ልጥፎች

የጭራቆች ቤርሙዳ ባለ ሰው ሙዳ .../የፊዳላት ውበት/

ምስል
የጭራቆች ቤርሙዳ ባለ ሰው ሙዳ። ከሥርጉተ©ሥላሴ  Sergure©Selassie 10.01.2019 ከእመ ዝምታ „የድሆች ምክር አስፈራችሁ፤ አግዚአብሄር ግን ተስፋቸው ነው። መዝሙር ፲፫ ቁጥር ፱“ የገማና ገዳዳ ሲዘረገፍ ባዳ ሲተረተር ገድጋዳ ሲሸበሸብ ዘንጋዳ ሲሳጣ ጎረድራዳ ሲታጠፍ ከርዳዳ ቁርንጢጥ በ ርጋዳ የተራራ ጎርዳዳ የጭካኔ ሙዳ አይተርጉሙት ጋዳ የጭራቆች ቤርሙዳ። ·        ተ ጣፈ 19.01.2019 ቪንቲ- ዙሪክ// 08.23 ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።  እንኳን ደህና መጡልኝ።  የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

የደብርዬ¡ ምሾ ይሁን፤ የአስተዛዛኞች ዓላማ እና ግብ ግን አልገብቶም!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዝብር ቅር ቅ። „አቤቱ እጅህ ከፍ ከፍ አለች፤ አላዩምም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላላች“  ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፮ ቁጥር ፲፩  ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 15.01.2019 ከእመ ብዙሃን። ·        ማ ሟሻ … ውዶች ክብሮቼ እነ ናፍቆት የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ? ደህን ናችሁ ወይ? ውይ ዛሬ ፏ ፍንተው ብሏለኝ አዬሩ፤ እትጌ ልዕልተይ ጠሐይ መጥታ ትፍነሸነሻለች - ታፍነሸንሻለች፤ ለነገሩ የዚህ ዓመት ክረምት ቀለል ያለ ነው። ምን ትፈሪያለሽ ብባል ክረምትን ነው የምላችሁ፤ አገር ቤት እያለሁ አብሶ አዲስ አባባ ኗሪ በነበርኩበት ጊዜ ክረምት እህቶቼ በፈረቃ ይመጡልኝ ነበር፤ ሆዴ ርብሽብሽ ነው የሚለው፤ በተለይ ነጎድጓድ አልወድም። በዬአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ እንዲህ የያዝነው ዘመን ዓይነት ሲመጣ ደግሞ ሳንክ አይጠፋም። ብቻ ጠሐይ ካለች ተስፋ ነው። ተስፋ ደግሞ ያጀግናል። ·          ተዚህ ላይ ዕለቱንስ አብረን ብናዘክር። ዛሬ ጥር ሥላሴ ነው። የጎንደሪት የልጅነት ጊዜ ታወሰኝ፤ የዋሾ ሜዳ፤ የማርገጃው ወይራ…  ዓይኔ ዕንባ አቀረረ። አያቶቼ ነዳይን ፍሪዳ አርዳው በቁርጥ የገና ጾምን እንዲፈቱ የሚያደርጉበት ዕለት ነበር ዛሬ - ትውፊቱ እንደዛ ነበር። ሸንበቆው ተሰንጥቆ፤ እንደ ካራ ይዘጋጃል፤ ጤፍ እንጀራው ዘንጠፍ ብሎ ታጥፎ በአዋዜ ቁርጥ ለሚፈልግ ቁርጥ፤ ጥብስ ለሚፈልግ ጥብስ አደግድገው መላከብርሃናቱ አያቴ እና ታናሽ ወንድማቸውም መላከብርሃን ነው አሱም እንግዶቻቸውን ነዳያን ያስተናግዳሉ፤ እህታማቾች ደግሞ ለቅዳሴ የመጣውን ቤት ለእንግዳ በማለት ደስ ብሏቸው ያሰተናግዳ

የአካዳሚ ነፃነት የትውልድ አውንታዊ ብቅል ነው!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  መ ሠ ረት። „የፃድቃን መንገድ ቅን ናት፤ አንተ ቅን የሆንህ የፃድቅናንን መንገድ ታቃናለህ።“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ© ሥላሴ Seregute©Selassie 14.01.2019 ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ። ·        እ ፍታ። እንዴት አመሻችሁ ውዶቼ ደህና ናችሁ ወይ? ይህቺ እንደነፍሴ የምወዳት አገር እምዝምታ ሲዊዝሻ ጸጥታውን እዬመገበችኝ ነፍሴን ታፍነሽንሸኛለች። እኔ ግርግር ጩኽት - ሁካታ-  የአገር ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አልፈቅደውም /ሰላማዊ ስልፉ/። ድምጽ የባዘበት ቦታ ይጨንቀኛል። አንድም ከቤቴ ድምጹ ከፍ ብሎ የሚሰማ ነገር የለም። እቃ ሲታጠብ በጸጥታ፤ በር ሲከፈትም ሲዘጋም በዝግታ ነው። ራሱ ጎረቤቶቼ ስለመኖሬ ወይንም ስላለመኖሬ የሚያውቁት ምንም ነገር የለም። ጸጥ ረጭ። እናላችሁ ሲዊዚሻን ሳስባት ለእኔ ተብላ የተፈጠረች ይመስለኛል። አብሶ እኔ ያለሁበት ቪኒቲ። ቪንቲ የቁልምጥ ስሙ ነው። ከዚህ ከተማ የተፈጠሩትም የገጠሙኝ ሁሉ ቤተሰብዐው ስብዕና ያላቸው ናቸው። ይህችን እንደ ወግ ቢጤ ካደርኩኝ ስለዛሬው ቁም ነገር ልንገራችሁ … ትውልድ። ·        ትውልድ። ትንተና የለውም እንዲሁ በመደዴው ስሄድበት ግን ትውልድ በመኖር ውስጥ ያለ የአገር መኖር ማለት ነው። አገር ለማኖር ደግሞ የትውልድ መኖር ብቻውን በቂ ነው ሲባል ጥማድ በሬ ገዝቶ ማሳ የሌለው ገበሬ ይሆናል። እና የትውልዱ መኖር መበራከት ብቻውን አገርን የማስቀጥል አቅም ሊኖረው አይችለም። ማሳው በበጎ በፈቃደኝነት፤ በባለቤትንት፤ በታማኝነት፤ በምክንያታዊነት መታነጽ ካልቻለ። ለዚህ ደግሞ አራት ተቋማት ወሳኝ ናቸው።   አንደኛው ቤተሰብ ወላጆች ወይንም