ልጥፎች

የኦሮሞ የተዋህዶ ልጆች የፈተና መባቻ።

ምስል
ልባዊነት። „አቤቱ ለምን ርቀህ ቆምህ?“ መዝሙር ፲ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 09.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ቋንቋ ጥበብ ነው። ቋንቋ እውቀት ነው። ቋንቋ ስልጣኔ ነው። ቋንቋ እድገት ነው። ቋንቋ ልሳን ነው። ቋንቋ ሙያ ነው። ቋንቋ ፍልስፍና ነው። ቋንቋን በሚመለከት ያለኝን እይታ በዚህ ፁሑፌ ማገናዘብ ይቻላል። https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_6.html ቋንቋ ሊቀ ሊቃውንትነት እን ጂ መወቀሻ ሊሆን አይገባም። ከአምስቱ የኦሮሞ ድርጅቶ የመብረቅ ወሳኔያዊ መግለጫ ማንፌሰቶ ወዲህ አማራ ግዕዝን በሁተኛ ቋንቋነት እንዲያጠና ዘመቻ መጀመሬ ይታወሳል። አሁን ዛሬ ከትኩስ መረጃ ዩቱብ አንድ መረጃ አገኘሁኝ። እኔ ግዕዝን የአማራ ህዝብ ማጥናት አለበት ያልኩት ለእኔ ለራሴ የትንቢት ያህል ነው የዛሬን መረጃ ሳገኝ የተሰማኝ። በወለጋ ብጹዕና አባቶቻችን መሰደዳቸው ብቻ ሳይሆን በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የያሬድ ዜማዊ ቅኝትም፤ በግዕዝ ቅዳሴም እንዲቆም መደረጉን አዳመጥኩኝ። ዝርዝርዝሩን እናንተው ሂዱበት ከሥር ሊንኩን እለጥፋለሁኝ። ዋና ቁም ነገር ግን ዛሬ የተፈቀደው የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የግዕዝ እግዳ ነገ ሃይማኖቱም እንዳይቀጥል የመጀመሪያው የክፉ ቀን ደወል ነው። የግራኝ ዋዜማ። የዳውዳውያን እና የጃውርውያን ፍልስፍና ይሄው ነው። „ቀስ እያለ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል“ የሚበለውን ልብ ትሉ ዘንድ በአክብሮት እግልጻለሁኝ። አሁንም ቅድምም ከኦነጋውያን ጋር ያለው ድርድር ትውፊታችን ላይ የተቃጣ፤ ማተባችን ላይ የተቃጣ፤ በአብሮነታችን የተሳለ ሰይፍ ሊያመጣ ስለመቻሉ የህሊና ዝግጁነት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ቅኖቹ ዶር ለማ መገርሳ

እሳት በሀረርጌ ከሰማይ እዬዘነበ ነው። እግዚኦ!

ምስል
ጸሎት! „እግዚአብሄር ቁጣውን አይምልስም፤ ከእርሱ በታች ረዓብ የሚረዱ ይዋረዳሉ። „ መጽሐፈ እዮብ ፱፲ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ  09.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እም! የዘንድሮው ደግሞ የጉድ ነው። ክፋታችን በዛ። መቀሌ አካባቢ የተነሳው የመሬት መናጥ መጋቢት እኩሌታ ላይ ነበር። ሴረኞቹ የህውሃት ማህበርተኞች የጥገና ለውጡን ዕቃባ ለማድረግ ሌት እና ቀን በሚተጉበት ሁኔታ። ከዛ ቀጥሎ በጉራጌ ዞን ተዉ አትበጥበጡ፤ አትወኩ፤ ይህን ምርቃት አትጋፉት  ሲል ያልተለመዱ የሰማይ ሦስት ቁጣዎች በአንድ ላይ ታድማዋል ። ታይቶ የማይታወቅ ዶፍ፤ ተሰምቶ የማይታወቅ የእዮር ደምጽ ተከስቶ የማያዋቅ የመሬት መገመስ። አንጅባራ ላይ ደግሞ ለማስታረቅ ይመስላል የምህረት እዬራዊ ታምር ታይቷል። ብሄራዊ ሰንድቅዓለማችን እዬተንቀሳቀሰ በራሱ ጊዜ ከፍ ብሎ ሰማይ ላይ ታይቷል። በቅርብ ጊዜም በዛው በደቡብ ሌላ ቤቶችን ከሁለት የተረተተረ ማዕት ተክስቷል። ከሰሞኑ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና ኦነጋውያን፤ ሆኑ ጃዋርውያን ይሹት የነበረው የሱማሌ ትርምስ መጨረሻውን የተወራረደው አብዬተ ቤተ ክርስት- ያነናትን በማቃጠል፤ ሰማዕታትን በመውገር እና በመግደል ነበር። አሁን እዬሆነ ያለው ቁጥ ደግሞ ፕላኔታችን አስተናግዳው በማታውቀው ሁኔታ ነው። ብፁዕን ቅዱሳን አባቶቻችን 4ኛው ፓትርያረከ ዘኢትዮጵያ አቡነ መርቀሪዮስ  ወደ መንበራቸው ፈቅደው ከስደት በተመለሱ ማግስት የሆነው የቤተ መቅደስ ድፈረት የዓለም አብያተ ቤተክርስትንያትን ሁሉ ያሳዘነው፤ ያ ድፈርት አሁን ከሰማይ እሳቱን እያዘነበው ነው። ለሃጣን የመጣ ለጻድቃን ሆኖ ነዋሪዎች  አሁንም ቁመው እያዬዩ ከሰማይ በሚወርድ ነበልባል ኑሯቸው

ጎንደር እንደ አባት አዳሩ ዓዋጅ አሰነገረ።

ምስል
ጎንደር እንደ አባት አዳሩ ዓዋጅ አሰነገረ። „ሰማያት የእግዚአብሄርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።“ መዝሙር ፲፰ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  09.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ከሰላም ሚኒስተር ምስረታ ማግሥት ጎንደር ላይ የሰላም መንፈስ መናህሪያ አህዱ ሆኗል። እናም ሥርጉትሻ ደስ ብሏታል። ከእንግዲህ በኋዋላ ጦርነትን አክ እንትፍ ብለን ልንጸዬፈው ይገባል። ጦርነት የሚስገኘው ትርፍ ቢኖር አመድ እና በቀል ብቻ ነው።  ጦርነት የትውልድ ብክነት ነው የሚያመጣው። ጎንደር ለ50 ዓመት ሙሉ በጦርነት መማቀቋ ልጅ ማውጣት አለመቻሏን ልብ ልትለው ይገባታል። ልጇቿ በህይወት ያሉትም ስደት ቅርምጥ አድርጎ ብልቷቸው ውጧቸው ቀርተዋል። ብቅ ሲሉ ደግሞ ኩርኩም ነው በዬ አቅጣጫው። መከራው ውሃ ያዘለ ተራራ ነው ልበላችሁ እኔም ስላለሁበት።  የጎንደር ልጅ ቤተስ መረዳት ዋንኛ ፕሮጀክቱ ስለሆነ በጦርነት የተጎሳቀሉ ቤተሰቦችን ለመርዳት በሚያደረገው ግብግብ ወጣትነቱን፤ ክህሎቱን፤ ህይውቱን መክሊቱን ሁለመናውን ሲያባክን ኖሯል። ከእንግዲህ ጎንደር ማንኛውንም አመጽያንን ላለማስጠጋት መቁረጥ እና መውስን ይኖርበታል። መንገድ መሪነቱንም ማቆም ይኖርበታል - ጎንደር። የተጠቀመው አንዳችም ነገር የለም። ቀን አውጥቶ ሁሉንም ለወግ ለማዕረግ አብቅቶ እናምሰግንህአለን ተብሎ እንኳን አይታወቅም። ሁልጊዜ ለአጃቢነት ከመታጨት ውጪ ጎንደር ልጆቹን ከብክቦ እልቆ ለማውጣት የማይፈለግ ስለመሆኑ ከሥርጉተ ሥላሴ በላይ ሌላ ምስክር ሊመጣለት አይችልም ለጎንደር። ጎንደር ልብ ሊገዛ ይገባዋል። ጎንደር በማስተዋል ሆኖ የለውጥ አካልነቱን ሙሉ ልቡን ሰጥቶ ሊዋህደው ይገባል። ጥገናዊ  ለውጡ ለጎንደር ቢጠቅመው

ተፈጥሯዊ አቀባበል።

ምስል
      ተፈጥሯዊ             አቀባበል። „አንተ ፊቴን እሹት ባልክ ጊዜ  አቤቱ ፊትህን እሻለሁ፤ ልቤ አንተን አለ።“  መዝሙር ፳፮ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ © ሥላሴ  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 08.11.2018 ·     መነሻዬ። https://www.youtube.com/watch?v=N01J5vKDPbQ Ethiopia: የፈረንሳይ ወጣቶች “ ንግስታቸዉን ” ብርቱካን ሚደቅሳ በደመቀ ሁኔታ ተቀብለዋታል !! ዛሬ ክብርት ዳኝ ብርቱካን ሜዲቅሳ ኢትዮጵያ ገብታለች። የመንግሥት አቀባልን ፎተውን አይቸዋለሁኝ። እኔ የመሰጠኝ ግን የወጣቶቹ ልዩ የቀይ ምንጣፍ አቀባበል ስለሆነ ትንሽ ልልት ወደደኩኝ። ባጋጣሚው አንዳፍታንም ላመስግን ለቅንብሩ ጥራት ሙሉውን ተከታትዬዋለሁኝ። ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ውስጧን አቅሟን ጥረቷን በቅንነት ለማበርከት አገር እንደገባች አምናለሁኝ። እያንዳንዱ እንቅስቃሴዋ የጥጋናዊ ለወጡን በመደገፍ፤ በማገዝ፤ በማበረታት ጥንካሬ በመስጠት ላይ እንደምትተጋም አስባለሁኝ አምናለሁኝ።  ለረጅም ጊዜ በአካል እንዲህ ልናያት ባለመፈቅዷ ብከፋባትም ዛሬ ሳያት ግን ሰውነቷም መንፈሷም ሙሉ መሆኑን ለመመልከት ችያለሁኝ። የሆነ ሆኖ ዛሬ በነበረው የጀግኖቹ የፈንሳይ ለጋሲዮን ኢትዮጵያዊ አንበሶች የአቀባባል ዝግጅት ላይ ቁምነገሩ ተፈጠሯዊ መሆኑ ነው ቀልቤን ስቦት ብዕሬን እንዳነሳ ያደረገኝ።  በነገራችን ላይ በድምጽ እማውቃቸውን ወላጅ እናቷን መኪና ውስጥ ወ/ሮ አልማዝን በጨረፍታ ለማዬት በመቻሌ እንኳን ለዚህ አበቃቸው ማለትን እሻለሁኝ። የኢትዮጵያ እናቶች እንዲህ ዓይነት ልጅ ሲወልዱ ፈተናውም የእነሱ ነውና። እሷንም እንኳን ለአገርሽ መሬት በሰላም አበቃሽ ማለትን እፈቅዳለ

ኃላፊነት የሁሉም ኃላፊነት ነው።

ምስል
ኃላፊነት የሁሉም ኃላፊነት ነው። "የአምላክ ልጆች ሆይ ለእግዚአብሄር አምጡ፤ ክብርና ምስጋናን ለ እግዚአብሄር አምጡ።" መዝሙር ፳፰ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  08.11.2018  ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? አቅምን፤ ብልህነትን፤ ታማኝነትን፤ መልካም ነገርን ማዋጣት ማግስትን ያሳምራል። ባለፈው ዓመት ይህ የጥገናዊ ለውጥ አዬር መደገፍ አስፈለጊነት አስመልክቶ ብዙ ነገሮችን ብያለሁኝ። መልካሞቹ ሰዎች ጥረትን አህዱ ሲሉ የተጋሁበት ምክንያት ሁሉም የአቅሙን ማድረግ ከቻለ ዛሬን ማግኘት ስለሚቻል፤ ዛሬን ማግኘት ከተቻለ ነገ እና ከዚያም ወዲያን ማግኘት ስለሚቻል ነበር። እኔ ዛሬ ማንሳት የፈልግኩት ስለ ኃላፊነት ጽንሰ ሃሳብ ትንተና ልሰጥ አይደለም። ግን ነገር ግን ኃላፊነትን ወደ ሌላ ከማሻገር በፊት እራስ ላይ ያለውን ኃላፊነት በቅድሚያ መወጣት ይገባል ለማለት ነው። ሁሉንም ነገር መንግሥት ሊከውን አይችልም። በሰለጠነው አገርም ብዙውን ሃላፊነት የሚሸከመው ህዝብ፤ የሃይማኖት ተቋማት እና የሲቢክስ ድርጅቶች ናቸው። ኢትዮጵያ ላይ ለዛውም የ50 ዓመት ቁልል ችግር አልበቃ ብሎ በተደራጁ ሃይሎችም የተሰሩ ሰው ሰራሽ ችግሮችም አሉበት። የሆነ ሆኖ ችግርን በማውራት ችግር አይቃለልም። የሰው ልጅ የአኔ ኃላፊነት ይህ ነው ብሎ መቀበል መቻል አለበት። ግዴታን እዬተወጡ መብትን መጠዬቅ ልንከተለው የሚጋባ መርህም ነው። ጥገናዊ ለወጡን መተቸት እችላለሁ ግዴታዬን ግን አልወጣም ማለት ሥርዓለበኝት ነው። ካለ ግዴታ መብት ካለመብት ግዴታ ኑረውም አያውቁም።  ለምሳሌ ልጆችን በሞራላዊ ዕሴት ማነጽ የወላጆች ንጥር ግዴታ ነው። ልጆች የሰውን ልጅ እንዲያከብሩ፤ እንዲያፈቅሩ፤ እ