እኛ ይሆን #የተወሳሰብነው ወይንስ #ኢትዮጵያ? ኢትዮጵያ ይሆን #የተተበተበችው ወይንስ እኛ?

 

እኛ ይሆን #የተወሳሰብነው ወይንስ #ኢትዮጵያ? ኢትዮጵያ ይሆን #የተተበተበችው ወይንስ እኛ?
ምዕራፍ ፲፬ ዛሬ አህዱ ልበለው።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እንዴት ሰነበታችሁ ማህበረ ቅንነት? ደህና ናችሁ ወይ እኛ ይሆን #የተወሳሰብነው ወይንስ #ኢትዮጵያ? ብዙ ሳደምጥ ሰነባበትኩኝ። እኛነታችን በዬትኛውም ፈርጅ ይሁን ማዕዘን ተጥመለመለብኝ ልበል ተፈተለተለብኝ? አለመረዳት? አለመግባት? አለመግባባት? ይሁን አለመፈጣጠር ትብትብ አለብኝ። እኔ ብቻ ይሆን ብዬ ራሴን እጠይቃለሁኝ።
ዛሬም ይጨንቀኛል።
ዛሬም ያሳስበኛል።
ዛሬም ያስለቅሰኛል።
ዛሬም ያሰጋኛል።
ለነገም ይጨንቀኛል።
ነገም ያሳስበኛል።
መዳረሻው ዳርቻው ምን ሊሆን እንደሚችል ነብይ ሽው ይለኛል።
ለምን? ዘመን ይጠዬቃል?
ስለምን? ፖለቲካውም ይጠዬቅ?
እንደምን የፖለቲካው ሹማምንቶች ከጫፍ እስከ ጫፍ ይጠዬቁ። ተጠያቂነት ይጠዬቅ። ኃላፊነትም ይጠዬቅ። እኛም እንጠያዬቅ። ትርፍ እና ኪሳራው የብትልናችንም ይመዘን። የትናንቱ መና ሲሆን የዛሬውስ የት ያደርስ ይሆን? ዝምታ ይሻል መናገር? መናገር ይሻል መራመድ? ወጥተው የቀሩት ልጆች ጉዳይ መጨረሻው የት ይሆን ፌርማታው? ለምን ቁርጥ ያለ ነገር አይገለጽም? ስለምን ተድቦልቡሎ፤ ተጠፍጥፎ ይቀርባል። የዕውነት አምላክ ዕውነቱን አስበራልን እና ቁርጣችን እንወቅ። መተከልም ከሞት የተረፋ ታገቱ ሰማን። ድብዛው ጠፋ። በዬጊዜው በገብሬ ጉሬቻም እገታ አለ። በአማራ ክልልም ወረርሽኙ እንደ መልካም ውርስ ከኦሮምያ ክልል ተቀድቶ የሰርክ ዜና ሆኗል።
ምን ነካን?
ማንስ አስነካን?
እንደምንስ ይዳን?
ከመካሰ ፖለቲካ እንዴት ይወጣ?
ከመበቃቀል ፖለቲካ እንዴት ይዳን?
ከትውልድ መማገድ ፖለቲካ እንደምን ይወጣ?
ምናችን ይሆን የታመምነው?
ከህሊናችን ውስጥ የትኛው ብሎን ወለቀብን?
ይህ የተድቦለቦለ ፖለቲካ ለትውልድ? ለአገር፦ ለአደራ? ለማን ይሆን የሚጠቅመው?
የመጨካከን፦ የመገዳደል ፋክክሩ መቼ ይቆማል? ማንስ ያስቆመዋል?
ትናንት ምሽት የመሬት መራድ ስሜት በብዙ ቦታወች ተከስቷል? ለምን? ስለምን? ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ሊመጡ ከዋዜማው ጀምሮ እዮራዊ ምልክቶች ነበሩ። እነኛ ምልክቶች ልብ ያላቸው ባይኖሩም። እኔ እዬተከታተልኩ እጽፍ ነበር። ማመሳጠር ባልችልም። ወደ ሰውነታችን፤ ወደ ቀልባችን፤ ወደ አደባችን እንመለስ። ሰው መሆናችን ያሸንፈን። ይህ ብቻ የከበደውን የተወሳሰበውን ችግራችን ሊፈታ እንደሚችል ይሰማኛል። የትቢት ክምር እራስን ይንዳል።
---------------
የነገረ ሞጋሳ ፍልሚያ።
Habtamu Tesfaye Gemechu
dpnsStooerd760y1m A59u9taa5f1t 529ih Meisi50t3ht83:mrt0aefYa ·
«ፊ/ማ ብረሃኑ ጁላ እና ጃል ጫላ (ቼኩ ቬራ)፦»
ፊ/ማርሻሉ ትላንት በተላለፈ ቃለመጥይቃቸዉ ላይ የአንድን ታጋይ ስም ጠረተዉ ሰለተጠለፉት የደምቢዶሎ ዩኒቨረሲቲ ሴት ተማሪዎች ሲያወሩ በሰማሁ ግዜ ከአራት አመት በፊት ጦራቸዉ ስሙን በጠሩት ታጋይ ላይ የፈፀመዉን አሰቃቂ ድረጊት አስታዉሼ እጅጉን አዘንኹ ተከዝኹ። አዎ የምሬን አምርሬ ይህን ሰረዓት እና ቅጥፈቶቹን ኮነንኩ ረገምኩት።
ፊልድ ማርሻሉ ጎንደሬዉ ያሉት ጃል ጫላ የዘመናችን ቼኩቬራ ነዉ! አዎ ታሪኩን ሰምታችሁ አረጋግጡ።
ጃል ጫላ በዘንድሮዉ ቋንቋ እናዉራ ካልን ቤተሰቦቹ አማራ ሊሆኑ ይችላሉ። እሱ ግነ ኦ ሮሞነቱን ተቀብሎ የኖረ ነው። ወለጋ ተወልዶ አድጎ የኦሮሞን ህዝብ ሰቆቃ እና መከራን እያየ ኖሯል። በስተመጨረሻም የኦሮሞ ልጆች በ OLA ስር ተደራጅተው በህባቸዉ ላይ ማብቂያ ያሌለዉን ስረዓትን መፋለም ሲጀምሩ ጃል ጫላ እኔን ምናገባኝ ብሎ እጆቹን አጣጥፎ አልተቀመጠም። ይልቁኑ እንደ ቼኩቬራ ሁሉ ከግፉዓን ጋር መሰለፍን መርጦ የኦሮሞ ታጋዮችን ተቀላቀለ። በቃ እንደ አንዱ የኦሮሞ ጨቁን ልጅ ለኦሮሞ ህዝብ አንድያ ነፍሱን እየተፋለመ መስዋዕት ለማድረግ ነፍጥ አንስቶ ግንባር ተሰለፈ። ይህ ነዉ ነዉ ቼኩቬራ ያስባለኝ። ቼኩስ ከፊደል ካስተሮ ጋር ተሰልፎ ከዚህ ጀብዱ የተለየ ኖሯልን?
ይህን በማድረጉ ግን አሰቃቂ ድረጊት በአዛዉንቶቹ ወላጆቹ ላይ ተፈፀመ። ሰኔ 5/2020 ምሽት ለጫላ ወላጅ ቤተሰቦች የመጨረሻ ምሽት ነበረች። የ75 እና 80 አመት እድሜ ባለፀጋዎቹ አቶ አሻግሬ ገበየሁ እና ወ/ሮ ፋንታዬ ዳኘ በቄለም ወለጋ አንፊሎ ወረዳ ሙጊ ከተማ ላይ ልጃችሁ የኦሮሞ ታጋዮችን ተቀላቀለ በማለት በቤታቸዉ ደጃፍ ላይ በጥይት እሩምታ አንድ ላይ ረ~ሸ~ኗቸዉ። ገድለዉም አልረኩም አስክሬናቸዉ እንዳይነሳ በማድረግ ሰዉን እየተከላከሉ አረስክሬናቸዉ በተገደሉበት ዉሎ እንዲያድር ተደርጎ በማግስቱ በልመና እና በሽማግልዎች አማላጅነት ነዉ አስክሬናቸዉ ተነስተዉ የተቀበሩት።
ይሄን ታሪክ ነዉ ዛሬ ኢታማዦር ሹሙ ያስታወሱኝ። በርግጥ እሳቸዉ የሚያሳስባቸዉ የአማራ ተወላጁ ጃል ጫላ ከኦሮሞ ታጋዮች ጋር መሰለፉ እንጂ ሰራዊታቸዉ በቄያቸዉ ስለገደሏቸዉ የጫላ ቤተሰቦች አይደለም። አንድ እድሜዉ ለአቅመ አዳም ደረሶ የራሱን የህይዎት መክሊት ስለተከለዉ ጫላ ምንም ሀላፊነት ያሌላቸዉ አድሜ የተጫጫናቸዉ ቤተሰቦቹ ለቁብ የሚበቃ ትዝታም ሆነ በማምሻቸዉ ዘመናት ህይዎታቸዉን በጥይታቸዉ የነጠቋቸዉ ሁለቱ ለፊልድ ማርሻሉ ቁስ ናቸዉ።
እያንዳንዱን ግድያ በዚህ ሁኔታ የሚፈፅምን ሰራዊት እየመሩ ነዉ እንግዲህ ዛሬ እሳቸዉ ንፁኅ ሆነዉ ጎንደሬዉ ጫላ የሸኔ አመራር ለማለት የበቁት። ክቡርነቶ ሆይ እኚህ በሀገሪቱ ጠብ-አንጃ አንስቶ የሚዋጋዎትን ተፋላሚዎች እኮ የፈጠረዉ እንዲህ አይነቱ አሰቃቂ አና አሰዛኙ የርሶ ሰራዊት ድርጊት ነዉ። አናም ሀያሉ ፊልድ ማርሻል ሆይ እረሶ የሰዉን ቤተሰብ እያስፈጁ እንዴት ታጋዮችን ለማሸነፍ የሚጥሩት እና እራሶትን እንደ አዳኝ የሚቆጥሩት?
የዛን ግዜ የሰራነዉ የጃል ጫላ ቤተሰቦች እልቂት ታሪክ ከስር ተያይዟል።»
Lualawi «ሉዓላዊ-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሉዓኣላዊ ሚዲያ ጋር ክፍል 2»
@highlight
 

https://www.youtube.com/watch?v=BJnpxYoLsTI

«ፊ/ማርሻሉ እና እስክንድር ተገናኙ? | ፕሬዝዳንቷ የታዬ ደንደአ ዕጣ ሊገጥማቸው? | የመቀሌው መፈንቅለ መንግሥት የፈጠረው ትርምስ | Ethiopia»

 

 
ውዶቼ ቸር አስበን ቸር እንሁን።
ቅን አስበን ቀና እንሁን።
ህዝባችን እና አገራችን የፈጠራቸው አምላክ ይጠብቅ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/10/2024

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።