ዘመን ራሱን ሲጽፈው / የፊደል ጽጌረዳ/
እንኳን ደህና መጡልኝ።
ዘመን ራሱን ሲጽፈው።
„ከቁጣው ጢስ ወጣ ከፊቱም የሚባላ እሳት ነደደ።“
ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergure©Selassie
10.01.2019
ከእመ ዝምታ
ዘመን ጸሐፊ ሆኖ
የአሳር ክምር- የዕለት ስንቅ እና ትጥቅ ሆኖ በጎታ ጎታ ሆኖ -መኖ
ዘመን ራሱን ሆኖ ---- ሊተርጉም ሊያስተረጉም
ሊያመሳጥር ሊያስመሰጥር
ሸርን - በግሬደር በዶዘር
ሊመነጥር በመክሊት ያለ ቀንበር
ተነስቷል ዘመን ድርሳኑን ሊያከበር - ሊያስከበር።
አምና ይህን ጊዜ ወሎ ላይ /// ራድ ዕንባ በራዳር ሲከመር
ቅዱስ ሚኬኤል በአደባባይ በሰው ሰራሹ ባለክንፍ ሲደበደብ
የእዮር ቁጣ ሲንር ሲንር ዕንባ ሲከንፍ ሲበር
ሲበረብር ሲበረብር የአስተርዮ እምታ ሲነባበር
ዘመን ሆይ! ራሱን እንዲህ ፃፈ … ሲቃው፤ እንባው አዬተናነቀው…
ትናንት እንደለፈ ዓዋጅ አሰነገረ አቤቱ! እያለ ሰዬመው ብሎ አለፈ
እልፍ ሲሉ እልፍ እንሆ በብርቱ ብርታት -ተገኜ
የአብይ ሱባኤ አሜንን ተናኜ - እንደተመኜ።
የማያልፍ የለም አለፈ በአለፈ እንሆ - ተዘከረ
ግንስ ግንስ ተራራዎች ተከማማረው
ተመካክረው ተማምለው …
ጉምን አወያይተው /// ከዛው የሙጥኝ ብለው ተደማምረው
በመቀንስ - ተቀንሰው በማባዛት ተረትተው
በምሾ ቤተኝነት ተደውረው - ተሳክረው
በላቀለት በፉርሽኛ - ሻኛዊ ህልም በልቀው
በመታበይ ተትንፍሰው - ተተርትረው ሊፈነዱ ተቦጫጭቀው፤
ድንኳን ጥለው ደመር ቀጥረው፤
ተቀጣጥረው ተቆጣጥረው ተፈተልትለው፤
አሉ እንዳሉ ኩሬ ሆነው።
ይህን ነው ዘመን የፃፈው
በኪሳራ ተገርብበው
ተከዝነው መከዘንን ዘግነው።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
ተጣፈ 19.01.2019 ቪንቲ - ዙሪክ // 09.30
መስል ከዲያቆን ዳንኤል ዕይታ ጹሑፍ የተወሰደ።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ