ደስየ ደጀኔ ነው"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ