"በጀርመን የገና በዓል ገበያ ላይ ጥቃት ያደረሰው ማነው? ለምንስ ጥቃቱ ተፈጸመ?" BBC የእኔ ዕይታም። #ሩህሩሁ #አገረ #ጀርመን እግዚአብሄር ያጽናህ። አሜን።

 

 

 

https://www.bbc.com/amharic/articles/c7vem6yjy23o

 

"በጀርመን ማግደቡርግ ከተማ ሕዝብ በተሰበሰበት የገና ገበያ ላይ በተፈጸመ የመኪና ጥቃት የ9 ዓመት ሕጻንን ጨምሮ አምስት ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።

አንድ ግለሰብ መኪናውን ሕዝብ በተሰበሰበት ገበያ ላይ እንደነዳ እና በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የጀርመን ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቡ ጥቃቱን ብቻውን ነው የፈጸመው ተብሏል።

የመጀመሪያው ድንገተኛ ጥሪ ሲደረግ ግለሰቡ መኪናውን የገና በዓል ገበያተኞች ላይ መንዳቱ ተገልጿል።

ድንገተኛ አደጋ ነው ተብሎ የታሰበ ቢሆንም ጥቃት መሆኑ ኋላ ላይ ታውቋል።

የእግረኞች መንገድ ላይ ነድቶ ሰዎቹን እንደገደላቸው ተገልጿል። መንገዱ ለአደጋ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል ነው።

ቢቢሲ ያላረጋገጠው ቪዲዮ ግለሰቡ መኪናውን በቀፍጥነት እየነዳ ገበያውን ደረማምሶ ሕዝብ ወደተሰበሰበት ሥፍራ ሲያቀና በማኅበራዊ ሚዲያ ወጥቷል።

የዐይን አማኖች ከእግረኛ መንገድ ሮጠው በማምለጥ ራሳቸውን እንዳዳኑ ተናግረዋል።

ግለሰቡ ወደ እግረኛ መንገዱ በገባበት መንገድ መልሶ መውጣቱን ፖሊስ አክሏል።

ግለሰቡ ጥቁር ቢኤምደብሊው አጠገብ በቁጥጥር ሥር ሲውል ታይቷል።

አጠቃላይ ክስተቱ 3 ደቂቃ የሚወስድ ነው።

እነማን ተጎዱ? ተጠርጣሪውስ ማነው?

በመኪና ጥቃቱ የ9 ዓመት ሕጻንን ጨምሮ አምስት ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።

ቢያንስ 41 የሚሆኑት አስጊ ሁኔታ ውስጥ ናቸው።

የሞቱት ሰዎች ማንነት ገና ይፋ አልሆነም።

ጥቃቱን የፈጸመው የሳዑዲ አረቢያ ዜግነት ያለው የ50 ዓመት የሥነ ልቦና ባለሙያ ታሌብ አል-አብዱልሞህሰን መሆኑ ተገልጿል።

የሚኖረው ጥቃቱ ከደረሰበት ከተማ በ40 ኪሎሜትር ርቀት በሚገኘው በርግበርግ ነው።

በግድያና የግድያ ሙከራ እንደሚከሰስ በዐቃቤ ሕግ ተገልጿል።

ተጠርጣሪው ጥቃቱን ለምን እንደፈጸመ ግልጽ አይደለም።

 

በ2006 ወደ ጀርመን እንደሄደና በ2016 ጥገኝነት እንዳገኘ ተገልጿል።

የጀርመን የአገር ውስጥ ሚኒስትር ናንሲ ፌሰር ተጠርጣሪው "ሙስሊም ጠል እንሆነ በግልጽ ማየት ይቻላል" ብለዋል።

ተጠርጣሪው በማኅበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ድረ ገጾች ላይ እስልምናን እንደሚነቅፍ የሚጠቁሙ ጽሑፎች የተገኙ ሲሆን፣ የጀርመን መሪዎች አውሮፓን ሙስሊም ለማድረግ እየተመሣጠሩ ነው የሚል የሴና ትንታኔም ያራምራል።

ከአንድ ዓመት በፊት ስለ ግለሰቡ ለፖሊስ ጥቆማ ቢሰጥም አስጊ መሆኑን የሚጠቁም ነገር አለማግኘታቸውን አመራሮች ተናግረዋል።

ስለ ጥቃቱ ምን ተባለ?

የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሹልዝ "ከማግደቡርግ የሰማነው ዜና ከፍተኛ ፍርሃት ፈጥሯል" ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ጽፈዋል።

የማግደቡርግ ከተማ ካውንስለር ኖኒ ክሩግ፣ የገና ገበያው ዝግ እንደሚሆን ተናግረዋል።

የገበያ አካባቢው መዘጋቱን አስታውቆ በጥቃቱ የደረሰውን ሐዘን ለመግለጽ ጥቁር ስክሪን ታይቷል።

የሳዑዲ መንግሥት ለጀርመን ሕዝብ ሐዘኑን ገልጿል።

"የጀርመን ሕዝብ ከጎናችሁ ነን። በጥቃቱ ከሞቱና ከተጎዱ ቤተሰቦች ጎንም እንቆማለን። እንዲህ ያለ ጥቃትን እናወግዛለን" ብሏል የሳዑዲ መንግሥት።

የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር "በጥቃቱ አዝነናል። ለሞቱት፣ ለቆሰሉትና ጥቃቱ ጠባሳ ለጣለባቸው ሐዘናችንን እንገልጻለን" ብለዋል"
 
#ሩህሩሁ #አገረ #ጀርመን እግዚአብሄር ያጽናህ። አሜን።
#የአስጠጋ አገር፤ #ነፍስን ያተረፈ አገር፤ #መኖርን ያስቀጠለ አገር፤ #በሙያ ቀጥሮ በከፍተኛ የክፍያ ደረጃ የሚያዝመነምን አገር እንደምን ይህን በሰል የበቀል በደል ይፈፀምበታል? ለምን ለደግነት ጭካኔ ይመለስለታል??? ለዛውም በከፍተኛ፤ በልዩ ሁኔታ በሚጠበቀው ባይናክተን እና አዲስ አመት። ህዝብን መንፈሱን ተስፋውን ጥቁር ማልበስ እንዴት ታቅዶ ይፈፀማል???
በቀጣይስ ስደተኛን በሚመለከት የአውሮፓ ህብረት ምን ውሳኔ ላይ ይደርስ ይሆን? ጀርመን እኮ አንድ ሚሊዮን የሶርያ ነፍሶችን ያተረፈ እናት ሆዱ፤ ሩህሩህ፤ የሰባአዊ መብት አይነታ ገቢረኛ አገር ነው። በዛ ዘመን ሌሎች የአውሮፓ አገሮችም ችግሩን ሼር ያደርጉ ዘንድ ወሳኝ ሚና ክብርት የእኔ ልዕልት የወቅቱ የጀርመን ጠቅላይ ሚር ዶር አንጊላ ሜርክል ነበሩ። ልዩ የዘመን ስጦታ ናቸውና። ኖቤል እንዴት እንደማይሸልማቸው ሁሉ ይገርመኛል።
የሆነ ሆኖ እንዴት ይህን መሰል #በቀል #በንፁሃን ላይ ሊወሰድ ተደፈረ? ለዛውም በህክምና ባለሙያ። አያችሁ ስንፈጠር ንፁህ ሆነን ነገር ግን፤ ንጽህናችን የሚያስቀጥል ተቋም አለማችን ስሌላት ክፋ ነገር ተበራከተ፤ የህግ ጥሰት ተስፋፋ፤ ስልጣኔን ስልጣኔ እያጠፋውም ነው።
ለዚህም ህግ የጥቂት ባለሙያወች ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡ እውቀት ይሆን ዘንድ አለማችን ልትሰራበት ይገባል። በተጨማሪም ህግን እና የፍቅር ተፈጥሮ ለሁሉም እንደ ተፈጥሮ ሳይንስ እና እንደ ማህበራዊ ሳይንስ ካሪክለም ሊነደፍለት ይገባል የምለው ለዚህ ነው። ልጆችም ሊማሩት ይገባል። በመደበኛ። ዓለማችን ሁልጊዜም ታስፈራኛለች። ክፋ ሃሳብ ስለተከዘነባት።
የሆነ ሆኖ ጉዳቱ ለደረሰባቸው ቤቴሰቦች ሁሉ #መጽናናትን እመኛለሁኝ። አይደለም የእኔ ቢጤ ስደተኛ የአለም ዜጋ ሁሉ ከጭካኔ ሃሳብ እና ድርጊት የሚወጣበት መንገድን ፈጣሪ ያሰናዳ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
22/12/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።


 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።