ትውልድ የማይተካቸው ኮ/ ጎሹ ወልዴ ቃላቸውን አተሙ!


ትውልድ ማይተካቸው ኮ/ ጎሹ ወልዴ 
ዛሬ ለኢትዮጵያ ህዝብ ዓለም አቀፋዊ ጥሪ አቀሩቡ። ቃላቸውንም በኢትዮጵያዊነት 
                አተሙ!
ከሥርጉተ ሥላሴ 20.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)

                            "በመከራዬ ሳሉ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሄር ጮኽሁ፤ 
                                                እርሱም ሰማኝ፤"
                                  (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፫)  

ትወልድ የማይተካቸው ኮ/ ጎሹ ውልዴ ዛሬ በውጬ እና በአገር ውስጥ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያወያነ ሁሉ ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሙሉ እግዛ እና ለቀናዊ ጉዟቸው ጥንካሬና ብርታት እንዲሆናቿው ለኢትዮጵውያን በሙሉ ታላቅ ዓለም ዓቀፋዊ ታሪካዊ ጥሪ አስተለላፉ። 

እኒህ ታላቅ ሙሁር እና የፖለቲካ ሊሂቅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ናቸውም ማለት እችላለሁኝ። ከአገር ከወጡ በኋዋላ መድህን የሚባል የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው ካደራጁ በኋዋላ በራሳቸው ፈቃድ ለተተኪ ወጣቶች ያደራጁትን መድህን ፓርቲ ያሰረከቡ የመጀመሪያው የፖለቲካ ሊሂቅ ናቸው።

ውስጣቸው ብቃታቸው ዕንቁ ነው። እኔ በልጅነት ኮ/ አሳፋ ሞሲሳ የሚባሉ ከፍተኛ መኮነን ይሆልታ ግንተ ዋና አሰትዳዳሪ ስለክቡርነታቸው እያስጠኑኝ ነበር ያደኩት። ስለሆነም በውስጤ የበቀሉ የፖለቲካ ሊሂቀ ሊሂቃን ናቸው ማለት እላለሁኝ። እንደ ዕድል ሆኖም ክቡርነታቸውን የተኳቸውን ወጣት ሁልት ረ/ ፕሮፌሰሮችንም በአካል ተገናኝቼ ተወያይቼም ነበር።

ሁልጊዜ ስለ ብቁ የአገር መሪ ሲታሰብ አስባቸዋለሁኝ። በደርግ ዘመን  ዓራት ዓይናማ ቁልፍ አካል ነበሩ። ሳይመቻቸው ሲቀር ወደ አሜሪካ ተሰደዋል። ተሰደው እንኳን ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ የነበራቸው ኤረቲክስ ልዩ ነበር። አክብሮታቸው ጥለውት ለሄዱት መንግሥት እና መሪ እጅግ ያለቀ ነበር።

ዛሬ ድምጻቸውን በመስማቴ ደስ ብሎኛል ከምል ሐሤት አግኝቻለሁኝ። እንግዲህ በፖለቲካ ድርጅት መሪነት ቅናዊ አድናቆት ከሰጡት ከመኢሶን መሪ አባ ቅንዬ ዶር ነገደ ጎበዜ ቀጥሎ የተገኙ ሊሂቅ ናቸው። እርግጥ ነው ከሲቢክስ ድርጅት መሪም ደጉ ዶር፣ ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ ይቀድማል። ዛሬ አብይ ኬኛ እዬለመለመ ነው። ተመስገን!

ቤቴ ሻማ በሻማ ሆኗል። ሁለት ድል ሁለት ጥምር ሐሤተ ማዕልት። ከሰሞናቱ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በተከፉባቸው አገራዊ ጉዳዮች ከልብ አዝኜ ነበር። ዛሬ ደግሞ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂም፤ ኮ/ ጎሹ ወልዴም መልካም የምሥራች ልከውላቸዋል።  
ውዴቼ ቅኖቹ ... የኢትዮጵያ አምላክ የተመሰገነ ይሁን። የቀደመውን ንግግራቸውን አቅማቸውን ታጣጥሙት ዘንድም ለጥፌዋለሁኝ። እኔ አዘውትሬ እንደ ውዳሴ ማርያም የማዳምጠው ስለሆነ።

 በተረፈ … መልካም የመደማመጥ ጊዜ። ተመስገን።
A personal support to PM Abiy Ahmed: Former FM Goshu Wolde - SBS Amharic
Colonel Goshu Wolde Historical Speech to US Congress in 1991
  • ·       ክወና።

የተከበሩ ኮ/ ጎሹ ወልዴ እግዚአብሄር እንኳን ይህን ቸር ወሬ እንዲሰሙ እረዳዎት። መኖረዎት ለ ለእኛም ለኢትዮጵያም ክብራችን ኩራታችን መኖራችን ነው እና ዕደሜዎትን ከፍ ያድርግልን።

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

የኔዎቹ እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።