አርቲስቱ አንጋፋው ዬጥበብ ቤተኛ ዶር አሊ ቢራህ በሥጋ ተለዩ። ወደ ዘላለማዊ ማረፊያቸው ተጠሩ።

 

አርቲስቱ አንጋፋው ዬጥበብ ቤተኛ ዶር አሊ ቢራህ በሥጋ ተለዩ። ወደ ዘላለማዊ ማረፊያቸው ተጠሩ። 

 
በሰፊ ሟርት ዘወትር ህልፈታቸው ሲታወጅ የባጀው ዶር አሊ ቢራ የመጨረሻው የስንብት ዜናቸው ትናንት ማምሻ ላይ በተለያዬ ሚዲያወች ተዘግቧል።
ዶር አሊ ቢራ በትውልዳቸው ፊሊፒን በዜግነታቸው ካናዳዊ የትዳር አጋራቸው ጋር በመሆን በትምህርት እና በህፃናት የትምህርት መሰናዶ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሳተፋ መቆዬታቸው የህይወት ታሪካቸው ይገልፃል። ይህም በትውልድ ባዕት እና በሮቤ ስለመሆኑ የህይወት ታሪካቸው ይገልፃል።
ዶር አሊ ቢራ በ1940 እኤአ በፍቅር ከተማዋ በድሬ ነበር የተወለዱት። ገና በታዳጊ ወጣትነታቸው ለቤተሰቦቻቸው እና ለጓደኞቻቸው በማንጎራጎር ወደ ጥበብ ቤተኝነት የዘለቁት አባ ወራ ሙዚቀኛ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው አንጋፋ ስለመሆናቸው ከ267 በላይ የሙዚቃ ምርት ባለቤትነታቸውን ያስገነዝባል። ከ40
አርቲስት አሊ ቢራ በሱማልኛ፣ በአፋርኛ፣ በሐረሬ፣ በአረብኛ፣ በአማርኛ ቋንቋወች በርካታ ሥራወችን የሠሩ ሲሆን ለአፋን ኦሮሞ እድገት እና መፋፋት ልዩ አስተዋፆ አድርገዋል።
አርቲስት ዶር አሊ ቢራህ በደርግ ዘመን ተሰደው በ97 ወደ አገራቸው ተመልስዋል። ለዚህ ይመስላል እራሳቸውን ሲገልፁ እኔ "የሃቅ ታጋይ ነኝ" ሲሉ በአንድ ወቅ የተደመጡት።
በትግል ተሳትፏቸው ዘመን ላቀነቀኗቸው አታጋይ ሙዚቃወች በአንድ ወቅት ፀፀት እንዳለባቸው ሲጠዬቁም አይፀፅተኝም ብለዋል። የሃቅ ታጋይነታቸው በዘመነ ህወሃትም ከፍተኛ ጫና እና እገታ ተጥሎባቸው ዬነበረ ሲሆን ዘመን ተቀይሮ የሬቻ ዬመጀመሪያው የሰላም ሽልማት ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል።
ጋሼ አሊ በድሬ ፓርክ ተሰይሞላቸዋል፣ በናዝሬት መንገድ ተሰይሞላቸዋል፣ በድሬ እና በጅማ ዩንቨርስቲወች የክብር ዶክተሬት ተሰጥተዋል፣ በኦሮምያ ልዩ ዬኒሻን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፣ በካናዳ ከፍተኛ አዋርድ አግኝተዋል።
አሻራቸው የትውልድ ስለሆነም ሞቱ ሳይሆን ከድካ አረፋ። በሥጋ ተለዩ የሚለው ቃል ይገልፃቸዋል። ገጣሚ እና ሙዚቃ አዋህጅ የነበሩት በ40 ከተሞች ታላላቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ላይ በመገኜት ለታዳሚወቻቸው የልብ አድርስ ተግባር ከውነዋል።
አርቲስት ዶር አሊ ቢራ ዘመናቸውን ያላባከኑ፣ በጥሪያቸው ውስጥ ከትመው የኖሩ፣ ለጥሪያቸው ዕውቅና ሰጥተው ጥሪያቸውን አክብረው ያስከበሩ ትጉህ፣ ታታሪ እና ባለ ቃና ዋርካ ነበሩ።
በዶክተር አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በእረፍት መለዬትን አስመልክት ኢትዮጵያ እንደምታመሰግናቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሃዘናቸውን ገልፀዋል።
ዶር አሊ ቢራ ታመው ሳለም በሆስፒታል ተገኝተው መጠዬቃቸው ይታወሳል። ዶር አብይ አህመድ ለጋሼ አሊ የቀረበ ስሜት እንደነበራቸው ያደረጉት ክትትል እና አትኩሮት ይገልፃል።
ዬማይቀርበት ወደ ሆነው ዘላለማዊ ቤታቸው ለሄዱት ዶር አሊ ቢራ ነፍሰወትን በአፀደ ገነት ፈጣሪ፣ አላህ ያኑር፣ ለመላ ቤተሰቦቸወት፣ ለአድናቂወችወት፣ እና ለወዳጅ ዘመዶቸወትም መጽናናትን እመኛለሁ።
የክብር እረፍት ለባለ አሻራ ጌጥም፣ መታደልም ነው። ይህን ያላገኙ እንደ ባከኑ፣ እንደ ባተሉ የሚለዩንም አሉና።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/11/2022

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።