የአማራ እናት ዘመኗ መቼ ይመጣ ይሆን?

 

የአማራ እናት ዘመኗ መቼ ይመጣ ይሆን?
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
ፀጥ ብሎ ህግ አክብሮ ቢሰራም #መገደል። እታገላለሁ ቢልም #መሰዋት። እማራለሁ ሲል #መታገት። እኖራለሁ ሲል #መጨፍጨፍ። ብቅ ሲል #መጨፍለቅ ወይ #መጠለፍ። አንደበቱን ሲገልጽ #ካቴና። የመከራው ሁሉ የምትሸከም ምስኪኗ የአማራ እናት፤ እህት፤ አክስት ሚስት። ወይንም የትዳር አጋር።
ትግሉ በዬፈርጁ የሁሉ መዳረሻ መከበሪያ፤ መሞገሻ፤ ቢላ ቅንጡ ቤት እና ሥልጡን መኪና መግዣ፤ ወይ መሸለሚያ መሞካሻ፦ ለሰብዕና ግንባታ። እና የአማራ እናት #ዘመኗ መቼ ይመጣ ይሆን???? የልብ አድራሿዋ ጥቃት አውጪዋስ ማን ይሆን???? ይህን መከራ አስቀድሞ መታገል ወይንስ እንደ ቄራ ሥጋ ለቅርጫ ማብቃት?????
ከአቶ ደጀን ፔጅ ነው ያገኜሁት። ሰሞኑን ጠቅላይ ሚር አብይ ቶርች አላደረግነም እያሉ ይደሰኩራሉ። የአዲስ አበባው የቢላ ቤት እስር ቤታቸው የግላቸው አይደለምን? ወለሉ በደም የጨቀዬ ስለመሆኑ ያፈኗቸው እኮ ገልፀውልናል። ይህስ ምስኪን የአማራ ባንክ ሰራተኛ አቶ ኢሳያስ በላይ በምን ህይወቱ አለፈ ይሆን? ሞጋች የለወት???? ድብልቅልቅ፤ ቅይጥይጥ ስላለ ድሮ እንሞግተወት የነበረው ይስከን ብለን እንደ ሳይለንት ማጆሪቲው ፀጥ አልን። ግራ ቢገባን።
የጠራ የትግል መስመር ቢኖር ግን ሃሳብ ያለው የለም የሚሉትን ዲስኩሮወትን #እንጦርጦስ የሚልክ ሃሳብ አመንጭተን መቀናጣተወትን #ቅስሙን በሰበርነው። ግን አቅጣጫው ባለዬለት ትግል አቅም ማፍሰሱም ሆነ መድከሙ ትርፍ እና ኪሳራው ተመዝኖ #ተጠሞን። እንጂ እርስወ እራሰወት አባል ሳይሆኑ #በውራጅ አባላት ይህን ያህል መዋለ ንዋይ ጊዜ ሲባክን ዝም - ዝም - ዝም ባልተባሉ።
"የደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የቆዳ ስፔሻሊስት የሆኑት ኤልሳቤት ተሾመ በአገዛዙ የብልጽግና ወታደሮች (ሚኒሻ )ጥይት ተገደ*ለች ።
ዶክተር ጥበቡ አለነ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የ2ኛ ዓመት የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ፕ/ት ሐኪም የነበረው ዶ/ር ጥበቡ አለነ ከሆስፒታሉ በር ፊትለፊት በሚገኝ አነስተኛ ሆቴል ተገድ*ሎ ተገኝቷል።
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ከመኪናቸው አስወርደው ገደሏ*ቸው።
በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት እየፈፀሙብን ነው። ይሄን መገንዘብ ግን አቅቶናል !!"
😭😭😭
ሰማዕታቱ ጀግኖቻችን ናቸው።
ሥርጉትሻ2025/02/02

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?