የአደራ እጬጌ! የውል አሥራት! የኪዳን መሆን!

ዬውጫሌ ውል አንቀጽ 17 ሳቢያ ነበርን?!?
      ባድመስ አህጉር ነበረችን!?!

  „ዬቅንነት፡ ቃል፡ እንዴት፡ ኃይለኛ፡ ነው!“
( መጸሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፳፭)
ከሥርጉተ© ሥላሴ (Sergute©Selassie)
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

 የአደራ እጬጌ! የውል አሥራት! የኪዳን መሆን!

·      እፍታ።

ጤና ይስጥልኝ የ እኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ። ይህ ደግሞ December 16, 2016 በፈረንጆቹ ቀን የተጻፈ ነው። ሦስት ቀን ይቀረዋል ሁለት ዓመት ሊሞላው ማለት ነው። ይህን ጹሑፍ የጻፍኩት የጎንደር የህልውና የማንነት ተጋድሎ ሳቢያ ነው ስላሉ  የኢሳት እና የግንቦት 7 መንፈስ ደጋፊ ሊቃንት ስላሉ ነበር። እኔ በብዙ ሰው ብዙም አይገረመኝም። እምገረመው ግን በጸሐፊ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ብቻ ነው።

እሱ በወያኔ ሃርነት ትግራይ አዋራ ፓርቲ ሥር ይመራ በነበረው በኢህአዴግ ውስጥ የሎጅስቲክስ ሠራተኛ ሳይሆን መደበኛ የፖለቲካ ሠራተኛ ነው የነበረው። ለዛውም መምህር። በዛ ሙት መሬት ላለ ዶግማ ትውልድን ማህበረሰብን መቅረጽ። ስለዚህ እሱ የሳቢያ እና የምክንያትን ንጥረ ነገር በስማ በለው ሳይሆን በእውቅት መሬት ላይ ሰርቶበታል ኑሮበታል። የሞገድ ፖለቲከኛ አይደለም። ነገር ግን ኤንም ቢንም እንዳይከፋው ሆነ እና ያ ገናና የአማራ ተጋድሎ በሳቢያ ተጥቅልሎ አረፈ።

ይህ ሲገርመኝ አነ ዶር ለማ መገርሳ ወደፊት ሲመጡ አብሶ ዶር አብይ አህመድ ሲመጡ ሌላ ሰብዕና ይዞ ነበር የመጣው። በቃ እማናውቅው ሰው ነበር የሆነው። እውነትን ለመወገነ ቅድመ ሁኔታ አያስፈለግም ነበር ለ አንድ በፖለቲካ ድርጅት ውስጥ መሬት ላይ ላለ ሰብዕና። ለወደፊትም ሚዛን ፋክት ቢሆን ነው ሰብዕናን አጽንቶ የሚያዘልቀው። የራስ ድርጅት አቅመ ቢስ ከሆነ አቅም ያለው ዕውነትን መደገፈ ሰብዕነት ነው። 

የሆነ ሆኖ በዛን ጊዜ የ አማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ሳቢያ እንዲ ምክንያተዋ አይደለም የሚለው ዝንባሌያቸውን የሞገትኩበት ጹሑፍ ነው።
እጅግ የሚገርመኝ ማንም ባልነበረበት ወቅት ድምጽ የአማራ ታገድሎን ሆኖ የኖረውን ሳተናው/ ኢትዮ ሪጅስተር በጎንደር የሚደረጉ ዝግጅቶች ሁሉ አንድም ቀን እናመሰግንሃለን ሲባል ሰምቼ አላውቅም። ያሳፍራል።
  
ቅኔው የጎጃም ህዝብንም በሚመለከት ራሱ ቀን ተውስኖ የምስጋና ቀን ሊኖረው ይገባል ብዬ ሁሉ ባለፈው ጽፌ ነበር። ነፍሱን መንፈሱን የሰጠ ቆራጥ ህዝብ ቢኖር ለእኔ የጎጃም ህዝብ ነው። ጎጃም ለእኔ ሃይማኖቴ ነው። 

ዛሬ ጥዋት የኮ/ደመቀ ዘውዱን ቤት ሙዚዬም መሆኑን ያበሰረ ዝግጅት አዳምጥ ነበር። ያስደሰተኝ ከዛ ሁሉ ዝግጅት ለእኔ የዶር ለማ መገርሳ ምስል በጥላ መሰራቱ ነው። ጎንደር አንዲህ ሲሆን ነው የሚያምርበት። የራሱን ሲሰበስብ የራሱን እህት ወንድንም ሲሾጓጥ የጎንደር ጀግና ሆኖ ሰምቼ አላውቅም። በዚህ ዘመን ግን እዬሰማሁን ነው ገንዘብ ዝናን ሲገዛ፤ ገንዘብ የታሪክ ባለድርሻ ሲያደረግ። በዚህም አፍራለሁኝ።

ጎንደርን እኔ እማውቀው ብቁዎችን ህሊናው ሲያደርግ ነው። ብቆዎችን ጎንደርን ጥለው እንዳሄዱ በጋብቻ እሰሮ ያስቀራቸዋል። እራሱ አጭቶ ድሮ ኩሎ እዛው እርስተኛ ሲያደርግ ነው እኔ ሳድግም ከቤተሰብ ያዬሁት።

ዓራት ዓይናም ሊቀ ሊቃንት ተመረው ወደ ሌላ እንዳሄዱ ማሰሪያ ነበረው። ውስጥን የሚቀልብ ፍጹም የሆነ ፍቅር። ለዚህም ነው እኔ ዶር ለማ መገርሳ ሊዩት የሚገባ ህዝብ ነው እና ወደ ጎንደር እንዲሄዱ እማሳስባቸው። ከሄዱ ግን እናቴን ማዬት ግድ ይላቸዋል።

እብዬም ሙጌራዋን አሰናድታ፤ ጓደኞቼን ታስተናግድልኝ እንደነበረው ሁሉ በጎድጓዳ ሳህን ሽሮዋን ተክተክ አድርጋ ትጠብቃቸዋለች። ማን ስለመሆኗ እዛው ኮሚቴውን ሲጠይቁ እሳቸው ከሆኑ ቤቷ ሰተት አድርጎ የሚወስዳቸው ሁነኛ ሰው ይኖራል ብዬ አስባለሁኝ።

ለማ የመንፈሴ ልብ ናቸው። በኢትዮጵያ ታሪክ ለማን የመሰለ የፖለቲካ ሳይንቲስት ምድር ፈጥራ በእኔ ዘመን ያየሁት እሳቸውን ነው። ለዚህ ነው 
ወላጅ እናቴ መነኩሴዋ እብዬ ብድግ ቁጭ ብላ እንድታስተናግድለኝ፤ እንድመትመርቅልኝም እምፈልገው። ከርታታ ልጇ ስለምን እንደ ተፈጠረች ታውቀዋልችና።  

በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ዶር ለማ መገርሳ ከኦህዴድ ሰብሳቢነት እራሳቸውን ዝቅ አድርገው ዶር አብይ አህመድ ያደረጉበት የስብሰባ አዳራሽ ነው የዴሞክራሲ ተቋም የመሰረት ድንጋይ። ያ የስብሰባ አዳራሽ ሙዚዬም ሊሆን የሚገባው።

በቃ የዴሞክራሲ ኢንስቲቲዩት ይከፈት ከተባላ ቦታው ጨፌ ኦሮምያ ላይ ነው መሆን ያለበት። ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ምድር የመምጣት ያህል ነበር ያን የሥልጣን ጥመኝት አብሾ ከልቶ የብረት በሩን በመክፈት መሆንን ያዘመረ ሰብል ያሳዩን። መሰረት ናቸው ዶር ለማ መገርሳ።
  
ዶር ለማ መገርሳ ተፈጠሯቸው ራሱ የምርምር ማዕከል ሊከፈትበት ይገባል። በ3 ሺህ ዘመናት ውስጥ የተገኙ ሰብል ለዛውም የህሊና ዓይን ናቸውና።
ውዶቼ ከፊደል ግደፈት በሰቀር አንድም የጭብጥ ልዩነት አልተነሳም፤ ከተፈለገ ሊንኩን ከሥር ስለጻፍኩት ማመሳከር ይቻላል።  አሁን ወደ ቀደመው የምልሰት ዝግጅቴ … ወደ December 16, 2016 እንዲህም ይል ነበር። 
   
·      መነሻ …

… ፈጽሞ! ማንነት ያለው ተስፋ ስላለኝ የመንፈስን እስር ዬመፍታት አቅሙ ፈተና ላይ አይወድቅም። ይልቁንም ማንነት ያለው መፍትሄ ዬመፍጠር ዕሴቱ ሆነ አቅሙ ጉልበታም ነው። ጉልበታሙ ማንነቴ ወደ ፊት ዬሚፈጥረው ግፊትና ዬሚጨበጥ ራዕዩ ደግሞ ትጥቅና ስንቄ ነው። በተሟላ ስንቅና ትጥቅ ዬተሰናዳ ማንነት ደግሞ ጉልህና አሸናፊ ነው። ከዚህ በኋላ ወይንም ከእንግዲህ ወዲያ በቃኝ ብሎ ለስንፍና እና ለፍርኃት እጁን አይሰጥም። ፈጽሞ! ዬመይሳው ልጅ ነኝና! /ይህ በእርግብ በር መጸሐፌ ሽፋኑ ላይ የሚገኝ ነው።/ እርግብ በር/ ሥጦታው ደግሞ ለንጉሦች ንጉሥ ለአጤ ቴውድሮስ ነው። ከአማራ ተጋድሎ በፊት … የታተመ ነው።
  
·       ግራሞተ - እልፍኝ።

በምልሰት ሦስት አብይ ሂደቶችን መቃኘት አሰኜኝ። ደማችን ዬሚነግረንን ማዳመጥ ግድ ይለናል። በአንድም በሌላ እያገረሸ ዬሚነሳው ዬዕውነትን ዝት አሻም! አታላግጥ! ወዲያልኝ! ማለት - ስለተገባም። ዬጓጎለ ወይንም ለበስ ያለ ዬውስጥ ቁስለት መተንፈሻ ሊኖረው ይገባል። ስለዚህም ተያያዦችን እንደ ተፈጥሯቸው - ተደጋጋፊ ሃሳቦችንም አክላ ለመሞገት እንሆ ተነሳች። እግረ መንገድንም ግፊያውንም ሳትዘል ዬምትለው ይኖራታል። እመቤቲቱ እትዬ  - ብዕር። ብራናው - ዬሳተናው ….

ዕልፍኞቹ ዬሁለት አካላትና ዬአንድ ፖለቲከኛ ብዕረኛ ነው። እነሱም ዬኢሳት ብሄራዊ ዬወቅታዊ ትንታኔ፤ ዬቢዢን ኢትዬዽያ ዝግጅትና እድምታው፤ ዬአቶ አስራት ገብሩ ዬህውኃት ማኒፌስቶ - ራሮት። ግራሞቴ በአማራ ተጋድሎ ምክኒያታዊ አመክንዮ ሃቅን ያልፈቀደ ልግመት ስላገኘሁበት ነው  - ግራሞት ያልኩት።

እልፍኝነቱ ደግሞ ዕውነትን ማዕከል በማድረጉ እንደ እኔ ቁስል ያለ መንፈስ ያለው ዬሃቅ ሐዋርያ ያዳምጠዋል። እትብት ነዋ! አጥንት ነዋ! ታሪክዊ ነዋ! አዎን! ዛሬ ጥቂቶች ነን። ነገ ግን ዬዕልፍ - እልፍኞች። ጥቃትን ተጎንጭቶ ለሽ ዬሚል ውርስ ከደማችን ዬለምና! ዬሚማርበት - ይማርበታል፤ ያልተመቸውን አሻም ይለውና ፊት - ይነሳዋል። እንደ ሥርጉተ ያለ ደግሞ ወጣ ብሎ፤ መቀነቱን በሁለት እጥፍ እንደ ነገሩ ሸብ ሳይሆን፤ በጥፍ ድርብ ጠብቅ አድርጎ ብዕርና እና ብራናን ያዋድዳል። እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም።

·       ዕውነትን ያነጠረ ተጋድሎ ዬምክንያት ጭንቅላት እንጂ፤ „ተራ ግጭት“ አይደለም! በተጨማሪም ባድመስ አህጉር ነበረችን!?!

እንደምን አሉ ዬተከበሩ አቶ አስራት ገብሩ። ጹሁፎዎትን ከሚከታተሉት አንዷ ነኝ። ጎርባጣውንም፥ ሸካራውንም፤ ዘንጣፋውንም፤ ለስላሳውንም እንደ ተፈጥሮው አስማምቶ ማድመጥ ዬሚቻለው ዬተገባውን ትኩረት ሰጥቶ ማንበብ ሲቻል ብቻ ነው።

ዬጹሁፎዎትን አጣጣል እውዳቸዋለሁ፤ ዬእርእስ ምርጫዎትንም እንዲሁ። ወደ ህብረ ብሄር አስተሳሰብ መምጣተዎት መልካም ነበር። ግን ዬመጣው አካለዎት እንጂ መንፈሰዎት አለመሆኑን ሥራዬ ብሎ ጹሁፎዎትን እንደ አንድ ከጎሳ ፖለቲካ ዬመጣ ግን፤ ህብረ - ብሄራዊነትን ተቀብያለሁ ዬሚል መንፈስ ዬምርምር ማዕከል ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።

አንድ ነገር ትዝ ይለኛል - እርሰዎ ከአረና ወደ አንድነት ሲመጡ ዬተለመደው ቀይ ምንጣፍ እንዳልተነፈጉ አስተውያለሁ። ይገባ ነበርም - ምርጥ ዘር ከእኛ ታች ላይ ከተወረወርነው „ትቢያዎቹ¡“ እነሱ ይሻሉኛል ብለው መምጣተውት ሌላም ቢደረግለዎት - አይደንቅም። ለምደነዋል።

ዬኃላፊነት ቦታዋም ቁልፏ „ልሳነ -አንድነት“ ነበረ። ያን ጊዜ እጅግ በጣም እርግጠኛ ሆነው ያስተላለፋት መንፈስ ነበር። ዬእኔን ተስፋዊ መንፈስ ዬቀቀለች ለዛም ነበር ዬስሜን አሜሪካ ዬአንድነት ድጋፍ ሰጪ ኃይል ዬቴሌ ኮንፍረስ ላይ ዬተገኘሁት - ልሞግተዎት ነበር። እርሰዎ አልተገኙም - ዬተገኙት ሌሎች አመራር አካላት ነበሩ። ስለማይመለከታቸው ጥያቄውን አላነሳሁትም። በጹሁፍም መሞገት እችል ነበረ። ነገር ግን ዬሚቀድመው ዬአዲሱ ዬአንድነት አመራር መሠረት ዬያዘ ተግባር መጀመሩ ስለሆነ - ተውኩት።

ስተዎው ግን በሂደት ጉዞዎትን ለመከታተል ጊዜ መስጠቱንም አምኜበትም ነው። አብረን ዕውነትን እንቅበረው ዕሳቤ ...

 „የአማራ ልሂቃን እንደሚታወቀው ከአሁን በፊት በአገር አቀፍ ደረጃ ነው መታገል ይመርጡ የነበረው፤ አሁንም ብዙዎቹ በዚሁ መንገድ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋራ በአንድነት መታገሉ የሚመርጡ ይመስለኛል።

እንደማነኛውም ህዝብ በውስጡ የሚኖረው ሰው ፍላጎቱና አስተሳሰቡ ስለሚለያይ የሚያሰባስበው አጀንዳም እንደዚሁ የተለያየ ነው የሚሆነው። ለምሳሌ ሸዋውና  በተለያየ  ሀገሪቱ አከባቢ የሚኖረው የአማራ ተወላጅ ሰፊዋን ኢትዮጵያ ትቶ የአንዲት ወረዳ፣ የወልቃይት ጉዳይ የሚመስጠው አጀንዳ ላይሆን ይችላል፤ የወሎውም፣ የጎጃሙም እንደዚሁ። በነገራችን ላይ የጎንደሩ እንቅስቃሴም ቢሆን የወልቃይት ጉዳይ ብቻ ከሆነ አጀንዳው የትግሉ ዓላማ የሚያሳንሰው ነው የሚሆነው፤ ሲጀምር የወልቃይት ጉዳይ የወልቃይቶች ነው፤ በጎንደር የሚኖር አማራም በአድዋ የሚኖር ትግሬም የሚያገባው ነገር የለም።  ሁሉንም ዜጎች በእኩልነት የሚያይ መንግስት ሲመሰረት ኗሪው ህዝብ ነው ወዴት መካለለል እንዳለበት የሚወስነው። ስለዚህ የህዝቡ ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሄ የሚሰጠው ጉዳይ ነው የሚሆነው። ከዚያ በኋላ ወልቃይት ወደ ጎንደር ይካለል ወደ ትግራይ ይካለል እንደ ጥንቱ አማርኛ እና ትግርኛ የሚናገሩ የአከባቢው ዜጎች በሰላም የሚኖሩበት ምድር ይሆናል።

ጎጃምን አላዩም ዬት ሄደው ነበር? ጉግል ያድርጉን ይዩ - በትህትና። አንጡራ ዬአማራ ሃብት ዓመታዊ ገቢ ለትግራይ ብልጽግና ሲውል ዬሱ ንብረት ዝርፊያ መሆኑን አሳምሮ ያውቀዋል። ጥቅሙን ዬሚጻረር ተጠቃሚ ዬለም። ተግባባን?

ምክር ይፈለግ!    [አስራት አብርሃም] October 4, 2016


ይህ አገላለጽ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ „አክሱም ለወላይታው ምኑ ነውን?“ ዳግም ትንሳኤን ያወጀ ነው። ለዚህም ነው አካለወት ብቻ ነው ህብረ ብሄርን ያሰኘው ዬመንፈሰዎት ጌታ ዞጎዎት ነው ያልኩዎት ቋንቋም አይደለም። ደማችን አማራ መሆናችን እንጂ አማርኛ ቋንቋ በመናገራችንም አይደለም። እርስዎ ዞገዎት ትግሬ እንጅ አማርኛ ቋንቋን ሙያወት አድርገው በመምረጠዎት ዬጎሳዎት ደም ዬአማራ ብሄር እንዲኖርበት ሊያደርግ ፈጽሞ አይችልም። ከሁለቱ ዬመወለድ ዕድል እስከሌለዎት ድረስ። እኛ አማርኛ ቋንቋ መናገራችን ሳይሆን ፍሬ ነገሩ ዞጋችን ትግሬነት ሳይሆን ዘብሄረ አማራ ነን! ትግሬ አይደለንም።

ስንፈጠር አማራ ሆነን እንጂ ትግሬ ሁነን አይደለም። ለመሆኑ ያን ያህል ዬአማራ ወጣት ያለቀበት ባድመ አህጉር ነበርን? ለዚህስ መልስ አለዎትን? ሶርያ ዬአውሮፓና ዬአሜሪካ ዬፖለቲካ አጀንዳ መሆኗ አውሮፓያዊ ወይንስ አሜሪካዊ ሁና ነውን? አመክንዮ ካላራደወት በስተቀር ለዚህ ህሊናዎት እራሱ - ያፋጥጠወታል። አይሸሹት ነገር። 

·         ሌላም በሌላ ጹሁፉዎት ያሉት ነበር …./አቶ አስራት አብረሃም/

„ሁለት መላጣዎች ጠብ የሚባል ነገር አለ፤ ሁለት መላጣ ሰዎች አንድን ማበጠሪያ የራስ ለማድረግ በሚያደርጉት ትግል የሚፈጠር ጠብ ነው። ወያኔ ቤተ አማራልሂቃን መካከል ያለው ጠብ ከዚህ የተለየ አይደለም። በአጠቃላይ የሚያራምዱት ፖለቲካ ያየን እንደሆነ ተከባብሮ በአንድ ሀገር የመኖርን መርህ የጣሰ፤ ኃላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ ነው። ነገር ግን ይህ ጠብ የጥቂቶች ለስልጣንና ለጥቅም የቋመጡ ወገኖች እንጂ በምንም መልኩ የህዝብ ጠብ አይደለም። ህዝብ ሲባል ግዙፍ ስለሆነ፣ አንዳንዴ በስግብግብ ልሂቃን ባልሆነ መንገድ ተገፍቶ ጎርፍ ሆኖ፣ ማዕበል ሆኖ ያልታሰበ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። አሁን በጎንደር የተከሰተው ግጭት ከዚህ የተለየ አይደለም።“

ባድመ ተራ ግጭት ነበርን? ባድመ ምን አላት? ወልቃይትና ጠገዴስ? ልቦዎት ያውቀዋል አሽዋና ወርቅን ማወዳደር እንደማይቻል። በዘረፋ፤ በውንብድና፤ በማናህሎኝነት፤ በትእቢት ዬተዘረፈ መሬታችን ነው፤ አንጡራ ሃብታችን እነ አርበኛ አባ ፍታውራሪ መለሰ ኃይሉ ደማቸውን ዬገበሩበት። መቼውንም ለድርድር ዬማይቀርብ!

ምን ታደርጉ ዬኢትዮዽያ ችግር ሲፈታ እዬተባለ ደማችነን እራሳችን ተረግጠነው ኖርን …. እኛን ሆኖ መፈጠር ይቻል ይመሥል - በባታችነት ዬካንሰር በሽታ ዬያዘው ዬሄሮድስ መለስ ማኒፌሥቶ ዘረፋው ዬታሰበው ዬሥነ - ልቦናም ነው። ማንነት Redmade አይደለም። ተወልጀነት ዬሰው ልጅ ዬመፈጠሩ ሚስጢር ነው። እኛም እንደ እናንተ እናንተም እንደኛ መሆን አይቻልም። አማራነት አይቀናም! አማራነት አይሸመትም!

ቀጠለች እላፊ መሄድን ይሁን ያለችው ብዕረዎት „በእኔ እምነት የአማራ መሬት፣ የትግራይ መሬት፣ የኦሮሞ መሬት ወይም የጋምቤላ መሬት የሚባል ነገር የለም፤ መሬት የሁሉም ዜጎች የጋራ ንብረት ነው። ዜጎች ደግሞ ወደፊት በሚመሰርተው ዴሞክራሲያዊ መንግስት ወዴት መካለል ትፍልጋላችሁ ትብለው በነፃነት ሲወስኑ በወሰኑት መሰረት የሚሆን ነው።“ 

እንደዛ ከሆነ በወረራ ዬተወሰደው መሬት ለምን አይለቀቅም? ቀድሞ ነገር መዝረፍስ ለምን አስፈለገ? በጉልበት ዬተነጠቀ አፈር ስለምን ነፃነቱን አታውጁለትም? መልቀቅ አለብን ብለው ለመፃፍ እንኳን አቅም ዬለዎትም። ዬቅዱስ ወንጌል ቃሉ ዬተገነባው በአፈር፤ በመሬት ባለቤትነት ነው።

ለዚህም ነው ከቅኔው ኣናት  „ወልቃይት አንችን ብረሳሽ ቀኜ ትርሳሽ“
ዬሱባኤ ተደሞ ዬተደመጠበት። ሌላውን ካልተመለከተው እርሰዎም ከማይመለከታቸው ውስጥ ስለሆኑ ስለምን ዝም አይሉም። እኛ ወተትና ማር ለምታዘንበው መሬታችን መጮህ እንችላለን። ለቀቅ - ያድርጉን።

ሌብነት፣ ዘረፋ፣ ስርቆት እኔና እርሰዎን በሚገናኘን ዬኢትዮዽያዊነት ህላዊ 
ዜግነት ወላዊ ዕሴት ሃፍረት ነው። እንደነገርኮዎት ዬወንጌል ታሪክ እኮ 
ዬቅድስት ሀገር ዬህልውና ተጋድሎ ዬርስተ - ጉልት ታሪክ ነው። ቅዱስ ወንጌልን ዶግማውንም፤ ዬዜግነት ሰብዕናንም መሸሸት ብቻ ሳይሆን እዬተዳፈራችሁት - እዬረገጣችሁትም ነው። አርማጭሆን ትጥቅ ማስፈታት - መጠቅለል 
በህልምም አይሆን። ጥርኙ ወንጌሉ ነውና።

 „የሁለት መላጣዎች ጠብ! – አስራት አብርሃም“  
·       መስቃ!
ተፈጥሯዊ ደንበሩ ተጥሶ ለተነሳው ህዝባዊ አብዮትተራ ግጭት „  ሲሉም አቃለውታል። ዬአውሮፓ ኮሚሽን ግብዣ መሠረቱ ዬጎንደር አብዮት 
ዬአማራ ተጋድሎ ገድል ነው ባይሆን ምክንያታዊ አምክንዮ ህልም
ነበር። ዬባለቤትነት እሰጣ ገባው እንደ ተጠበቀ ሆኖ። ዬሰባዕዊ መብት 
ድንቅ ተሟጋቹ  ዬአትሌት ሊሊሳ ግብዣ ሳቢያ እንጂ ምክንያት 
አልነበረም። አቅም አለን በተነሳንበት ዓላማ ነው ነገሩ - ዬነበረው። 
ዓይነዎትንም ጆሮዎትንም ቢቀረቅሩት ዕውነት ዕውነት ናትና መራራን - ትሸልማለች። ተወደደም - ተጠላም።

እውነት ለመናገር ዬሚሊዎኖች ዬዘር መጥፋት፤ መፈናቀል፤ እሰራ ግድያ፤ 
አፈና በምክነት ዬደረሰው ዬትውልድ ድርቀት - በአንድ ዬለበጣ ቃል 
ሸብልለው ዬተከደነውን ራዕዮዎትን እንደ ቄጠማ እዬዘከዘኩልን ነው። 
ለዚህ ሊመሰገኑ ይገባል።እግዚአብሄር አውቆ ሰማይን አርቆ“ 
እንደሚባለው እንኳንም ፈጣሪ ለሌላ እርድ አላዘጋጀን።ሁሉ ለበጎ“
እንዲሉ …

ሽፍቶች ቤዚንና ክብሪት ይዘው ዝቅ ሲል ሱቆችን ከፍ ሲል ፋሲል ግንብን ለማቃጠል ዬወንበዴ ቡድን አምላኪዎች በጥፋት  ተሰማርተው ዬፋሲል ግንብን ያህል ክብርና ሞገስ ዬነበረውን ቅዳሜ ገብያን ሲያነዱ ምነው ብዕረዎት አንዳች አላለች? ፈነጠዘችን? ደስ አላትን! ፈንድሻውን እረጨች ወይንስ እንደ ቅኖቹ አብራ አለቀሰችን? አዘነች? እኮ! ምን አለች!?

እኔ ለነጭ ጓደኞቼ ስነግራቸው ግራ ነበር ዬተጋቡት። እንዴት? አሉ። ዬበታችነት ለሚንጠው ተፈጥሮው ይሄው ስለመሆኑ፤ መንገር ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ሊንኮች ነበር ዬላኩላቸው። ለሰው ልጅ ከሚለቀሰው በላይ አልቅሻለሁ። ባድማዬ ሲቃጠል መንፈሴም አብሮ ነው ዬተቃጠለው። ምን አልባት ለእርስወና ለመሰሎዎት ግጥግጥ ሊሆን ይችላል።

ምናችሁ ተነክቶ? - እንደ እኛ ታሩና ትክን ትሉ?  ይህ ታሪክ ይቅር ዬማዬለው ዬማንኽሎኝነት ተግባር -  ያሳፍራል! ያሸማቅቃል! - አንገት ያስደፋል! እዩኝ እዩኝን ወደ ደብቁኝ መቃብር ዬቹቻ ያለኽ ያሰኝ ነበር። 

ምን ይሉኝታ ካልተፈጠ ---- …..ጋዳ፤ … ቀጣዩ ትውልድ - ትውልድን በሚያጠፋ መሰሪ ዓላማ መሰማራቱ እንደ ትግራይ ዬላዕላይ ጠበቃነታችሁ በዚህ ሊሰሙት በሚቀፍ እጅግ አፀያፊ ምግባረ ብልሹነት ተግባር ተተኪዎቻችሁ ሲሰማሩ በተጸዬፋችሁት ነበር፤ ግንስ ያዬነውም ዬሰማነው ዬለም።

ጎንደር እኮ ህይወቱ ነው ለትግራይ። ጎንደር ሆድ ነው ለትግራይ። ጎንደር ለትግራይ እናት አንጀት - ዬራህብ መዳህኒት ነው። ጎንደር ለትግራይ እናት ጡት ናት። ትናንትም ዛሬም። በምን ሁኔታ ጥንዝል ብሎ ዓመት ይዞ እስከ ዓመት ያ  … እንደ ጎርፍ በወገራ በር ይተም ዬነበረው ቤተሰብን በፍቅር ተቀብሎ፤ ለራበው - አብልቶ፤ ለጠማው - አጠጥቶ፤ ለታረዘው - አልብሶ፤ ነፍሰጡሯን ስትወልድ አርሶ፤ ልጇን ልጄ ብሎ ተቀብሎ፤ መጠለያ ላጣው ወገኑ መጠለያ ሰጥቶ፤ 
ያለውን ሁሉን አካፍሎ፤  ትናን፤ ርህርህናን፤ መስጠትን፤ ማጉረስን፤ መጽናናትን፤ መከራ መጋራትን፤ ለቃል ማደርን -  እውነት  መግቦ መቻቻልን አቁርቦ ዬኖረ ታላቅ ህዝብ ነው። ዬደግነት ተቋም ዬአብርኃሙ ቤት ነው -  ጎንደር።

ለዚህ ህዝብ ነው እሳት ዬታዘዘለት። አምላክን እምታምኑ ከሆነ አምላክን ፍሩ! ቀን ያልፋል …    …እንዳለፈው ሁሉ። ትውልድ ግን ይቀጥላል። ቢያንስ ለነገ ዬትግራይ ህፃናት ስትሉ ለሥጋ -  አትገዙ፤ ለቅዱሳኑ መንፈስ - ተገዙ። ነገ እነኝህ ቅዱሳን ዬእናንተ መስቃና አፍ እላፊነት ዬትዕቢት ዕዳ መከራ ተሸካሚ እንዳይሆኑ ውስጣችሁን ግሩት። 

ጥጋብ ለጋዳፊም ለሄሮድስ መለሰ ዜናዊ አልሆነም። ዝግ ብሎ መራመድ ትውልድን ይታደገል። ዛሬ እኮ ይህ ሁሉ ማዕት እዬወረደበት ለእናንተ መብራት እሱ ሌት ተቀን ቆሞ ራት ያበላል። ግፍ ተሸክሞ በድንግልና እና በንጽህና አንጡራ ሃብቱ እሱ ጨለማ መሸለሙን እያወቀ ለነዘመናይ ጧፍ ሆኖል። ኧረ!? ፈጣሪን ፍሩ!? ማዕት ከዙፋኑ ይታዘዛል።

·       ልክ ያልተሰራለት ጥጋብ።

ከአራት ዓመት በፊት በነበረኝ መረጃ… ጎንደር ላይ ዬገብያው ጣሪያ ዬነካ እንደ ነበር ነው። ዬተያዘ ዬተረዘዘው ነገር እንደሚጫን ኑሬም አይቸዋለሁ። መሬቱን ተቀምቶ። ወገኑ እዬታረደ፣ ዘሩ እዬጠፋ - ምርቱ እዬተዘረፈ - ጥጋቡ አላስችል ሲል በሰላም ላቀረበው ጥያቄ ቤዚንና መትረዬስ።

ዬሱዳን ወታደር ዬጭካኔ ህማማት በጎንደር መሬት ላይ መፈተኛ ሆነ - ዬአረመኔ - ዬድርቡሽ ዬጅምላ ጭፍጨፋ መሞከሪያ አንባ አንባ ጊዮርጊስ ዬስቅለት ህማማት ታወጀበት። ከቶ ስለዚህስ ምን ተሰማችሁ? ይሄ ለእናንተ ዬተመቼ አዬር ነውን? ለመሆኑ ከዬትኛው ፕላኔት ላይ ነው ክቡርነተዎ ዬሚኖሩት?

አዩ መሬት አፈር ትንፋሽ ነው። መሬት አጥንት ነው። መሬት ደም ነው። መሬት ህልውና ነው። መሬት ነብስ ነው። መሬት መኖር ነው። መሬት ተስፋ ነው። መሬት ወንዝ - ሸንተረር - ነፋሻ - ተራራ ዬውበት መግለጫ የመፈጠር ቅኑ ልዩ ዜማ ነው። መሬት ጠረን ነው ወዝ። መሬት መንፈስ ነው። መሬት ነገ ነው። መሬት ፖለቲካ ነው። መሬት ነገ ነው። መሬት ዬልብ ምት ሙቀት ነው። መሬት ኢኮኖሚ ነው። መሬት ሃይማኖት ነው። መሬት ርስት ነው። መሬት ውርስ ነው። መሬት ትውፊት ነው። መሬት ሥልጣኔ ነው።  መሬት! አዎን መሬት - ትውልድ ነው። መሬት ቋሚ ዬህይወት ቀለበት ነው። ከባድማችን በፋሽስት ሥርዓት - ተነቀልን። ውሃችንም አልቀረለት ተወረናል - በወንበዴ ቡድን።

ደንበራችን ተከዜ ነው። ዬአማራ ተጋድሎ ተልዕኮውን ሳያሳካ ቀበቶውም  - መቀነቱም አይፈታም። ትጥቁ ሁሉም በሚችለው መስክ ዬበኩሉን ድርሻ ይወጣል። ዬተኛን እንዳይመስላችሁ። ያን ጊዜ ተራ ግጭት“ ስለመሆኑ ያዩታል። ድርጊቱ፤ ገድሉ - በራስ መተማመን መንፈስ ለሌለው ሃይል ዬህሊና ቦንብ ነው። ሰላሙን ዬቀሙት ጥጋበኞቻችሁ ናቸው።


ዬሄሮድስ መለስዬአማራ መቃብር“ ቅዥት መዳህኒዓለም አባቴ ግባ መሬቱን ያውጁለታል።  ለዘራፊ ዬድምጽ ሥርዓት አያስፈልገውም። መሬታችን፤ ባድማችን፤ ቀያችን፤ ድንበራችን ዬእኛ እንጂ ሌላ ኃይል ይበይንበት ተብሎ ዬሚሸለም ዬቅልሞሽ ጨዋታ አይደለም።

አይዞችሁ ተብላችሁም ከሆነ - ቃሉ ዬዱቡሽት ቃል ነው ዬሚሆነው። ውስጥ ለውስጥ ስምምነት ሊኖር ይችላል፤ ስለ አጥንታችን አናቀላፋም!  እንደ ድሮው ዬሰውን ቤት ከማደራጀት ዬራሳችነን ጉዳይ እራሳችን ባሊህ በማለት ዬሚፈራውን አቅማችን ዬውስጣችን ብልጽግና እንዲሆን ይደረጋል። ዝምታ ፍርኃት አይደለም! 

በአማራ ሊህቃን ተስፋ እንዳለዎት ገልጸዋል - ወጀቡ እንሱን ሳይሆን ዬዕውነት አርበኞች ዘንድ ስለሆነ ለእኔ ሊህቅ ዬምለው ዬግላዊነት ሌጋሲ ሳይሆን - ዬኢትዮዽያ እናቶች እንባ ቅኔ ዬገባውን ብቻ ነው። ሊህቅ ዕውነት ብቻ ነው በዕንባ  - ትርጓሜ። አማራ ነኝ ማለትን ያልደፈረ - ዬአማራ ልጅነት - ዬአማራ ሊህቅነት ማዕረግ አያሰጠውም። 

ድሮም እነሱ ድሎት ነው ዛሬ በጠላትነት ተፈርጆ ከሊቅ እሰከ ደቂቅ ዬሚደቁሰው። ዛሬም ያሉት ዬዛ ተልዕኮ አስፈጻሚዎች ናቸው። ከዘመነ ዬትግራይ መሳፍንት በላይ ሌላ ሰቆቃ አንዣቦ - እነሱንማ እያዬን ነው። ዬወገን ሞት - ዬሺህዎች ዬአማራ አርበኞች እስር - ዬመርዝና ዬቦንብ ስንቅ ሲሆን ለእነሱ ልቅና ዬአንድ ዬፖለቲካ ድርጅት አንድ ቀንጣ ነፍስ ያሰናዳው ማኒፌስቶ ይበልጥባቸዋል። አልጎረበጣቸውም። ዬእሱ ዬተጋድሎ ገድል እሱ ባልተገኘበት ለቀረመት ሲውል አያርመጠምጣቸውም። ገድሉና ታሪኩ በጠራራ ጠሐይ ሲነጠቅ አላንገበገባቸውም

ዬአማራ ሊሂቃን ከዞጋቸው ዬሚበቅልን ብቃት ነቃዮች ናቸው። ዬአማራ ሊሂቃን ቢበዛ ቢያስከትሉ ሥጋ ወንድማቸውን። ዬገብያው ሰው ሁሉ ዬእነሱ ስለሚመስላቸው ካለ አጥር - ቅጥር ብቻቸውን ይሮጣሉ - ሲወድቁም እንዲሁ። ለዚህም ታላቁ ዬብዕር ሊቅ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ ዬቅርብ ጊዜ ምሳሌ ነው።

በዓመታቱ ምን ተደመጠ? ሥሙ ተነሳ? አሟሟቱ እራሱ እንደ ክቡር ሳይንቲስት ኢንጂነር ቅጣው ዬተከደነ ነው። ሌላው … በሌሎች ሊቃናት ደግሞ ኢትዮዽያዊነት ጉልቱ ምላስ ላይ ብቻ ነው ዬሚቀረው። ሁሉም በህሊናው ዮዞጉ ጣዖት አምልኮ ተገዢ ነው። ገና አዲሱን ንድፍ ሲያስበው መዋቅሩን ዬሚሞላው ዬዞጉ መንፈስ ነው። 

„ዘመድ ከዘመዱ … „ እንዲሉ። አጥር ቅጥሩን አሳምሮ ይገነባል። ዬተረፈው ዬቦታ ድልድል ለሌሎች ከአማራ ውጪ ይመደባል። አማራ ዬሚመጥን ዬለም ዬሚባለውም ለዚህ ነው። አማራ ሴቷ እንጀራ በመጋገር ወጥ በመሥራት - ወንዱ ለዘበኝነት ለውትድርና ነው መደቡ። ዬወያኔ ተግባራም ይሄው ነው።
እህህ! ሁሉም ነፍስ ዬሚንቀሳቀስበት መሬት በቀይ መብራት ሲጋይ - ዬትግራይ መሳፍንቶች እትብት ግን ዬደረሰባት ዬለም። 

ለዚህስ ምነው ብዕረዎት ታቀበች? ኢንተርኔቱም አለ። ሌላው በጨለማ ዋነኛዋ ልዕለ ርዕሰ - መዲና ትግራይ መደበኛ ተግባሯን ተረጋግታ ትከውናለች። ይሄ ይደላል - አይደል? ጎሽ ያሰኛል¡ ዬጀግኖች ቁንጮ አቶ አታላይ ዛፌ ሰቲት ላይ ዬደረሰባቸውን ሲገልጡ ሰውነቴን ነበር ዬወረረኝ። „ተጠማኝ ሲጠግብ ባለ እርስት“ ይሆናል እንዲሉ።  ይብቃኝ። ደህና ይሰንብቱ - በትሁት መንፈስ።

·       ዬውጫሌ ውል አንቀጽ 17 ሳቢያ ነበርን?! ዕውነትን ያነጠረ ተጋድሎ
 ሳቢያ ሳይሆን ዬምክንያት ጭንቅላት ነው።

„ዬኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት ካውሮፓ ነገሥታት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ በኢጣልያን መንግሥት አጋዢነት መላላክ ይቻለዋል።“ ይህ አንቀጽ ዬዓለምን ጥቁር ህዝብ ነፃ ያወጣ ዬህልውና መሰረት ነው፤ መብቱን ለሞግዚትነት ለመስጠት ያልፈቀደ ዬጥቁር ህዝቦች ጠሐዬ ነው። ነባቢተ ነፍሱ ዬጎንደሩ አብዮት ዬአማራ ዬህላዊነት ፈጣሪም ዬምክንያት ጭንቅላት ነው።
 
ዬጎንደርን አብዮት ጥያቄ ዬትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ሊመልሰው 
አይችልም። በትግራይ መንግስት ሞግዚትነትም ዘላቂ መልስ አይገኝም። 
ዬእሱ ወኪሎች ባልተሳተፋበት ዬአለው ህገ መንግስትም አቅም ዬለውም። ጥንታዊ ተፈጥሯዊ ደንበሩ ማንም አስምሮ አልሰጠውም  - አባቶቹና 
እናቶቹ ደማቸውን ገብረውበታል። 


ትግራይ መቼ ነው ዓለምዐቀፍ ድንበር ኑሮት ዬሚያውቀው - በታሪኩ? አሁን አለው። ዬሰቲት ከኤርትራ ጋር በኡምናሃጀር በኩልም እንዲሁም በሱዳን በኩል ያለው ወስን ገበጣ ጨዋታ አይደለም። ደም ነው! አጥንት ነው! ቀልዱ ይቁም!

ስለሆነም ሰሞኑን ዬሰማሁት ቃለ ምልልስም ስለ አለ እግረ መንገዴን ማስተካከያ መስጠት እፈልጋለሁ። ከጉዳዬ ጋርም ተያያዥ ስለሆነ፤ አብዮት ዬትም ቦታ ሊነሳ ይችላል። በዚህ እስማማለሁ። 

ሳብያ ዬአብዮት መቀስቀሻ ሊሆን ይችላል በዚህም እስማማለሁ። ሳቢያን ዘሎ ምክንያትም ዬአብዮት አዲስ ምዕራፍ ከፋች ሊሆን ደግሞ ይችላል። በምክንያትና በሳቢያ መሃከል ሰፊ ልዩነት አለ። 

ዬአማራ ተጋድሎን የወለደው የጎንደሩ አብዮት የወልቃይትና ዬጠገዴ ዬማንነት ዬብሄርተኝነት ጥያቄ ህዝባዊ ንቅናቄ ሳቢያ ሳይሆን ምክንያታዊ ነው።
ሰሞንተኛም አይደለም። በመቅድምነት በሀገራቸው ዱር ቤቴ ብለው እነ አርበኛ አበጀ በለው ዬታገሉለት - በኋላም በተለዬ በትጥቅ ትግል ሆነ በሰላማዊ ትግል ሲታገሉት ዬነበሩ ዬተደራጁ ተቋማት መሬቱ ላይ አሉት። ብዕርም አላረፈችም ዬአፈርዬወሰን ጉዳዩ ዬደም ጥሪ ነው።

ዕምቁ ቁስለት ብሄራዊ ሆኖ አደባባይ መዋሉ ነው አዲሱ ነገር። እምቁ ዬአማራ ክብር ዘረፋ ከብሄራዊነት አልፎ ዓለም ዓቀፍ ዕውቅናው መጎልበቱ ነው አዲሱ ትዕይንት። እንዴት እንደሚያርመጠም እኮ ተውልዳችሁ ስላላያችሁት ነው። እሳት እኮ ነው እረመጥ! ይህን ዬሃቅ ምስባክ አጋድሞ ማዬት አይቻልም። ዕውነት ደፋሩ አለና።አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ“  እንዲሉ

ዬህልውና ተጋድሎው ርዕሰ አጀንዳ ይዞ ነው ዬተነሳው። ህዝባዊው ንቅናቄው ያልተደፈረውን ዬፖለቲካ ዓናት ዋልታው አድርጎ ነው ዬተነሳው።ልዑዐላዊነቴ ይጠበቅ! አገራችነን አሳልፈን ለሱዳን አንሰጥም!ሲል፤ ዓለም ዓቀፋዊ ድምጽ ነው፤ ሀገራዊ ዬሆነ ዬወሰን ጥያቄ ነው - ዬነጠረ።ድንበሬ ተከዜ ነው!ሲል አባቶቼ የከፈሉት የደም ዋጋ ይከበርማለቱ ነው፤ብሄራዊ ዓርማዬ ቀዳማይ ነው!ሲል ጠረኔ የአባቶቼ  - የጀግንነት ውሎ -ህይወቴ ነው ማለቱ ነው። በብሄራዊ ሰንደቄ አትደራደሩ ነው - ዕድምታው።

ዬወገኖቹን ደም አልግባብ ፍሰት ይቁም! በማለት በድፍረት ሲያወግዝኢትዮዽያዊ አብሮነቴ ላይ እቃ እቃ አትጫወቱ ማለቱ ነው።አማረነት አሸባሪ አይደለም! አማራነት ይከበር!  የማንነቴ ደሜ - አማራነቴ ኩራቴ - አማራነቴ ጨዋነት ክብሬሲል አትዳፈረኝ እኔ ዘብሄረ - አማራ ነኝ ማለቱ ነው፤ድምፃችን ይሰማ!ሲል ዬሃይማኖት ጣል- ቃገብነት ይቁም ነው።

ከዚህም ባላይ ዬሆነው ድንቅ ነገር ከመጨረሻው ዬፖለቲካ እርከን ዬደረሰው አቋሙ በቃኝ! የጥቂቶች አንባገነናዊ ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ አገዛዝ። አዲስ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እፈልጋለሁ። አንተ ግን በቃህ በእኔ ላይ ዬጫንከው ህግ ከእንግዲህ በእኔ ላይ አቅም እንዲኖረው አልፈቅድለትም። ዶሮ ጠባቂ አድርገው። እኔን ለመግዛት አቅምም አቋምም ዬለህም ብሏል።ጎጃምም በደሙ አትሞበታል። ታዲያ ምን ተፈልጎ ይሆን ዬሳቢያ እራፊ ዬተጣለለት? ይገርም ዘመኑ ….

ሳቢያ ዬሚባለው ዬደሞዝ ጭማሪ፤ /ቤት - ክሊንክ - መንገድ አልተሰራልንም ቢል ነበር። ሥራ ስጡን አላለም። መንፈሱ ኢትዮጵያን በስር ነቀል ለውጥ ዬእኩልነትና ዬፍትህ ሀገር እንድትሆን ነው ተጋድሎው። ስለዚህ በመላሾ፤ በጥገና፤ በተሃድሶ፤ ገድሉን ማደናቀፍ አይቻልም። ሳቢያ አይደለምና።

ለዚህም ነው እንኳንስ መተርጎምና ማመሳጠር ገድሉን፣ ተጋድሎውን ማንበብ አልቻልነም ያልኩት። ደግሞ ሁሉንም ራድ አስይዟል። ዬዘገባው ሽፋኑ ይቁም እስኪያሰኝ ድረስ። እማይገባን መሰላችሁ ----ን?

ኪዳኑ - ህዛባዊነት፣ ጠረኑ - ብሄራዊነት፤ ትንፋሹ - ጀግንነት፤ ቀለመ ብሩህ - ዬአብሮነት ራዕይ፤ ውስጡ  - ሰባዊነት፣ ነፍሱ -ድርጁ፤ አፈፃጸሙ - ብልህነት፤ ራዕዩ - ዬጠራ፤ ህልሙ - ትርጉም፤ ዕድምታው - ቅኔ፤ ምኞቱ - ርትህ። አጀንዳው ኢትዮዽያዊነት። ረቂቅ፦ ሥልጡን፦ የፍቅራዊነት ዕልፍኝ። ዬእኩልነት ዓምድ። ይሄ ልቅና ከዬትኛውም ዬፖለቲካ ድርጅት እቅም ጋር አይመጣጠንም። ትውልዱ አንቱ ነው - ዬቀደም። ስለሆነም ሳቢያ ሳይሆን ከምክንያት በላይ ዬሆነ አንጎል ነው።

ሳብያና ምክንያት ዬማሌ ፍልስፍና ዬትምህርት መንትዮሽ-ዘርፎች ናቸው። ሥርጉተ ኮርሱን መውሰድ ብቻ ሳይሆን - በቋሚ ዬፖለቲካ ሠራተኝነትም ተግባሩን ኑራበታለች። ገድለኛው ዬጎንደር አብዮት ዬነፃነት ተጋድሎ ህላዊ መንፈስ በእንቢተኝነት ዬተቀመረ በፍጹም ሁኔታ ዬተደራጀ፤ ሥልጡን - ዬበቃ ዬአመራር ክህሎት ቃናዊ ሞዴል ነው። ስለሆነ ሳብያ ሳይሆን ዬምክንያት ማዕከላዊ ሴል Nucles ነው። ባለቤቱም ህዝብ ነው።

ሰው ዬዘራውን ብቻ ነው ማፈስ ዬሚችለው።በአማራ መቃብር ላይ ታላቋ ትግራይን እንመሰርታልን ይህ ለወያኔ ልቡ ነው ዬደሙ መዘወሪያ። ዬአንድም ዬፖለቲካ ድርጅት ማኒፌስቶ  በአማራ መቃብር   ላይ   ዬምትገነባ  ሀገር    ሳይሆን    - በትግራይ   ነፃ   አውጪ ማኒፌስቶ  መቃብር ላይ - አማራውን   ዬጨመረ   ዬእኩልነት  ሀገር ታላቋን ኢትዮዽያን  ለመመስረት  እንታገላለን    የሚል ዬደፈረ - እሩቁን ጊዜ ከብሩህ ዬአለኝተኝነት ተስፋ በብልህነት አዋዶ ትግሉን አህዱ ያለ አለን?! 

ይህ መሠረታዊ ዬነፃነት አስኳል ተቀብሮ ቆይቶ የመንፈሱ ትንሳኤው ዬታወጀው፣ በጠኃዩ ዬአማራ ተጋድሎ በጎንደር አብዮት ነው። ይህ ደግሞ ቅርፃዊ ሰይሆን ይዞታዊ ዬሆነ ዬነፃነት ተጋድሎ ነው፤ ለመሆኑ ዬውጫሌ ውል አንቀጽ 17 ሳቢያ ነበርን??

ይህን ዬሚመልስ ህሊና ዬአማራ ተጋድሎን አብዮት እውቅና ለመስጠት ከወገብ በታች አይራመድም።  ተንሳፋፊም አይሆንም። ተጋድሎው ሥር - ነቀል ለውጥ በመንፈስም በአካልም - ሁሉንም ከውስጡ መለወጥ እንዳለበት በአጽህኖትና በተደሞ አስገንዝቧል - ለዛውም በጨዋነት።
 
ስለሆነም ዬጎንደሩ አብዮት በዬትኛውም ዬፖለቲካ ድርጅት እጅ እንደ ዳንቴል ያልተሰራ - ምክንያታዊ ዬበቃኝ ገድል ነው! እሬቻ ላይም ጀግኖች በቃኝ ወያኔ!“ በማለት ደም ገብረውበታል። ዬመደማመጡ ቀለሙ ሚስጢር ይሄው ነው። እኛ ዬመተርጎም አቅም ዬለንም። ሚሊዮኖችን - አሰልፏል። አንቅቷል - አደራጅቷል። ሊቃዊ - መገናኛ! ያንጎላቸ መንፈስን ሁሉ ተነሱ - እንነሳ ብሎ በተደሞ ቀስቅሷል … ከዛ በኋላ መንደፋደፍ ሆነ።

·       ዬታማኝነት -  ሽሽት ጅማሮ።

ጨዋታን ጨዋታን ያነሳዋልይላል ጎንደሬ፥ ቪዢን ኢትዮዽያን በሚመለከት አድናቆትም ክብርም አለኝ። ለጥረታቸውም ዬትህትና  -  ምስጋና። ስለሆነም ሁልጊዜ በራዲዮ ፕሮግራሜ እንዳለ ሙሉውን ሊንክ ሳደርገው ቆይቻለሁ። ወደፊትም ይቀጥላል። በቅርብ ጊዜ በተካሄደው ግን ቅሬታዬ ጉልህ ነበረ።
ዬአማራን በአማራነት መደራጀት ለሀገር ካለው ጠቀሜታ ጋር ያሰጋው ዬብዕር አባት - ባለቅኔ ዬፃፈው ስላልተመቸኝ ይህኑንም አክዬ ከአንድ ወር በፊት ገልጨለታለሁ። ዬተውኩትንም መፃፍ ያስጀመረኝም ዬእሱ ዬብዕር ንድፍ ሚዛናዊ ለማድረግ ነው።

ቪዢን ኢትዮጵያ ሁለት ዬኦሮሞ አክቲቢስቶችን ሲጋብዝ ለእያንዳዳቸው 20 ደቂቃ በድምሩ 40 ደቂቃን አስልቶ ነበር። ያው ተጋባዦቹ ባይገኙም። ነገር ግን ለዛ መንፈስን ላረካ፤ ዬእኛ - ዬሁላችንም ሊባል ይገባ ለነበረው ግን - ሰፍ ተብሎ ሙቀቱን ለመዝረፍ ዬሁሉ ዓይን ማረፊያ ዬሆነው ዬታሪክ ዓምድ ዬአማራ ብሄርተኝነት ተጋድሎ፤ አንድ አክቲቢስት 20 ደቂቃ። 

በውጥረት ተጀምሮ በውጥረት ተጠናቀቀ፤ አንዲት ደቂቃ ለመነ። ወይ መዳህኒተ ዓለም አባቴ! ወደ ሰላሳ ደቂቃ ዬሚሆን ነበር - መንፈሱም ጭብጡም ተቆራርጦ በጥድፊያ ተሰንጎ ዬፈጀው። ኢትዮ ሚዲያ ሙሉውን ባይለጥፈው ኖሮ እንደ ተጎዳሁ እቀር ነበር።

ለአንድ ዬፓርቲ ማኒፌስቱ መንፈስ ሊበልጡም ይችላሉ - በአማካኝ አራት አቅራቢ ነበር። 80 ደቂቃ ማለት ነው። ዬፓርቲ ጉባኤ እስኪመስል ድረስ። ተስፋ ዬተጣለበት ቪዢን ኢትዮዽያ፤ ለተመሰረተበት ዬድልድይነት ዓላማ ታማኝነቱ ሽሽት እንደጀመረም - አይቸበታለሁ። ይሄ ዬውስጥ ስቃይና ህመም እኔን ዬአማራ ደም ያለብኝን ዘብሄረ - አማራዋን እንጂ  - አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪውን ረመጡ - አያክትተውም።

አስተውሎትም ዬነበረ አይመስለኝም። ከአማራ ተጋድሎ ፍጥረተ ነገሩና እዬደረሰበት ያለው ዬማግለል ፖለቲካ በፊት ቢሆን ኖሮ -  እኔንም ላይገባኝ ይችል ይሆናል። አለት ነበርኩ - ዬሚላክልኝን ሊንክ ዬማላዳምጥ - ዝርዝር ዬማላነብ። ዛሬ ግን ጊዜ ዬገለጠልኝ ቁልፍ አለ። ሚዛኔ አማራ ላይ ሲደርስ ገልባጣ መሆን አይኖርበትምና። ቀደም ባለው ጊዜ ዬገነገኑ ጥቃቶች ሁሉ ስለምን ለሚለው መልስ ለማግኘት ተስኖኝ ነበር።

ዬሆነ ሆኖ መድረከ ላይ ያሉ ወገኖች - ዬአማራ ተጋድሎ አክቲብስት ወጣት አቻምዬለህ ታምሩ ፕረዜንቴሽኑን ሲቀርብ feedback ዬላከልኝ መልእክት ነበር። ስልቹ ፊት ነበር ያዬሁት እንዲህ ዬምንጠላ ከሆነ - ዬወተት ሙቀትን ማሳደድ ስለምን አሰፈለገ?

አደባባይ ላይ ዬወጡእንዳያማም ጥራው እንዳይበላም ግፋውዬመገለል ተራራዎች - በተናጠል ስንጠቃ ዬቆዬንበትን ዬጥቃት ዘመን መልኩን - ቁመናውን - ዛላውን በተጨባጭ ለማዬት አስችሎኛል። ስለሆነምበቃኝ!ዬሚባለው ወያኔ ብቻ ሳይሆን - ተመስጥሮ በትቅቅፍ ዬተያዘው ዬአማራ ጥላቻ ዬመንፈስ ጣዖት ጋርም መሆን ይጠይቃል። 

ብቻ … በፊትም - በጀርባም - በጎንና ጎንም ያሉትን አደጋዎች ዬጠላቴ ጠላት ወዳጄ ሳይሆን - በቅን ልቦና ሰባዕዊነትን ያከበሩ ንግግሮች አትኩሮቶች ያስፈልጋሉ። ለዚህም ነበር ቪዢን ኢትዮዽያ ዓላማዉን ሲያስተዋውቅ ከልቤ መንፈሴን ሸልሜው ዬነበረው። ሚዛን ዬጠበቀ ዬእኩልነት ቤተ - ዬሃሳብ ነፃነት ይሆናል ነበር ራዕዬ። ገለልተኛ ይሆናል ዬሚል ዕምነት ነበረኝ። በዝበት ለሚናጡ አመክንዮች መድህን ይሆናል ዬሚል ህልም ነበረኝ። ህልሜ ዬብትን አፈር ጥግ ያገኝ ይሆን?

·       ቪዢን ኢትዮዽያ ሆይ!

እውነት ለመናገር ለአድማጫችሁ፤ ለአድናቂያችሁ መንፈስ አልተጠነቀቃችሁለትም፤ ከተልዕኳችሁ ሁለመናነት አንፃር ተመጣጣኝ ዬሆነ ሚዛናዊ አስተዳደር - አላዬሁበትም ሌላው ቁም ነገር አንድ አቻም ብቻ አልነበረም - ሚሊዮኖች ለሚያቀርባቸው ፋክቶች ዘብ ይቆማሉ።


ብሄርተኝነትን ዬሚኮተኩቱ እንዚህ መስል ግዞቶች ናቸው። ዬንጉሦች ንጉሥ ዓጤ ቴውድሮስን ለዛ ድንቅ ኃያልነት ያበቃው ዬመናቅ፤ ዬመገፋት ግዞት ነው። „ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም።“ ልብ ከሸፈተ ዬአቅም ጎታም ይሸፍታል። „ከራስ በላይ ንፋስ“ እንዲሉ።

ሌላም በአጋጣሚ ማንሳት እምሻውዬድምፃችን ይሰማምጉዳይ ተጋድሎው ለዛሬም ለነገም ዬሰላማዊ ትግል ቋሚ ቤተ - መፃህፍታችን። ዝክረ - መዘክራችን ነው። ስለዚህአስታውሱን እስኪሉ ድረስ መጠበቅ አልነበረበትም። 

በእነሱ ዙሪያ ብቻ በ2013 ወደ 45 ደቂቃ ዬሚጠጋ ትንተና ቀርቦ አዳምጫለሁ። ለእኔ እንደዛ አክብሮት ማግኘቱ ዬሚያስወቅስ አልነበረም። በቅንነት ካዬነው። እርግጥ ዛሬ አቅማቸውን ስለ ገነቡ ጥገኛ ዬሚያደርጋቸው ምንም ነገር ዬለም። ተግባራቸው አንጥሮ አጉልቶ አውጥቷቸዋል። ዬተጋድሎ ገድሎችን ከፓሮፖጋንዳ ፍጆታነት አለፍ ያለ ዕውቅና ለመስጠት ወረተኛ ባንሆን ጥሩ ነው

 ድምፃችን ይሰማዬሰላማዊ ትግል ዬጽናት / ቤታችን ነው። ዬተስፋ ልምላሜ ቋታችን ነው። ደምም - ተገብሮበታል። ካቴናም ዕለታዊ ኑሮ። 

ዬአማራ ተጋድሎ ግን ሰብሉ በስውር ተመስጥሮ መጋቢ ማንፌስቶ ሆኖ - እንኳንስ 45 ደቂቃ ቀርቶ አማራ ማለት ወንጀለኝነት ሆኗል። አማራ ሆኖ መፈጠርም። በዘመቻና በንቀት በመሳደድ ላይ ይገኛል። ቅዱሳን መላዕክት በአንደበታቸው ቃሏን እስኪያወጡ ድረስ ባዶ ስድስት ተበይኖበታል። ከቶ አንቺ ዕውነት ሰው ሆነሽ ችሎት ብትገትሪው ዕብለትን ምን በነበረ?

ዛሬ … ዬአማራን ድንቅ ተጋድሎ ከሚያቃልሉ መንፈሶች በስተቀር - ዬተጋድሎውን ገድል ዕውቅና በሰጡ ቅን ዬኦሮሞ ፕሮቴስት አክቲቢስቶች ሳይቀር በአንድም በሌላ ዬውግዘት ዘመቻው ቀጥሏል። 

ለውጭ ዜጎች አድማጭ፤ ጥሪን አክብሮ ዬተገኜ እንግዳ ንጉስ ነው። ለእኛ ደግሞ እንደ መናኛ ዬሚታይ ማበሻ ጨርቅ…. ስለሆነም ዬአማራነትን ስሜት ኮትኩቶ በማሳዳግ ቀጣዩ ትውልድ እኛ ያለፍንበት ዬሽታሽቶሽ ዬሥነ - ልቦና ጥቃት መውረስ አይኖርበትም።

ይህንን ቁልጭ ብሎ ዬሚታዬውን መገፋት፤ እንደማይጠቅም እቃ መታዬትን፤  መድህኑ ዘብሄረ - አማራ በጥራትና በብቃት ጸጋዎቹን ሁሉ ተጠቅሞ መደራጀት ሲችል ብቻ ነው። ዬሽፍንፍን ኑሮ መቃብር ላንመለስበት መቀበር አለበት። ኢትዮዽያዊ ዜግነታችን እኮ ተቀምተን ነው በያልፋል - እምንኖረው። ዕምቅ ህመሞች አሉብን።

 ዬነፃነት ትግሉን አቅም እንዳያኮስስ በመስጋት ነው ዝም ያልነው እንጂ፤  በዬትኛውም ሐገር ስደተኞች ታሪክ ታይቶ - ዬማይታወቅ ድርብ ጭቆና አለ በኢትዮዽያውያን ላይ። ስለሆነም ከዘርፈ ብዙ ዬብረት ካቴና እስር ዘብሄረ - አማራን ለማስፈታትአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪነትሳይሆን ይህን ዬገነገነና ዬገረዘዘ ዬሥነ - ልቦና ጫና ማስወገድ ዬሚቻለው የአማራ ደም ያለበት - ለጉዳቱ ቅርብ ስሜት ያለው ተቋም ብቻ ነው።
 
በድርድር ዬአማራን መንፈስ አቅርብልኝ ተብሎ ዬሚሸለም-ም አይደለም። ደሙ ሲኖር ብቻ ነው ለአወንታዊውም ሆነ ለአሉታዊው በኽረ ብይን መስጠት ዬሚቻለው። ስለሆነም በጠራ መንፈስ ለህመሙ፤ ለቁስሉ መጣኝ ፈውስ እስኪያገኝ ድረስ ብቻ ሳይሆን፤ ለዘላቂ ህልውናው አስተማማኝ - ከብረት ቁርጥራጭ ዬተሰራ ቋሚ ተቋም ያስፈልገዋል። ለሁልጊዜም ጽኑ ጠባቂ ኃይል።
እኛ ለሌላው ክብር ልዕልና እራሳችን እንደ መስቀል ርሚጦ እዬረመጥን - ተሞግተናል በዛም ዬመጣውን ጅራፍ ዕጣ ነፍሳችን ሁሉ አስተናግደናል። ሁሉንም  ተቀብለናል። 

አይዟችሁ ቀርቶ- ግልምጫውና መሳደዱ በቀረልን ምንኛ መታደል በሆነ ነበር። ዬሆነ ሆኖ ለዘብሄረ - አማራ ማንም ዬለውም። ያለው ራሱ ብቻ ነው። ግን ዬአባቶቹ አምላክ ፈጣሪ አለው። በዚህ ልጽናና …

·       „አዲስ አበቤዎች።“

በሉን ስለተባለ ትእዛዝን መተላለፍን አጽመ ርስታችን ዬሆነው ደማችን ይጸዬፈዋል። እኛ ዬአንድን ሰው ተማላ ፍላጎት እንዲህ እናከብራለን።
አማራነት መርህነት ነውና። አማራነት ሕግ አክባሪነት ነውና ነውና! 
ሌላው ደግሞ ዬምዕላቱን ዬተጋድሎ ገድል „ዬአማራ ተጋድሎ“ ለማለት „ዬአማራ ተጋድሎ ዬከፋኝ ሠራዊት፤ ኃይል“  ለማለት ከሊቅ እስከ 
ደቂቅ ምጥ ላይ ይገኛል።

ዬሆነ ሆኖ ያው ዬፋርጣ ልጅ ስለሆንኩኝ መውጫ መግቢያውን ባላውቀውም፤ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ግን አዲስ አበባን በሚመለከት ከመጀመሪያው መሪ ሃሳብ ብነሳ - መከራ ዬሥልጣኔ ደረጃን አይጠይቅም። ጎንደር ደግሞ ርዕሰ መዲና ዬሆነችው ከአዲስ አባባ በፊት ነው፤ ሥልጣኔውም እንዲሁ።

ዬፎቅ ሳይሆን ሃብታችን ዬሥነ-ልቦና ሥልጣኔ ልቅና ነው ያለን። ዬዓለም ዬቅርስ ባለውለታነታችን እንደ ተጠበቀ ሁኖ። ሁለተኛው ደግሞ ዬአዲስ አበቤዎችን ሰላማዊ ሰልፍዬኦሮሞ ማህበረሰብ ዓርማ“ አስደነገጠው ሌልኛው መከራከሪያ ነጥብ ነው። ሀገራዊ ዬአራት ፓርቲዎች ህብረ - ስምምነት ውይይት ላይ እኮ ከብሄራዊ ሰንደቅ  - ዓላማው እኩል ሆኖ ፊት - ለፊት ነበር፤ ኮከቤ ዬሚላቸው ልጆቹ ዓርማው ባለበት ንግግር ሲያደርጉ ተመልክቷል፤ ዬኦሮሞ ፕሮቴስት ወጣቶችም ይህንኑ ዓርማ ይዘው ሲወጡ አይቷል።

ስለዚህ ይሄ ዬሚያስበረግገው አይመስለኝም ልምምድ / ቤት በአንድም በሌላም አዬተደረገ ስለሆነ። እኔ ዬአመኔታ ማጣት ችግር ይመስለኛል። ተቀጥቶበታልና ስለዚህ ህሊናን ዬሚለውጥ አመኔታን ገላጋይ ዕውነትን
ይሻል።

አዲስ አበቤ መቼስ በራዲዮና በቴሊቪዢን አዬር ላይ ህዝብን ማደራጀት አይቻል ነገር። ለሙቀቱ ቅርብ ስለሆነ - ዜና እና ፕሮፖጋንዳንም ለይቶ ያውቃል። ዬቤተሰቦቹን መርዶ በቅርብ ያያል። እስሩም ህይወቱ ነው። 


ዬአማራ ተጋድሎ መስዋዕትነቱ ዕውቅና መነፈጉ ብቻ ሳይሆን ባለቤትነቱንም መነጠቁን አሳምሮ ይገነዘባል። በተደሞ ሃቅን ያበጥራል፤ ስለዚህ ላልጠራ ራዕይ እንደ ቀደመው እራሱን ለመገበር ዕሴቱ አስተማማኝ መሰረት ይሻል። ማገዶነት ለብላሽ እንዳይሆን ይሰጋል። ያለው ለዚህ ይመስላል።

ህዝባችን ንጽህና ዬመንፈሱ ገዢ ነው።  ዘብሄረ - አማራ ከሀምሌ እስከ ህዳር ዕጥነት ድረስ ያደረገው ዬጀግንነት ተጋድሎ በሥም አልቦሽነት ሲላወስ ከቆዬ በኋላ - ዬሌላ ገድል ተብሎ ዕወጃን አዳምጧል። ዬሚቀድመው ዬባለቤቱ መነሻ ክብር መሆን ሲገባው - ዬደሙ ግብር ለፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ለጋሲ ተሸለመ።
ለተራበ ትቼ ለጠገበ አዝናለሁ“ ሆነ ነገሩ። 


ዬሀምሌ ዬጎንደር አብዮት ባይነሳ እንደ ተለመደው ለሽ ነበር። አምና ታች አምና ምን አዬን? ምን ሰማን? እሰጣ ገባ ዬለ - ፊሽካ ተነፋ ዬለ። ድል ዬገባ በደጅ ይመስል - ጸጥ እረጭ ነበር። ይሄን አዲስ አበባ ያለው ዬአማር ልጅ ልብ ይላል። እኛ እንኳን አላዬንህም - አላሰማንህም ብንል -  እሱ ግን ዬወላፈኑ ጠረን ተጋሪ ነውና ማግስትን አጥብቆ በአጽህኖትይፈራዋል። ለዚህም ነው ዬጎንደሩ ዬአማራ ገድል በሳቢያነት ብቻ ተትበስብሶ -  ዬውሽማ ሞት ሆኖ እንዲቀር ዬተፈለገው።

ጀግናችን ኮነሬል ደመቀ ዘውዴ፤ ዬድንቅነት መርህ ንግሥት ይርጋ እና ሌሎችም ውሾን ያነሳ ዬሆነው። ባይነሳ ዬሚመርጡ አሉ - ግን አይቻልም። በማናቸውም ዬዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ዘገባ ላይ ዬአማራ ተጋድሎን ምሶ ዬሚቀብር ስለመሆኑ ሳይታለም ዬተፈታ ነው።  

መቆናጠጫ ቦታ ከተያዘ በኋላ ደግሞ ቁርጥ ያለች ቀጭን ትእዛዝ ይመጣል። እዬለቀምክ አስወግድ! አይቀሬ ነው።  ዬበቀል ምላጭ ይሳላል።እጸድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች።“ እንዳይሆንልብ ያለው ሸብ።“ ዬደነደ ልብ ከጉልበታም አቅሙ ጋር መጥቶ ሊደፋበት ይችላል። ተቀማጭ ዬሆነውም ለዚህ ይሆን? አላውቅም -  ዬማይመች ጠረን እዬሸተተኝ ነው።

ትናንት በቃለ- አቀባይነት ዬሰማነው ድምጽ ዛሬ ዬለም። (አርበኛ ዘመነ ካሴ በአርበኛ መንግሥቱ ወ/ዬስ ተተክቶ VOA ላይ አዳምጫለሁ። አርበኛ ዘመነ ካሴ አንድ ነገር ቢሆን - አምኖ ዬተከተለው ዬአርበኛ አንዳርጋቸው መንፈስም ይፋረዳል። በብቸኝነት ዘመናቸው ዬተከተላቸው ዬቃል ኪዳን በኽረ ልጅ ነው። አደራ መብላት ትውፊታችን አይደለም። ለእሳቸው መንፈስ ሲል ነው እንዲህ በጨካኞች አድራሻ ዬለሽ፤ አስታዋሽ ዬለሽ ሆኖ ዬሚታዬው።) ለነገም ዋስትና ዬለም። ከዛም መታረድ --- ኑሯቸውን ትተው እንደፈጣሪያቸው ዬሰውን ልጅ አምነው ተሰደው። በመሬቱም መቀቀል። ዬቀዬ ትውልድ ዬትናንቱ ላይበቃ ዛሬም በሁለት አውሬዎች ተጠበሰ።

ራሱ አዲሱ ቃል አቀባዩ ዬሰጡት መግለጫ ኃላፊነትን ለመሸከም ሙት ነበር። አቅሙን ያጠናም አይደለም። ዬኦሮሞ ፕሮቴስት - ዬአማራ ተጋድሎ ዬእኛ ዬመንፈስ ገድል ነው ይል ነበር።  ማደራጀት በቃ ጋዜጣ ላይ ዬሚጻፍ ቃለ - ማህላ መስሏቸዋል።

 „ከላበደ በቀር ዱባ ቅል አይጥልም“ ማደራጀት ሳይንስነቱ ዬህሊና ለውጥ መሬት ከያዘ ዬተጨበጠ ተግባር ጋር ሲዋህድ - ሲከወን ነው። በስማ በለው ህዝብ አይደራጅም።  ይህን ደግሞ ወላፈኑ ላይ ያለው ያውቀዋል። እኛ በስሚ ስሚ ነው ሀገር ያለውን ዬአሁኑን ዬምንሰማው። ለእሱ ግን ኑሮው ነው። ይህነን ድንቡልቡል ጉድ ዬሰበረውን መንፈስ እንዴት ማቃናት ይቻላል? ታማኝነት እዬተናደ ነውባለተመዘገበበት ዮፖለቲካ ድርጅት „አባሌ ነህ፤ በአንተ መሰረትነት መዋቅሬን ዘርግቻለሁ፤ ለፋሽስት ግድያ፤ አፈና ዕውቅናውን በፊርማዬ አረጋግጫለሁ“ እዬተባለ።

በራሱ ዬነፃነት ፍለጋ ጉዞ ጋሬጣ ሲተከልበት ምን ይሁን? ይህ በፍፁም ሁኔታ ከብዙኃን አሜኔታ ጋር ከመቃብርህ ላልቆም ያሰኛል። ማደራጀት እኮ መሬት ላይ ዬበላውን በልቶ - እሱን ሆኖ- ችግሩን ተጋርቶ አፈሯ ላይ ተኝቶ ዬረዥም ጊዜ ዬትእግስት ተግባር ነው።

ዬእነ ዳዛን አቀበት ለመውጣት 6 ሰዓት ይፈጃል። ጫካው ከቁመት በላይ ነው። አንድ ሰው በጉዞ ላይ ቢዘገይ ዬሆነ ዛፍ ያስፈልጋል እዚህ ነኝ ለማለት። ቆለኛ ቁጭ ብሎ ስብሰባ ተሳትፎ አያውቅም። ዬተኳሽነትን ሰብዕና ተላብሶ በርከክ ብሎ ነው ዬሚያዳምጠው። ሴቷ ነጠላ ለብሳ ሳይሆን አደግድጋ ነው።

ከቅፍትያ እንቃሽ ወር ባልሞላ -  ዬሀገሬው ሰውም አይችለውም እንኳንስ ሌላው - ሥርጉተ እኮ ዬጋሜና ቁንጮ ዘመኖ በማደራጀት ሙያ ስክን ያለ ነው። ከአንዱ ወረዳ ወደ ሌላው በእግር ለመጓዝ በሰላሙ ጊዜ ከ7-10 ቀን ነው።


 ሁሉሙ ዬመንፈስ ወታደር ለመሆን ከእውነት ጋር መታረቅን ይጠይቃል። ዬተግባር መሪው ያልሰከነ ጋላቢ ስሜት አይደለም ዬማሸነፍ ኃይሉም ቅጥፈት አይደለም።  ያስገምታልመስዋዕትነት በገብያ ህግ አይተዳደርም።
በመላ ኢትዮዽያ በትንንሽ ከተሞች ሳይቀር መዋቅራችን አለ። ዬህዝባዊ አብዮቱ ባላቤቶች እኛ ነን። (አቶ መንግስቱ ወ/ ዬስ ዬአግ7. ፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊና ቃለ አቀባይ)“ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተሆኖ - ዬታሰረው ከ40,000 በላይ ዬሆነ ወጣት እንዲረሸን ዕውቅና መስጠት።

ይህ ሰብዕዊነት ዬሚባል ዬርህርህና ክኒን እንዴት በጥብጦ መጋት ይቻል ይሆን? ይኽው እያደመጥ ነው ዬፋናዬን ዕንባ እዬተጣራ ነው ሰሚ ቢገኝ? … ሰፊ ህዝብን ካለ ብጣቂ ርህራሄ ፋሽስት እንዲያርደው ሳንጃ ማቀበል ምን ይባል ከቶ? እንዲያው ምን እንበለው?   „ዬኦሮሞን ከአንድ ዓመት በፊት አሁን ዬወልቃይት ጠገዴን  ሁሉሙ ዬእኛ ሃብት ነው።“ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ“ ያሳፍራል! ያሳዝናል!

ታዲያ ሌላ ቦታ ለምን አልተቻለም?  … በሁሉ ቦታ ከሆነ … ዬውሸትም ዓይነት አለው። „ዬያዝካቸውን ጨርስልኝ - ለእኔ ለውጩ ማህበረሰብ ደህና ዬፖለቲካ ዬደም ትርፍ ይሆንልኛል ለአንተም ለወንጀልህ መሸፈኛ“

አቤት! ------------ ያአንተ ያለህ ዬእኔ ጌታ …
 ዬህዝብህ ዕንባ  -------- ሆነ ከርታታ!

አቤት ጭካኔ!“ ዕንባን እንጠብቃለን። አድሮ ለሚገኝ ነገር ድፍረትን መሸሸት በፍጹም ሁኔታ ዬተስፋም - ዬታማኝነትም ገዳይ ነው - ጤዛ!  ---በንጽህና እና በቅድስና ዬሚካሄድ ተጋድሎ በሌጋሲ፤ በኢጎ ጥማት ጋዬ። ሺዎችንም ለእርድ …. በዚህች መሬት ምን ያህል ጊዜ ልንኖር ይሆን? „ዬትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው።“ መረዳዳቱ መልካም ቢሆንም ክንዳዊ ታሪክን መንጠቅ ተፈጥሯችን - አይደለም።

አቶ መንግስቱ ወ / ዬስ ግንቦት 7 ሲፈጠር ምንም ዓይነት ፖሊስ ዬሌለው መሆኑን እራሱ አያውቁም። ዬኦሮሞ ፕሮቴስት ዬማስተር ፕላን ሆነ ዬጠገዴ ወልቃይት ጉዳይ - ግልጽ ዬሆነ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖሊሲዊ ንድፍን ይጠይቃል።

በሱዳንና በኢትዬዽያ ዬድንበር ጉዳይ ሳንዱች ዬሆነ ህዝብ አለ። በሱዳን ወታደር እና በወያኔ ሠራዊት። ለዚህ አቤቱታ ዬድንበር ኮሚቴው ፊርማ ባሰባሰበት ወቅት ላይ ግንቦት7 እንደ ዬፖለቲካ ድርጅት አልፈረመም። ያን ጊዜ እኔ ስከራከር - ሽንጤን ገትሬ ስሟገት ዬነበረበት አመክንዮ ግንቦት7 ፖሊሲ ስሌለው ተጠያቂ ሊሆን አይገባም ብዬ ነበር። አሁን ደግሞ ቴርሞ ሜትሩ ሲግል ዬእኛ ነው። እውነት - እግዚኦ! ያሰኛል። ከምን ላይ መንፈሳችን ይረፍ?

ወያኔ ጫካ በነበረበት ጊዜ ራዲዮ ፕሮግራሙን እከታተል ነበር። አጫጭር ዬራዲዮ ድራማዎችም ነበሩት። አንድም ቀን መዋቅራችን ውስጥ ለውስጥ ዘርግተናል ብለው አያውቁም። በዚህ ጥንቁቅነታቸው አባሎቻቸውን፣ ተከታዮቻቸውን አትርፈዋል። ተቀናቃኞቻቸውንም አሸንፈውበታል። ፈተና ዬማይረታው መስመሩ ዘር ነው። አባሎቻቸው ከላይ እስከ ታች በመንግስትና በፓርቲው መዋቅር ሆነው ሙሉ ፍላጎታቸውን በሙሉ ነፃነት ተረጋግተው ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ዲስፕሊናቸው ብረት መዝጊያ ሆኖላቸዋል።

ኢፌድሪ ተደራጅቶ ነው ዬጠበቃቸው - ለህወሓት። ሁሉም ክ/ ሀገር ከሁለት ከሦስት ሲሸነሽ ትግራይ ራስ ገዝ ነበር። በለስ ቀንቷቸው ውጭ ሀገር ዬሚወጡት እንኳንስ ያን ጊዜ - ዛሬ ሁለቱም ሻብያም ወያኔም ሥልጣን ላይ ሆነው - ዬውስጥ አርበኞቻቸው ዬአንድነት ኃይሉ ባለሟል - ዬፖለቲካ አማካሪ ናቸው። ሚዛን እንዳይዛባ ቀጥ ብለው ዘብ እንደ ቆሙ ናቸው። ዬሚወገደውን በግራና ቀኝ እያስወገዱ - ዬልባቸውን እዬሠሩ። ዬእኛ ዬፖለቲካ ፓርቲ ዲስፕሊን ደግሞ ዬማስታወቂያ ሰሌዳ፤ ፖስተር።

አዳምጡት በአክብሮት VOA Presents Arebegnoch Ginbot 7 Spokesperson

ዬሆነ ሆኖ አዲስ አበባ ላይ ከሦስት ዓመት በላይዬድምጻችን ይሰማ“ ተጋድሎ ጥንካሬ ሥነ - ሥርዐታዊ ዬአመራር ጥበብ ያስገኘው ዬሰላማዊ ትግል ቅኔ ነው። ዬጣይቱ ልጆች ዬኮፐን ሀገን ዳግም ትዕንሳኤም ለእኛ ለሴቶች ልዩ ቃናዊ ዬታሪካችን ጉልላት ነው። 

ስለዚህ መሬት ላይ ከተኖረ በህሊናዊ ሥራ ላይ ማተኮሩ መልካም ነው። ዬደመቀውን ምጣድ ላይ አቅም ከማፍሰስ - ባልደመቀው ምጣድ ወይራ ፍልጦችን ማቀራረቡ ይሻላል እንላለን እኔና - ብእሬ።

ተግ ያለው ዬአዲስ አበቤዎች ብዕርም እንዴት ሊያስተዳድሯት እንዳሰቡ ተጀምሮ ስለተቋረጠ ቢቀጥል አይከፋም። ብርድ ብርድ ብሎትም ከሆነ ካፌኖሏን። ዬጉዞ ፕላኑም መውጫ መግቢያው ለፋርጤዎች እንዳይጠፋን አብሮ ይጣፍልን ብለናል። አልሰልጥኗችን ለህትም እንደበቃው ሁሉ። ሌላም ዬአዲስ ዙሪያ ገባ በአብዮት ወላፈን ሞቅ ደመቅ ባለ ሰሞንዬአንድ ዞግ ዬእምቢተኝነት ድምፅ“  ተብላ ብቅ ብላ ወደ ጫጉላ ዬተመለሰች ነበረች -  እሷም ታቱ ብትጀምርስ …..?

ሌላው መሰረታዊ ነገር ለወያኔ መንፈስ ዬኢትዮዽያ እርዕሰ መዲና ትግራይ ነው። ዬአደጋ መስመርም ዬለበትም። ለኤርትራም ከእሱ ዬቀረበ ዬለም። 20,000 እስከ 30,000 አለው ዬሚባለው ሠራዊት መቼቱ እንዴት ነው?

አልገብቶም!! ዬታጠቀ ኃይል በጥሪት ተቀማጭ መሆን። ምን አልባት ዬአማራ ዬከፋኝ ሠራዊት ከተገበረ በኋላ ምርጡ ድል ለእነ እንትና ታስቦ ይሆናል። ለዛ ከተበቃ ….  ሌላ ዬመከራ ድግስስ ይኖር - ይሆን?  ለአዲስ አበባም 774 ኪሎ ሜትር ይልቅ አፋር አዋሽን ይዞ ቀረብ ይል ይመስለኛል እና እንዴት ነገሩ? … አልገብቶም!!

·       መዳረሻ።

በመሆን ውስጥ ዬኖረ መኖር ሁልጊዜም አሸናፊ ነው። በተላጣፊነት ወይንም በቅጥልነት፤ ወይንም በቁሮነት ዬደባል መንፈስን ዬሙጥኝ ያላለ መንገድ፤ በመንፈሱ ጉዞውን ሲያስበው፤ ገና ሲወጥነው ነው ስኬቱ ዬሚታዬው። „ዬሚያድግ ጥጃ ከገመዱ እንዲሉ።“

ፈተናን አያቅዱትም። በራሱ ፈቃድ ከመጣ ግን አዲስ ዬህይወት መንገድ ነው። ለዚህም ደጋግ አባቶቻችን መፈተን አዘገዬህብን ብለው በሦስት - በአራት ሱባኤ ፈጣሪያቸውን ዬሚማጸኑት። ዬአማራ ተጋድሎ ዙሪያ ገባው በፈተና ቢወጠርም ዬሰው ዬእጅ ዬዳንቴል ሥራ ባለመሆኑ - ጥበቡን ከመዳህኒታ ዓለም መጠበቁ ዬነገ ጧፍ ነው።

እራሳችን እንድናይ፤ እንድንመረምር - ዬቆምንበትን እንድናዳምጥ፤ እልህ ፈጠረ። ቁጭትን አገላገለ። በጽናት በሁሉም መስክ መትጋትን አጎረሰን። እኔ ማን ነኝ? ብለን መልስ ለመሻት መባዘናችን ዘመኑ በቃችሁን ያወጀልን - ዬመጀመሪያው ዬህልውና ምዕራፍ ነው።

ውስጥን ማልማት፤ ለውስጥነት ክብር መስጠት - ከሌላ ዬሚጠበቅ ዬምጽዋዕት ቅንጥብጣቢ ሳይሆን በመዳፋችን ያለ፤ ማድረግ ዬምንችለው ሃብታችን ነው። ልዩነቱ በተፋቅንበት እንዳለን ሆነን እንደ አባይ ወንዝ አላግባብ ያፈሰስነውን ውሃ - ለራሳችን ዬሥልጣኔ አቅም ለማዋል፤ ተጠቃሚ መንፈስ ማግኜታችን ነው።

በባይታዋርነት ህልውናው ዬከሰመችው ጸጋችን ጠሐያዋ እንድታዬው ለውስጣችን መፍቀዳችን ነው። በተጠማኝነት ተደማጭነትን ማታከታችን ተምሶ ተቀብሮ፤ ቀዳሚው ነፍስን መታደግ መሆኑን ማድመጣችን ነው። ወከባው ካለ ቀጠሮ - ካለ ክፍያ - ዬነበረው ዬነፃ አገልጋይነትም ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ዬሥራ መልቀቂያውን ለባለጊዜዎች ስላቀረበ ነው።

·       ለምን ዬሉም አይበሉን?

- እኛው እኮ ነን ዬለነም ያልናቸው - በእነሱ አይፈረድም። እራሳችን - ሸሽተን። በራሳችን ያፈርን - እኛው! እራሳችን ዬፋቅን - እኛ። እራሳችን ከውስጣዊ ተፈጥሯችን ያገለልን - እኛው። እኮ! ስለ ምን ዬሉም አይበሉን? ቤታችነን ዬሸረሪት ማድሪያ አድርገን ለማይከፈልበት ቤት በጽዳተኝነት ያዋረድን እኛ እኮ! ለምን ዬሉም አይሉን? እራሳችን ዋሽተነው ዬኖርን እኛው እኮ! ስለምን ዬሉም አይበሉን?! አለን ማለት እንደ መርግ ሲከበደን ስለምን ዬሉም አይሉን? እሚያስጠጋ ለማይገኝበት --- አዬነው እኮ! አንዲት ተጨማሪ ደቂቃ ልመና። ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር እንዲህ ይሰደዳል።

ለውስጣችን ቅድሚያና አትኩሮት መስጠትን ዬህሊናችን መስመር ማድረግን ይጠይቃል። ቢያንስ ለራሳችን መንፈስ ዬስብዕዊነትን መብትና ነፃነት እንፍቀድለት። ወቅቱ ከቂምና ከምቀኝነት ዬጸዳ ግን ወደ ራስ ተመልሶ ከውስጥ ጋር መተዋወቅን ይጠይቃል። አትኩሮትን ይሻል። አስፈሪ ጊዜ ነው። በተለይ ለአማራው።

ዬቀደመው „ስትታገል እንደ ኢትዮዽያዊ ስትገደል፣ ስትጨቆን፤ ስትገፋ እንደ አማራ“ ነበር። አሁን ደግሞ ይሄ ተገልብጦ „ስትደራጅ እንደ አማራ ስትሞት እንደ ኢትዮዽያዊ።“ ምክንያቱም ቋንቋውን ዬተናገረም አማራ ነው። ዬሚልም አለ። ግራ ዝንባሌም አለ። ባሩዱ ይዘንብበታል፤ ዬሃሳብ ቦንብም በእሱ ላይ ይለቀቃል። ለማግስትም ቢሆን በድርብ አጣብቂኝ እንዲሰቃይ አማራውን ዬሚያደርግ ምልከታም እያዳመጥኩ ነው።

ቁጥር ሥፍር ዬሌላቸው መጠራቅቆች ሞት ላይ ለተጠመደ ዬዋህ፤ ደግ፤ እሩህሩህና ፍቅር ለሆነ ማህበረሰብ ….. እትዬ ጠሐይ ትመጣ ይሆን ወይንስ መጎም ያሰኛት ይሆን?

ጡሑፉ ያልተጨመረበት ስለመሆኑ ለማማሳከር።
https://www.ethiopianregistrar.com/amharic/archives/28016

ሰሞኑን አቶ አስራት አብርሃ ደግሞ ድንጋጤ ላይ ናቸው። ምን አልባት የ አንጀት በሽተኛነተቱን ሽፍት እንዳናደርግ እዬሰጋሁላቸው ነው። ለውጡ በሳቸው ላይ የመጣ ያህል እርር ኩምትር እያሉ ስለሆነ ይህ ተጣፈ።


መነሻው ይህ ቃለ ምልልስ ነበር። የ አማራ ተጋደሎ ሲነሳም „ተራ ግጭት“ ሲሉ ዘመን ብለው ነበር እና በዛን ጊዜ የሞገትኩበት እና የሰሞናቱ LTV ቃለ ምልሳቸው አካላቸው እንጂ ልባቸው ከዞጋቸው ላይ ስለመሆኑ አዳምጠናል። ማን ፈርስታቸው እንደሆነ …

https://www.youtube.com/watch?v=lqnbY2L_ExM

LTV WORLD:SEFEW MEHEDAR:

ጫናው በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ትግራይ አማራጮችን ልታይ ትችላለች ክፍል 1

LTV WORLD:SEFEW MEHEDAR:

ድል ለአርበኞቻችን!
አማራነት አይቀናም! አማራነት አይሸመትም!

ለዬኔታ ጊዜ ዬከበረ ሰላምታዬን ሰጥቼ - ልሰናበት።
ዘንጠፍ ያለች መሸቢያ ጊዜ እመኛለሁ።


                                       ቡናም ጠጡ። 
                                እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።