የፈጣሪ፤ የእናት እና የልጅ ውለ ወግ -በቅኔ ዘጉባኤ ህዋዊ ጠረጴዛ።
የሰለሥቱ ጥምር
ትምህርተ ተመክሮ።
የፈጣሪ፤ የእናት እና የልጅ
የበሰለ፤ የበቀለ፤ ያሰበለ
ብልህ ውለ - ወግ።
„ልጄ ሆይ ቃሌን ብተቀበል፣
ትእዛዜን በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፣
ጆሮህን ጥበብን እንዲያድምጥ ታደርጋለህ፣
ልብህን ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ።“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፪ ከቁጥር ፩ እስከ ፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
21.11.2018
ከአገረ ደናግሏ ሲዊዝሻ።
·
እፍታ።
እንዴት ናችሁ ቅኖቹ? የነፃነት ታጋይ ወገን ሲታሰር የሚከፋችሁ፤ ሲፈታ ደስ የሚላችሁ፤ ሰው ሲቸገር
የሚጨንቀችሁ ሲቃለልለት ፍስሃ የሚኖራችሁ፤ ሰው ሲሰቃይ የሚመራችሁ ከስቃይ ሲፈወስ የምትፈኩ፤ ልጆች ከወላጆቻው ተለይተው ካቴና
ሲባላቸው የምታነቡ ነፃ ሲሆኑ ደግሞ በሐሤት የምትፍነከነኩ ቸሮቹ የአገሬ የልዕልት ኢትዮጵያ ልጆች ከቶ እንዴት አላችሁልኝ?
ተስፋ ካለ ምን ያስፈልጋል ትሉኝ ይሆን? ተስፋን ስንቅ የሚያደርጉ ስለተፈጠሩበት ሚስጢር ጥበብ
ያላቸው ስለመሆኑስ? ሄውዞን የተቃኙ እንደማለት። አጥቁሮ ያከሰለን፤ ተስፋን የዋጠውን ቀን አልደመጥ ብሎ እንጂ ተስፋን ሰንቆ ማን
ጦም ውሎ ያድራል? ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተስፋ ባለቅኔ ናቸው።
ቅኔኛም ብቻ ሳይሆን ቃላት አዲስ የመፍጠርም፤ የማራባትም /የማግሰስ/፤
የማዘመንም እና ለህሊና ምቹ እና ጣፋጭ፤ ለጆሮም ድሎተኛ አድርጎ የማቅረብ አቅማቸው በመሪ ደረጃ በእኔ ዕድሜ የመጀመሪያው ናቸው።
ጣዕሜ የሆኑትም ከዚህ አንጻር ይመስለኛል። ቅንነታቸው እና ርህርሀናቸው ደግሞ የህሊና ካሊም ነው።
· ቅኝተ ተህሊና።
የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ንግግሮች ሌላ ሰው እንደሚጽፍላቸው የሚገምቱ አሉ። ይህን የቀደመ ንግግርቸውን
ካላደመጡት፤ እንደ አንድ የትህርት ሌሰን እንዳለጠኑት ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩልም ኢትዮጵያዊነትን ከእኛ ወሰደም፤ ተዋሰውም አለበት።
አለፍ ሲልም ከሌላም ቀሰመም አለበት። ዘመኑ ተለውጦ ዛሬ አድናቂያቸው መሆን ያስቻለ አቅምን ቀለመመቅደም ከከሳ የማድመጥ ፈቃድ
ሰጥ ካለመሆን የመነጬ ሊሆን ይችላል።
የሆነ ሆኖ ምን ያህል ጥልቅ የሥነ - ጹሑፍ አቅም እንዳላቸው ይህ ቅኔያዊ የውል የኪዳን ሰልስትዮሽ
ሥነ - ግጥማቸው ይገልጽልናል። ተውኔታዊም ነው። ጥያቄያችን ጥርጣሪያችን ሁሉ መልስ ያሰጠዋል ካለ መቁንነ ጊዜን ለአደብ ከሸለምን።
በተጨማሪም ገጣሚነት በባለቅኔነት ብቻ ሳይሆን የግሥ እርባታ ዜማው የተለዬ ነው። የሥነ ቋንቋ አንደበትም ናቸው ልሳነ ቋንቋ። በውነት ይመስጣል። ተጽዕኖም ይፈጥራል ከራስ ጋር
ወደ ሄውዞ ምልሰት እንድናደርግ ዘንድም የህይወት ጥሪ አለበት።
የዕውቀቱን ደረጃም ከፍ አደርገውታል ብዬ አስባለሁኝ - እኔው።
ቋንቋ በኽረ የዕውቀት ዘርፍ ነውና የመኖር እልፍኝም። ለዛውም ከአፍሪካ ተለይታ ለተፈጠረች የራሷ የፊደል ገበታ ላላት ውብ አገር።
ስለ አገር ለተፈጠረ ይህም ቅኔው ነው። ይህም ዳዊቱ ነው። ይህም ድርሳኑ ነው። ስለራስ በራስ ወስጥ ጌጥኛ መሆን።
ዶር አብይ አህመድ /አሜኑ/ የማይታወቁ ለመተርጎም የሚከብዱ ሲሆኑ፤ ቃላትን የመፍጠር አቅማቸውም
የዚያኑ ያህል ርዕሰ አምዴነታቸው አንቱ ነው። በዚህ ጀርመኖችም ሊቆች ናቸው። ጀርመኖች ቋንቋቸውን ዘመን ሰጥ ልቀት በማሰጠት እረገድ
አንቱ ናቸው። አሁን ጉግልን አግሰውታል፤ አራብተውታል፤ ስዋሰዋቸው ውስጥ የክብር ቤተኛ አድርገውታል። ኢንተርኔትን የኤሌትሪክ ፖስታ ቤት
አድርገው ተርጉመውታል። በዬጊዜው ቋንቋቸው በእድገት እንዲጓዝ ተቋማዊ ፍልስፍና አላቸው። ችግሩ ክብደቱ ነው። ከባድ ነው እኔን
ያሸነፈ።
በቃላት ሃሳብን ራዕይን ምናብን
የመግለጽ አቅም እና የመተርጎም አቅም ጣዕሙ እኛኑ ይመስላል ጀርመንኛው። ይህን እርእሰ ጉዳይ የዛሬ 6 ወር ገደማ ነበር የጀመርኩት፤
ስለኛ ለመሆን ውል ያለበትን ባለቅኔ ጠ/ሚር ቅኔውን ለመፈታተሽ። ግን ዘገዬ። ቢዘገይም አልቀረም እንደ ታሰበ። ስለምን ዘገዬ ሆነ
ቢባል አንደኛው ግጥምን ለመተርጎም ጊዜውም አቅሙም ስለሚጠይቅ ነው የዘገዬው። ሁለተኛው ደግሞ ይኼወኛው ይቆይ ሌላው ይቅደም በማለትም
ነው። ሰልስተኛው ግን ውሉን አጀማመሩን ጥቂት እዮባዊነትን በማጉረስ እስቲ ይታይ ለማለት ነው …
· ቅኘተ ተምናብ ህላዊው።
ዛሬ ግን ሙሉ ወርዴን በማለፊያ መቀነት ሸብ አድርጌ ተያይዠዋለሁኝ። ተፍጣሜ ላደርሰው። እችል
ይሆን? ትጠዬቅ ወፊቱ። ግን አልፎ አልፎም ከጹሁፌ ጋር ለማመሳከሪያነት ስጠቀምበት እንደቆዬሁም ይታወቃል። አልተረሳሳነም እንደ
ማለት። ተ-ትናንት በስትያም „በአችን“የጸሑፌ እርገት በዚኸው በሥነ - ግጥሙ መቅደመ ሥንኝ ነበር ስንብት ያደረግነው። መኖር ዕጣ ሰጥቶኝ
በሰለሥቱ ዕለት ደግሞ እርገትን ውረድ ብዬ ይኸው ተነስቻለሁኝ። ለመሄድ? ወደዬት በሉኛ? ወደ ባለቅኔው የምልሰት ዘመን… ከጽልመት ጋር ስለተፋለሙበት የውል ጠረጴዛ።
አሁን ወደ ተናሳሁበት ርዕሱ እንደማስበው … „ውል ያዋውላል ታንኳ ያሻግራል“ ይላሉ ጎንደሬዎች
ሲተርቱ። እውነት ነው። ይህ ብሂል ከእኔ "የውል" መጸሐፌ ላይ መቅድሙ ይገኛል። ውሉ የእናት እና ልጅ ስለሆነ ቀለበቱ እትብታዊ ነው። ሥጦታውም ልክብርት እናቴ ለእብዬ ነው። እትብታዊነቱ ደግሞ ፈቀደ እዮር ነው። ስለዚህ በሰልስተኛ ዘለስኛ ቅኝት ይሁንበት በለን መከረን። እናማ እንዲህ …
· ተመነሻ ተመድረሻ።
የግጥሙን ህሊና እና ብሌን መታሰብም፤ መደመጥም፤ መጣጣምም ያለበት ከዚህ አንጻር መሆን ይኖርበታል
ብዬ አስባለሁኝ። ከቁሳዊው ዓለም ወጣ እንበል እንደማለት። በገሃዱ ዓለም ውል ሳይሆን በመንፈሳዊው ዓለም፤ ነፍስን ለመስጠት ከቆረጠ መንፈስ ጋር ቁርኝቱ እንዲህ በመሰለ
መሆን ይታይ እንደማለት። ትንሽ ጠ ዕዳ መንፈስን እንሰንቅም እንደማለት። ዕለታዊ ሳይሆን ውሎ ዘላቂ ትርታ ነውና። ማዕልቱን ለመጨረስ ወስኜ ሳልተኛ አደርራለሁኝ ብዬ ወሰንኩለት።
ምን ሰዓት ላይ እንደምቋጨው አይታወቅም። ላንጋው ይሆን? ከ6 ወር በኋዋላ ነው የተነሳብኝ ልበል
ወይንስ ጣፊው ጣፊው ብሎ ያገረሸብኝ። የሰንበቷ „አችን“ የጻፍኩበት ጭብጥ ነው እንቅልፍ ጠል ውሳኔ ያቀበለኝ። ይመስለኛል። ተመስገን አቤቱ „አችን“ ስለ አንተ እኛን ስለሸለምከን። አሁን ድረስ አርምቱ ገትሮኛል ልክ አሁን 15.34 ነው። የገብያ ትልም ነበረኝ ግን ይቅር እሱ ... ተባለ ተወሰነ።
ፈጣሪ እኛንም ስለሰጠን ይመስገን። ምስጋናንስ ተመስገኝስ የሰጠን እሱ አይደለም። በነገራችን
ምስጋና የፍቅራዊነት መርህ ቤተኛ ነው። የሚያመስገን ፍቅር ገዢ ያደረገው ነፍስ ብቻ ነው። ብቻ ይመስገን መመስገን ለማማስገን ለሰጠንም። „አሜን“ በሉ!እንዲህ እያልኩ ልምጣ …
ቀኑ ተቆረጠ ግን ለውል መፍቻ የስኬትን ትልመ ማሳ እንደ አቅሚቲ እንሂድ በትርጉማዊ አብሮነት
ለማለት … ቅኔው የባለቅኔው ዩጠ/ሚር አብይ አህመድ ነው። አላዛሯ ኢትዮጵያ እንዲህ ዘምና ባለቅኔ ጠ/ሚር እንሆ ሰጣት። ምንተስኖት
ሸለማት ሸለመን። አይደከመውም እና አንድዬ ተመስገን ይመስገን። ምስጋና ስለሰጠን ስላቀባልን ስለፈቀደልን፤ ምስጋናን እራሱን ስለጠበቀልን
ስለ አበቀለልን ተመስገን! ይገባል! ለተገባው ውል እና ውል ተኮር ትትርና።
„አንቺ አገር ኢትዮጵያ“
· „አንቺ ሐገር ኢትዮጵያ ልኑርልሽ እንጂ ሌላ እኔ ምን አልኩሽ
ትላንትሽ
ከዛሬሽ ታሪክሽ ከዕውነትሽ ሥምሽ ከዕውነትሽ“
v ውስጡ በዕኔ
ዕይታ…
መኖሬን ፍቀጂ እና ለኪኝ። መኖር ከታሰረበት አገር መፈጠረ እስከዚህ ያስኬዳል።
ሲቀጥል ያለውን በምን ስሌት ትናንትን ተዛሬው ጋር ማወደድ ይቻል ይሆን? በማን ሊንክነት? በዕውነት
ዕውነትንት ከሆነ ከመፍትሄ መድረስ ይቻላል። እንዲህ ይላሉ ባለ ቅኔው ጠ/ሚር "ታሪክሽ አንቺን ሲገልጽ ከእውነት ነው። ሥምሽም ዕውነት ነው። ዕውነትም አንቺው
የኛው ነሽ። የዕውነትን ሥነ - ምግባር ሞራላዊ ዕሴት እምዬ እናትዬ ነሽ።"
"ጌታው¡ ዕብለት አንቺን የመግለጽ ድፈረትም አቅም የለውም
ነው። አቤቶ¡ ዕብለት
በዬወለሉ ተገኙልኝ እሷኑ ልግለጥ ቢል ለራሱም ደረጃውን አለማወቁን ይገለጥበታል፤ እናም ዝም ክርችም ዝግት ቁልፍ ቢል ይሻለዋል።
ማን እንዳቺ ውብዬ የዕውነት ማህደር? የአንቺን ልዕልና ዕብለት የመሸከም ወርዱም ቁመናውም ተፈጥሮውም አይችለውም።"
ባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ኢትዮጵያን ጸራቸው አድርገው፤ በጥርሳቸው ነክሰው የተነሱትን
የውስጥ እና የውጭ ሃይሎችን፤ እሷን ቅኝ ለማድረግ የተመኟትን የመንፈሰ ጸላዬ ሰናይ የምክክራቸው ላዕላይ እና ታህታይ ኩነታቸውን
በፍጹም ሁኔታ የአይዲወሎጂያቸውን ልዕልና አክሎ መሠረታቸውን ከሥሩ የነቀሉበት ጥልቅ ቅኔ ነው። ለቀደሙት የግራ ፖለቲካ ተፈላሳፊዎችም እሳቤ
ቅስሙን የተዳፈረ ጀግና ቅኔያዊ አጋላለጥ ነው። ተመስገን!
·
„ዕድሜሽ ከብስለትሽ ኑሮሽ ከሁላድሽ
አልጣጣም
ብሎ ላይሰምር ተዛንፎ“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
የ100 ዓመት ታሪከኞችን የናዱበት ነው ይህ ስንኝ። በፍጹም ሁኔታ አልራሩላቸውም። "የዘመን ግንድ
ነሽ!" ነው የሚሉት ባለቅኔው። በሌላ በኩል ደግሞ ይሄኛውን ከላይኛው ዕውነት ጋር ሲያያዝ የሚፈጥረው ረቂቅን መንፈስ ውህድነት በርቁቅ
ይገልጻል።
„ሁላድሽ“ አዲስ አማርኛ ነው።
አማርኛው ዜማ ያለው ቅኔ ነው። አመልካች ተውላጠ ሥምም ነው። ሁለመናሽ
/ ዕጣ ፈንታሽ/ ዕድልሽ/ተፈጥሯዊ ዕጹብ መክሊትሽ/ ለማለት ይመስለኛል። ይመስለኛል ነው ያልኩት ክቡሩነታቸው ይጠዬቁበት የጭብጣቸውን
የቃላት ፍቺ ዘር የሚያውቁት ባለቅኔው ብቻ ስለሆኑ። ውበት እንደ አካባቢው ይተረጎማል "ህልምም እንደ ፈቺው" አይደል የሚባለው።
የገዘፈውን የዕድሜ ጸጋሽ የሚመነጨው ከሁለመናሽ ዕውነትነት ጽንሰት ነው እንደ ማለት ነው። መዋለ
ዕድሜሽ ጥሬ ጮርቃ የወረት አይደለም። ተዛንፎ ካለመጠኑ ስለተተረጎመ ነው ስምረት ብሎ ነገር ውሃ የበላው ቅል ሆኖ የተኖረው። ከራስ
የልተነሳ ፍልስፍና የብል ቤተኛ ነው።
የበሰለ የጠራ የነጠረ ዝልቅ ቅኔኛ ነሽ ብናውቅበት ኖሮ፤ ግን እርግማን አለብን ይህንን ዕውነት
በጸና መሠረት ላይ የማነጽ፤ የተሰጠሽን መክሊትሽን በመቀበል እና በዛ ላይ የፀና ትውልድ ለመገንባት አቅማችን ተባደግ ሆነ። አልታደለንምና።
አንቺ የተፈጠረሽበት የበሰለ ጸጋ ጋር ፍጥረቶችሽ አልመጠነውም ነው። እውነት ነው።
·
„ተሆኝ ያለው ወዲያ የሆንሽው ግን ከወዲህ
በለሰሚው
ግራ ነው ተቃርኖ ተላልፎ“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
"በለስሚው።" በለስን የሚሰማ፤ የጸጋን ክህሎት መለከት የሚያዳምጥ ምክነት። ግን በለስ ራሱ መዳህኒት
ስለመሆኑ፤ መከራን ቻይ ስለመሆኑ ስንቶቻችን እናውቃለን። ቁሩን እና ሐሩሩን ወጀብን እና ዶፉን መካች ስለመሆኑስ? ከቀን አድራሽ ስለመሆኑስ?
ያው ልክ እንደ ግመል ዓይነት ተፈጥሮ አለው ኑሯቸውም በአንድ አዬር
ሁኔታ ነው። በለስ አዋጊም ተዋጊም ነው። ውጪ እሾሕ ወስጡ ገነት።
„ተሆኝ“ ይህም አዲስ የቅኔ ቃና
ያለው አዲስ ሥህናዊ አጠቃቀም ነው። ምርቃት አለሽ። ታጥቦ ፈጥሮሻል። ሁኚ ብሎ አምላክ በፈጠረሽ የምርቃት፤ የረድኤት፤ የበረከት ልክ
መሆን ሳትችይ መቅረትሽ ፍቺ ያልተገኘለት፤ መዳህኒት ያልተገኘለት፤ ፈቺ ጀግና ያልተገኘለት ግን በተቃርኖ እንዲኖር ራሱ በራሱ የተፈረደበት
ማለት ይመስለኛል። በጣም ጥልቅ ነው። መንፈስን ይሞግታል።
„ግራ“ ህግ ታላላፊውን የውሰቱን ርዕዮቱን ነው ወርቁ፤ ሰሙ ደግሞ ቅንነት ጎድሎናል፤ ቀጥ ካለው
አስተሳስብ ጎባጣውን፤ ከደልዳላው ተፈጥሮሽ ኮረኮንቹን፤ ከተመስጦ ጸጋሽ የአሽዋውን፤ ከምርጥ ባለምርቃትነት ድቀቃቂውን ትቢያውን እንመርጣለን ነው።
ስለሆነም የተፈጥሮን ህግም ተላላፊዎችን ነን።
በመንፈስ እነ ብላቴ ጌታ ሎሬት
ጸጋዬ ገ/ መድህንን እና አብዬ ለማን፤ አነ ዶር አዲስ አለማዬሁን ድንግል መንፈስ ድረሱላት ብሎ የሚማጸን የሥነ - ቃል ልዩ መስህብ
እና አወራራድ አለው። ትርጉም ረቂቅ ነው። ግራውም እራሱ እራሱን የሚቃረን እራሱን ኢትዮጵያ እንደትፈጠር ከተሰጠው የምርቃት ትርጉምነት
ጋር አስማምቶ ለመኖር ያልቻለ ደሃ ነው። የአስተሳሰብ ድህንትን ለማጠዬቅ ይመሰልኛል። በማንነቷ ላይ የተቃጣው መከራ እራሱም የተፈጠረባት
አባሪ ተባባሪ ሆኗል ነው። የራስ ተቃርኖ። ራሰን መሆን መሳን። ከራስ ለመነሳት ድፈረት ማጠት። ራስን ንቆ ብድርን ትውስትን ማከበር
ኪሳራ አወራራጁ የትወልድ ብክንትን ስለመሆኑ ያጠይቃል - ቅኔው።
አምላክ ሲፈጥርሽ በምክንያታዊ ሳህለ ኪኑ ቀድሶ ባርኮ ነው፤ እኛ ህግ ተላልፈን ስጦታሽን አይሆኑ
አድርግን አባከነው። እንኳንስ ለልጆችሽ ለተከፉት ሁሉ ጥላ ከለላ እንድትሆኚ አድርጎ ነበር አንድዬ የፈጠረሽ ግን „ግራ“ ዘመም
ፖለቲካ አይሆኑ አድርጎ ረቂቅነትሽን በእኩይነት በክሎ ለራስሽም መቆም እንዲሳነሽ አድርጎ አኮሰሰሽ፤ አከሳሽ፤ ጸጋሽን ተዳፍሮ እና
አሳንሶም በመንፈስ ሸነሸነሽ።
ግራ ፍለስፍናው ተፈጥሯዊነት ጋር መጻረሩ ነው አንቺን የቀበረሽ። ቅነንት ተፎጥራዊነት ነው። አዎንታዊነት ተፈጥሯዊነት ነው። መቻቻል
ተፈጥሯዊነት ነው። ትናንትን ማከብር ተፈጥሯዊነት ነው። ርህርህና ተፈጥሯዊነት ነው። ይህን ማብቀል፤ መስቀጠል የተሳነው ነው ግራ
እና ሁለመናሽን ግራ አደረገው ነው …
ስለዚህም ለሌላ ተራፊዋ ተመጽዋች ሆንሽ ነው ሚስጢሩ። ለራስ አለመብቃት። እንደራስ ለመሆን ካለመቻል
ብክነት የመነጨ ነው። በዚህ ውስጥ መቆርቆሩ፤ በውስጥ መቁሰሉ አገርኛ መስተዋድዱ ልባዊ እና ከመንፈስ የተነሳ ተፈጥሯዊ ፍቅር ከእናት
አገራቸው ጋር እንዳለ ይገልጣል። ቃል ኪዳን አለባቸው እኛ በማናውቀው እሱ በሚያውቀው። ይህ ቁሰል ዕደሜ ሙሉ እንዲሰናዱ አደርጓቸዋል
ብላ ሥርጉተ ሥላሴ በጽኑም በአጽህኖትም ታምናለች። ለዚህ ነው ከዛሬ ዓመት ጀምራ በአብዩ አሜኑ አክቲቢዝም ላይ የተጋችው።
እኛ ያልታዬን ግን እሱ የታዬው አምላካዊ ሥጦታ እንዳለ አምናለሁኝ፤ እቀበላለሁም። ለዚህ ነው
አብይ ኬኛን ሙግት ስጀምር አሁንማ በዓይኔ መጣህ ብዬ የኢሳቱን ጋዜጠኛ አቶ ማስረሻ ዓለሙን ሆነ መሰሎችን እሰከ የሚመካበት ሚዲያ
ሆነ ድርጅት የሞገትኩት። ሃግ ይባል ይገባው ስለነበር። የእዮር ሥጦታ በመደዴ ስሜት ሊቀነበጥ ሆነ ሊቀነደብ ስላማይገባውም።
የትውልዱ ዘመን ይዞ
ዘመን ብክነት የውርንጫ ድካሙን ከልቡ የእኔ ብዬ ስመረምረው ስለኖርኩ የህሊናዬ ማጣሪያ ወንፊት መንሹ ማን እንደሆነ ስለማምነበትም
ወጥቶ መሞገቱን ባሊህ አልኩት።
ሙግት የሚነሳው አንድ ነገር ብቻ ነው አጀብ፤ የጎርፍ ጭብጨባ፤ የጤዛ ካባ፤ የሳሙና አረፋ ማርዳን
ብቻ ነው። ዝናን መናቅ ከዕውነት ጋር ያገናኛል። ትውልድን ለማትረፍ ደግሞ ከዚህም በላይ ዋጋ ቢያስከፍል የጸጋ ስጦታ ነው። መታደልም ነው። በመከራ በስተጀርባ
ያለው እርካታ ይበልጣል። ስለሆነም ሆንኩበት።
· „ለማኝ ጉድ ቀላዋጭ ሁልጊዜ እርዱኝ ባይ ሹምን ደጅ ጠኚ
እግረኛ
ተሳዳጅ አሻግሮ ተቁለጭላጭ ተመጽዋጪ ስትሆኚ"
v የህሊናው
ብሌን በዕኔ ዕይታ…
„ጉድ ቀላዋጭ?ለዚህም አብዝቶ ሂያጅ“ ከድህነት ከልምና በታች ምን እንቀላውጥ? „ሹምን ደጅ
ጠኝ“ ያሉት ጠበንጃ ብቻ የሚገዛሽ የሚያስተዳደርሽ ዕወቅት ላለው ቤተኛ ባይታወርነት የተፈረደበት፤ ስለሆነሽ በልጆችሽ ነፃ መንፈስ እና ፈቃድ የመዳኘት አቅም በማጣትሽ በልመና
ባክነሽ። በልጆችች የህሊና ብቃት ለመመራት ዕድሉ በመንጠፉ ተሰዳጅ ሆንሺ።
ዘመንሽ ልማና ሆነ፤ ተስፋሽ በልመና ሆነ፤ የማድርግ
አቅምሽ በልመና ጥገኛ ሆነ። ይህም ብቻ ሳይሆን ተረጅነትሽ በወርድሽ በቁመናሽ ልክ ራስሽን ችለሽ ለመቆም ስለሚሳንሽ በሚሰጥሽ ምፅዋት
ልክ ዝቅ ብለሽ፤ ተመጽዋች ሆነሽ፤ በራስ የመወሰን እቅምሽ ሳስቶ በሌላ ሃሳብ ተገዢ ለመሆን ተገደድሽ። መኖርሽ በልመና በመከርኮዱ
የነፃነት ተምሳሌነት ክብረኛነትሽን አልቦሽ አድርጎታል።
የልጆችሽን አጽም ዘርግተሽ ተመጽዋች መሆንሽ ለአንቺ አፈጣጠር ከማይገጥም
ሁነት ጋር ተጣብቀሽ ለመኖር ተገደሻል። ስጋትሽ ኑሮሽ ሆኗል። ከዛሬ ነገ ይውጡኝ፤ ይሰለቅጡኝ፤ እጃቸው ያጥርብኝ ይሆን እያልሽ
ፍርሃት ነግሶብሻል። ለመኖርሽ ባለርግጥ የሚያደርገሽ የራስሽ ነገር የሌለሽ ለልመና አግርሽን የማይደከመው ልጆችሽም ለስደት እግራቸውን
የማይደክማቸው ናቸው … „ተቁለጭላጭ“ የሰው እጅ ጠባቂ። ህመሙ አጥንትን ይሰነጥቃል።
· „ቁጭታ አንገብግቦኝ የእኔን ነገር ትቼ
አንችን
ቤቴ ብዬሽ የእኔን ቤት ረስቼ“
v የህሊናው
ብሌን በዕኔ ዕይታ…
„ቁጭታ“ ይህም ሌላ ሰም እና ወርቅ ነው። እንደ ሰምና ወርቅ ማዬት የሚቻል ይመስለኛል። „ቁጭታ“
መሥራት እያቻልኩ ታስሬ። ማሰብ እዬቻልኩ ተቀፍድጄ፤ መሥራት የሚችሉም መሰሎቼም መሥራት እንዳይችሉ ታሽገው። በሃሳቤ ልክ እንዳልራመድ ታቁሬ። መሥራት የምችልበት የነፃነት
ማሳ አጥቼ የፈጠራ ክህሎቴ ተደብቆ፤ የሥራ ፈላጊነት አባል ሆኛለሁ ሲሆን፤ በ አቅሜ ልክ ርምጃዬን እንዳልቀጥል ታገትኩኝ። ወርቁ ግን ብሄራዊ የሳት ላንቃ
የሆነ የሚንገበግብ የውስጥ እሳት አለብኝ ይህን መከራሽን ቁጭ ብዬ ለማዬት ያላስቻለኝ የውስጥ መግል አለብኝ።
ስለሆነም እኔን ማዬት
ትቼ፤ የራሴን ኑሮ በተለያዬ ሁኔታ ማደራጀትና ማስማማት ስችል የቤቴን መሠረት፤ የነፍሴን ጉልቻ ቸል ብዬ አንችን ማስቀደሜ ይሄው
ነው ሚስጢሩ፤ ውስጤ ያለው መግል መንፈሴን እረፍት ፋታ ቢነሳት ነው። በዘመነ ደርግ እንዲህ የመሰሉ የሠራዊቱ አባላት ሆኖ የፖለቲካ
ድርጅት መሪዎች ነበሩ።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ በፍጹም ሁኔታ የቀደሙትን ታሪኮች ለማስቀጠል የቆረጡ፤ የወሰኑ። እሳቸውም እንዲህ ዓይነት የድንግልና ውስጠት ነው ያላቸው። ይሄንንም ለፖለቲካ የሚሆን
ሰብዕና ስሌለው ኢንትሪግ ነገር ስላለፈጠረበት „ተው ብዬው ነበር“ ያለው ጓደኛቸው አርቲስት ጌትሻ ለዚህ ነው።
„አንችን ቤቴ ብዬ“ ኢትዮጵያዊነቴን ወድጄው አክብሬው ከአፍርሻ ጋር ለመኖር
ቆርጬ፤ የእኔን ቤት እርግፍ አድርጌ እረስቼ ጓዳዬ ላይ መቀመጡን ትቼ፤ አንችኑ በውስጤ ጎጆዬ አደረኩኝ። ዘለግ ሲል የጥንት የጥዋቷን
የፍቅር ቤት፤ የመቻቻል ቤት የመናፈቅ የመሳሳት ምኞት ነው።
ዶር አብይ አህመድ /አሜኑ/ ከግልኝነት ጋር የተፋታ በጥልቅ እትብታዊ
ገምድ ከኢትዮጵያዊነት ጋር የተዋደዱ መስተጋብር ስለመሆናቸው ቁልጭ ብሎ ይታያል።
„አዲሱን መልክሽን አዲሱ ሰምሽን
አዲሱ ገጽሽን አዲሱን ነገሽን
ልስል ባጀሁ እንጂ ውስጤ እዬነደፍኩሽ
ውዴ ከዚያ ወዲያ ሌላ እኔ ምን አልኩሽ“
v የህሊናው
ብሌን በዕኔ ዕይታ…
የተስፋ መንገደኛ ናቸው። „አዲሱን መልክሽን አዲሱን ሥምሽን“ የሚያስጎመጅ ህልውናን የመፍጠር፤
የማበጀት ምናብኛ ሥህነኛ አናባቢኛ። እሩቅ ናቸው የምለው እኔ ዶር አብይ አህመድን ለዚህ ነው። አላዋቅናቸውም ገናም አናውቃቸውም
ባይም ነኝ።
ምን አልባት ከእኛ የሚቀጥለው፤ የሚቀጥለው ታቦቱ ያደርጋቸው ይሆናል። ምናባቸውን ይረዳላቸው ይሆናል። ድንግልና ያለው
መንፈስ የመፍጠር ምናብ ነው። ሸሩ ተንኮሉ ኢንትሪጉ ቅናቱ ቅብረቱ ሁሉም አሰናካይ መንገድ ዘጊ አዛጊም ከውስጥ የሚጻደበት ዘመን
ምናበኛ መሆናቸው ይህ ሥንኝ ይገልጣቸዋል።
ለዚህ ነው የአዲስነት ሐዋርያነት የተሰጣቸው። ይህ የአዲስነት ሐዋርያነት የራሳቸውን ሰብዕናቸውን ለመገንባት ሳይሆን የተሰጣቸው
ነው። ያሸተ ምልከተኛ መልክተኛም ምልክትም ናቸው ለአዲሰኛ።
„ልስል“ „እዬነደፍኩሽ“ ሳል ጭንቅንሽን ልጋራ፤ ቲክ ቲክ የሚለውን የሌሊት ግርማውን ጥሶ እንቅልፍ
የሚነሳውን ሳላዊ አስማታዊ ችግርሽን ልጋራው ወደድኩት፤ ፈቀደኩት ነው። መተንፈሻ ያጣውን የሰራ አካላትሽን መተንፈሻ ቧንቧ ለማበጀት
ታተርኩ፤ ሁለተኛው ሥዕል መሳል ሲሆን የምናብ እርህብተኛ ስለመሆናቸው
የሚያሳይ ነው።
ኢትዮጵያን በምናብ ዲዛይን የማድረግ ራዕያቸውን ለመግለጽ ነው።
ጠ/ሚር ዶር አብይ አህመድ የ100 ቀን እርምጃቸው
እኮ ታቅዶ የቆዬ የህሊና ሰብል ስለመሆኑ ማንም አሊ አይለውም። ድርጁ የሆነ እንቅስቃሴ ነበር ያደረጉት። ሉላዊው ዓለምን ጉድ ያሰኜ። ራሳቸውን እራሱ ያደራጁ ናቸው። ያልተደራጀ መንፈስ ራሱ ግጥማቸው አይደለም። በምንስ ሊግባቡ? እንዴትስ ሊፈቃቀዱ ከላግጣሙ።
በሌላ በኩል በም/ጠ/ ሚር አቶ ደመቀ መኮነን ከተመራው እስራኤል ከሄደው ልዑክ ቡድን ጋር የሳይንስ
እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር ሚኒስተር በነበሩበት ጊዜ አንድ ጋዜጠኛ የዛሬ 25 ዓመት ኢትዮጵያ ምን መለክ ይኖራታል ብለህ ታስባለህ ብሎ ሰተይቃቸው ያ እረጅም ነው እኔ የማስባት ኢትዮጵያ ሙሉ አቅማችን ከተጠቀምን ባነሰ ዘመን ትገኛለች ብለው ነበር የመለሱት። የሳምንቱ መግቢያ
ንግግራቸውም ይዛመዳል።
ለጋህርን የትውፊትም የተስፋም አዲስ ከተማ ለማድረግ ያለውን መርሃ ግብር ሲገልጹ እኔ ከውስጤ ስታደምበት ትርጉም ይህን ነው።
እውነቱን ብናገረው መንፈሳቸው ውስጤ ነው። እህቴም የምትለው መንፈሴን ይድላው ሲል ነው የምትለኝ። ቅናዊም ቃናዊም ነውና ለዛቸው።
ክብሩነታቸው የሚያልሟት ኢትዮጵያ በሁለመናዋ የተፈወሰችውን
ኢትዮጵያን ነው። ከሳል ከጉንፋን ከአስማ፤ ከትክ ትክ፤
ከማጥለቅለቅ፤ ከማቅለሽለሽ ከህሊና ሪህ ነፃ የወጣች።
ምናቤ የሚያልምሽ የነገይቱ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የውራጅ ያልሆነ በራስሽ ጥበብን እንደ ተፈጥሮሽ
ልጠበብሽ ማለትን ነው ያጸኑት።
ይሄም ከማርክሲዝም ሌሊዝም ፍልስፍና የወጣ ሐገር በቀል በሆነ ፍልስፍና ልቀምርሽ ስንዱ ነኝ ነው።
ሰው የመፍጠር ማህንዲስም ናቸው።
ውስጤ አንቺው ነሽ ውስጤን ሳልስት ሰጥቼሻለሁ። ለዛም እተጋለሁኝ። በዛም ውስጥ እጸድቃለሁኝ፤
አንቺ በውስጤ የበቀለሽ ጽላቴ ነሽ። ልጽድቄ ጽናቴ ምርኩዜ ይሆናል ነው። ሌላማ ለራሴ ልኑር ብል ምን ይገደኝ ነበር ነው። ክብርም
ኩራትም የአንቺ አዲስነት ነው ለእኔ ክብሬም ኩራቴም አፈሬ ነው መስመሬ ነው።
አንቺ ከምንም
ቁሳዊ ሃብት በላይ ውዴ ነሽ። ስለሆነም በግል ህይወቴ ምቾትና ድሎት
ሳይሆን የአንችነትሽ ብሥራት አዲስነት ዜና ይበልጥብኛል ነው። ጥሩ ዜናን በርቀት የመመኘት ህልመኝነት። አዲስነትን ብሥራትን ከማግሥት
ጋር ለማዋል ራስን ለመስጠት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያመለክታል፤
· „እንደሚሽቀዳደም እንደ ባህር ቅርድድ
አንዳች
እንደነካው ሊሰፋ እንደሚነጉድ“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
„አንዳች“ ሃይለ ቃል ነው የመንፈስ። አንዳች የተጠናወተው ሱስ የለብኝም። ባለ ማራቶኑ „የባህር
ቅርድድ“ የከንቱ ውዳሴ፤ የሥም ትግል ሩጫ፤ የዝና ምናምንቴ አይደለም ምኞቴ። እንደ ዱባ የተቀረደደ፤ ካልልኩ የተንቦረቀቀ ሰብዕና
ምኞቴ አይደለም። አዬር ላይ ተንሳፎ በአዬር ሠረገላ ላይ የተሰፋ ቦላሌ ለመሸመት፤ ለሽቅድድም የታለመ ህልማም ራዕይ ከራሴ የተነሳ
አይደለም።
ለራሴም የሰብዕና ግንባታ አሽዋ፤ ስሚንቶ እንዲሆን አይደለም ስላንቺ ያልኩት። በግብታዊነት በሚነጉድ
ጦሮ፤ በስሜት በሚገፋ ሞተር አይደለም ህሊናዬ፤ ማንም የሚለጋው የአዬር ላይ ኳስ ጨዋታም አይደለም ህልሜ ሆነ የምናቤ ትጥቅ። የእኔ
ህልም በታላቅነትሽ ልክ፤ በዘመን ቆይታሽ ልክ፤ በትውፊተ ታሪክሽ ልክሽ፤ በሰው የመገኛነትሽ ሚስጢር ትክክለኛ ቦታሽን፤ ትክክለኛ
ደረጃሽን አንቺን እንደ ሌሎች የሥልጣኔ እርክን በሙሉ ሞራላዊ ተፈጥሮሽ ክብርሽ ልዕናሽን ከመንበርሽ ማዳረስ ነው።
·
„ቢያንስ በዙሪዬ በፍቅር መንጭጬ
እንደገና ደግሞ በፍቅር ነቅቼ ለከርሞሽ ተግቼ"
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
„መንጭጬ“ አዲስ ቃል ነው። ቅኔ ነው። ምንጭ ከሚለው የተራባ ይመስለኛል። የፍቅር ምንጭ ከውስጤ
አለ። ያ ለአንቺ ያለኝ ተፈጥራዊ ፍቅር ነው ውስጤን ያነሳሰው፤ ለውስጤ ቡና የሆነ ተኝቼ እንዳላድር ቀንም እንዳላቀላፋ ብርታት፤
ንቃትን የሰጠኝ፤ ያ ፍቅር ነው ለከነገ ወዲያ እንዳስብ እንድተጋ እንዳልታክት ያደረገ።
ፍቅርም አንቺ ነሽ። ያን ፍቅር የሰጠሽኝ
አንቺው ነሽ። የሰጠሽኝን ፍቅር ለማራባት እተጋለሁኝ። የፍቅርሽን ቃል ኪዳን የኔ ብቻ ሆኖ አይቀርም ፍቅርን ለማልማት የፍቅር ሰፊ
ማሳ አለስልሼ ህሊናን በፍቅር ላሰብል የፍቅር ገበሬ ለመሆን ተሰነድቻለሁኝ፤ ቆርጫለሁኝ። እኔ እንደማስበው ለዚህ ነው የወደድኩት ሁሉ ውደዱልኝ የሚሉን።
ማዋደድ ማፈቀር ማስታረቅ ከእናቸው ጋር የውላቸው ማህለቅ ስለሆነ።
ይህ የሁልዮሽ ዜጋዊ ፍቅር ከርሞ ባጅቶ ዘልቆ አልምቶ አስብሎ ማዬት ነው ሩጫዬ … ለዚህም ሃይለኛ
ታታሪ ሠራተኛ እሆናለሁኝ። ፍቅርን ሳትሰስቺ ስትሰጭኝ እንዳመከንው
ሳይሆን አቅም ፈጥሬ አቅም እንዲሆን በማስቻል ላይ እበረታለሁ። ኢጎን የቀበርኩት ለዚህ ተልዕኮ አስባርከሽ የፈጠርሽኝ ዕለት ነው።
·
„እናቴን የአንቺን ሥም ዝናር ድግ አድርጌ
አንችን አደግድጌ፤“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
ሥሜ ሳይሆን ሥምሽ ነው ዝናሬ።
ሥምሽ ነው ፅናቴ። ሥምሽ ነው ግማዴ። ሥምሽ ነው ስግደቴ፤ ሥምሽ
ነው ፆም ጸሎቴ፤ ሥምሽ ነው ምህላዬ ሱባዬ፤ መኖሬ፤ ሥምሽ ሥሜ መለያዬ አሻራዬ መሆኑን ስቀበል በግማድሽ ሸክም የሚደረሰውን ፈተና
ሁሉ በሰጠሽኝ ፍቅር፤ በሰጠሽኝ ሃይል እና ጽናት ልክ የመሸከም አቅም አለኝ። ዝግጁ ነኝ!
ምክንያቱም ከግማዱ የማገኛቸው በኽራት
አዕማደ ሚስጢራት ስላሉ። ግማድ የመሰቀል ሸክም ነው። መስቀሉ ሃይል ነው። መስቀሉ ጽናት ነው። ጽናትሽ ነው ጽናትን ያበቀለልኝ። ሁሉንም አቅም ከ ንቺ ስጦታ የበቀለ ነው። መስቀሉ ድህነት ነው። በዚህ ፈተናዎቼን
ሁሉ እረታለሁኝ።
መሰቀሉን ስሸከም ደግሞ ስላንቺ ያለኝን አክብሮቴን አደግድጌ ታጥቄ ነው በአክብሮት ስለአክብሮት፤ ቃሌን በገቢር ለማዋል ስንዱነቴ የውስጥሽ ነው ስለእኔ በይልኝ። አንቺን
ውዴ በማድረጌ የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ፍቅርሽ በውስጤ ከትቤው አለ፤ ፍቅርሽን ስጥቼ ከብክቤው ስለምገኝ ፈታና በሚረታው ግማድሽ
መሳሪያነት መዳንሽን አስባለሁ። ስለማዳንሽም እኳትናለሁኝ። ምጥቁ የቃል ማሰሪያ ነው።
· „አንችን አንችን እሚሉ
በሥምሽ
‘ሚምሉ ሥምሽን“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
በአንቺ ፍቅር የተጸነሱ፤ የተወለዱ፤ ጠርተው አንስተው የማይጠግቡሽን ቅኖችን ሁሉ አሰባስባለሁኝ።
የጎደላቸውም ቢገጥሙም ሁሉን ችዬ ልጆችሽን አሰባስቤ አቅም አደርግልሻለሁኝ። ምርኩዞችሽ አደርጋለሁኝ። ልጆችሽ አንቺን ማተባቸው፤ አንቺን ስንቃቸው፤ አንቺን
ትጥቃቸው ያደረጉ ካንቺ እናነትነት ለመናሳት ከማይታክቱት ጋር በመሆን ባልኩሽ ልክ እሆናለሁኝ።
ልጆችሽ በመልካም እንዲሚስነሱሽ
የቤት ሥራው እኔ እውስዳለሁኝ። ይህን እንግዲህ መዳህኒዓለም አባታችን የአቡነ ሳሙኤል ዋልባን ገዳምን ሲመሠርት አንችን የሚያከብሩ
ስለ አናቺ የሚኖሩ ብሎ ለእናቱ ለቅድስት ለድንግል ማርያም የገባላትን ቃል ኪዳን ሁሉ የሚያበሥርም ነው።
አንቺ አጀንዳቸው፤ አንቺ ቁምነገራቸው፤ አንቺ ህይወታቸው የሚሆኑ ልጆችሽን በማዕድሽ አበዛልሻለሁ
ነው ሚስጢሩ። እሷን የማይሉትን ሁሉ ወደ እሷ መንፈስ እንዲቀርቡ ሁሉ ጥረዋል እኒህ ባለቅኔ በትረ ምህረት።
ይህን ደግሞ አደርገዋል። ለዛውም በድፍረት። የተፎካካሪ
ፓርቲዎችን
ሆነ የግል ታጋዮችን፤ እሳቸውን በጥርሳቸው የያዙትንም በግልጥም በሸምቅም የሚዋጓቸውን፤ የቀኑባቸውን ሁሉንም በእቅፍ በአሃዳዊ
ወጥ መንፈስ ከእነ
ዥንጉርጉሩ ፍላጎት እና ባህሪያቸው ጋር ለመሸከም ያደረጉት ተጋድሎ የዚህ ቃልኪዳን ፍሬ ዘር ነው። ይገርማሉ።
· „ ሲሆንም ሳይሆንም
ሲሞላም
ሰይሞላም
ሁሉን
እንደ ሁሉ ስላንቺ ሚችሉ
ከጉያሽ
‘ሚውሉ ልጆች ልሰራልሽ ከመባከን ሌላ
ፍቅር
ልዘራብሽ ከመኳተን ሌላ
ለዘጻዕት
ጉዞሽ ከመሰጠት ሌላ“
v የህሊናው
ብሌን በዕኔ ዕይታ…
„ሁሉ እንደ ሁሉ ስለ አንቺ 'ሚችሉ“ ይህን ለማግኘት ጋዳ ነው። ስለ እሷ ቢሆንማ ስለምን የክት
እና የዘወትር ቤተኛ እና እዳሪ ይኖር ነበር።፡አገር ውስጥም ውጪ አገርም። ትርፍ ዜጎች እኮ አለን። ሁሉም ቁልፉ ሲኖረው ያዬነውን የኖርንበት ነው። ብቻ
የዶር አብይ አህመድ ምናባዊ ድንግልናው ይደንቃል።
ይህን ሥንኝ ከላይኛው ጋር እጅ ለእጅ፤ መንፈስ ተመንፈስ ላያይዛቸው "ውስጣችው አንቺን አንቺን
የሚል" ጠረን ያላቸው። ባለፈው ሰንበት ላይ „አችን“ እያሉ አዲስ አባባ ላይ የነበረውን ሰላማዊ ድባብ የገለጹበትን የምስጋና መንፈስ
በዚህ ውስጥ ማዬትም ይቻላል። በዬዓወድዓመቱ የሚአስተላለፉትም መልዕክት ፏፏቴው ከዚህ የውል ሰነድ ነው።
ሥምሽን ለሚያነሱ ብቻ ሳይሆን ስለንቺ ለመሆን፤ ሁሉንም ለመስጠት የማይሳናቸው፤ የተግባር አንበሶችን
ለመፍጠር በከፋሽ ለታ፤ በተቸገርሽ ለታ የክፉ ቀንሽ ሊሆኑ፤ ጸንተው ሊቆሙ የሚችሉ ልጆች እንዲበራከቱ በፍቅር ትውልድን በመገንባት
ለትንሳዔ ጉዞሽ እባክናለሁኝ።
ጥሪሽን ለሚያከብሩም ክብረትን አልማለሁ። ሌላማ እኔ ምን እፈልጋለሁ። ለትውልዱ ብክነት ለመሳቆም አንቺ
ለሰጠሽኝ ፍቅርና ውለታውን የሰጠሽኝን ፍቅር ለትውልድ ግንባታ ለማዋል መትጋቴ ነው እንደ ሃጢያት የታዬብኝ እንጂ እኔ ከአንቺ
ሌላ ምንም ፍላጎት የለኝም ነው። ፍላጎቴ ነሽ ኢትዮጵያ ነው። እጹብ ድንቅ ነው። ትውልድን በአዎንታዊነት በተሟላ ሞራላዊ ክህሎት የማበጀት ህልመኛ ናቸው።
„ፍቅር ልዘራብሽ ከመኳተን ሌላ
ለዘጻዕት
ጉዞሽ ከመሰጠት ሌላ“
ይህ እንግዲህ የነበረባቸውን መራራ ዘመን ቅኝት ይገለጣል። ቅንነት እኮ ያልተለመደ ነገር ነው
በሊሂቃኑ ዘንድ። ጥምዝምዝ ጥምንምን ነው ምናባቸው እራሱ የኢትዮጵያ ሊቃናት አብሶ ፖለቲከኞች ኢሊቶች የሚባሉት።
ከዚህ ማዕቀፍ ያመለጡት ለዚህም ነው ከከባዱ ቦታ ላይ ይወረወራሉ አባ ቅንዬ ባትለው ከገነቡ በኋዋላ፤ እሳቸው ባበጁት፤ ባደራጁት ሌላ ይሾምበት እና እሳቸው ደግሞ ሌላ ቦታ ይወረወራሉ፤ ሥልጣናም ሲሆን እንዲሁ።
የተመደቡበትን ቦታ በብቃት ተወጥተው ያን ደግሞ አርቀው አደራጅተው ለወግ ለማዕረግ ሲያበቁ አይተው ሰብላቸውን ሳይጨርሱ እንደገና ደግሞ ሌላ
ቦታ ይላካሉ ሲፈለግ በዲሞሽን፤ ሲፈልግ በዕድገት፤ ሲፈልግም እንደተፈለገው … ግን ቃል አለባቸው እምዬን እንደ እንዳዩት አገር
ለማድረግ።
ይህ የተስፋ ከተማ ምስረታ ላይ ውጭ ውጪውን ለገብያ የማሰብን መንፈስ አገራዊ ለማድረግ ያላቸውን ህልም አንዱን ፈርጅ
ለገሃር ላይ በቅርቡ እንደሚጀመር ተበስሯል። የንጉሶች ንጉሥ የ አጤ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥቱ መዘክርንትም በዚህ ምክንያት ያታጨ ነው። የዛ መራራ ዘመን ፍትጊያ ግብዕት ይኸው ነው።
· „አንቺም ታውቂያወለሽ የለኝም ሌላ ቃል ከትንሳኤሽ ኋዋላ
ውዴ
ታውቂዋለሽ ውዴ ታውቂኝ አለሽ“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
ዶር አብይ አህመድ የፖለቲካ ነጋዴ አይደሉም። ይህም ይህ ቅኔ ውስጣቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳዬናል።
ለትንሳኤሽ መዳረሻ ነው የምተጋው ነው የሚሉት። እኔን ለመተርጎም አንቺ ሌላ አስተርጓሚ አያስፈልግሽም፤ አንተዋወቃለን ይሏታል አላዛሯን እናት ኢትዮጵያን። የውስጥ ለውስጥ
መንገድ አለን፤ የሚስጢር ክህሎታችን አለ።
ይህ እንግዲህ አንዲት እናት በማህጸን ከጽንሷ ጋር የሚኖራት ተፈጥሯዊ የመተዋወቅ እዬራዊ ረቂቅነትን ዓይነት ሚስጢራዊ
ቁርኝታቸውን ነው የገለጹት። በመከራዬ ቀን፤ በመከራሽም ቀን አብረን በ እትብት ካናል ተኗኑረናል። ስላንቺ ምን እንደማስብ ታውቂያለሽ፤ መጸሐፍ ገላጭ
አያስፈልግሽም ነው።
· „ዛሬ ሳይሆን ትናንት አሁን ሳይሆን ድሮ
ያኔ
ምንም ሳልሆን ምኔም ተቀይሮ“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
ከልጅነቴ ጀምሮ ጸንሸሻለሁኝ። አንቺን ወተቴ አድርጌ አድጌያለሁኝ።
ዛሬ ያለሁበትን ደረጃ ተይው። በልጅነቴ የፈቀድኩልሽን ስብዕና ዕሰቢው። ራሴን ሰጥቼልሻለሁኝ። ዛሬ በሥም ክብር ላይ ነኝ። እኔ
ግን አንቺን የምወደው ትቢያ ላይ እያለሁ ከልጅነትም ነበር።
ቃል ኪዳናችን ዛሬ ሳይሆን የትናንት የቀደመ አብሮ አደጌ ነው። ባንቺ ላይ እኔ
አዲስ ባለሥልጣን አልሆንብሽም። እንደምታውቂኝ እንደዛ ባተሌ ልጅሽ ዛሬም እይኝ። እዘዥኝ፤ ተቆጭኝ፤ ገስጪኝ፤ ምክሪኝ፤ ቆንጥጪኝ።
አንቺ እኔ
ካንቺ በታች እንጂ ከአንቺ ፍላጎት በላይ አይደለሁምና እንደ ሃሳብሽ ለመኖር ታውቂኝ አለሽ። ድህነትሽ መከፋትሽ አለስበረገገኝም፤
ይልቁንም ወስኜ አንቺን እንድሆንብሽ አድርጎኛል። ኢትዮጵያዊነት ከሃሳብ በላይ ነውና።
·
„ከርመን ልንገናኝ ኑረን ልንሰናኝ አልቦነት ተሽሮ
እኔ እና አንቺ እኮ ነበረን ቀጠሮ“
„ልሰናኝ“ ይሄም አዲስ ቃል ነው። የዜማ አወራረዱ ቅኔያዊ ሲሆን ሥንኝ ከሚለው ሥረዎ ቃል የተነሳ ነው። ቃል ልሆን ሰዋሰው ልሆን የሚልም ነው፤
ልንጻፍ፤ ልነበብ አናባቢም ተናባቢም ሆነን መጸሐፈ ትርጉም ሚስጢር ሆነን ልንዋህድ ላንላለይ ወንዝ፤ ደንበር፤ ጋራ ሸንተረር የልዩነት
ግድግዳዎች ላይለያዩን፤ ወቅት፤ ዓመት ምዕት ላይገድበን በአንድምታ በስዋሰዋዊ ቅኝት ከውላችን ልንውል ኪዳን አሰረናል እኔ እና አንቺ።
· „አዋቃለሁ ታውቂያለሽ ምንም ጊዜው ረዝሞ
ካገርም ቢሰፋ“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
ረጅሙን ጉዞ በቀጠሮ ርዝመት፤ በውቅያኖስ ስፋት፤ በሂደቱ ትብትብነት ከውላችን የሚያወጣን ማንም
ምንም የለም። ከኪዳነች ፍንክች አንልም። በጽኑ ፍቅር ገንብተሽኛል። ጽኑ ፍቅርሽን መግበሸ አሳድገሽኛል።
የዚያ ውለታ በጊዜ እርዝማኔ
ሊከስም ወይንም ሊወይብ ወይንም ሊጠወልግ፤ ወይንም መሃን ሆኖ ሰብል አልቦሽ ሊሆን ከቶውንም አይችልም። እንዳመንሽኝ ታማኝሽ ነኝ
ምንጊዜም።
· „ቀጠሮ ክቡር ነው ካገርም ቢሰፋ
ቀጠሮ
ክቡር ነው የእንገናኝ ተስፋ
ለዚያ
ነው ያለሁት ዬቀጠሮሽ ቦታ“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
„ቀጠሮ“ መቃጠር፤ መዋዋል፤ ጊዜን፤ ቃልን፤ ውልን፤ ኪዳን የመጠበቅ የተስፋ ማህደር ነው። ያ
ቀጠሮ ደግሞ የሐገር ትንሳኤ ቀጠሮ ነው። በዚህ ትንሳኤ ትውልድን በፍቅር የመገንባት ቀጠሮ ነው። ለዛ ቀጠሮ በተሰጠው ቦታ ለመገኘት
ውላችን ጽኑ ነው።
በሌላ በኩል አንቺን በሚለከት ጊዜም ወቅትም ሁኔታም ቦታም ዘመናይነትም፤ ሥልጣኔም የፈለገ ቢደረደር እኔም እኔም
ነኝ፤ ሁልጊዜም የአንችው ነኝ። አንቺም ውዷ እናቴ እኔም ውልሽን አፍርሼ የማላሳፍርሽ ልጅሽ ነኝ። ስለሆነም በውላችን መሰረት
ሰማይ እና ምድር ቢደባለቁ አንቺን ገሃዱ ዓለም አባብሎኝ አድዮዬን የተስፋ አገሬን ትቼሽ የትም አልሄድም።
ከሳቀመጥሽኝ ቦታ በሰጠሽኝ አደራ ልክ ታገኝኛለሽ።
ተልዕኮው ውላችን ትውልድን ከብክነት ማዳን ነውና የሚከፈለውን ከፍዬ ቃልኪዳኔን ጠብቄ ታገኝኛለሽ፤ አገኝሻለሁ አንቺ ከህልሜ ጋር
ትገናኛላችሁ፤ አይዞሽልኝ ውዴዬ።
ለዚህ ነው ዛሬ በጠ/ሚር ቢሮም ተስፋ በሌሎችም ቀጣይ ፕሮጀክቶች ተስፋ ቃሉ ጎላ ብሎ ደምቆ እንዲታይ
ሚስጢሩ ከእናት ጋር ውል የተስፋ ስለነበረ ነው። አላዛሯ ኢትዮጵያም የተስፋ ውሏን ተስፋ ከሰጠችው ተስፋዋን ከሳረከበችው ልጇ
ጋር በእዮር ፈቃድ ተገናኝተዋል። ተመስገን።
· „ በቀጠርሽኝ ቦታ ሙሽራዬን አንችን ሰርግ ላገለግል ህልምሽን ልፈታ
ለዚያ
ነው ያለሁት የእኔን ነገር ጥዬ ለቀጠሮሽ ብየ
ካዋልሽኝ
እዬዋልኩ ካኖርሽኝ እዬኖርኩ ስትጥይኝ ተጥዬ“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
የቃና ዘገሊላ ሠርገኝነት ኢትዮጵያ ስትሆን አገልጋዮዋ፤ ባሪያዋ ሎሌዋ በመሆን የትንሳኤዋን
ጧፍ ለማዬት መናፈቅ ነው ህልሜ፤ ለዚህም በተሰጠኝ ቦታ አንገቴን ደፍቼ፤ ተጫኞችን ችዬ፤ ግልፋጮችን ችዬ፤ ሲሰጡኝ በልቼ፤ ሲነሱኝ
በርትቼ፤ ከቃልሽ ጋር ብቻ አንችን ተማምኜ ሲሻቸው ሲወረውሩኝ፤ ወደታች ሲያርዱኝ ማዕቱን ታግሼ፤ ቁሩንም አብርጄ፤ ስደትን ሳልናፍቅ፤
ኩርፊያን ሳላስተናግድ፤ አሁንም አለሁኝ በቃልሽ በቃሌ ቃል አባይ ሳልሆንም።
ለህልማችን ስል ነገም ለሚመጣው ታች መውረድ ሆነ መውጣት፤
ወርውር ሆነ መረገጥ በጥበብ እና በስልት እያስናገድኩኝ አንቺን ትንሳዬሽን ለማዬት በቃልሽ ቤተኝነቴ እዘልቀለሁኝ። የህይወቴ፤ የነባቢቴ፤
የመኖሬ ሙሽራ አንቺው ነሽ። ለሙሽርነትሽ አገልጋይነት በመመረጤ ቃሉን ጠብቄ ቃሉን ህይወት ለመስጠት እተጋለሁኝ።
· „መቼም ታውቂኝ አለሽ መቼ የእኔ ሆነና የአንቺ እኮ ነው ልቤ
መቼ
ከእኔ ሆነና በአንቺ ነው አሳቤ መቼ የእኔ ታውሶት“
„ታውሶት“ አንዲስ የአጠቃቀም ቃል ነው ቅኔ ነው። ትውስት ከሚለው ቃል የተገኘ ነው። ዕቃ በመዋስ
ዕቃ በመመለስ ከትውልድ ጋር ያለውን ተወራራሽነት በንግግራቸው ውስጥ የተለመደ ሲሆን በዚህ ላይ ቅን „እኔ ራሴ የትውስት“ አይደለሁኝም።
ውስጤን ሳልዋሰው ውስጤን ውስጥ ማድረግ የቻልኩኝ ኢትዮጵያዊ ነኝ ነው። ውስጤንም አብረን ስላለሽ ታውቂዋለሽ ሌላ ምንም አልሰጠሁሽም
አሁንም የነበርሽበትን „ልቤን“ ውረሽው። የሰጠሽኝን ውስጠት ሰጥቼሽ መኖሬን አንችም ታውቂዋለሽ። መስጠት ትልቅ ቃል ነው። መስጠት
መሪ ቃል ነው።
መስጠት ፍቅራዊነትም ነው። የሚወዱትን ራስን መገብር መስጠት ከሁሉም በላይ ነው። የሰጡትን ያህል በክብር ማብቀል
እና መስተላለፍም ማተበኝነት ነው።
ኑሮን ሰጥተዋል ለሚወዱት ለሚያፍቅሩት ለኢትዮጵያዊነት። እሷ ናት ጽንሳቸው። ይህ ስለመሆኑ ደግሞ በኢትዮጵያ እና በእሳቸው
መካከል ያለው አንድዬ ዳኛው ሁሉ የሚቻለው አምላካችን አማኑኤል ብቻ ነው። ከእሱ ሌላ በማህላቸው ያለውን ዕውነት ጠንቅቆ የሚያውቅ
ሰውኛ መስታውት የለም። ፕላኔታችንም የውስጥ ባህሪያችን የሚያነብ ራዲዮሎጂ ገና አልፈለሰመችም።
· „አንችኑ ቀዳሽ ነው አንቺን ባይ መንፈሴ
ለእኔ
እኮ ባዳናት አንችን ነው ምትኖረው መከረኛ ነፍሴ“
v የህሊናው
ብሌን በዕኔ ዕይታ…
„ባዳናት“ አንደኛው መዳን ነው። አዳኙም አንድዬ ነው። ሥልጣኑም የእሱው ነው። ሁለተኛው ደግሞ
ባይታዋር ነው። ስለ እኔ ማሰብ ለእኔ ባይታዋር
ነው። ለዚህ አይደለም የተፈጠርኩት። ስለ አንቺ ማሰብ ግን እኔ ከራሴ በላይ ነው። የነፍሴ መከራ ጥንስሱ ይህ በመሆኑ
ነው።
አንችነትሽን በውስጤ ለውስጤ ስለሸለምኩኝ። ድንቅ የቃል መሆን ብይን ነው። ከአንቺ በላይ እኔን አልወድም። ይደንቃል። ግለኝነትን የተዋጋ ሊሂቅ። ኢጎ የፈጠረበትን ውል ያከሰረ ጀግና። እኔ
እንኳን ከዚህ ተፈጥሮዬ ባፈነገጥ ማዳን ትችያለሽ የምህረት ምንጭ ነሽና። የይቅርታ እምቤት ነሽ እና። ከአንቺ ጸጋ እንዳልወጣ አንድነሽኛል።
እኔው ምስክርሽ ነኝ ስለውስጣዊ ህልውናዬ በውስጤ ስለመከተምሽ። በመምህረት ቀብተሽኛል። በይቅርታ ቀድሰሽኛል። አንቺ ቤተመቅደሴ
ነሽ፤ ስለሆነም ውስጤ አንቺን አንቺን ነው የሚለው ጣዕሜን።
„አንችኑ ቀድሼ“ ሥርዓተ ቅዳሴ
ፈጣሪ አምላክ እኛን ስለሰጠን በመረጣቸው ሊቃናት በረቀቁ ኢትዮጵያዊ ሥርዓቶች የሚፈጸም
ከድንቅ በላይ የመንፈስ እርካታ ነው።
ሥርዓተ
ቅዳሴ ራሱ ቅዱስ ነው። ስለሆነም „ሰዓትት፤ ዝማሬ፤ ወረቤ፤ ዜማዬ፤ ድጓዬ፤ ቅኔዬ፤ ዝማሜዬ አቋቋሜ፤ ንባቤ፤ ውዳሴዬ፤ ድርሳኔ፤
ብሉዬ አዲሴ፤ ንባቤ መጸሐፌ፤ ዝማሜ መሆንሽ ለጋሃዱ ዓለሜ ሳይሆን
የመንፈሴ ሰቅ ነው።
· „እጭቅ ካለው ዱር፤ ጉም እስከታፈነ
ጭው
እስካለው በርሃ ‘ሽዋ እስካለሆነ“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
"እጭቅ" መፈናፈኛ አዬር ከመከነበት። ክፉነትን ነው በዚህ አገላለጽ እኔ የተረዳሁት። በዚህ ውስጥ አገርን በምኞት ልክ ለማገልገል ያለውን የነጻነት ረህብተኝነት የፈተና የውሃ ልክ
ነው የሚገልጹት። በፈተና ውስጥ ሁሉም አለ። እሰቸጋሪ የሚባሉት ሁሉ በነፃነት እና በምኞት ፍለጋ ሂደቶች እንደ ተፈጥሯቸው ይታገላሉ።
አዬር እስከማጣት ይደርሳል ፈተና ሲጫን። አንዳንድ ጊዜ ራስን ረስቶ በራስ ውስጥ መኖር ደግሞ የተፈጥሮ ህግ ሆኖ ህጉ ህግታን ጥሶ
ሲፋልም ውሎ ያሳድራል። የማን ደም ፈሰሰ እያለ ሲያፋልም ይባጃል አብሶ ራስን መሆን ለተሳነው ነፍስ። ራስን መሆን የቻለው ደግሞ
ለሰጠው ፈቃድ ዕድልኘንቱን ቢቀድሰው እንጂ አይጸጸተውም።
· „የሰማይ መስኮቶች የማይከደኑበት፤ ዶፋም ተረተርሽ
የጸሐይ
መንቀልቀል ገሃነም ከሚያስነቀው ዋያማም ምድርሽ
እኔን
ታውቂኝአለሽ ጥቁር አፈርሽን ላይ ጽናትን ፈርሽን
ፍቅርነን
ጎዝጉዘን እልህ አቀባብለን ይቻላልን መዘን
ተስፋን
ሰንቀነው፤
እኔ አንችና እግዜር ነን አብረን የነበርነው።“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
„የሰማይ መስኮቶች የማይከደኑበት።“ በልግን፤ ክረምትን፤ በጋን፤ ጸደይን፤ ተፈጥሮ እና ውበቱን
ያዋደዱበት ድንቅ አገለላጽ ነው።
እዬራዊ ህግጋት ጥሰት በሰው እጅ ሊፈጸምባቸው አለመቻላቸውን ነው አጽህኖትን ያቀዳጁት።
ይህ አምላክ
አለ፤ ሁሉ የሚቻለው ብሎ ከሚያምን ጽኑ ሃይማኖተኛ የሚጠበቅ ነው። የትኛውም የሥልጣኔ እርከን የሰማይን ቁጣ የመቀዬር፤ የሰማይን
ተፈጥሯዊ ሂደት የማስቆም እና የመገደብ አቅም የለውም።
በዚህ ውስጥ ሊለካ፤ ከቶም ሊመረመር የማይችለውን የፈጣሪን ጥበብ በብዕር
ክራር እና በገና የምስባክ ያህል ገልጸውታል። የነብዬ ልብ አምላክ ዳዊት ቅኔያዊ የማመን መንገድን የእኔ ያሉበት ነው። ይባሩኩ!
ሰማይ መስኮት አለው፤ ግን አይዘጋም ወይንም አይከደነም። ከሰው የማድረግ ጣሪያ አቅም በላይ ስለሆነ።
„ዋያማም።“ ይህም ብዙም ያልተለመደ ቃል ነው። ጭራውን ለማግኘት ሞከርኩት። በርሃማ ለማለት
ይመስለኛል። ግን በርሃው የሰው ልጅ እና ተፈጥሮ ከሚችሉት በላይ የሆነ። ያው ቃሉን እራሱን ለማስቻል አጠንከሮ የባለቤትነት ስሜቱን
ያደመቀው „ማም" የሚሉት ሁለት
ፊደላት ናቸው።
እነኝህን ሁለቱን የመጨረሻ ፊደላት ነጥለን ስንመለከታቸው ደግሞ ‚ማም‘ ሥነ ግጥም ህግ የለውም፤
በአንድ ሥንኝ ውስጥ የፈለጉት ያህል የተለያዬ ቋንቋ የመጠቀም ብቻ ሳይሆን እርእስ አልባም የመጻፍም ሙሉ መብት አለ። ስለዚህ
„ማም“ የሚለው እንግሊዘኛው ከሆነ እናት በሚለውም እኔ አይቸዋለሁኝ።
በዓለም ውስጥ ድንቅ መጠሪያ የግሎባል ዓለሙ የጭብጡ ድርድር የውል መቋጠሪያ
ነው። የቁልምጫ ነው። ቁልምጫውም ተፈጥሯዊ የሆነ የዕብለት ግሽበት የመይጨፍርበት፤ የሽንገላ ስንጥቅ የማይሰግርበት።
በሌላ በኩል „ዋያ“ ዋያ። ዋይ! ዋይ! ከሚየሰኘው ከማይቻለው የበርሃ ቋያ መከራ እንደ ማለት
ይሆን ብያለሁኝ። ግን እርግጠኛ አይደለሁኝም።
ሌላው „የጸሐይ
መንቀልቀል“ ጸሐይ ምላሳማ፤ የወጣላት የሙቀት ተናጋሪ ለዛውም ተጣድፎ ተናጋሪ አድረገው አቅርበዋታል። የደም ዓይነታቸው ቢ የሆኑ ሲናገሩ ይፈጥናሉ ይባላሉ። አሁን እትጌ ልዕልት ጠሐይ ደመ ቢ ሆናለች ተዚህ ላይ።
ግዑዝን የሰብዕ
ገጸ ባህሪ ሰጥቶ መጻፍ ልብ አንጠልጣይ የሥነ ጹሑፍ ውበት ነው። ለዛው ልበለውን? በሌላ በኩል ሙቀቱ ራሱን እንደ ጧፍ ወይንም እንደ ሹግ ነበልባል ሆኖ በሚጋረፈው ቃጠሎ
መማገድ ለማለት ይመስለኛል።
ሌላው „ጽናትን
ፈርሸን“ ዋው! ውብ ሥንኝ ነው። ጽናት መከራን የመቀበል፤ ፈተናን የመቋቋም የመቻል ልዩ ስጦታ አቅም ነው። ጽናት ውርስም
ነው። ይህን ፈተናን የመቀበል እና የመቋቋም አቅም እንደ ልዩ የተሰጠ ምቹ ዕድል እንዳዩት ነው ጠ/ሚር አብይን በዚህ ውስጥ ያዬሁት። ፈተናንም ሰልጠንውበታል፤ ፈተና ፈርተው የሚሸሹት አንዳችም የውል መስመር አይኖርም ማለት ነው። ማለፊያ!
„እልህ አቀባብለን“ ዋው!
ይህም ውብ አገላላጽ ነው። ከእናታቸው ጋር ያላቸውን የውል ሰነድ የተግባር አስኪሆን ድረስ እልሁ እንደ ባሩድ አንጠጣሪ ዒላማ መቺ
አድርገው ነው ከዚህ ላይ የሳሉት። አሉታዊ እልሁ ነው ማህንዲሳቸው። ቅዬሳው ሁሉ በእልህ ቀልሃ ነው ማለት ነው። ወሸኔ!
„ይቻላልን መዘን።“ ከሚሊዎን
ቃላት ውስጥ የተመረጠ የታገድሎ ምርጥ ነው „ይቻላል“„የይቻላል" አክቲበስትነት ምንጩ የተስፋ ማህበርተኛ እና የአውንታዊነት ቤተኝነት ሲሆኑ
ብቻ የሚገኝ ነው። ይቻላል ብሎ የሚነሳ ሰው ጠንካራ ፍጹም ታታሪ ሠራተኛ ነው የሚሆነው። ሥራን ፈጥሮ፤ ሥራን አብጅቶ፤ ሥራን በይቻላል
ተስፋ ይጠልፈዋል።
ሥራ እራሱ ከሠራተኛው ዕድሉ ሲገጥም ማለት ነው። ሥራ ህይወቱ
የሆነ ሰው ይቻላልን ይደፍራዋል። ይህ የውል ሰነድ ሲፈራረሙ
አፈራራሚያቸው እሱ አንድዬ ብቻ ነው። አንድዬ ደግሞ እኛ ከማናውቀው ያደመነ መከራ አድኖ፤ ከአጥቂ ሰውሮ፤
ዕድሜያቸውንም ቀጥሎ
ጠ/ሚር ከሆኑበት ዕለት ጀምሮ ከሦስት
የሞት ፍርድ እና ከአራት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አድኗቸዋል።
ምክንያቱም ንጽህናቸው ከሰው
ሰውኛው ይልቅ አደራውን ከሰጣቸው ከእሱ ከአማኑኤል በላይ የሚያውቀው ስሌለው። ምክንያት አለ እዮራዊ። ዕድሜው ከሰጠን፤ ዕድሜውን
ከጨመራላቸው አንድዬ ያቀደው በአቀደው ሠርቶ የሚያሳዬን ጊዜ የሚገልጠው መልካም ነገር አለ ብዬ አምናለሁኝ። እኔ የተስፋም ጥመኛ
ነኝ። ተስፋዬ ደግሞ አምላኬ ነው።
· „ የቢስ የቢሱን ተይ እኔም ትቼዋለሁ
ይሄን
ፍቅራችነን የልብሽ የልቤን
ዬዘመነ
ኪዳንሽ የዕድሜ ኪዳኔን
ማተብሽ
ማተቤን
ቢስ
አይይብን በይ
አይዬን
ብያለሁ“
v የህሊናው
ብሌን በዕኔ ዕይታ…
እኔም ብዙ ጊዜ ከቤተሰቦቼ ጋር ስለ ዶር አብይ አህመድ ስወያይ ቢስ አይይብን እላለሁኝ። „ቢስ
አይይብን“ ቃሉ ጎንደርኛ ነው። ዓይን አይይብን፤ የተከደነ ሲሳያችን ክፉ አይንካብን እንደ ማለት ነው። የእናት እና የልጁ ውላዊ
የቃል ኪዳን ሰንድ በፍቅር ላይ መሰረት የጣለ ስለሆነ የሁለታችን ፍቅር እሰከ መቃብር ድረስም ሰው አይይብን።
ሚስጢሬን ስነግርሽ
ሚስጢርሽን ስትነግሪን አብረን ልንዘልቅ የዕድሜ ልክ ውል ኪዳን ማህላ
አለበን። ዘመንሽ በሰጠሽ ልክ ትሆኝልኝ ዘንድ አሰብሻለሁኝ። አሳቤዬ ሲሟላም እንደ አሳብሽ ሆኜ ታገኝኛለሽ ነው። መተንበይ ነው።
ትንበያውን ጠባቂ እኔን መሰል ተስፈኞች ደግሞ አለን። የተስፋቸው ጉዞ ፈቃጅ ታዳሚዎች። ለዚህም አንድዬ ደግሞ አለልን ነው። ተስፋን ፈጣሪው ተስፋን አብቃዩ ተስፋን አስባይው ተስፋን ጠበቂው።
„ማተብ“ አንችም ማተበኛ ነሽ ለልጆችሽ፤ ይህን እኔም አውቃለሁኝ። እኔም አንቺ ባለሽ ማተብ
ልክ ፈጥረሽኛል እና ከተፈጥሮሽ ላልውጣ ውሌ ውልሽ፤ ውልሽ ውሌ ነው። የጋራ ስምምነቱን ወድጄው አክብሬው አደረገዋለሁኝ። ብቻ አንቺም
ኑሪልኝ እኔም ኑሬ ፈቃድሽን ለመሙላት ያብቃኝ ነው። ያደርገው ብለናል!
· „ያስለቀሰኝ ፅልመት ከሉ እንዲገፈፍ እንዲነጋ አውቃለሁ
ስለዚህ
ውዴ ሆይ!
በተጋፊ
ወጀብ በዓውሎ ንፋስ ውስጥ ቢሆንም ጉዟችን
በእሾኽ
ባሜኬላ በኩርንችት ባጋም ቢያዝ መንገዳችን
ይህን
‘ሚሻገር ነው ተስፋዬ የተስፋችን“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
መንጋትን ማሰብ የፈጣሪ ስጦታ ነው። እሱን ያመነ የመንጋት ደቀመዝሙር ነው።
„ያስለቀሰኝ ጽለምት“ እም! ከዚህ ላይ ብላቴው ሎሬቱ ጸጋዬ ገ/መድንህ "ወንድ ልጅ ብቻውን ነው የሚያለቅሰው፡ ያለውን የገለጠ አህድ ነው። ለቅሶው ደግሞ በድቅድቅ ውስጥ ሆኖ የተስፋ ጭላንጭል በሌለበት እንደሆነ ነው ያሰበኩት።
ሌላው ድንቅ ብሎኝ እንደ ሰብዕ የተመለከትኩት ዕድምታ ኢትዮጵያን አንግሰው ነው ሆይ!ያሏት ነው። እግዚአብሄር ሆይ! እናታቸውን
ስለ አክብሮት ከዚህ በላይ ውሰጥን የሚያሳይ ራዲዮሎጂ የለም።
የፍቅራቸው ልክ ወደርየለሽ ስለሆነም ውዴ! ነው የሚሏት። ታድላለች
አላዛሯ ኢትዮጵያ እንዲህ ከውስጡ ፍላጎቷን ያናጸ ማህንዲስ ልጅ ማግኘቷ፤ የጉዞው አድካሚነት አይደለም ትናንት ዛሬ ሰው በሰራው ችግር ወደ 2 ሚሊዮን ወገን ከሁለመናው
ተፈናቅሏል። መቋቋም የሚችል የጽናት አውራነት አላት አላዛሯ ኢትዮጵያ። ተመስገን!
ከሰሞናቱም ሌላ ቤንዚን እንዳለ በት/ቤት ተቋማት እዬተደመጠ ነው አሶሳ ላይ። ችግር አምራቹ የራስ ወገን ነው። ካለደም
ላልኖረ፤ ደም ካለዬ አውሌው አይነሳም። ልክ ከአለ አልኮል የማይሰሩ ነርቦች እንዳላቸው ፍጡራን ማለት ነው። ደም ናፋቂ እፉኝት
መርዛም ተልኮ ያለው እንደ ትናንቱ ዛሬም ያምሳል። አንዱ እሳት ሲጠፋ ሌላውን እዬቆሰቆሰ ያማግዳል። ምን አለ እሳቱ ከእሱ ደርሶ እስኪያነደው ድረስ ወይም አንድዬ ፍርዱን እስኪሰጥ ድረስ እዮራዊውን እሳት እስኪያዘነብ።፡
ትናንትማ በድቅድቅ ውስጥ ነው የተኖረው። ድቅድቅ ሲባል ሰው ብርሃን አለ ይላል። ብርሃን ማለት
የሰው ልጅ የራሱ ጌታ፤ ራሱን መሆን ሲችል ብቻ ነው። ለዛ ደግሞ በተስፋው ልክ መኖር ሲፈቀድለት ነው። በተስፋው ልክ መኖር መፈቀድ
ማለት ደግሞ ሰው ነህ፤ ዜጋ ነህ መባል ሲቻል ነው። ይህም ማለት ያልተቀፈደደ የተፈጥሮ ነፃነት ሲኖር ብቻ ነው።
ነፃነት የሚባለው
ነገር በሌለበት የሰው ሰራሽ መብራት ይሁን
የሰማዮዋ የልዕልት ጸሐይ ብርሃን ልትሰጥ ከቶውንም አይቻላትም።
ሰው በታሰረ ህሊና ከኖረ ኖረ ሳይሆን እዬሞተ ቆመ ማለት ነው። የፈተናው እርዝማኔው፤ የሳህዋ
ቁመቱ፤ የአባሳው ወርድ እና ስፋቱ ይለያይ እንጂ ሁሉም አብዛኛው
ደርሶታል ብዬ አስባለሁኝ። ራሱ በዳዩም ተኝቶ አያዳርም፤ ራሱ በዳዩም የህሊናው ጌታ አይደለም።
በዳይ እና በደል አብረው ሲኖሩ
ከተበዳዩ በላይ እዬተሰቃያዩ ነው
ኑረናል የሚሉት በዳዮች እራሳቸው።
የሆነ ሆኖ ያን ዘመነ ጽልመት ብለው ነው የገለጹት። በምን ያህል ስቃይ ውስጥ እንደነበሩ
ያሳያል። ይህ ማለት ከሚያምኑበት ጽኑ መንፈስ እና ያን ለማድረግ ከመቻል ችሎት ጋር ሰብር ላይ ነበሩ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ህሊና
ላለው ፍጡር እጅግ የመኖር ግማድ ነው። ይህን ላለማዬት ሳያዩ የሚኖሩ ዕድለኞች ናቸው።
እሳቸው ደግሞ አልይህ አልስማህ ብለው ተሰደው ለመኖር አልሻህም ብለው ግን ዕውነት በሚሉት ምሽግ
ውስጥ ሰቆቃውን በድርብ እዬተጋፈጡ የእናታቸውን መከራ በሪሞት ኮንትሮል ድል ሳይሆን
ወቅት ሁኔታ ጊዜን ጠብቀው ተጋፍጠውት ዛሬን
ካስገኙት ምርጦቹ
ተርታ አሳልፏቸዋል።
ይህን የነጠረ ዕውነት የእናት እና የልጅ አልካዳሽም አልከዳህም ውል ተሸክሞ ከዚያ ጽልመታዊ
ሥርዓት ጋር አብሮ መሥራት ፈተናው ፈታይም ነው ገማጅም ነው። ይህ ጹሑፍ የተጻፈው ጭራሹኑ የተስፋ ጭላንጭል ባልነበረበት ወቅት ስለመሆኑ ሥንኞቹ ይገልጣሉ።
ምክንያቱም በቅኔው ውስጥ ያሉ ሥንኞች ምሬት እና ራሮትም
ጽናትን ጎራርሰው አሉበት እና።
· „ እናም ሜዳ ተረተርሽ ሸለቆ ጋራሽን
ሰርጥ
ባህር ሃይቁን ጅረት ተራራሽን
ቆላ
ወይና ደጋ በርሃ ምድርሽን
መረሬ
አሸዋ ዋልካ ሸክላ አፈርሽን
በዚህ
ሁሉ መሃል እናቴ ዓለሜ ገራገር ህዝብሽን
በፍቅር
አልብሰን ሰማያትን ከድነን
እንደተቃጠርነው
እንደተዋዋልነው የምንገናኝ ነን“
v የህሊናው ብሌን በዕኔ ዕይታ…
„መረሬ
አሸዋ ዋልካ ሸክላ አፈርሽን።“ ከአፈር ሸክላም ይሰራል፤ ሸክላም የቤት ውስጥ አገልግሎት ይሰጣል፤ መሬቱም ሰብልን
ትሰጣለች። ሰው
ካለ ዕህል እና ውሃ አይኖርም ግን ይህን የሰው
ልጅ የመኖር ሚስጢር አክብሮ ለመኖር መሬትን አክብሮ መነሳት ይጠይቃል።
በቀደመው
ወያኔ ሃርነት ትግራይ በአውራነት በመራት መከረኛ አገር ስለመሆኑ ኢትዮጵያ እንደ አገር ትታያለችን የሚል መጠይቅ ያጭራል። መኖርን
የሰጠች ምድር ስለሆነች፤ ያን የሰጠች እናት እንደ ሰጠችው፤ በሰጠችው ልክ ተሁኖላት ወይ ወይንስ እዬተቃጠለች እዬነደደች ነበርን?
እኔ አይደለሁም ግጥሙ ነው የሚያመሳጥረው። ዛሬስ ብዬ ግን እኔው ልጠይቅ መታበዩ አለቻል አቅሙ አልሸከመው ብለው አልተፈጣጡም ወይ?
ሁሉም ሆኖ ወጀቡም፤ መከራውም፤ ሰቆቃውም፤ ተስፋ ማጣቱም፤ ተስፋ መነጠቁም ሆኖ ግን የህዝቡ
ደግነት በተመስጦ ቀርቧል። „በዚህ ሁሉ መሃል እናቴ ዓለሜ ገራገር ህዝብሽን“
ለዚህ ገር ህዝብ የተጋባውን ያህል ፍቅር አለመሰጠቱ ጎርብጧቸዋል። ሁሉንም መከራ በፍቅር አስታግሶ ህዝብ የሚከበርበት ዘመን መናፈቅንም
ያመላክታል። ውዴ ይሏታል፤ ዓለሜ ይሏታል፤ ሆይ! ይሏታል አላዛሯን ኢትዮጵያ።
ኢትዮጵያ አላዛርም ናት። ድንቁ ነገር ያከበሩት ህዝብ በአጭር ቀን ውስጥ አክብሮቱን ለግሷቸዋል። አጥቋሪዎች ጠቃጠቆ ህውከት አቅደውበት ለማሰናከል ቢታታሩም። አክብሮት ተፈጥሯቸው ነው። ሁሉንም ጸጋ አክብረው ስለሚነሱ መታበይ ስሌላቸው ነው ልባችን የሸልምናቸው። በምናብ የሚኖረው ደግሞ ብጥስ እና ቅንጥሱን ያሳዬናል። ትዕይንት ነው መቼም ዘነድሮ የሰጠን።
ኢትዮጵያ ከሳቸው የጠዬቀቻቸውን፤ እሳቸውም ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ተስፋቸውን ለማሳካት ያለውን
የፍዳ ኩርንችት አሸነፈው እናታቸው የምትፈልገውን ለማቅረብ አርግጠኛ መሆናቸውን ከዚህ ላይ ያሳዬናል። እናታቸው የፍቅር አቅርቦት አምራች እንዲሆኑላት ነው የጠራቻቸው። ምኞት እና ተስፋችን ጋር
መገናኘታችን አይቀርም ነው የሚሉት ምንም ጽልመት ቢወረንም። ትንቢት ነውን ወይንስ ነብይነት?
ግን አቅማቸውን አሳምረው ያውቁታልም። በራሰቸው ሃሳብ ውስጥ የሰከኑ ናቸው። እኔም የምወድላቸው ይህን ነው። ሃሰብ አላቸው የማይነጥፍ።
· „ዛሬም እንደ ጥንቱ
ልክ
እንደ ትናንቱ
እኔ
እና አንቺ እግዜር አንድ ላይ እስካለን
በካብነው ተስፋ ልክ
በዕምነታችን
ልክ
እንገናኛለን።“
ዕምነት መታመን ማመን። የሠለስቱ ጥምረት። ሦስቱ ነው ለድርድር የተቀመጡት በክብ ህዋዊ ጠረጴዛ።
ቅድመ ማዕከለ እና ድህረ ዓለም ንጉሥ ክርስቶስ፤ አላዛሯ ኢትዮጵያ እና ጠ/ሚር አብይ አህመድ።
የውላቸው መሰረት ተሰፋ ነው። አላዛሯን
ኢትዮጵያ እንደ ተፈጥሯዋ ማድረግ። ማህንዲሳቸው መቻል ነው፤ መሳሪያቸው ጽናት ነው፤ መነሻቸው ልዑቅ ሃሳብ ቃል ነው፤ መድረሻቸው
የጥንት የጥዋቱን ክብር ከግርማ ሞገሱ ጋር በትውፊቱ ልክ ከ21ኛው ምዕተ ዓመት የሥልጣኔ እርካብ ጋር አስማምቶ አዋዶ በፍቅር መንበር
በብልጽግና ላይ ማዋል ነው። እኩል ማድረግ አንቀትን ቀና እድርጎ መሄድ።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጀመረውታል፤ ቁልፉ ተስጥቷቸዋል፤ አብሶ ብአዴን ለዚህ ይመሰገናል በተለዬ ሁኔታ። ሲያጣ የጦመውን ሳይሆን ፈቅዶ የሰጠው ቅንነት ታሪክን እንደ አባቶቹ ጥፎታል በወረቅ ቀለም። ፈጻሚው እግዚአብሄር ነው። በዚህ ውስጥ
ከእያንዳንዱ በግል ከሁሉም በጋራ የተግባር ገበርን ይጠይቃል። ከሁሉ በላይ ቅንነት፤
እዮባዊነት፤ እና አዎንታዊነት።
„የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር
ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱
ቀኖች ይሸልካሉ። ቀኖች ማራቶኖች ናቸው። ቀኖችን በሩጫ የሚቀድማቸው ቢኖር ሰከንድ እና ብርሃን
ብቻ ናቸው። ሰከንዶች የቀኖች ሦስተኛ ትውልዶች ናቸው። የልጅ ልጅ ልጅ እንደማለት።
በዚህን ጊዜ ውስጥ ዕድልን መጠቀም ለሚችሉት
ብቻ የተሰጠ
ስጦታ ነው። እራሱ ዕድልን ማወቅም ልዩ ዕድል ነው።
አሁን የኢትዮጵያ የተፎካካሪ/ የተቃዋሚ/ የተቀናቃኝ ድርጅቶች
በውነቱ ዕድለኝነታቸውን አላወቁበትም ብዬ አስባለሁኝ - እኔ። ከብዙ መከራ እኮ ድነዋል። ዓመት ይዞ እስከ ዓመት እጃችሁ ከምን ሲባሉ
በተራዘመ ትግል አልቀው አልቅው ብዙዎቹ ሥማቸው ብቻ ነው
የቀረው። ዘነዘናቸውን። ምን አልባት ቀኑንም ፈጣሪን ሳይጠይቁ
መንገድ
ጀምረውም ይሆናል። ከስኬት ጋር የተላለፉት በዚህም ነው። ሌላው ኢትዮጵያን አጋምሶ የማዬት ጉዳይ ነው።
በዚህ መለመላውን በቀረ ሥም አደብ ገዝቶ ደግሞ በዕድል መጠቀም አልችልበት ብለው ጉግስ ላይ
የነበሩትን ሳስብ ምን ቢሰጣቸው ይሻላቸው ይሆን ያሰኛል። የሰው ልጅ የያዘውን ይዞ ነው ቀጣዩን ማስላት ያለበት። ያን ከሚያሳጣ
እኩይ ነገር ጋር አብሮ መጣበቅ መቼም የጤና አይመስልም።
የሆነ ሆኖ ዘለግ ያለ ባለ ቅንነት ዝናሩ ሙሴ በቀደመው ጊዜ ታች ሆኖ
የተዋዋለውን የድንግልና ኪዳን በምን መልክ ውስጡ ይነበብ ነበር ለሚለው ከታች የለጣጠፍኳቸው ማያያዣዎች ተጨማሪ ዋቢ ይሆናሉ ብዬ
አስባለሁኝ።
ስለዚህ አጫጭር ስለሆኑ እነሱንም በማድመጥ ግጥሙንም በመቃኘት ዘለቅ ካለው ሙሴያዊ ረጅም ጉዞ ጋር አብሮ በድርጊት
መጪ ነዋ!
የተውኔት ነፍሶች ይህን የሰለስቱ የውል ቅብብል ትውፊት ለመድረክ ቢያበቁት ምርጫዬ ነው። በተለይ
ቅኑ ገጣሚ ጋዜጠኛ የፊልም ሁለመና እና ፈጣሪ
አቶ ፍጹም አስፋው።
ለእንደዚህ ዓይነት ህሊናን ቤተኛ ከሚያደርጉ ከዕውነት ብሌኖች የመነሳት ሙሉ አቅም ብቻ ሳይሆን
የተሰጠውም ስለሆነ ፍጹሜ። አገሬ አገሬ የሚያሰኝ ፤ ውስጥን ያነበበ፤ የተረጎመ እና የመሳጠረ የተደሞ ድማሜ ያለው ወዘናማ የራስ
ጠረን ያከበረ ለዛም የማሰን አዚም ያለው ቅኔ ነው። ዕጹብ ትወና ይወጣዋል።
ፍቅር ብዙ ዓይነት ነው። የአገር፤ የተፈጥሮ፤ የሙያ፤ የቤተሰብ፤ የሃይማኖት፤ የትዳር፤ የክህሎት፤
የጓደኛ፤ የተፈጥሮ፤ የሰው ልጆች፤ የትውፊት፤ የታሪክ፤ የብሄራዊ ሰንደቅዓላማ፤ የቃል፤ የሃሳብ፤ የፍልስፍና፤ የመኖር፤ የነፍስ፤
የማድረግ፤ የሥራ፤ የልጅ፤ የቤተ ዘመድ፤ የማህበራዊ ኑሮ፤ የግል፤ የፋሽን፤ የጥበብ፤ የማሰብ፤ ማለቂያ ዲካ የለሽ ጅረተ በርካታ ነው።
ግን ከሁሉ የሚለቀው ግን የአገር ፍቅር ይመስለኛል። አገር እራስም ነውና። አንድ ሰው እኔም አገር ነኝ ብሎ ከተነሳ አገር ያስፈልገኛል
ይላል።
ለሚያስፈልገው ነገር ደግሞ አገር
የሚያስፈልገውን ሆኖ ለመገኘት ይኳትናል። ለዚህ የታደሉ ብጹዐን ናቸው። በዚህ ቅኔ ውስጥ ራስን አሸንፎ የወጣ ለራሱ ህሊና ታማኝ
ለመሆን የቆረጠ፤ ለውሉ ውልኛ የደፈረ ጀግና ውስጡን አሳይቶናል። አብሮ መጓዝ ወይንም ተንጠባጥቦ መቀረት የእያንዳንዳችን ምርጫ
ነው … ቅኖች ግን አያብሉም፤ አያወላዱም ምንግዜም እንደ ትናቱ ሁሉ ከአባ ቅንዬ ጋር … ናቸው ነን!
Ethiopia - Dr Abiy እንዴት ሰዉ በ1% ልዩነት ይሰቃያል?!
Ethiopia - ….ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች! ትለወጣለች!
እድልን በታማኝነት መጠቀም ያስፈልጋል!
Ethiopia - Dr abiy ሚኒስትር ከመሆንህ በላይ ሰዉ ነህ!
ዶ/ር አብይ አህመድ ለፈረንጅ ጋዜጠኞች የመለሰላቸዉ ድንቅ መልስ!
Ethiopia - New Dr Abiy - አንድ ሰዉ ብቻዉን መለወጥ ይችላል!
የኔዎቹ ቅኑዎች ውዶቼ ታዳሚዎቼ ዛሬ ሳልተኛ ጉልት ብዬ አደርኩኝ፤ ዋልኩበትም ባጅቼበታለሁም። አቋራጭው
ከተኛሁ ሃሳቤ ይበተንብኛል ብዬ ነው ዛሬን የሸለምኩት። ብዙ ጊዜ ነበር የተጠመድኩት ይህን ለመፈጸም ግን በበቃኝ ሞግቶኝ ዛሬ
ግን አሸንፌው ለፍጣሜ በቃሁኝ። ከዚህ በላይ ልሂድ ማለትን ለፈቀደ ቅኑ ነፍስ አሁንም ቢሆንበት ደስታውን አልችለውም። በተለይ ትውና
ላይ ከዋለ ነፍሴ ታርፋለች። ኑሩልኝ ለምንጊዜም። ታድሮበት ያለቀበት ሰዓት አሁን ነው 16.52 እንደ ሲዊዞቹ።
ኑሩልን!
ኢትዮጵያዊነት
ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
ቅንነት ግጣሙን ሲያገኝ የተፈጠረበትን መንበር ላይ ያዋውላል!
አዎንታዊነት ማሸነፍም
ነው!
የመሆን መቅኖ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ