እንሆነት ... ዴሞክራሲ

ወትሮም።
„የእግዚአብሄር ባርያዎች እግዚአብሄርን ያመሰግኑታል።
እርሱ የተመሰገነ ነው። ለዘለአለም የተመሰገነ ነው።“
ተረፈ ዳንኤል ቁጥር ፷፩

ከሥርጉተ©ሥላሴ
29.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


የመፍትሄው መንገድ ወትሮም አንድ ነው። ከግራ ዝንባሌ ጋር መፈታት። ራስን ማሸነፍ። ነገር ግን ግራ ሁልጊዜም ግራ ነው። የአላዛሯ ኢትዮጵያ የህልውናው ችግር ይሄው ነው። እራሱን ችሎ እኮ የአላዛሯ ኢትዮጵያ የህልውናዋ የማንነቷ ታጋድሎ ያስፈልግ ነበር እኮ። 

የዚህ ዝንባሌ አለው ተብሎ ነው እኮ ነው የአማራ የህልውና የማንነት ታገድሎም የተፈራው፤ የተገለለው፤ ዕውቅና ሳያገኝ ተድብስብሶ እንዲቀር የተፈለገው። ምክንያቱም ጨቋኝ እና ተጨቋኝን ፈጥሮ ኢትዮጵያን ለማመስ ዋነኛው ፒላሩ ይሄው ነበር እና። ይልቅ ቀቀድሞው ጠ/ ሚር አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ዚንባቢዎ ሰሞኑን ለውጪ ሚዲያ በሰጡት ቃለ ምልልስ የአማራን ተጋድሎ አውስተው ነበር። ተመስገንም ብያለሁኝ። 

የሆነ ሆኖ ወትሮም ቢሆን ይሄው ነው የ43 ዓመቱ ለፍትህ እና ለነፃነት፤ ለህግ የበላይነት እና ለሃሳብ ልዕልና ተጋድሎ መደረጉ አንዱን በዳይ ሌላውን ደግሞ በዳይ በማድረግ ነበር። ሊዘህም ነው የ አማራን የህልውና የማንነት ተጋድሎ ያን ህዝበ ጠቀም ለማድረግ ያለው ቀናነት ዘሞ እንዲቀር የተደረገውም ሥሩ ያ ነው። 

አሁንም በግራ በቀኝ ያሉት ወጀቦች የዛ ቅሪት አካል ናቸው። ሥር ነቀል ለውጥ ከኢህአድግ መራሹ ይታለማል? ይገርም ነው ዘንድሮ፤ እራሱን ኢህአዴግ ያክስምልን በራሱ ሜዳ ተጫውቶ? እንዴት ይደንቃል ይሄ ጥንዝል ፍልስፍና።  ለውጡን የሚመራው ኢህአዴግ ሆኖ ማለት ነው። ኢህአዴግን አንይህ ብሎ ነገር አዋጪ አይደለም። 

በዚህ ዙሪያ አሉታዊ ሃሳቦችን እንደ ካብ መደርደር ለእኔ የማያውቁት አገር ናፈቀኝ ዓይነት ነው የሚሆንብኝ። በእጅ ያለን ነገር እኛ እናውቀዋለን፤ መቼ ነው አብሮ የተጠመረው ሲቀጥል ታይቶ የሚታወቀው? 

ኢህአዴግ ውስጥ የሁለቱን ተጋድሎዎች መንፈስ እንመራለን የሚሉ በግንባሩ ውስጥ የተፈጠሩ ቅን እና እጅግ ብቁ አቅማቸው በሁለመና ሙሉዑ የሆኑ መንፈሶች ባይኖሩ የአማራ እና የኦሮሞ የተጋድሎ መስዋዕትነቶች ባክነው ነበር የሚቀሩት ያው እንደ ተለመደው። ያ ደግሞ ድርብ ኪሳራ ነበር። ረጅም ሌላ የመከራ ቀንበርም ነበር። 

በነፃነት ፈላጊው የነበረው ሂደት ያ ቅናዊ መንፈስ ቅስሙ ተሰብሮ እንዲቀር ነበር ትጋቱ በዶቦ የነበረው። አቅም አለኝ ያለ ሃይል ሁሉ ታግሎ ታግሎ ሳይችል፤ ነገር ግን በሰው ፈቃድ ብቻ ሳይሆን በፈጣሪም ፈቃድ ሃሳቡም ከሰው ባላይ ስለነበረ ለሁሉ እሸት ቅመሱን እንዲህ ለሁሉ በእንሆነት አደለ ….

የትኛውም የተፎካካሪ ፓርቲ ይህን ዕድል ቢያገኝ ዛሬ ኢህአድግ ካሰገኘው 1/10 እንኳ እንደማያሟላ ይታወቃል። መጀመሪያ አንተ ሰው ነህ፤ አንቺም ሰው ነሽ፤ ሁላችንም ሰዎች ነን ብሎ የመነሳት አቅም የለም። አዲስ ሃሳብ ማፍለቅም እርም ነው። ወትሮም ሆነ ዘንድሮ በዛ በተኖረበት የግራ ዘንዶ ዝናባሌ የቁርሾ አዟሪት ላይ አሁን ተቸክለው ነው የሚታዬው። 

አሁን ውጪ አገር የነበሩት የተፎካካሪ ፓርቲዎች አገር እዬገቡ እንዳሉ፤ ሊገቡም ያሰቡ እንዳሉ አዳምጣለሁኝ። ውጪ አገር ባለው ኢትዮጵያዊ የመንፈስን አንድነት ፈጥረው ነው ወይ አገር የገቡት፤ ለመግባትስ ያሰቡት ሲባል ምንም ነው። ከፍለው፤ በትነው፤ አስገልለው፤ አሳድመው ነው። ስንት ቅናዊ መንፈሶች ተጨመታትረው ከስመው ቀርተዋል።  

ከዚህ ያለው አጋ ላይቶ የተቀመጠው፤ በፍርስራሽ የቁርሾ ናዳ ላይ በዬጉድቡ የተጎደበው እኮ የተነካ ነገር የለም። በነበረው እንደ ነበረው እንደ ወትሮ ነው ያለው። በወትሮ ተለምዶ ከተሆነ ደግሞ አሁን ያለው አገራዊ ቅናዊ ለወጥ ጋር የሚገጥም አይደለም። በወትሮ መንፈስ ላይ ስለመሆኑ ኢትዮጵያ ላይ ከሚዲያ ታታሪዎች ጋር ጠ/ ሚሩ ያደረጉ የጥያቄ እና የመልስ ውይይቶች ዋነኛ ምልክቶች ናቸው።

አሉታዊው ወትሮን ማጠብ ካልተቻለ አሁንም ስለማግስት ለማሰብ ይቸግራል። ዜጋ በሲሶ በእርቦ መሸንሸን ቢሆንም ያ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ችግር ብቻ አይደለም የግራ ዘመም ፖለቲካ ሁሉ የነፍስ መደወሪያ ነው። በልዩነት ግድግዳ ተፈራርጆ ስለ ዴሞክራሲ እጮኻለሁ ቢባል ለእኔ ተረት ተረት ነው። ዴሞክራሲ መጀመሪያ ሲታስብ ማቅረብን፤ ማቀፍን ያክትታል።

ኢህአድግ እኮ ሆኖበት እያሳዬን ነው። አብሶ የአብይ ሌጋሲ የሆነበት መስመር ድንቅ ነው። ታረቅኩኝ ሲሉ የውነት ነው። እርቁን ሲክሱ ፍዳውን ሲይ፤ ሲብጠልጠል የባጀው ተባደዩ አዲሱ ካቢኔ በዳዩን አክብሮ፤ አቆለባባሱ፤ አንጥፎ ጎዝጉዞ ከተገባው በላይ ዕውቅናው አግልቶለት እንዲያውም ፕሮፖጋንዲስቱም ሆኖ ነው።

በነፃነት ተጋድሎ ዘመናት ስንት ጉድ ነው የነበረው። ተራራው እኮ ብዛቱ ወዘተረፈ ነበር። ተራራን እጅ ለመንሳት ሰልፉ ይህ ነው አይባልም በዬስብሳባው ስታዘበው የኖርኩት ይህ ነበር። ይህ ሁሉ ከንቱ መሆኑን ስሜን አሜሪካ ላይ ዶር አብይ አህመድ አሳይተዋል። የኞቹ ይህን ያደርጋሉ ወይ ቢባል ትናንት አላዬንም፤ ዛሬም የቂም ቁፋሮ እያዬን ነው፤ ነገም ከዚህ እልፍ የሚል ነገር ለመጠበቅ ይከብዳል። 

ተፋላሚህን የእኔ ሳትል በይቅርታው መስመር ተሰልፌያለሁ ማለት መቼም ትርፉ ትዝብት ነው። ተፋላሚዬ ብለህ የምታሰበውን አንተ ባተቀርበው መደመሩ ሲያቀርበው ደግሞ አንተን ያቅርሃል ... የሚታዬው ይሄው ነው፤ ነገር ግን አንተም የነፃነት አታጋይ ካሸነፍክም መሪ ለመሆን ነው የተደራጀኸው። በዛ በምትራው ማህብረስብ ውስጥ ያ ያገለልከው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ስለመሆኑ እንኳን ገና ት/ ቤት መግባት አለብህ። 

የአብይ መንፈስ ማግለልን፤ ክትር መሥራትን፤ ደንበር ማበጀት ያሸነፈ ጀግና ነው። ይሄ ሆኖ ነው የሽግግር መንግሥት፤ የተጽዕኖ ፈጣሪዎችን አንድነት መንግሥት አሁን ደግሞ አንድ ልዩ የበላይ አለቃ ኮሚሽን በሉት ምንትሶ ቅብጥርሶ ተቆጣጣሪ ነገርም ይፈጠር እዬተደመጠ ያለው።

ምንድነው ይህ ሁሉ ኳኳቴ። እምንፈልገው አይደለም ከምንፈልገው በላይ የሆኑ ቅን ቸር ትሁት መንገዶች ተጀምረዋል። ህዝብ ካልመረጠን ልናገልግል ፈቃደኞች አይደለነም እያሉ ነው መሪዎች፤ ከዚህ በላይ ምን እንደሚፈለግ አያታወቅም።

ሌላው አሁንም የቅድመ ሁኔታ ድርደራው ነው። ሥርዓቱ ሲዘረጋ እኮ አገርም እንደ አገር ክልሎችም እንደ ደረጃቸው፤ ምን አልባት ክ/ አገራዊ ከተሆነም ሁሉም እንደ አቀሙ ሚዛኑን የጠበቀ የሃብት፤ የተቋም ግንባታ፤ የሃለፊነት ክፍልፍል ይኖራል።

ይልቅ ሁሉም ሰው አዕምሮው መሆን ያለበት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር የግንባሩ በፖለቲካው ዘርፍ ማለት ነው ከሊቀመንበሩ በታች ቁልፍ ቦታ የያዙ ናቸው። በዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ እና አመራር ደግሞ በመንግሥት ጉሮሮው ሃላፊነት የተሰጣቸው ለሳቸው ነው። ይህም መቼም እጅግ ከባዱ ፈተና ነው። ይህን ሞግቶ ማሸነፍ ነው ሊቀድም የሚገባው። 

ነፃ ምርጫ፤ ነፃ ሚዲያ፤ ነፃ የሲቢክስ ድርጅቶች ማቋቋሚያ፤ ነፃ የእምነት ተቋማት ግንባታ፤ ነፃ መኖር እና አመክንዮቹ ሁሉም በሳቸው ሥር ነው። ሥር ነቀል ለውጥ የሚያስፈልገው ከዚህ የአዲስ የዴሞክራሲያዊ ሰዋዊ ሥርዓት የግንባታ ጉሮሮ ለውጥ ላይ መሆን ሲገባው ወቅታዊ ያልሆኑ፤ በአጅግም ለአሁን የለውጥ ተስፋ ጠቃሚ ባልሆኑ አመክንዮች ዙሪያ አቅም ማበክን ነው የሚታዬው።

እኔ ሳዬው፤ ሳዳምጠው ቃለ ምልልሱን ሆነ መግለጫዎችን ሬድ ሜድ የሆነች ኢትዮጵያን የማለም ያህል ነው። ወይንም እዮራዊቷ ኢትዮጵያ። ከተጨባጩ በፍጹም ሁኔታ መንፈሳችን አብሶ የነፃነት ፈላጊው ወገን ሩቅ እንደሆነ ነው እኔ የማስበው።  ወይንም ስልተ ቢስ ሆኗል ማለት እችላለሁኝ፤ ወይንም አልገባውን ቀድሞ ነገር የነፃነት ትግሉን ራዕዬ ብሎ ሲጀምረው።

የፍላጎት ቅደመ ተከተል ሊኖረን አልቻለም፤ ድሎችንም፤ ትሩፋታቾንም የምናቃልልበት መንገድ ያው ልክ እንደ ወትሮ በነበረው አሉታዊ መንገድ ነው። ማለት አልዳነም። ጊዜ የሚጠይቁ፤ ጥናትን የሚሹ፤ ተመክሮ የሚያስፈልጋቸው፤ ስከነትን አብዝተው የሚሹ ጉዳዮች አሉ።

ተገልጠውም የማይነገሩን ውስጥ ለውስጥ እዬታሹ ያሉ የድርድር መስኮችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ማሰብም ይገባል። ከዚህ በመለስ ያለው የእነ ተሎ ተሎ ቤት እንዲሆን ይፈለጋል …. ያ ደግሞ በግብር ይወጣ ዛሬ ይገናበል ነገ ይፈረሳል ... ፓርቲዎች እኮ ሲጣመሩ፤ ሲዋህዱ፤ ሲቀናጁ ኖራዋል አንዳቸውም ሲዘልቁ እና ልድል ለራሳቸው ሥም እና ዝና እንኳን ሲበቁ አልታዩም። 

መጀመር ሳይሆን መጨረስ አቅምን - ብልህነትን - ማስተዋልን - መቅደምን - ማድመጥን - መላቅን፤ ጥበብን ይጠይቃል። ለዚህ ነው የአብይ ሌጋሲ ያ የወደቀ ግንባር ነፍስ አዘርቶ የሚሊዮኖችን ድጋፍ እያስገኘለት ያለው። አንድ አብይ እኮ ነው የተቀዬረው እንጂ ሁሉም ነገር በነበረው ነው ... ግን ጥበብ የአማራር በለጠ እና የእኛ አስኘው መንፈሱን ... 

ሌላው ህሊናን መለወጥ የአዋጅ ጉዳይ አይደለም። በአዋጅ እኮ ይህን ልሙጡን ብሄራዊ ሰንድቅዓላማ መያዝ እንደማይቻል ተደንግጓል። ህዝብ ሲፈልግ ግን ህጉን ጥሶ፤ ሞቱን ፈቅዶ ከ2016 ጀምሮ ይዞ እዬወጣ ነው። አሁን ትናንት አማሮ ላይ እራሱ እንዲሁ አይቻለሁኝ።

አላዛሯ ኢትዮጵያን ስናፈርሳት መኖራችን ማሰብ ይገባል። 

ቅን አለመሆን ማፍረስ ነው። አዎንታዊ አለመሆን ማፍርስ ነው። ቂመኛ መሆን ማፍረስ ነው። ትእግስት ማጣት ማፍርስ ነው። ይቅርታ አለማድረግ ማፍረስ ነው። ይቅርታ አለመቀበል ማፍረስ ነው ወዘተ ... 

ከዚህ አንጻር በመንፈስም ያችን መከረኛ እናት አገር ስናቆሳቁላት ሁላችንም ኑረናል። አሁን ልዑል እግዚአብሄር ይህን ጊዜ ባርኮ እና ቀድሶ ሲሰጠን አቅም ስናዋጣ፤ እራስን በማሸነፍ፤ እራስን በመግራት፤ እራስን በመቅጣት እሳቤ የጉበጠውን በማቃናት መሆን አለበት። 

ይቅርታ እኮ ቃሉ የሚያምረውን ያህል ይቅርታን ለራሳችን መጀመሪያ መስጠት ያስፈልጋል። መቼ እኛ እራሳችን ከራሳችን ጋር ታረቅን እና ነው ሌላው ይቅርታ የምንስጠውስ፤ ከሌላውስ የምንቀበለው። በፍጹም አልተረቀንም እኮ። ስንት ነፍስ ነው ስናቆስል መንፈሱን ስናባክን የኖርነው። ለመሆኑ ዛሬስ አረፈናልን?

ሺ ሚሊዮን ጊዜ ስለ ዴሞክራሲ ሲዘመር እሰማለሁኝ። ዴሞክራሲ እኮ ሁሉንም የሚያረካ አይደለም። ሁሉን የሚያስደስት አይደለም። ዴሞክራሲ አሸናፊ እና ተሸናፊ አለው።
ዴሞክራሲ ማለት አሸናፊ እና ተሸናፊው በሃሳብ ሲሆን ተሸናፊው ሃሳብ የአሸናፊውን ሃሳብ ተቀብሎ አሸናፊው ደግሞ ተሸናፊውን ተቀብሎ አቻችሎ አብሮ የመኖር ጥበብ ነው እንጂ አሸናፊው አንድ ሃሳብ ነው። የአብላጫውን ድምጽ ያገኘው። ስለዚህ ደስታው በዴሞክራሲ አንጻራዊ ነው።

አሁን እንዲያውም አሸናፊም ተሸናፊም የሌለበት ጉዞ ላይ ነው ያለነው። ይህ መቼም የሰማይ ታምር ነው። የኤርትራን ጉዳይ የአፈጻጸም ሁኔታ ከቁምነግር መጽሄት ተጠይቀው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሲመልሱ ሁላችንም የታዘብነው ዕውነት፤ እኛ ብቻ ሳይሆን  ኤርትራ መንግሥትም የአውቀው ሃቅ እያለ፤ እሳቸውም የነጠረው እንቁ በእጃቸው እያለ "እናንተ እና እኔ ሠራሁት ያለው አካል ነው" የፈጸመው ነበር ያሉት።

በዚህ የለውጥ መንፈስ ውስጥ አሸናፊ ቢባል ኢትዮጵያ ነው ያሸነፈችው። ኢትዮጵያ ናት ከዥንጉርጉር አመክንዮች ጋር ታርቃ አስታራቂ የሆነችው። የምህረት አደባባይ የሆነችው ኢትዮጵያ ናት።

በሰብ ደረጃ ግን አሸናፊም ተሸናፊም የሌለበት ጉዞ ላይ ነን። ይህ ደግሞ የሚጠቅመው ለሥነ - ልቦና ነው። ተሸናፊ የሆነ አካል ቀጣዩን ተስፋ ለማቀድም፤ ለመከወንም የሞራል አቅም ያንሰዋል። መንገዱም የከሳ ይሆናል።

ይህን ቁምነገሬ ያለው አብያዊ መንፈስ ሁሉም አሸንፏል በሚል ተሸናፊም አሸናፊም በሌለበት ሁኔታ በስክነት፤ በጥንቃቄ፤ በላቀ ብልህነት አቻችሎ እዬመራው ነው። ግነት አለበት የሚሉ ሃሳቦችን አዳምጫለሁኝ። በፍጹም ግነት የለበትም። እንዲያውም ካለዘመናቸው የተፈጠሩ መሪ ያደርጋቸዋል ዶር አብይ አህመድን በሁለገብ፤ በሁለንትና ብቃታቸውም በርህርህና ሰብዕናቸውም። የዬአገሮችን የዘመናችን መሪዎች እኮ እንከታተላለን የ እኛው ቀርቶ ... ይበልጣሉ ... 

ፊታቸው ራሱ የተስፋ ገጽ ነው ያላቸው። እርግጥ ነው አቅማቸው ያስፈራቸው ሰዎች ቀረቤታቸውን አስታከው መንገድ የሚያስቱ ነገሮችን ሊፈጥሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ግን ሊኖር ይገባል። ለምሳሌ ጎንደር ሲሄዱ ከኮ/ ደመቀ ዘውዱ ጋር እንዳይገናኙ የተደረገበት መሰረታዊ አመክንዮ ከዚህ አንጻር ሊታይ ይችላል።

ሌላው የተሰጠውን ዕውቅና ያህል በተመሳሳይ ደረጃ ላሉት እንዳይሆን የሚደረገውም በዚህ መንገድ ነው፤  አኩራፊ እንዲፈጠር ይፈለጋል። ይህ ደግሞ ሰውኛም ነው። ግራ ዘመሙም ስራው ይሄው ነው። መስገለል መካተር በዘመቻ ወዘተ …

ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን ሰብዕናው ንጹሁ የአብይ ሌጋሲ ወጣ ገቡን፤ ኮረኮንቹን አቻችሎና አስማማቶ ይህን አጣጥሞ እዬገሰገሰ ነው። ቀደም ብዬ ያነሳሁዋቸው ሰው ሰራሽ ሳንኮች እንደ ተጠበቁ ሆነው።

መንገዱ አድካሚ ቢሆንም ግን ቀና ስለሆነ ተስፋን ማጨት ያስችላል። ለዚህ ነው እኔ የተጋሁበትም። እሰቦት ከ9 ወራት በፊት የነበረውን ነገር ስታስቡት እኮ ድቅድቅ ጨለማ ነው የነበረው። ኤርትራ ወደ አዲስ አባባ ብታሰብ በአውቶብስ ከሆነ በአፋር ወይ በትግራይ ወይ በወሎ ካልሆነ እንዴት አልፋ አዲስ አባባ ልትደርስ ትችላለች። 

በአውሮፕላን ቢሆንም ማረፊያ ከሌላት እንዴት አዲስ አባባን መሬት መርገጥ ይቻላል። ለሩቅ ህልማችን አማራጭ ስለጠፋ ስይሆን ሙሉ ድንቅ አቅም ስላለው የአብይ መንፈስ ከመቅድሙም መደገፍ መበረታት ይጋባው ነበር። ግን የሳተው ስቶ ሌላው እንዲስተው ደግሞ በወል ተዘምቶበት ነበር። አሁንም ቅቡልነቱን ለማሳሳት የተጀመሩ ነገሮች አያለሁኝ። ይህ ዘመን የተሰጠው ከፈጣሪ ስለመሆነ የመንፈስ አቅም እንሰትም ይመስላል። ስለሆነም ማንም ገድቦ አጨንጉሎ ሊያስቀረው አይችልም። 

ያ ቅናዊ መቅድመ መንገድ „ጣና ኬኛ“ ሊደገፍ፤ ሊበረታታ የሚገባው ከዚህ አንፃር ነበር። ይህ ሁሉ ፍሬ „የጣና ኬኛ“ ምርት ሰብል ነው። ያ „ጣና ኬኛ“ ባክኖ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ በለመድነው እንደ ወትሮው ታቱ በተስፋ ቆራጭነት ቀጣይ ነበር። እበሶ በታንቡር የተሞሉ የተስፋ መንገዶች ጊዜው እዬራቀ በሄደ ቁጥር እርቃናቸውን መቅረታቸው አይቀሬ ነበር። 

ወያኔም አውራ ፓርቲነቱን አያስነካም፤ እኛም እራሳችን እናውቀዋለን፤ በሰላው መንገድ እንኳን ክትር ለማበጀት የማይታክተን ነን እና። ቅን ሰው ፍልስ ብሎ የጠፋበት ጊዜ ነበር እኔ ስመለከት። አሁንም ቢሆን ቅኖች የውነት ቅኖች ጥቂቶች ናቸው። 

ቀን የገነባነው ማታ የምናፈርሰው ከሆነ አሁንም ነገን ማግኘት ይችግረናል። መፍትሄው እራሰን ማጠብ ነው፤ ለዚህ መብቃት በራሱ ተመስገን ሊባልለት፤ ሊከበር፤ ሊደነቅ ይገባል። የተሰጠውን ያከበረ ምርቃቱ ይቀጥልለታል፤ የናቀ፤ ያዋረደ ደግሞ ምርቃቱ ይነሳበታል።
በዚህ ባለፈው ወር እንኳን ያዬነው አይተናል። ያዳመጥነውንም አዳምጠናል። 

ላይ መንበር ላይ የነበረው መንፈስ የተነፈስ ጎማ ሲሆን። ስለምን? ምርቃትን ካለማወቅ የመጣ ሳንክ ነው። በተከበርከው ልክ መሆን የራስ ምርጫ ነው። ያን ከሳትክ ጥፋቱ የአንተ እንጂ የለውጡ ነፍስ አይደለም። ስለዚህ „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳልን“ የጎንደሮችን ብሂል መከተሉ ይበጃል።

ትናትን ስለ ሉላዊቷ የመቻቻል እናት ጠቅሼ፤ ዶከተር አብይ አህመድ ጀርመን ሊጋበዙ ይቻላሉ ብዬ ነበር። ዛሬ ይህን ዜና አዳመጥኩኝ። ክብርት ጠ/ ሚር አንጌላ ሜርክል ጋበዙ፤ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ይሁንታ ሰጡ።

መቼም ሥርጉተ ዘንድሮ ጉደኛ ሁናለች አይደል? የውነት ከሁሉም ነገር በላይ የብርቱዋ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ጠ/ ሚር አንጌላ ሜርክል ግብዣ ለእኔ ከደስታም በላይ ሐሤቴ ነው። ዘርፈ ብዙ ትርጉምም፤ ዘርፈ ብዙ የህሊና ሚስጥር አለውና። ኢህአዴግም እንደ ግንባር እንኳን ደስ አለው፤ አብሶ ለለውጡ ሌት እና ቀን ለሚታታረው የአብይ ካቢኔ ታላቅ የምሥራች ነው። የ ኢትዮጵያ ህዝብም ራሱን በዬሰከንዱ ገብሮበታል ... 

የጀርመን መንግሥት ኢህአዴግ ኢ- ፍትሃዊ እንደ ነበር አሳምረው ያውቁ ነበር፤  የኢህአዴግን ግብዣም አልተቀበሉም ነበር እንኳንስ ጠ/ ሚሩ በክብር ሊጋብዙ ቀርቶ። እና ለውጥ ይሏችኋዋል ይህ ነው … እዛ ውስጥም ላደፈጡም የግንባሩ አባልተኞችም ይህ ተቋማቸው ሊሆን ይገባል።
 https://www.satenaw.com/amharic/archives/22886
"የጀርመኗ ቻንስለር በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ"
ማስታወሻ ለቅኖች - አቅምም ላላቸው። 
  
ጀርመንን ጨምሮ በአቅራቢያ የሚገኙ ኢትዮጵውያንም አቅም ያላቸው ማለቴ ነው ድጋፋቸውን ለመስጠት መሰናዳት ይኖርባቸው ይመስለኛል - ከቻሉ። የጀርመን መንግሥት እናመስግንሃለን ሊባል ይገባል። 

የመጀመሪያዋ የአንድ ሉዑላዊ ሃያላን አገር መሪ ናቸው ዶር ወ/ሮ አንጌላ ሜርክል የኢትዮጵውያኑ ሰልፍ እስከ ካቢናቸው በርሊን ላይ ወጥተው እውቅና የሰጡ፤ አገር ቤትም ሄደው በነበረ ጊዜ ተፎካካሪዎችን ውክል አካላት አነጋግረዋል፤ እስከ መጨረሻው ድርስ ስለ ነጻነት እስረኞቻችን ጉዳይ እዬደወሉ ይከታተሉ ነበር፤ ሲፈቱም ኢትዮጵያ የሚገኘው ኢንባሳያቸው አውቅና ሰጥቷል።

የቆሼ የወል ሃዘንም የጀርመን መንግሥት ቀድሞ ነበር በኢንባሲው ሰንደቁን ዝቅ አድርጎ ያውለበለው። ጀርመን አጀንዳው የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ነበርና። ስለዚህ እናመሰግናለን ማለት ለፈጣሪም መልካም ነገር ነው።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
የኔዎቹ ውዶቼ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።፡  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።