ማህበረ ትሬኮላታ-በክህሎት ተረታ // የፊደል ወለባ/

ማህበረ ትሬኮላታ - በክህሎት ተረታ!
„አቤቱ በአንተ ታምኛለሁ እና ጠብቀኝ።“
 መዝሙር ፲፭ ቁጥር፩

ከሥርጉተ©ሥላሴ
 Sergure©Selassie
10.01.2019

ከእመ ዝምታእንኳን ደህና መጡልኝ።



ጋርድ ተሰልፎ በትሬኮላታ
የአጋም ቀጋ ቱመታ
የእንኮሸሸሌ ሻጋታ
የጨጎጎት እሩምታ
የምላስ ሰልፍ ብርጌድ ጋጋታ፤
የባሩድ ወግ በበቃህ - ሊረታ
በምላስ ወለምታ ሲምታታ
ዘመን በሲዖል ማህበር ሲመታ፤
የሰው ብርንዶ በሰልፍ - በፈረቃ - በተርታታ - በትርታ
የባለሳምንቱ የዋይታ እዬዬ ሊደራ ተሰልፎ ሁካታ
የሴራ ሰናይ ትርትር በውሽክታ አመሉን ሊያደርሰ - ፈገግታ
አለለቀም አሉ ገረፍታ
ደመካሴ ቆምሶ ትጥቅ ካላስፈታ?

አይሽርም ደም ካላዬ የከንቱ ኩርፍታ!
የጤዛ ክምር ጉባኤ እንደዋዛ እንዲህ ሲፈታ
የቅርሻ ኮረፌ ግምል የማታማታ
!እንዲህ እንደዋዛ ወይ ጉድድድ - ተረታ?!

የትውልድ ብክንት ሲሰክን በክህሎት ዕድምታ
የማቄን ጨርቄን ሰርግና መልስ ግርታ
አለሁ ቢልም በየለም ሲሾልክ ሲነፍስበት በቁዘማ ወይ ጉድ!- ተፈታ!

እንኮይ የእርግባን ኩልልልልልልልልልልልልልልልልልታ፤
የብዙኃን ሐሤት የተስፋ ግራቢቲ መቅዲል - እርካታ
የጨለማ ህልም በበቃችሁ በፍትኃት እንዲህ - ሲፈታ
ብሩክ በአስተርዮ በሥርዬት በተደሞ -ተደሰታ
የልቅና ክዋክብት ፍካት በእዮር ሆነለት እልልልልልልልልልልታ!

ተጣፈ 19.01.2019 ቪንቲ - ዙርክ// 09.0008.44/
ኢትዮጵያነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

የኔዎቹ ኑሩልን።
ማለፊያ ጊዜ!


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።