ኢትዮጵያዊነት አያረጅም! ስለዚህም እድሳት አያስፈልገውም።




እንኳን ደህና መጡልኝ።

„ዕውቀትን ለማን ያስተምረዋል? 
ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? 
ወይስ ጡት ለጣሉ ነውን? ትእዛዝ
በትእዛዝ ሥርዓት በሥርዓት ሥርዓት በሥርዓት፤
ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ“

ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፰ ቁጥር ፱ -፲

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከእማ - ሲዊዘርላንድ
11.01.2019


"ኢትዮጵያዊነት መታደስ አለበት ኢትዮጵያዊነት እንደገና መሠራት አለበት አዲሲቷ ኢትዮጵያን እንግነባ" የሚሉ ድምጽች ይሰማሉ። መልካም ነው። ከሆነ። ይህ ማለት ኢትዮጵያዊነትን መጠገን በሚለው በአዎንታዊነት የሚታይ ሲሆን በሌላው ዕድምታ ግን አሉታዊ ነው። መታደስ፤ በአውነታዊነት መገንባት ያለበት የእኛው አንጎል ነው። 

አሉታዊነቱን እንዲህ ልግለጠው … ኢትዮጵያዊነት በእኔ ውስጥ ያለው አርጅቶ አያውቅምና። መወደሱም ራሱ ውስጤም ኑሮዬም ይገልጠዋል። ምን አልባት ኢትዮጵያዊነትን እንደ አንጡራ ጠላት ለሚዩት ኢትዮጵያዊነት ሳይሆን ራሳቸው መታደስ ይኖርባቸዋል። ከማዕቀፉ በወጡ ቁጥር እዬሾለኩ ስለሚቀሩ። 

ኢትዮጵያዊነት የሚያረጀው አስረጅተውት የኖሩት የብልጠት ፖለቲካ ፍልስፍናቸው ያደረጉ የንፋስ ተጠዋሪ ፖለቲከኞች ናቸው። ወጀቡ በለጋው ቁጥር ኤን ላለማስከፋት ኢትዮጵያዊነት በስርዙ መደራደሪያ አድርጎ በማቅረብ፤ ቢን ለማፍነሽነሽ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ በዚህ እንዲያ በዚያ በማለት አደናግሬን በመከተል።

ኢትዮጵያዊነት አያረጅም፤ አይሞትም፤ አይሰበረም፤  አይቀበረም። ኢትዮጵያዊነት ከዚህ ቀደም እንደምለው እሸት ነው። እያሸ እያፈራ እዬሰበለ የሚሄድ የገነት ፍሬ ነው። ስለሆነም እንደ አሮጌ ቤት ወይንም ህንፃ እድሳት አያስፈልገውም። መታደስ ያለባቸው በሱ ውስጥ ሳይኖሩ ኑረናል ለሚሉት የአስተሳሰብ ደካሞች ብቻ ይሆናል።

ኑረናል ሲባል በክትር - በግለት - በወሰን - በደንበር ዜጋን እንደ ነዶ ጨርቅ በመሸንሸን አይደለም። መኖር ሲባል በመኖር ውስጥ ያለውን ሁሉ የእኔ ብሎ በመቀበል ነው። የዜግነት የክት እና የዘወትር በፈጠረ ህሊና፤ በሰው ተፈጥሮ ላይ ተደራጅ እና አትደራጅ ብሎ በሚጫን መንፈስ ላይ መኖር ፍልስፍናው ወና ነው። 

በመኖር ውስጥ ያለው ሰው የራሱ ነፃነት አለው። ነፃነቱን ደግሞ ሲፈጠር በፈጣሪው/ በአላህ የተሰጠው ነው። ሰው የሰው የፈጣራ ውጤት አይደለም። ስለዚህ ከዬዘመኖች የማንፌስቶ አለቆች ወይንም ምስለኔዎቻቸው ደጅ የሚያስቆመው፤ የዜግነት ፍርፋሬ የሚያስለቅም ምንም ነገር የለም። 
ስለሆነም በፈጣሪ ጥበብ እንደ አምሳሎ ባደረገው ፍጡር ሰውን እዬሸነሸኑ እንደ ብትን ጨርቃ ጨርቅ መኖርን ማሰብ አያቻልም። ኢትዮጵያም በመኖር ውስጥ ያለች፤ የነበረች፤ ወደፊትም የምትኖር አገር ናት። ኢትዮጵያ የእንቧይ ካብ ወይንም የአሽዋ ድርድር አይደለችም ፈርሳ የምትሠራ። 

ራሱ ከፍልስፍናው ጀምሮ የተናደ ድርጅት ወይንም ማህበር ግን ግንባታውን መጀመር ያለበት የሰው ልጅ መፈጠሪያ ናት ኢትዮጵያ ብሎ አምኖ መነሳት ይኖርበታል። ስሜን ኢትዮጵያም የታሪኳ እንብርት ነው ብሎ መቀበል ይጠይቃል። የታሪክ እንብርት ሆኖ መቆዬት የሥነ መንግሥት ምስረታ ምኽዋር አለ ከዛ መንደር ማለት ነው። ያ ደግሞ ትናንትንም ዛሬንም ወደፊትም የሰጠ የመኖር ጸጋ ነው ማለት ነው።

ይህ ማለት የዘመናት አገናኝ መንፈስ ናት ኢትዮጵያ ማለት ነው። ኢትዮጵያ አገር በመሆኗ ዜጎቿ ኢትዮጵውያንም ትውልድ በመተካካት የሚኖረባት በመሆኑ ታላቋ የወል መጠሪያ ኢትዮጵያዊነት እያሸተ ቢሄድ እንጂ የሚያረጅ ሊሆን አይችልም። ፍልስፍናው ራሱ ኢትዮጵያዊነት ሉላዊ ነው። በዚህ መንፈስ ውስጥ ብዙዎች ተፈጥሯቸውን አግኝተውባታል። እንደ ሃይማኖት የሚያዩትም አሉ። ኢትዮጵያዊነት ገናናም ተፈሪም ማንነት ነው። 

በኢትዮጵያዊነት ውስጥ በመኖር እና ባለመኖር መሃከል የአሰተሳስብ ንደት ይኖራል። አስተሳቡ በወጣ ገባ በማስትሽ ተጣብቆ የኖረ ከሆነ ስንጥቅ ስንጥር ዕሳቤ ከኖረ ያን ራስን ገዝቶ፤ ራስን ሆኖ ጭንቅላትን ማደስ ይገባል፤ ለማደስ ደግሞ ቂመኝነት ተጠይፎ በተፈጥሮ ውስጥ በመሆን እንጂ በግርዶሽ ሊሆን አይገባም። 

ስዚህ ያረጀው የተሸረሸረው የፋደሰው የተፋቀው ራሱ የካህጂው ህሊና እንጂ ኢትዮጵያዊነትማ እነሱን ለእራሳቸው አዳኛቸው ነው። ኢትዮጵያ ብሎ ሲነሳ ብቻ ነው ማዕረጉም ክብሩም ጉልላቱም የሚገኘው። ኢትዮጵያዊነትን አክብሮ የሚነሳ ነፍስ ህያው ነው። 

ስለምን?  ኢትዮጵያዊነት የሚያረጅም፤ የሚፋድስም፤ የሚጋም ማንነት ስላልሆነ። ለዚህ ደግሞ አናብስታት ካለፈው ዓመት ጀምረው ተግተው አድባባይ ወጥተው „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው፤ ስንኖር ኢትዮጵያዊ፤ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን“ ብለው የሚሊዮኖችን ልብ እንደ ምሽት ማህሌት ገዝተውበታል። 

ፍቅር ታላቁን ስጦታ በገፍ ዝቀውበታል ሜዞ ሳያወጡ። የቅኔው ዕንቡጥ የቴወድሮስ ካሳሁን ኢትዮ አፍሪካኒዝም ምስባክነቱ ነው ሚሊዮኖች ልባቸውን የሸለሙት። በውስጡ ለኖሩ የታማኝነት ቅዱሳን መንፈሱ ረድኤቱን ይልክላቸዋል። 


እሸቱ ኢትዮጵያዊነት መንበር ላይ ዛሬ ውሏል። ለዚህ ነው ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ „አገር ናት“ በማለት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሲናገሩ የታምኝነት ቅዱሳንንነታቸው ከውስጥ ስለሆኑ ነው። ስለቦረና እና ስለ ዋልድባ ገዳም የምኽዋር ረቂቅ አመክንዮ ዓለምን ዛሬም ድርስ የሚሞግት የፍልስፍና ውቅንያኖስ ስለመሆኑ ኢትዮጵያዊነት ስለተቀበሉ ነው። ምርቃት ከዚህ መሰል የእውነት ማህደር ይፍልቃል። ምርቃት ደግሞ ማግሥትን ያደራጃል፤ ይመራል ያስተዳድራል  ...ምንም የሞገድ ፕሮፖጋንዲስት ሳያስፈልገው። 

 ብፁዑ አባታችን አቡን ዮሖንስ የስሜን ጎንደር አገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዳሉት „ከትርጉም በላይ“ የሆነ ገድል በምድራችን ተከውኗል። ይህን አጀንዳ ያደረገ ልቅና ነው በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ስለመኖሩ ዘመኑ የተረጎመው። አሁን በዚህ መንፈስ ውስጥ ተጠቃሚ ለመሆን መጣር እንጂ ለኮፒራዩቱ መንደፋደፍ የተጋባ አይደለም። ምክንያቱም በልማና ዘመን ተገፋ …  ጥበብ የሌላቸው ሰዎች ናቸው በሰዎች ተፈጥሮ ላይ መቀስ የሚያስፈልጋቸው እንጂ ኢትዮጵያዊነት ለሚያቅፋማ ሁሉም ወገኑ ነው ...

                                    ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ይገለጻል።
                                   የኢትዮጵያዊነት መወድስ ይህ ነው!

ኢትዮጵያዊነት የፖለቲካ ካርታ መጫወቻ ሳይሆን በውስጡ እዬኖሩ መከራውን ተቀብሎ በመከራው ወስጥ በቅሎ መጽደቅን፤ ማስበልን ይጠይቃል። ዓራት ዓይናማውን የተግባር ገበሬ ይጠይቃል ኢትዮጵያዊነት። ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያዊነትን በውስጡ የሰነቀ ዜጋ ቅደመ ሁኔታ አያስፈልገውም ሰውን ያህል ታላቅ ፍጡር ለመቀበል።

ኢትዮጵያ ሲባል ሉዓላዊ ክብሯን ይጨምራል። ሉዓላዊ ክብሯ ደግሞ በደም በአጥንት የከበረ እንጂ በቅኝ ግዛት የተሰመረ መሰመር አልነበረም። ስለሆነም ለዚህ ጥሪም መቅደም ይገባል። አይደልም ፊርማ ሞትስ ቢሆን? እነ ጀግና ኮ/ አብዲሳ አጋ፤ እነ ዘርአይ ደረስ፤ እነ አብርሃም ደቦጭ፤ እነ አጤ ቴወድሮስ፤ እነ አጤ የሖንስ ራሳቸውን የገበሩበት ሚስጢር እኮ የመንፈስ ልቅናው ቁልፉ ከደማቸው ጋር ውህድ ስለሆነ ነው።

መቅደም ቀርቶ ፊት ማዞር ከሆነ ኢትዮጵያዊነት ከፖለቲካ ትርፍ ማጓጓዣነት አያልፍም። ስለዚህም መንገዱ ጣር ስለሚሆን ወልቆ መቅረት ዕጣ ፈንታ ይሆናል። ያዬነውም የታዘብነውም፤ ያስተዋልነውም ይኽንኑ ነው።

ዘመን በተቀዬረ ቁጥር በሌሉበት፤ ባልነበሩበት፤ ባልፈቀዱት ውስጥ አለሁ ቢባልም ስቃይና መከራን የፈቀዱ ወገኖችን በመቀበል እና ባለመቀበል፤ በማዳን እና በማባከን፤ በማቀፍ እና በማግለል መሃል ባሉ ግጭቶ ፍርሶ እንዲህ መቅረት በዬዘመኑ ዓመት ድገሙኝ እንዲህ አይልም ነበር።

የሰው ልጅ ነኝ በሚለው ነገር ውስጥ መጀመሪያ መኖሩን ማረጋገጥ ይኖርበታል። የዜግነት ፖለቲካ የሞገድ ፖለቲካ አይደለም። ተማርኩም አልተማርኩም፤ ሌላ ቋንቋ ቻልኩም አልቻልኩም፤ ጎንደሬ ሆንኩኝ አልሆንኩኝ፤ አማራ ሆንኩኝ አልሆንኩኝ ሰው መሆኔ ብቻ በቂ ነው ለድርጅት የፖለቲካ መሪነት ተወዳድሬ አሸናፊ ለመሆን፤ ድርጅቱ ኢትዮጵያዊ ከሆነ ኢትዮጵዊነቴ ይበቃዋል። የስሜን ሰው መሆኔ ለድርጅቱ መንፈስ ጥዮፍ ሊሆን አይገባም።

በዚህ እሾኽማ ፖለቲካ ዜግነት አይታሰብም። ላይ ላዩን ለሚያው ሰው ሊመስል ይችላል። ግን ዕውነቱ በዜግነት ውስጥ መተሳሰብ፤ መተዛዘን፤ መረዳዳት፤ መጠያዬቅ፤ ይቅርታ ማድረግ፤ ይቅርታ መቀበል፤ ማድመጥ፤ መስጠት፤ መቀበል፤ ማክበር፤ የሃሳብ ልዩነት መቀበል፤ የሃይማኖት ልዩነትን መቀበል ይገባ ነበር። ግን የለም፤ አልነበረም፤ ወደፊትም አይኖርም። ስለምን? የዜግነት የክት እና የዘወትር ወሰን እና ደንበር ስላለው በጥነሙ የጆሮደግፍ በሽተኛ ፖለቲካ ምክንያት።

ዜግነት ማንም የሚሰጥ፤ ማንምም የሚነሳው አይደለም። በደሜ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነኝ። ይህን የሚጋፋ በዚህ ላይ ዲስክርምኔሽን የሚፈጠር የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የራቀው ድንቡልቡል ሰብዕና ነው። በዜግነት ውስጥ ማርጀትም መታደስም የለም። ዜግነት ለዜጋው የመኖሩ አናባቢ ነውና።

ውዶቼ ኢትዮጵያዊነት ሊከፋው ይችላል እንደ ጭቃ ምርጊት ቤት ግን አይዘምም፤ አያረጅም፤ ስለዚህም ዕድሳት አያስፍልገውም።  ኢትዮጵያነት እውነት ነው። ኢትዮጵያዊነት የነፃነት ፍልስፍና ምኸዋር ነው። 

ለመሆኑ ሳይንስ ያረጃልን? ዕውነትስ ያረጃልን?! ለመሆኑ መቼ ነው ዕውነት ዕድሳት ፈልጎ የሚያውቀው?!

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።



                                          ክብረቶቼ ኑሩልኝ።

                                            መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።