የአቶ አስራት አብርሃም የሳት ውስጥ ፕላስቲክ ትዕይንት።፡
ለአቅመ አዳም ያልደረስ የፖለቲካዊ ልቅና እርቃን።
„አቤቱ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅ ነገር የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በእውነት
አደርገሃልና፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ሰምህንም አመሰገንላሁ። ከተማይቱን
የድንጋይ ክምር የተመሸገቸውን ከተማ ውድማ እንድትሆን የሃጣዕንም
አዳራሽ ከተማ እንዳትሆን አድርገሃል።“
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ከቁጥር ፩ እስከ ፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ (Sergute©Selassie)
03.1.22018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
የአቶ አስራት አብርሃ ናፍቆት ይህ ይሆን? አበስኩ ገበርኩ!
ከቶ የጋንቤላን ጉባኤ አልተካታተሉትንም በደም የበቀለ
እህል በላን እኮ ነው ያሉት ታዳሚዎች።
· መነሻ
https://www.youtube.com/watch?v=lqnbY2L_ExM
LTV WORLD:SEFEW MEHEDAR:
ጫናው በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ትግራይ አማራጮችን ልታይ ትችላለች ክፍል 1
LTV WORLD:SEFEW MEHEDAR:
ጫናው በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ትግራይ አማራጮችን ልታይ ትችላለች ክፍል 2
አዘጋጅ እና አቅራቢ አቶ ዘለዓለም ደረጀ።
· ሃሳብ ማስኬጃ።
ኤል ቲቪ የአመራርን ልቅና የሚዘጋጅ ዝግጅት ነበረው። ዝግጅቱ በማከብራቸው በቄስ ዶር ገመችስ ደስታ ነበር የሚቀርበው ቃለ ምልልሱንም የሚመሩት እሳቸው ነበሩ። እናም ቀደም ባሉት ጊዜያቶች ጀምሮ እከታተለዋለሁኝ። በተጨማሪም ሃይማኖታዊ ሙግቶችን ደግሞ በልዕልት ቤትሻ ታፈስ እከታተላለሁኝ። አሁን ከሆነ ፖለቲካዊ ሃርድ ቶክን ማለት ያስችለኛል በመደበኛ እከታተለለሁኝ።
የልዕልት ቤትሻ የመግቢያውን አቅራረብ ትህትናዊ፤ አክብሮታዊ ብታደርገው እና እኩል መንፈስ ለዜግነት ከሰጠች፤ እንዲሁም ከራሷ ስሜታዊ ፍላጎት ወይንም ከሌሎች ገፊ ሃይሎች ቆስቋሽ ፍላጎት ጋር ሳታነካካ ራሱን በቻለ ጥበብ እና ዲስፕሊን ለመምራት የአቅጣጫዋን አቅሙን ካሳደገችው ቤትሻ ለሃርድ ቶክ አወያይነት የመጀመሪያዋ አንስት ይወጣታል ብዬም አስባለሁኝ።
እርግጥ ለሷም ምራቁን የዋጠ ኳች ያስፈልጋታል። የዛሬ ልጆች በራሳቸው ጥረት ከሚወጡት ወይንም ከሚበቅሉ በስተቀር ተከታትሎ በተሰለፉበት መስክ የሚያንጻቸው ሆነ የሚቀርጻቸው ኳች የላቸውም እንደ እኔ ዘመን አይደሉም እንደ ማለት ነው።
እኔ በጋዜጠኝነትም ሆነ በፖለቲካ አደራጅነቴ በጣም ዕድለኛ ነበርኩኝ። ትውልድ የማይተካቸው የሙያ አባቶቼ አሳምረው ገርተው፤ መከረው፤ ሲያስፈልግም እንደ ወላጅ አባት ገስጸው እና ተቆጥተው ነው ያሳደጉኝ። ዕድለኛ መሆኔ ወጥቼም እንኳን እንዲህ ዓይነት ድንቅ ገጠመኝ ነበረኝ።
ከፖለቲካ የህዝባዊ እና የሙያ ማህበራት አደራጅነት ወደ ራዲዮ ጋዜጠኝነት ስዛወር አንቱዎች ትውልዳዊ ድርሻቸውን ተውጥተው ህሊናዬ አብቅለውታል። ወደ ጹሑፍ ዓለምም ስገባ እንዲሁ። እዬሠራሁ ማሰልጠኛ ነበረኝ ማለት ነው። ዛሬ በህይወት ያሉም ስላሉ ሁሎችንም ዝቅ ያለ አክብሮታዊ ትህትናዊ ምስጋና አቀርብላቸዋለሁኝ።
እንዲያውም አዬር ላይ እዬነበብኩኝ ረጅም ዜናዎችን ቆራርጬ አርሜ ደቂቃውን የማጣጣት ጸጋ ሁሉ አጎናጽፈውኛል ማለት እችላለሁኝ። ምኖቼ ልበላቸው? ህይወቶቼ ናቸው። እዚህም ሲዊዘርላንድ በወሰድኳች አጫጭር የጋዜጠኛ ኮርሶችም እንደ ዕድል ሆኖ ከሙያው አዛውንቶች ከጀርመኞች እና ከሲዊዞች ጋር ዕድል ስለገጠመኝ ተጨማሪ መልቲ ባይታሚን መግቦትን ተሳክቶልኛል።
የዛሬዎቹ ግን ዕድሉ የላቸውም። ስለምን ቢባል ቅንነቱ የለም። የበለጠን ለማውጣት ትጋቱ የለም። ሁሉም ሚሠራው ለራሱ ዝና እና ውዳሴ ብቻ ነው። በፖለቲካውም ሲታይ እንዲሁ። ለዚህ ነው እኔ የዶር አብይ አቀረራብ ምርኮኛ የሆንኩት። ዕውቅት ለማውረስ፤ የሚበልጣቸውን ለማብቀል ስስታም አይደሉም። ዶር ለማ መገርሰም እንዲሁ በተግባር የተደፈቱን ዕንቁ ናቸው።
አሁን የጠ/ሚር አብይ አህመድ የአመራር ጥበብ መቅኑን የለውም ኦን ላይን ላይ የነጻ ት/ቤት ማለትም ያሰችላል። የሱማሌው የወቅቱ መሪ አቶ ሙሱጡፋ መሐመድ ዑመር ወደፊት ለመሪነት ተዋዳዳሪ ሊሆኑ የሚችሉ ሊሂቅ ናቸው። ዕድሉን አልነፈጓቸውም እንዲያውም ፈልገው አግባብተው ቦታውን ሰጥተዋቸዋል። ክብርት ዳኛ ብርቱካም ሚዴቅሳንም እንዲሁ። ዕድሉን አልተነፈገችም። አላዛሯ ኢትዮጵያ ሰው ማብቀል የሚችሉ ሊሂቃን በሁሉም ሙያ ዘርፍ በእጅጉ ያስፈልጋታል። ይህ ተተኪ የማበቅል ወሳኝ ትውልዳዊ ድርሻ ጣሻ የወጣው ነበር።
ይህ መስክ ወና ነው። ምደረ በዳም ነው። ስለዚህ የበለጠ ሲወጣ የማይከፉ ሊቅ ትጉሃን ያስፈልጉናል። አሁን የዶር መራራ ጉዲና ከኦህዴድ ህዝበ
ቅቡል ሊሂቃን የፖለቲካ ወጣት ሳይንቲስቶች ጋር ያለባቸው ቁልጭ ያለው
ችግር ይኽ ነው። እንኳንስ ሊፈጥሩ ሰብለው፤ አፍረተው የወጡትን ለመቀብል፤ ሆነ ዕውቅና ለመስጠት ቆጥቋጣ ሆነው እኔ እማያቸው። ደግሞም በድርቡ አዝኜባቸዋለሁኝ እንደ አንድ አድናቂ ዜጋ።
በሳቸው ሌጋሲ የሴት ሊቀሂቃን የጨለማ ዘመን የተፈረደባቸው ናቸው። የዛሬ ስንት ዓመት አነሳባቸው የነበረው ጥየቄ ዛሬም ሙጃ እንደዋጠው ነው። እስካሁን ለጠዬቅኳቸው መሰረታዊ ሴት የፖለቲካ ሊሂቃንን ደግፎ፤ ረድቶ አብቅቶ የማውጣት አቅም በፍጹም ሁኔታ የላቸውም። ለጥያቄ መልስ አልባ ሊሂቅ ቢኖሩ እሳቸው ናቸው። ደግነቱ እሳቸው አይደሉም አሁን የአገር ብሄራዊ መሪ።
በዚህ ውስጥ ነው እንግዲህ እነ ቤትሻ ብቅ ያሉት። ቤትሻ አቀራረቧን የድምፆዋን ቶን ከቁጣ ማዕቀፍ አውጥታ ጥንካሬዋን ብስጭቷ እንዳይጫንባት ጥንቃቄ ማድረግ እንድትችል ሪሄርስ የሚያደርጋት ሰው ካገኘች ብርቱ ናት። አቀራረቧ ማለቴ የጥያቄዎችን ጅረት እዬፈጠረች አስልቺ እና ችኮ ፈጽሞ አታደርገውም፤ መነሻ ዓለማውንም በራሷ ጊዜ ከዋናው ዕንብርታዊ ጉዳይ እዬወጣች ተብትባ አድራሻ ቢስ አታደርገውም።
መነሻዋም መድረሻዋም ማዕከላዊ ነጥቧ ላይ ስለሚሆን ቀልብ ትገዛለች። እኔ እውዳታለሁኝ አከበራታለሁኝ። አሁን ከአቶ ጌታቸው እረዳ ጋር ያደረገችው ውይይት የልብ አድርስ ስለነበር የማዕካላዊ መንግሥት አንደበቱ፤ የጠ/ሚር ቢሮ አማካሪው አቶ ጌታቸው ረዳ እንደ ብልጠታቸው አቅም አጥተው፤ ማምለጥ ተስኗቸው ትብትብ ነበር የሆኑት። መውጫ መግቢያ ነው የነሳቻቸው። ልዕልት ቤቲ አክብራ ትግራይ ድረስ ሄዳ ግን እርቃናቸውን ትታቸው ቀበቶ አልቦሽ አድርጋቸው ነው የተመለሰችው። ሴታታ!
ይህን ብቁ የአጠያዬቅ አርት፤ ጉልበታም የአቀራረብ ዘይቤ ለራሷም ብሄር ወይንም ለራሷም የዕምነት ተቋም ወይንም ለራሷም ውስጣዊ ስሜት ሆነ ለአለቆች ግርዶሽ ፍላጎት ካላደረገችው፤ አድሎዊ ካልሆነች የወጣላት የመጀመሪያዋ መቅደመ ሃርድ ቶክ አንስት አወያይ ይወጣታል።
ተስፋ አለኝ እንደምታሻሽል።
እኔ እንደ እህት እምመከራት የጋዜጠኛ አቶ ሥሜነህን ባይፈረስ የአቀራረብ የአያያዝ፤ የልተገነነ፤ ልኩን በወጉ የለካ አክብሮት እና የትህትና ጸጋ ደግማ ደጋግማ በማዬት በግልም እሱን አግኝታ ምክር እንዲሰጣት ብታደርግ እና የልምድ ልውውጥ ብታደር ጎልታ ትወጣለች። ብድር የማያስኬድ በቂ አቅም አላት። ደፋርም ናት።
ትልቁ ችግር የእሷ አገባቧ ነው። ስትጀመረው ደራሽ ሙላት ወንዝ ዓይነት ነው። በገጠሩ አነጋገር ፈረሰኛ ውሃ ሙላት ነው። ይህ አፒታይት ዘጊ ነው። ድንገቴ ገጸ ባህሪም ዓይነት ነው መቅድሟ። ብጥስ ይልና ነው የምትቀጥለው። አገባቧን በፍጹም ሁኔታ መለወጥ አለባት። አንዳንድ ጊዜ እኔ እደነግጣለሁኝ ወደ ዋናው ውይይት ስትገባ መንፈሴ ሳይያያዝ ነው የሚሆነው።
መንፈስ ማስያዥ ይፈልጋል። በዛ ላይ ሴት ናት። ሴት ርህርህናዋ እና ፍቅራዊትነቷ እራሱ መገባ መንገድ መክፈት ይኖርባታል። እራሱ ድምፆን መግራት ይኖርበታል መግቢያ ላይ። አግባብታ ነው አድማጩን መጀመር ያለባት። ፈግጠው ዓይነት ቃና ነው የላው አገባቧ። በድንገት በር በርግዳ ከሆነ ግን በአቅሟ ላይ ስውር ተጽዕኖ ያርፍበታል። አብሶ አተያዮዋ … እናታዊ ፍቅርን መመገብ ይኖርበታል፤ አትኩሮትን መለገስ ይኖርበታል። ትህትናን መቸር ይኖርበታል።
አስተውሳለሁኝ አንድ ጊዜ ወንድሜ ከዶር መራራ ጉዲ እና ከፕ/ በዬነ ጵጥሮስ ጋር እዬተወያዬሁ ለካንስ በርቀት ጥሞ ሲያስተውሉኝ ቆይቶ ጉትት አድርጎ ወሰደኝ እና እስኪ አተያዬሽ ሙያዊ ብቻ ሳይሆን ሴታዊ ይሁን ያለኝን አልረሳውም። እኔም እንደ እሷ ኮስተራ ስለሆነኩኝ። ድምጼ ግን በጣም በጣም የተጋራ ነው፤ ልስልስ ዝንጥፍጥፍ ያለ ነው። አብሶ ራዲዮ ላይ እና ቤተ እግዚአብሄር ላይ።
የሆነ ሆኖ አሁን እኔ የዶች ቬሌዋን ልሙድ የውይይት ዓይነትን የምትመራው አወያይ ልዕልት ሽዋዬ ለገሰን የነፍሴ ያህል ነው እምወዳት። ማስተርም አደርገዋለች ጸጋዋን ብዬ አስባለሁኝ። መክሊቷ ህብራዊ ነው። እርጋታው ቃናው ይስባል። ለአንግዶቿ እና ለእኛ ለአድማጮቿ ያላት ትሁት መንፈስ መጨበጥ መዳሰስ ይቻላል። ለዛውም ራዲዮ ሆነ ግን ቪዥዋል እስኪመስል ድረስ። ታሞናሙነዋለች ማለት ያስችለኛል። በልሙድ አወያይ ከቀደሙት የወላጅ አባቴ አቨይ ልዩ ክብር የሆነችው ልዕልተይ ወ/ሮ /ትዝታ በላቸው፤ እንደ ጋዜጠኛ ልዕልተይ ወ/ሮ አርያም ተክሌ ናት ልዕልት ሽዋዬ ለገሰ። Stolz+
በተጨማሪም ለልሙድ አወያይነት ኢትዮጵያ ውስጥ ካዮኋዋቸው አንስቶች ሁሉ ላቂያዋ አወያይ አማራ ማስ ሚዲያ ልዕልተይ ማህደር ብርሌውም ሁለመናዋ ይመስጠኛል። እነኝህ ከላይ የዘረዘርኳቸው የልሙድ አወያይ አንስቶች ናቸው። ሁልጊዜም አዘውትሬ እማስባት አርያምዬ አንድ ትልቅ ሰብል አስብላለች ብዬም አስባለሁኝ። አጽድቃለች። ተከታለች። እንዲህ ዓይነት የታረመች፤ ዕውነትን ብቻ የወገነች፤ መተላለፍን የማትድፈር ዕንቁ አንስተ ሴት ጋዜጠኛ አላዛሯ ኢትዮጵያም ስላላት እኔ ደስ ይለኛል። ሁልጊዜ ሳልጠግባት ነው ጊዜው እልቅ የሚልብኝ ልክ እንደ ጾመ ፍልሰቲት የጋዜጠኛ ሽዋዬ ለገሰ የቃለ ምልልስ ዝግጅት መሰናዶ።
እነኝህ አንስት ጋዜጠኞች እንደ እኔ ትዝብት ከውስጣቸውም ከውጪያቸውም ገፊ ሃይል የሌላቸው፤ ያልወገኑ፤ ለማዋጣት፤ ለማሳጣት፤ ለማጣጠል፤ መጠራቀቅ ለመፍጠር፤ ግነት ለመፍጠር፤ ለማቀጣጠል ብለው ሳይሆን ዕውነትን ወግነው የሚነሱ ዓራት ዓይናማ አንቱዎች ናቸው - ለእኔ መንፈስ።
ወደ ኤልቲቢ አወያዮዋ ወደ ልዕልት ቤተልሄም ታፈሰ ስመጣ፤ ዓይነቱ ልሙዱ ውይይት አይደለም። ሥነ ምግባሩ ወደ ሃርድ ቶክ ያደላ ነው። የውይይቱ ሆድ ዕቃ ተፈጥሯዊ ባህሪው የግድ ጠንከር ያሉ ሃሳቦችን ማንሳት ይጠይቃል። ቃላቶች ሥንኞች ረገጥ ብለው ለመቀረብ ግድ ይሆናል። በተረገጥ ፍለጋ ላይ ጫን ተደል የሆኑ ፍጥጫዎች ሊገጥሙ ይችላሉ። ይህ ተፈጠሯዊ ነው። ጫን ተደል የሆኑ መረጃዎችና አቅፎ ዕውነትን የመፈለግ ፈለግ ግብግብ ስለሆነ የቃለ ምልልሱ ዓይነት አርቱ የተለዬ ነው። ስለዚህ መንፈሱ ከመደበኛው ከልሙዱ ፈንጋጣነት ቢያሳኘውም አገባቡ አጀማመሩ ግን ዱብዕዳ ዓይነት መሆን አይኖርበትም።
የሰው ልጅ ህሊና በመጠጥ እና በውሃ አይኖርም። መንፈስ ልስሉስ ጥበባዊ መግቦት ይሻል። ልዕልት ቤትሻ ስትጀምረው እኔ ባንባ ሥር ወይንም ሾላ ሥር ተቀምጬ ሳነብ ሾላው ይሁን ባንባ በራሱ ጊዜ ዱብ እንደሚለው ነው የምመለከተው። ደራሽ ነገር ነው የሚሆነው።
አንዳንድ ጊዜ ባንባ ከራስ ላይ ካረፈ የህመም ስሜትም አለው የዕውነት።
ጎንደር የምትኖሩ ባንባ ሲደርስ ፋሲል መወኛ ሂዱ እና ከዛ ከዛፉ ሥር ቁጭ
በሉ እና እዩት፤ የሎሚ ተክልም ያለው ካለ እንደዚሁ። እንኳን ደህና
መጣችሁ ሆነ አድምጡኝ ተማች መሆን አይኖርበትም ነው ፍሬ ነገሩ
ልሙድ ቃለ ምልልስ ይሁን ጠንካራው ሙግት። ተፈጥሮ እንደዛ ቢሆን
እንኳን ራሰን መግራት በቅደመ ሪህርሳል ይቻላል። ደግሞ ደጋግሞ በግል
የቪዲዮ ክሊፖች እራስን ማረም በእጅጉ ያስፈልጋል። እንቆቆ የሚጠጣ
ሰው ዶሮ ማታ እዬተባለ ነው … አብሶ የ ሃርድ ቶክ ከሆነ ለተዋያዩ በዚህ መልክ መሆን ይገባዋል። ፈቅዶ መገኘቱ እኮ ግምሹን የውይይት ክፈለ ጊዜ አድሎታል ማለት ነው።
· ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ።
ከቶ ሰላምታውን አዘገዬሁት ይሆን? ይቅርታ። ውዶቼ እንዴት ናቸሁ ደህና
ናችሁ ወይ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ከልዕልት ኢትዮጵያ ስስት ከእናንተ ከውዶቼ የመንፈስ ሃዲድ ናፍቆት በስተቀር ደህና ነኝ። ትናንት የሚመች ሁኔታ ላይ ስላልነበርኩኝ ያዬሁት ነገር አልነበረም አገር በቀል ዜናዎችን።
ዛሬ ግን ዘወር ዘወር ስል የኤል ቲቪ ቃለ ምልልስ ጋር ገጥ ለገጥ ተገናኘን እና ክፍል አንድ እና ክፍል ሁለትን ቃለ ምልልሱን አዳምጥኩት። ሁለት አገራችን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረጉ ኢትዮጵያ ፈርስቶች፤ አንድ ደግሞ የትግራይ ጉዳይ ህሊናቸው የሆኑ በድምሩ ከሦስት ኢትዮጵያዊ ዜጎች ጋር ነበር ውይይቱ አዘጋጅ እና አቅራቢ አቶ ዘላለም ደረጀ።
የውይይቱ ዓይነት ልሙድ ነው። እርግጥ ነው ደግሜ ለማድመጥ አልቻልኩም በሰው ቁስል የሆነ ድፈረት ስላዬሁበት። ለዚህም ነው እነዚህ ነፍሳት እና አንጡራ የዘመናት የሰው ልጆች ቅርስ አመድ መሆን በምስል ማስደገፍ ግድ የሆነው።
ደግሞ ማድመጥ ስለምን የዳነውን አንጀቴን ማቁሰልም ነው። ብዙ የቪዲዮ ማስረጃዎችን ማቀረብ ይቻላል የ27 ፋሽታዊ የወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራርን ግን ምን ያደርጋል ብሶትን በሰተቴ በዬማዕለቱ ቢያርቡት። ለዛው ዛሬ ኢትዮጵያ አሸንፋ የምስራች ጧፍ ምርት ላይ ሆና… የሆነ ሆኖ ግን ከፍትህ ጋር ለመገናኘት የማይችል መንፈስ ከገጠም ግድ ይሆናል ጥቂቱን ማንሳት። ታሪክም ስለሆነ።
· እንደ ሚዲያ ኤል ቲቪ።
በቅድሚያ ግን ከዋልታ አወያዮች ለዬት ያለውን የኤል ቲቢ ወጣት አወያይ ቢችል እሱ ባይቻል ግን እንደ ድርጀት ኤል ቲቪ ቴሌቮዥን ሊያስተካክለው ወደሚችለው ጉዳይ ሁኔታ ላምራ።
አንድ ሚዲያ በሚያስተላልፋቸው ጉዳዮች ላይ ብርቱ ጣምራ ኃላፊነት አለበት። ሀገራዊ ሃለፊነት። ትውልዳዊ ኃላፊነት፤ ሙያዊ ኃላፊነት። አገራዊ ሃላፊነት ማለት ህዝባዊ ሃላፊነት ማለት ነው። ሃላፊነቱ እንዲህ 27 ዓመት ሙሉ የህንጻ ግንባታ ያህል እንኳን ባለቤት አልባ ሆኖ የኖረውን የትውልድ ህሊና በትሩፋታዊ ዕሴት ትውልዳዊ እሴትን ማነጸ ነው ዋንኛው ተልዕኮው ሊሆን የሚገባው፤ ቢያንስ ዛሬ ጊዜውን መሻማት ያስፈልጋል። የተቃጠለ የነደደ ያረረ ትውልዳዊ መንፈስ ባክኖ ቀርቶልን። አምልጧል።
ከኢትዮጵያ ትውፊት ትልቁ አክብሮት ነው። አክብሮት ለአላዛሯ ኢትዮጵያ መለያ ዓርማዋ ነው። ስለ አክብሮት ኢትዮጵያ ፊደል ቆጣሪ አይደለችም። ጸሐፊ አቶ አስራት አብርሃም የውስጥ ደማቸው እዬተንተከተ ምን አልባትም በቀጣይ ወራቶች የአንጀት በሸተኛ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ አስባለሁኝ፤ የቀድሞ ጠ/ሚር የነበሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን „ሃይለማርያም“ እያሉ ነበር በደም ፍላት ሲያኑሱና ሲጥሉ የነበረው። መቼ ይሆን ከፉክክር አዟሪት የሚወጡት የተጋሩ የፖለቲካ ሊሂቃን? ይንፍቀኛል?
እሳቸው እኮ ሊሂቅ ነኝ ብለው አገር ልመራ እችላለሁ ብለው በፓርቲ አካልነት የነበሩ ሰው ነበሩ። በለስ ቢቀናቸው በዬትኛው ሞራላዊ አቅም ይሆን የታሰበው ያ ህልም። እስኪ ከዶር ለማ መገርሳ ለመማር ይፍቀዱ። የሚያበሳጫውን እንኳን እንዴት አስታመው ውስጣቸው እርር እያለ እንደሚያቀርቡት፤ በአንዲት ሳምንት እኮ ነው 700 ሺህ ህዝብ ተፈናቅሎ በተጨማሪ ደግሞ 50 ሺህ በሙያሌ በኩል መሰሉ ተፈጽሞ ግን ዋጥ አድርገው ያን ያህል ለብሄራዊ ነፃነት ሲተጉ የነበሩት ብቻ ሳይሆን ከእነ ዶር ደብረጽዮን ጋር በአንድ ጠረጴዛ ሲወያዩ የነበሩት። ያ እኮ ህሊና ላለው አንድ የትውልድ ዩንቨርስቲ ነበር እኮ!
ማንም ሰው መማር የሚችለው በዩንቨርስቲ ብቻ አይደለም። ሁሉም ቦታ ልማር ከተባላ ዕውቀት እንደ ማር ወለላ ይዘንባል በኢትዮጵያ መሬት -ዛሬ። አብሶ መሪነትን በመመኘት ግን የህሊና ዕጠባ ገና ያልጀመሩት፤ በአንደበታቸው ሞግተው መርታት አቅሙ የተሳናቸው እኒህ ሊሂቅ ከዚህ መሰል በዕድሚያቸው ትይዩ ካሉትም ትሁታዊ የሊሂቅነት መደበኛ ት/ቤት መማር ግድ ይላቸዋል፤ በስተቀር በፈቃድ ከመድርኩ ዘወር ማለት ነው። ምክንያቱም ትውልድ ህሊናው አረም ሊበቅልበት ስለማይገባ። በሌላ በኩል ለፖለቲካ መሪነት አንደበት እርቱነት የንግግር ጥበብ ጸጋ ድርድር ሊደረግበት የማይገባ ወሳኝ ጉዳይ ነው።
እኔ የአቶ ሃይለማርያም ደሰአለኝ ፈን አይደለሁም። እንዲያውም ሥልጣኑን በፈቃዳቸው እንዲለቁ ደልዳዋ እምቤት ባለቤታቸው ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ እንዲያግዟቸው ለረጅም ጊዜ ስጽፍ ኖሪያለሁኝ። ራሱ የተፈሪነት ማህባውም የላቸውምና።
በሌላ በኩል በታሪክ አጋጣሚ መሪ ሆነው ሰላጠፉት ጥፋት ስለሚጠይቁበት ጉዳይ ህግ ይጠይቃቸው። ይህም የእኔ የቤት ሥራ አይደለም። የእኔ ጉዳዬ ሉላዊው የትውልድ ጉዳይ ነው። ይህ ዲጅታል ዓለም ያለው መከራን አስተካክሎ አዋህዶ ለመጓዝ ዓለም እራሷ እያመለጣት ያሉ ጉዳዮች አሉ ብዬ አስባለሁኝ። ቤተሰባዊ፤ ማህበራዊ ዕሴት ድርቅ እዬመታው ነውና።
ወደ አገሬ ኢትዮጵያ ስመጣ ትውልድ አለ እንዲያውም አሁን እጅግ በሚገርም ሁኔታ ኢትዮጵያ የታዳጊ ወጣቶች አገር እዬሆነች ነው። ሃላፊ ተብለው የማያቸው ወጣቶች እራሱ ይገርመኛል። የወጣት ብቻ ሳይሆን የታዳጊ ወጣት አገር መሆን ጠቀሜታው የጎላ ሲሆን ትኩረቱ ግን ህሊና ጠገብ መሆን አለበት። ወጣት በተፈጥሮው ግልፍተኛ፤ ችኩል፤ ስልቹ፤ ግን አቅመ ሙሉ ሲሆን በሌላ በኩል ንጹህ ብላክቦርድም ነው። በመቀበል ሆነ በማስፈንጠር እረገድ። ይህ ለእኛ አጀንዳችን አልሆነም።
በተጨማሪም አቶ አስራት አብርሃ የጥበብ ቤተሰብ ናቸው ጸሐፊ ስለሆኑ፤ የቋንቋ ሙሁርም ስለሆኑ። የተሰጣቸውን ጸጋ እና ሙያዊ ክህሎት ብራና ላይ ጥሞኝ ነው አጣጣሉን እማነበው፤ የፈለገ ግራ ይሁን ወጣ ገባ። ወይንም ቀጥ ያለ።
ጥበብ ከሁሉ የላቀ የአዕምሮ ብስለትን ቤተኝነት ይገልጣል፤ ከሁሉ በላይ ጥበብ ወገንተኝነቷ ለዕውነት እና ለርትህ ነው። ጥበበኛ ከራሱ ከቤቱ መልካም ነገሮች ነው የሚነሳው። ከትውስት ይልቅ የራሱ የሆኑ ነገሮች ይመሰጡታል። በዛም ትውልድ ይቀርጽበታል።
እናላችሁ ውዴቼ … ገነቦ፤ እንስራ ጀበና ጆሮ አለው እንኳንስ የሰው ልጅ ቀርቶ። እንደዛ እያንጠለጠሉ እንደ ቆሎ ጓደኛቸው „ሃይለማርያም“ ሲሉ ለትውልዱ ምን ዓይነት የጥበብ ሰውነት እያሰተማሩ ስለመሆኑ ልብ አላሉትም?
እሳቸውም ከምን ዓይነት ቤተሰብ እንዳደጉ ያሳጣል። ግን ከምን ዓይነት ቤተሰብ እንዴትስ አይነት አሰተዳደግ ነው እንዲህ ዝንጠላዊ አጠራር የሚመጣው? ነውር ነው። እንደ ኢትዮጵያም ሃራም ነው።
እርግጥ ነው የጥበብ ሰው ቢሆኑ አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ብዙም አይደንቅም። የቀደሙት የሚያሰተምሩት ቀረቤታን ስለሆነ አንተ/ አንቺን እንደ ቀኖና በህሊናችን ሰሌዳ ስለጻፉት እኛም መርህ አድርገን ስለወሰድነው።
ብቻ አቦይ አብርሃም እንዴት አድርገው ይሆን ልጃቸውን ያሰደጉት? የሚገርምው የኤልቲቪ አወያይም አቶ ዘለአለም ደረጀም ይህኑኑ መደግሙ ነው። ‚ሃይለማርያም‘ እያለ ሲጠራቸው ሰማሁኝ። ከቶ ጆሮዬ ይሆን? እጅግ ጉልህ ግድፈት ነው። ይህን የኤል ቲቪ ቴሌቪዥን በፍጥነት ማሰተካከል ይገባዋል። ማለት ኤልቲቪ የመንግሥት ሚዲያነት ሞራሉ ከኖረው።
ሌላው የግል የፖለቲካ ድርጅት ልሳኖች ሆኑ ጸሐፍት ሆኑ አወያዮች እና ተወያዮች ብዙም አይደንቅም ለምደናዋል። ተንጠልጥሎ መጠራቱን እና። ትውፊት እንዳሻው መረጋገጡ ብቻ ሳይሆን ስለሚያደርጉት ነገር ሁሉ ትውልድ ይማርበታል ብለው አሰበውትም አያውቁም አጀንዳቸውም አይደለም።
አሁን መንግሥት አለ፤ መሪ አለ ተብሎ ሲባል እንዚህ ጥቃቅን የሚመስሉ ግን 27 ዓመት የተኖረው የልቅነት መከራ፤ የሺሻ የጫት የትውልድ ግንባት አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ እንዲህ ዋናውን እንብርቱን፤ ሰቁን መለያችን አክብሮት ይህን ያህል ሲጠቀጠቅ ዝም ሊል አይገባውም ኤል ቲቪ። ተወያዮች እንዲህ መስመርን አልፈው ሲሄዱ ማስተካከል ሲገባ እራሱም አወያዩ ያንን መድገሙ እጅግ ማዘኔን በግልጽነት እና በቀጥተኝነት መግለጥ እሻለሁኝ።
ሌላው አቶ ሃይለማርያም ደስ አለኝ የተጻፈላቸውን ማንበብ የማይችሉ ሰው ስለመሆናች ይታወቃል። ባለፈው ዓመት „ስብስቆ“ በጣም በርካታ ጹሑፎችን ጽፌያለሁ ስለ እሳቸው። አቅም ብቻ ሳይሆን መክሊትም ይጠይቃል መሪነት። መክሊት ብቻ ሳይሆን ጥበብም ይጠይቃል። ትህትና ብቻውን መሪ ሊያደርግ ፈጽሞ አይችልም።
ሌላው አሊ የማይባለው ጉዳይ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ 5 ም/ጠሚኒስተር በኢትዮጵያ ታሪክ የተሾመው በዘመነ አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ነበር። ይህ ማለት ለሥሙ ነበር ማለት ነው።
እሱም ብቻ አይደለም ጠ/ሚር ሁለት ነበሩ። ሁለቱም የትግራይ ሰዎች ነበሩ። ከላይ ከቁንጮው ከጎን እና ከጎኑ ከበስተጀርባ ከነበሩት በላይ። ውልፍት አልነበረም። ተሰቅዘው ነበር የተያዙት።
በቃኝ ለማለት እንኳን ፈቃድ አስፈላጊ ነበር። ሁለቱ የግርዶሽ ጠ/ ሚኒስተራት አቶ አርከባይ እቁባይ እና አንባሳደር ስዩም መስፍን ነበሩ። ታስታውሱ ከሆነ መጋቢት 24 ቀን ጠ/ሚር አብይ አህመድ እርክክብ ሲያደርጉ አረካካቢዎች እነሱ እንጂ አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ አልነበሩም። የአቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚኒስተርነት ፌክ ነው የነበረው። ልክ እንደ ዴሞክራሲ ግንባታ ሚ/ር፤ እንደ ዕንባ ጠባቂ ሚ/ር/፤ እንደ የህጻናት እና የሴቶች ሚ/ር፤ እንደ ሰብዕዊ መብት ኮሚሽን፤ እንደ ምርጫ ቦርድ ግርዶሽ ነበር። ምዕራባውያንን ለማታለል። ችለዋል ወይ? ዓለም አምኗቸው ነበር ወይ? ሲባል ውስጡ ለቄስ ነው።
ዓለም ለአቅም አዳም የደረሰ ፖለቲካዊ ጭብጥ ሲጠበቅ ነው የኖረው። ሲያገኙ ደግሞ ምን ያህል እዬደገፉ እንደሆን እየታዬ ነው። አቅም ያለው ይህን ሁሉ ዝክንትል ችግር ተሸክሞ የሚያሻግር ክህሎት ነበር ሲያልሙ የኖሩት። አማራጭ መጥፋቱ እንጂ በአንድ ብሄር ሊሂቃን ብቻ አገር ስትደወር፤ አገር ስትቀቀል፤ አገር ስትታመስ፤ አገር ቁሚ ተቀመጪ ስትባል መኖሯ ይታወቃል። ለዚህም የአውሮፓ ህብረት የሰራው ዶከመንተሪ በራሱ ምስክር ችሎትም ርትህም ነው። ይህን ድፍን ዓለም የሚያውቀው ታሪክ ነው። ሲአይኤ፤ ኬጆቪ ምን ይሠራሉና?
ይታወቃል የትግራይ ሊሂቃን ቅርፊት ጠማኝ ወይንም ተጠማኝ መሆናቸውም ትናንትም ዛሬም። ቅርፊቱ ደግሞ አህአዴግ ነው። 27 ዓመት ስለታለፈው መከራ ማን ምን ሲያደርግ እንደ ነበር ራሱ ትግራይ እና ጎንደር በንጽጽር በሳትላይት የተሰራው ሉላዊ የፎቶ ኤግዚብሽን ምን እንደነበር አንዱ ተጨማሪ ገላጭ ጉዳይ ነው። ምን ያህል ይከታተሉት እንደነበር። ይህን ማመን አልፈቀዱም አቶ አስራት አብርሃ እና መሰሎቻቸው።
የዓለም የሰብዕዊ መብት ጉባኤ እኮ ቀልቡ ኢትዮጵያ ላይ ነው የነበረው። የአሁኑ ኩርፊያም፤ ተደፈርንም፤ ህልማችን ራቁቱን ቀረም እኮ ምንጩ ይህ ነው። እኛ ከሌለን አገር ትቀውሳለች ተብሎ ያለው ደባም ምንጩ ይሄው ነው።፡የአሁኑ የደቦ የብሶት ዕንባም የደመር ውሎም እኮ ይህ ጨፍልቀን እና ደፍጥጠን እኛ ላይ ሌላው በሁለተኛ በሦስተኛ ዜግነት መማቀቁ ተገታ እኮ ነው። መጫን ቀረብን ነው። ኢትዮጵያንም እንዳሻን ማለብ ተገደበብን ነው። ሁሉም ሊሂቃን የሚስማሙበትም ይሄው ነው።
የአሁኑ 2 ሚሊዮን ህዝብ ካለ በደሉ በሰው ሰራሽ ሴራ እና የቀዝቃዘው
ጦርነት ውጊያ ሰለባነት መፈናቀል እኮ ይኸው ነው። የእሳቸውም የአቶ
አስራት አብርሃም ማለቴ ነው እንዲህ ከእሳት እንደገባ ፕላስቲክ እርርር ኩምምትርትር ጭብጥብጥ ጭምትርትር ማለት እኮ የትግራይ የበላይነት ቀረ ነው። የወያኔ ሃርነት የሰባዕዊ መብት ረገጣ ማረሻ አቅሙ ተገታ ነው። የሰብዕዊ መብት ፋሱ እጀታው ወላለቀ ነው። ያሳዝናል።
ስለዚህ የበላይ ሳሉ ለነበረው መልካም ነገር ሆነ መልካም ላልሆነው ነገር ተጠያቂው አውራው ፓርቲ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ እና ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። ነገም እንዲሁ ነው። እስከ ቀጣዩ ምርጫ አሁንም ኦዴፓ ነው ለሚጠፋውም ለሚለማውም ተጠያቂ እሱው ይሆናል አውራ ፓርቲ እሱው ነውና።
· አይዋ አንድበት ጉድህ ፈላ?
እኔ እንዲህ አቶ አብርሃም አስራት አንደበታቸው በተፈጥሮ ካቴና የታሰረ መሆኑን አላውቅም ነበር። ከግምቴ በታች ቁልቁል ረግረግ መወረዳቸውን እዬተከታተልኩት በአንጻሩ ደግሞ የፈረሰው አንድነት ፓርቲ እንኳንም ፈረሰ እንዲህ ከበሰበሰ፤ ከታቆረ፤ ከታከተው መንፈስ ጋራ አብሮ ከሚማቅቅ በማለት ተመስገን ብያለሁኝ። እናንተስ ውዴቼ? ያው ያ መከረኛ አማራ ነበር ቀንበር ተሸካሚ ሁን ተብሎ ለእነ አቶ አስራት አብርሃ ወዳሴ ዝና ልቆ መውጣት አንጋች እንዲሆን የሚፈለገው።
በሌላ በኩል ይህ ከዞግ ድርጅት ወደ ዜግነት ፖለቲካ መምጣት በዶር ነጋሶ ጊዳዳም በአቶ አስራት አብርሃም የታዬ ገመና ነው። የአማራ ተጋድሎ በተነሳ ጊዜ የገብያ ግርግር ነው የትም አይደርስም ጉዳዩ እዛው ሰፈር ወልቃይት የማያልፍ ነው፤ እንደ ጎርፍ እዩት ብለው ሲጽፉ አቶ አስራት አብራሃም አንድ ጹሁፍ ሞግቼ ጽፌ ነበር በ2008 እ.ኢ.አ። እርእሱን አላስተዋስውም።
ዛሬም እዛው ከኩሪያቸው ላይ ሆነዋል። ያን ጊዜ እዚህ ይደርሳል ያላሉት የጎንደር የአማራ ተጋድሎ አብዮት በሥመ ትግሬ ስጋት ውስጥ የነበሩ ንጹሃን የተጋሩ አባላትን በሙሉ ነፃ አውጥቷል። ይልቅ ንጹሃን እንኳን ደስ አላቸው።
ሌላ ነፃ አውጪ ይህን ዕድል አግኝቶት ቢሆን ኖሮ እንደ ተለመደው ሁሉም ጠፍቶ፤ ሁሉም ተደምስሶ ከዜሮ ይጀመር ነበር። ይህ በፆም በጸሎት የማይገኝ የድል ብሥራት በሆነ ነበር ለቤተ ተጋሩ። ግን አላወቁበትም።
ከ ዚህ የለውጥ አራማጆች ውጪ ዕድሉ ሌላ እጅ ገብቶ ቢሆን ኑሮ ማን የበለጠ ይጎዳ እንደ ነበረ ደግሞ ዓለም ያዬው ነበር። አሁን ይልቅ ተመስገን ማለት ነው የሚኖርባቸው፤ ይህን ያህል ሰማይ ጦር አውርድ በሎ ከማጣወር እና መሬትን ካለ በደሉ ከመደብደብ። ምድር ምን እንድታደርግላቸው ይሆን የሚሹት? ቀበጤዎች። ይህን ሁሉ መከራ የቻለ ህዝብ ምስግናው ቀርቶበት ደግሞ ይወቃሳል። እነሱ አዲግራት መቀሌ አክሱም ታማኝነትን ግጠው ሲያነዱት ቅር አይላቸውም እኮ? ሽንት በኮዳ ሞለተው ወልደያ ላይ ሲያርከፈክፉ ማዕረጋቸው ነው።
እንደሳቸው አስተሳሰብ ደግሞ ዘሩ ስለመከነበት፤ አካሉ ስለጎደለበት፤ ጥፍሩ ስለተነቀለበት፤ ከእንሰሳ ጋር ስለታሰረው፤ ተገድሎ አድርሻው ስለጠፋበት፤ በአውሮፕላን አብራሪነት ተመርቆ ወደ ግብርና ሥራ ስለተሰማራው፤ በወጣትነቱ ጡረታ ስለወጣው፤ በመኮነንነቱ ታግሎ ከለ እድሜው በጡረታ የተገለለው፤ ከዚህ ደሙን ከፍሎ ላደረሰ ጀግና ጡረታ ወጥቶ ቤቱ ተገልብጦ እሰከ ቤተሰቡ ለመደምስ ነፃነቱን ለመገፍፍ ለተደረገው ጣሪያ የነካ መታበይ፤ ቤንዚንና ክብሪት ቦንብና ጠበንጃ አስታጥቆ አገር ማንደድን፤ ግርማቸው ነው።
በሚሊዮኖች ስለተፈናቀለው ወገን፤ አድራሻው ስለጠፋው ወገን፤ በአንድ አጋዚ ስንት ነፍስ ስለጠፋበት፤ አገር በቁሟ ስለተሸጠችበት፤ አገር በቁሟ ከትወፊቷ፤ ከታሪኳ፤ ከባህሏ ስለተራቆተችበት መቀጠል ነው የሚያብሰከስካቸው፤ የሚያቃጥላቸው አቶ አስራት አብርሃምን።
እሳቸው ወያኔ ሃርነት ትግራይ የተጋሩ ቤተሰብ ስለሆኑ ሲገደል፤ ሲያርድ፤ ሲያሳደድ፤ ሲዘርፍ፤ ሲያዋርድ፤ ሰያሳድድ፤ ሲወር፤ መቀጠሉን የሚደግፉ የውስጥ አርበኛ መሆናቸውን ገመናቸው ዝክዝዝክ ብሎ ተመልሰው ቁመው እንዳይሄዱ ሆነው እርቃነ ነፍሳቸውን ቆመዋል። እግዚኦ!
አሁን ለእኔ የሚታዩኝ እንደ መለመላ ግንድ ነው። መቼም አሁን እንዴት ቀበቶውን ታጥቀው ገበርዲኑን ለብሰው እንደሚሄዱ አላውቅም። ሰው እንዲህ የሚያያዝ ነገር ውል ይጠፋበታልን? እጅግ ይገርማል? ማህከነ!
ይህን መሰል ሃሳብን የመግለጽ ችግረኛ መሆናቸውን እኔ በፍጹም አለውቅም ነበር። እኒህ ነበሩ ዜግነትን ማዕከል ያደረገው የአንድነት ፓርቲ ልሳነ ጉባኤ የነበሩትን? ለነገሩ ቦታውን በያዙ ማግስት የጻፉት አርቲክል የዚህ ገመናቸው ዋዜማ ነበር። በወቅቱ ልብ ያለው አልነበረም። ብቻ ድራማ በድራማ ባጅቶበት የሁሉም ነገር እንደ ጥንቸል መሞከሪያ ጣቢያ የነበረው መራራ ሰንብት እንደ ቅንጅት ያደረገው አንድነት ፓርቲ እንኳንም ፈረሰ ይህን እሾኽ ተሸከሞ የአገር ዕዳ ከሚሆን። ትውልድም ከሚመክንበት።
· ዘመን የሰጠው ቀን።
የዜግነት ፖለቲካ ፌክ ይኸው ነው። ያን ጊዜም በ2008 ስጽፍላቸው አካለዎት እንጂ ነፍስዎት ኢትጵያዊ ዜግነትን አትንፍቅም ብዬ ጽፌ ነበር። አሁንም እምለው ይኸው ነው። አስተሰባቸው የነፃነት፤ የእኩልነት፤ የፍትህ፤ የሚዛናዊነት እና የተጠያቂነት ጸር ሆኖ አግኝቻዋለሁኝ።
ሁሉ ነገር ትግራይን ካልነካ ብቻ ነው የሳቸው አርበኝነት¡ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ልዕልናው ስለተደፈረ እና እዛ ሸጎሬ ውስጥ ስለተማከለ ቁጭት አለባቸው፤ ንዴት አለባቸው፤ ጸጸት አለባቸው።
ከእውነት ጎን የቆሙ አንድ የነፃነት ታጋይ ሳይሆኑ ዕብለትን፤ ዘረፋን፤ ወረራን፤ የሰዎችን ሰቀቀን እና ስጋትን፤ ለወንጀል እና ወንጀልን ለሚሠሩ የደገፉ፤ የቆሞ የወገኑ የጭቃ እሾኽ መሆናቸውን በሚገባ ደርባባው የኢትዮጵያ ህዝብ አይቷቸዋል በጥሞናም አዳምጧቸዋል። ተመስገን!
ያን ጊዜ እኔ በ2008 ስጽፍ ያልተረዱ ወገኖችም አሁን እንዲህ ገመና ዝርግፍግፍ ሲል ያዩታል። እንዲያውም አንድ ጊዜ ጸሐፊ አቶ ኤርምያስ ለገሰ እሳቸው የፃፉትን እንደ ናሙና አድርጎ ሲጽፍ ተችቼ ሁሉ ጽፈያለሁኝ። ምክንያቱም ወደ አንድነት ለፌክ ከተቀላቀሉ ጀምሮ ሥራዬ ነበሩ እና። አብሶ ሥልጣኑን በቀይ ምንጣፍ ከተረከቡ በኋዋላ የጻፉትን እሳቸውም ያውቁታል ልብ ያለንም እናውቀዋለን እና። ብቻ አንድነት የፌክ ድራማ አዳራሽ ነበር። እውነተኞች ደግሞ የካቴና ቀለብ።
· ጫና ከበዛ እንዲህ እና እንዲያ?
ሌላው ትግራይ የፈለገችውን እርምጃ መውሰድ ትችላለች። አይደለም ትግራይ ኤርትራም ከኢትዮጵያ ተነጥላ አይታዋለች። ኤርትራ እኮ የቀይ ባሕር ሰቅ ናት። አሰብም ሌላው አንጓ ነው። የ አፍሪካ ቀንድም ልብ ናት። ህዝቧም ሥራ ወዳድ እና ሥልጡን ነው። ይህም ሆኖ ከ ኢትዮጵያ ከጠረኗ ተነጥላ አፍሪካዊ ሲንጋፖር እንደ ህልሟ መሆን አልቻለችም።
በሌላ በኩል ኤርትራ እያለችላት ትግራይን እኮ ደርግ ጥሎላቸው ወጥቶ ነበር። ለትግራይ ነጻነት የታገለው ማሌሊት ትግራይ ሲለቀቅለት ምን ይላሳል ምን ይቀመሳል? በቃ ቀበቶውን ጠበቅ አደርጎ ዕድሜ ለጅሉ አማራ ትጥቅና ስንቅ እንዲሁም መንገድ መሪ ሆኖ ራሱን 27 ዓመት ሙሉ አሳረደ። እርግጥ ነው ጎንደር ግን ለተራዘመ ጊዜ ገትሮ ይዞ ተዋድቋል። በራሱ ስንቅ እና ትጥቅ።
ታሪክ ተደግሞ ብናዬው ልማዳችን ነው። አሁን ኤርትራ ስትገነጠል እልልታ ነበር። ድምጽ ሲሰጥ ወደ መስቀል አደባባይ ብቅ ብዬ አይቼ ነበር። እጅግ የደከሙት በምርኩዝ ሄደው ነበር ድምጸ ውሳኔ የሰጡት። እልልታው ግን መራራ ሆኖ 20 ዓመታት ተቆጠረ። ዛሬ ኤርትራ በመንፈሷ ወደ ኢትዮጵያ ስትቀላቀል ደግሞ እልልታ ሆነ። የቀደመው የአንድነት ሁኔታ በጥገናዊ መንፈስ ነበር፤ ቁልምጫም ልክ አልነበረውም። ቁልፍ ቦታው ለእነሱው ነው። ነጭ ለቫሾች ዲታዎች አራጊ ፈጣሪዎች እነሱው ነበር። ዛሬ ያነን እናምጣው ቢሉ አይቻላቸውም። ወርቅ ከቀለጠ ይፈሳል እና። ማንስ በጅ ይላል። እንደ ሁለት አገር ግን እንደ አንድ እትብታዊ ጎረቤታሞች በልክ ነው ሁሉም ነገር የሚሆነው።
ኤርታራ አይታዋለች፤ ቀምሳዋለች፤ መለዬት መራራነቱ የመንፈስ ነው። እግዚአብሄርም ተከፍቶባቸዋል። ማዬት ጥሩ ነው። ቀሪው ጊዜ እንዳንለያዬ
ሆነን ውህድ እንሆናል። እኔ በዚህ ጥርጣሬ የለኝም። ማዬት ተቋም ነውና።
ይህን ያደረገው የኢትዮጵያ አምላክ ነበር ለመልካምም ለደግም ነበር።
አሁንም ለመልካም እና ለደግ ከሆነ እግዚአብሄር የወደደው ይፈጸም ትግራይን በሚመለከት። አላዛሯ ኢትዮጵያ የሚቀርባት አንዳችም ነገር አይኖርም። በዬጊዜው እንደ ማስፈራሪያ፤ እንደ መያዣ ሆኖ ሊቀርብ አይገባውም። ገመዱ ብቻ ነው ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚቀርለት። ወይንም የብረት ሰንሰለቱ፤ ወይንም መታለቡ …
· ከጋህዱ ዓለም ወጣ ሲባል ...
እንደ መንፈሳዊነት ሲታይ ደግሞ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ የሰማይ እና የመሬት ወሰን ቢከለልም ጌታ የለሿ አድዮ መስከርም ላይ በዙር መቀነት ከስሜን እሰከ ደቡብ ከቀይባህር እስከ አዋሽ፤ ገናሌ፤ ባሮ፤ ተከዜ፤ አባይ ጎዴ፤ ሙያሌ ጠረፍ ድረስ ከምስራቅ እስከምዕራብ እልልታዋን እያስነካች እንዴት አላችሁልኝ እያለች ተንቆጥቁጣ ከች ትላለች።
ጌታ የለባት፤ አዛዥ የለባት፤ ሳጅኖች አያዟት። ተጋሩ ሊሂቃኑ ከመጋቢት 24 ቀን ጀምሮ እዛው መቀሌ ላይ መሸጉ። መንፈሳቸው በዬለም ነው ኢትዮጵያ መሬት ላይ ግን አድዮን ማን የትኛው ብርጌድ አገዳት? መስከረም ላይ ካለ ቢዛ ትግራይም ነበረች። ሁሉ ውቅያኖስ ቢኖር፤ ሰማይ ቢኖር ምድር ቢካለል አድዮ አበባ ኤርትራም አለች ኢትዮጵያም አለች።
እናም አድዮን የነቀለ ተጎጂው እራሱ ነው። ምክንያቱም አድዮ በዬትኛውም ኢትዮጵያዊ ደንበር ማህል ዳር ሳትል ጠርዝ ቁንጮ ጅራት ሳትል እንዴት ባጃችሁ ማለቷ አይቀሬ ነውና ተወደደም ተጠላም፤ ፊትም ኮሶ ተሆነ የውሸት ውሽክታም ተደረገ። ከሁሉ በላይ የኢትዮጵያ አሸናፊው ሃይል ማህንዲስ እዮር ብቻ ነው።
አሁንም ልዕልት ትግራይ የፈለገችውን እርምጃ ብትወሰድ አድዮም ትኖራለች። ዛሬ ዓይንህ ጥርስህ እዬተባለ የሚንቆለባበሰው ክብር ነገ ግን እንመለስ ቢባል አይገኝም። ፈጽሞ! ለትግራይ ህዝብ ያለው መጠኑን የሳተው እንክብካቤ ያቅለሸልሻል።
ቀድሞ ነገር ጎንደርም፤ ወሎም፤ አፋርም ከተዘጋ ትግራይ ምን ትሆናለች? ኤርትራ ስለቀመሰችው ከእንግዲህ ለማሌሊት አርበኞች ፊት ትሰጣለች ተብሎ በህልምም አይታሰብም። የማይደፈር መንፈስ አላትና።
እንዲያውም ያው መከረኛ ስደቱ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ይጥለቀለቃል እንደ ተለመደው፤ መከረኛው ጎንደር እና ወሎ ደግሞ እንደ ፈረደበት ተሸከም ይባላል እንጂ ማንም እገነጠላለሁ ይበል ያደርገውም አንዲት ቋት ሳይሞላ ይመለሳታል። „ላም እረኛ ቢያኮርፍ ምሳው ራቱ“ ይሆናል ነው ትርፉ።
አሁን በሸንፈት ላይ ላለው የወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ የውስጥ አርበኛ ሁሉ ድንኳ ጥሎ ያልቅስ፤ ሌላው ግን ይህን እያነሳ እና እዬጠላ እነሱን ለማስረዳት መደከም የለበትም። ሲፈልጉ ይቀጥሉ ሳይፈልጉ ይጠቅለሉ።
ልመና፤ ማቆላመጥ፤ እንክህ እንክህ ማለት በፍጹም እሰፈላጊ አይደለም። ማዕከላዊ መንግስት ያለው የ እነሱ የፓርቲ አባል እና ደጋፊዎች ባጀት እኮ ከዬት የሚመነጭ ይስላቸዋል። የፋፍሪካቸው ጥሬ ዕቃና ምርት የት ላይ ነው የሚራገፈው? ጥቅሙን የሚጻረር ተጠቃሚ ኑሮ አያውቅም፤ ትናንትም ተጠቃሚዎች እነሱው ናቸው ዛሬም ያን ሁሉ በደል በቡድን ፈጽመው ቀጥቅጠው አንበርክከው ገዝተው ተጠቃሚዎች እነሱው ናቸው።
እንዲያውም ዳኑ ስንቱ ታሥሮ ስንቱ ተሰዶ ስንቱ መዋቅር ተንዶ ይዘለቃል እራስ እግሩ እኮ እነሱው ናቸው። 27 ዓመት እኮ አንድ ትውልድ ነው። ብልሁ ወጣት ሊሂቅ ዶር ጌታቸው ደረስ እንዲህ ጭብጡን አስቀምጠውታል።
ESAT Bezih Samint Sisay with Dr Semahegn Gashu and Dr Derese Getachew Fri 25 May 2018
በሙያ በልምድ በዕውቀት በታቀደ ሁኔታ ተሰርቶበታል። ከእንግዲህ ግን አራጦ መርገጥም መግዛትም መጠቀምም አይቻልም። አንድ ሰው እስከ ጥፍሩ ድርስ ሰው የጠፋ ይመሰል በስልጣን መነከር አይኖርም። ስልጠናውም ድልድሉም እኩል ነው። ውክልናውም እንዲሁ።
አስመስሎ በህብረ ብሄር ፓርቲም በፌክ ኢትዮጵያዊ ዜግነትም ፊጥ ቀርቷል። እርማችሁን አውጡ። ያው መሞከሪያ ጣቢያው አማራ ነው ዛሬ አማራ ልብ ገዝቷል። አቅም መዋል ካለበት ቦታ ብቻ ነው የተደሞ ዕድምታው። ይህንንም „በሙያ በልብ ነው“ ይወራረዳል። በዬትኛውም መስክ ሙሉ ተጠቃሚዎች እነሱ ነበሩ እነተጋሩ። ቀረ የሚባል ነገር የለም። ሥነ - ጥበብ እኮ ብቃት ቀርቶ ዞግ ከሆነ እዬገለማው ዘመን ባጀበት ውጦት የሆዱን በሆዱ አደርጎ። ተሳህለነ! ዘመናዮች ደግሞ ወርቅ ልብሳቸው እንዲህ ነው ...
እንዲህ ገመናውን እዬዘረገፈ የሚነገርን ሁሉ አሁን የሚኖረው እራሱ በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት እንጂ በሌላ አለመሆኑን ቢያውቀው ደግሞ ጥሩ ይሆናል። ሲበዛ ማርም ይገለማል። በዚህ ይቀጠል ከተባለ የሚጨንቀውን ይጭነቀው፤ የሚከበደውን ይክበደው አሟራ ቀላቢው አምላክ ኢትዮጵያን መቼውንም አይረሳትም።
አብሶ ቅኑን አማራ ፈጽሞ ፈጣሪው አይረሳውም፤ ትናንትም ጉሮሮ ነው ዛሬም ጉሮሮ ነው፤ ነገም ጉሮሮ ነው። ትናንትም አሻጋሪ ነው ራሱን ረስቶ ዛሬም እንዲሁ። ይህን አምላክ የሰጠውን ጸጋ እና በረከት ግን ኢትዮጵያዊነታቸውን ለባንዳዊ ተልዕኮ ለሚያውሉት ቁብ ሊሰጠው፤ እልህ ሊገባበት አይገባም። ለእናቱ ሊሰጣት ከሚገባው ፍቅር ቅንጣቢ ሊቀንስባት አይገባም። የአያት ቅድመ አያቶቹ አደራ አለበት።
ይልቁንም የማህበረ ደራጎን መንጨርጨሩ ቀጥሎ እንዲለይለት የለውጡን መንፈስ ተንከባክቦ በትጋት ሁሉም እንደ አንድ አንዱም እንደ ሁሉ ከአብይ ሌጋሲ ጋር ጠንክሮ በመትጋት ፋሺዝምን፤ ናዚዝምን ከምደረ ኢትዮጵያ በመንቀል፤ የአረመኔነትን፤ የራስ ወዳድነትን ሥርዓታዊ ዶክተሪን ሥረ መሰረቱ መንፈሱን በማስወገድ የደርሻውን ሊወጣ ይገባል እያንዳንዱ በግል ሁሉም በጋራ።
አብሶ የመንግሥት ሠራተኛው በዬቢሮው ያለውን ሳቦታጅ በማጋለጥ እና ትርፍ ሰዓት ጨምሮ በመሥራት ማናቸውን የሻጥር ሴራዎችን ደርምሶ አላዛሯ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሁለገብ መሪ ሆና የምትወጣበትን ትጋቱን በተግባር ማስመሰከር ይኖርበታል። ካለ ቀነ ቀጠሮ። ይህ የተስፋ ጣዝማ ለነፃነት ለራባው የድል መባቻ ብቻ ሳይሆን የድሉ መሰነበቻ የስቀዩ ደግሞ መደምደሚያ ድንቅ የታምር ዘመን ነው። ተመስገን!
መልካም ጊዜ ላይ ነን። ፌክ የሆኑ ነገሮች በሙሉ የማናዘርዘሪያ ጊዜያቸው አሁን ነው። እማዝነው ግን ለትግራይ ቀጣይ ትውልድ አብረን ቀጠልን አልቀጠልን ተለያይተንም በሰላም ለመኖር የፖለቲካ ሊሂቅ ልጆች የሌሉት መሆኑ ነው።
ትግራይ የወላድ መሃን ነው የሆነችው። ባገለግራጫም መክኖባታል። አንድ ጊዜ ከቶ ትግራይ ግራጫማ ጸጉር የላትንም ብዬ የውስጥ ቁስለቴን ጥፌ ነበር። አንድ የምህረት የእርቅ አበው ግን አሉን ደጉ አቶ ገ/ መድህን አርዕያ በስተቀር አንድስም እንኳን ልጆቹ ኢትዮጵያን አጋደመው ስለራዱት ማህበረ ሲኦሎች መስክሮ ከድምጽ አልባዎቹ ከኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ጎን ደፍሮ ሊቆም አለመቻሉ እጅግ ያሳዝናል።
በተረፈ የአቤል ዕንባ ምንጊዜም ስለሚጨኽ እኔ በተጋሩ ሊሂቃን ትእቢት እና እዮርን አብዝቶ የመዳፈር መከራ እሳት፤ ትል ከሰማይ እንዳይዘንብ፤ የሚመኩበት የአሽዋ አንገናባት በአንድ ቅስፈት በመሬት መራድ እንዳይወድም፤ ወይንም ቀጣዩ ትውልድ ሲወለድ ያልተስተካከለ አዝጋሚ አዕምሮ ይዞ እንዳይፈጠር ነው የምሰጋው። በሰው ልጅ ላይ የደረሰ ግፍ እና በደል እንዲህ የቅልሞሽ ጨዋታ ስላልሆነ። እንዲህ የጌም እንድርቺ እንድርቺ ሳላልሆነ።
እንደ ቸርንቱ ብዛት የንጹሃን የተጋሩ ቤተሰቦችን ዕንባ ቆጥሮ ልዑል እግዚአብሄር እንዲህ ውሉ ጉዞው የማይታወቀው፤ መያዣ መጨበጫ የሌለው ግራኞች መከራ ተጋሪ እንዳይሆን ያሳስበኛል።
እኔ ጉዳዬ የዕብለት ጋሻ ጀግሬውችን የናዚ ማንፌሰቶ ባንዳዎች ጉዳይ ሳይሆን የድምጽ አለባዎቹ እናቶች የዘመናት ዕንባ ስለሆነ እጸልያለሁኝ - አብዝቼ።
ትዕቢት እማ ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ በላይም አልነበረም፤ ከአባ ጳውሎስ በላይም አልነበረም። ከእዮር ቁጣ እና ውሳኔ አንዳቸውም አላመለጡም። በዳይ በበደሉ ልክ ራሱ ፍርድ ሲሸከም የተገባ ነው፤ በእነሱ ህጻጽ ግን ለኃጣን የመጣ ለጻድቃን የሆነ ዕለት ነው መከራው። የሰማይ ቁጣ ህግ ስሌለው … ይህ እኔን ያሰፈራኛል።
እርቃናቸውን የቀረቱ፤ የፖለቲካ አቅማቸው ለአቅመ አዳም ያላደረሱት ጸሐፊ አቶ አስራት አብርሃም ግን እንዴት ብለው ከእንግዲህ በህዝብ አደባባይ ሊቆሙ እንደሚችሉ፤ እንደምንስ የጥበብ ቤተኛ ሆነው ሊቆሙ እንደሚችሉ፤ እንደምንስ አንጀታቸው ከበሽታ ላይ ሳይወደቅ እንሚቀር እግዚአብሄር ይወቀው።
እኔ የአንጀት በሸተኛ ሆኜ ነው የኖርኩት በእነሱ መሪዎችማንፌሰቶ አረመኔያዊነት ምክንያት። አሁን ደግሞ ታምራዊ መዳን ላይ ነው ያለው አንጀቴ። ሃኪሞች የአንጀት ኤክስፐርቶች ከሚገልጹት በላይ ውጤታማ የሆኑበት ምክንያት ሌላ ምንም ሳይሆን መጋቢት 24/2010 የሰጠኝ ትንሳኤ ፈውስ ልዩ ጸበል ነበር። ጫና የለበትም አንጀቴ አሁን። ስለዚህም ወደ ተፈጥሯዊ ሰላሙ ተመልሷል። መዳህኒቶቼም ቁመዋል።
እኔ „የነፃነት ሃይል ነኝ“ የሚሉ አንዳቸውም ይህን ዕድል ቢያገኙ ሰለማውቃቸው የልቤ አይሆኑም ነበር። ከበሽታዬም አልፈወሰም ነበር። የአሁኑ ለውጥ ግን ከመጀመሪያውም ጀምሮ አብሬው የቆምኩት የውስጡን ድንግልና በማስተዋል መርምሬ ነበር። አላፈርኩም። አንገቴንም አልደፋሁም።
ያን ጊዜ አብይ ኬኛ የእኔ ብቻ ነበር ሳታናው ድህረ ገጽን ጨምሮ ሁለት ነፍስ ብቻ። አንድ ብዕር አንድ ብራና። ዛሬ አብይ ኬኛ የሉላዊ ነው። ያን ጊዜ አብይ ብዬ ስገባ ለሙግቱ ሪፈረንስ ማድረግ ስለነበረብኝ አንድ ሺ ለማግኘት ጉግል ላይ አብዩን ፈላጊ አይቻልም ነበር አሁን ወደ 4 ሚሊዮን ገብቷል።
ነገ ደግሞ የአፍሪካ የሊደርሽፕ የተጽዕኖ ፈጣሪዎች መሪ አብይ ኬኛ ስለሚያሸነፍ ቁጥሩ በ30 ሰከንድ ከ4 ሚሊዮን ከዚህ በላይ ይሄዳል። ከዚህም በላይ ሉላዊ ሸልማቶችም ይቀጥላሉ። ታምር ነው ኢትዮጵያ እያሰተናገደች ያለችው። ራሱ የተባበሩት መንግሥተት የሴቶች ክፍልም ይህን ጉዳይ ባሊህ ሊለው ይገባል። ገድል ነውና።
ለዚህ ነው እኔ በ2017 በዚህ ሰው ጭንቅላት ውስጥ ብሄራዊ ቀን የሚያስወስን ቁምነገር አለ ብዬ አብይ ኬኛን ከፍል 6 ማጠቃለያ ስሰራ የጻፍኩት።
https://sergute.blogspot.com/2018/05/05.html
ካልኩት ነገር አንዳችም አልጎደለበትም። ይህ ታምር ለእነ አቶ አስራት አብርሃ መብረቅ ሆኖባቸዋል። እሰይ እልልልም ተመስገንም ብለናል ---- ቅኖቹ ደግሞ!
ከእንግዲህ ለታላቋ ትግራይ ዳግሞ ማንሰራራት እንደሚታገሉ በገደምዳሜ ነገረዋናል አቶ አብረሃም አስራት። በሽምቅ ውጊያ እያዘናጉ መጪነት አፈር ለብሷልና። ኢትዮጵያ ከእንግዲህ የኢትዮጵውያን ጥገት እንጂ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ጥገት ብቻ መሆኗ የማይቀጥል ስለመሆኑ በፍጽምና መናገር ይቻላል። እርማቸውን ያውጡ። ተሰባስበው ደመር ይቀመጡ ማህበረ ማሌሊት።
ምክንያቱም የዚህ ሁሉ ታምራታዊ ጉዞ ምክንያቱ የእዮር የበቃችሁ ደወል ስለሆነ። እዮር እኮ ጠ/ሚር አብይ አህመድን ጠልፈው ለመጣል ሲሟመቱ በዋዜማው ምልክት አሳይቷቸዋል።
https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_25.html
ልክ ለራስ መንገሻ የሖንስ እንዳሳዬው። ምልክት ብዬ ጽፌላቸው ነበር። ራስ መንገሻ የሖንስ ግን በአምላካቸው በጽኑ ስለሚያምኑ አምላካቸውን አዳመጡ እና ከሽንፈት ከውርደት ዳኑ። የአሁኖቼ ደግሞ እንጠራራለን ሲሉ ደግሞ ምልክቱን ይቀጥልላቸዋል።
የሰማይ ታምር ዛሬ ኢትዮጵያ መሬት ላይ መጻፍ እስኪያቅት ድረስ ውጦናል። ታምሩን እኮ አሳይቷል። የመሠረተችውን ፓርቲ በሾጤ ገብቶ የሚዲያ ኮከብ ሲኮን የ አንድነት መሥራቿ የትናንቷ ወጣት ብርቱካም ሚዴቅሳ እራሱ እዮር ምን ያህል የከፍታ ቦታ እንደሰጣት፤ ያሰደዷት፤ የተቀናቀኗት፤ የገፏት፤ ያሰከፏት ሁሉ በእሷ መንፈስ መመራት ግድ ሆነባቸው። ስለምን? የዚህ ዘመን አውራ መሪ ውሳኔ ሰጪው ዲዛዬነሩ ሉዑል እግዚአብሄር ስለሆነ።
· ሽፍት አደረገን
እኔ ከአንጀት በሸታ ስፈወስ አሁን ደግሞ ተረኛው አቶ አስራት አብርሃም ይሆናሉ ማለት ነው። አያያዘቸው ከውስጥ ስለሆነ ጉዳታቸውም የውስጥ ነው የሚሆነው። ሽፍት አደረገን ማለት ነው። ተመስገን!
ሃዘኑ ከውስጣቸው ገብቷል። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕው መንግስት መቅኑ በጥበብ ፍስስ ሰላለ። ሳያስቡት ሳያልሙት፤ ስለሆነም ዕናባቸውን በወያኔ ሃርትነት ትግራይ የሰንብት ዶፍ ምክንያት አፍሰዋል፤ ዕናባቸው የፈሰሰው በውስጥ ነው። ያፈሱስት እንባ በውስጣቸው አመቅው ያያዙት የ100 ሚሊዮን ህዝብ የስቃይ ዘመን ፍሰሃቸው ስለነበር ያ ስለቀረባቸው ነው። ለዚህ በትርጉም የሚቃና አንድም ሁኔታ አይኖርም።
ከሁሉ በላይ የዚህ ለውጥ መሰረታዊ ሞተር መንፈስ ደግሞ ነገረውናል። እሱም ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ነበር። ለድላቸውም እሳቸው ነበሩ ማለት ነው ኮነሬሉ። ቅብዕ ስላለቸው ቅብዕቸው ተሰውሮ ነው የቆዬው። አልደፈረም ብለው ሲነሱ ደግሞ ታዬ በዓለም አደባባይ።፡
እሳቸው ግፍ በደል ክህደት ሲፈጸምባቸው ደግሞ ምክንያት ሆነው ይህን መብራታዊ ዘመን አመጡልን። ንጹህ መንፈስ ስላላቸው። ሌላ እነሱም እኛም እማናነሳው የካዱት እና የከዱት እዮር በአጸደ ነፍስም ሐሴት ያደርጋል የድብ ባህሩን ተጋዳይ ጎንደሬን በሚመለከት።
የጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ታሪክ የሰራበት ቤት በሙዚየምነት ተመረቀ ህዳር 23 ቀን 2011
ዘመን እንዲህ ነው ይከሳል። ዘመን እንዲህ ነው ታሪክ ይሰራል። ዘመን እንዲህ ነው ይፈውሳል። ዘመን እንዲህ ነው ያድናል። ዘመን እንዲህ ነው ዋጋን አብዝቶ ይከፍላል።
እኛ ዋጋችንን እዮር ከፍሎናል። ስለሆነም ዕለታችን ሁሉ በሻማ ብርሃን አሽሞንሙነን እግዚአብሄርን እያመሰገን ለለውጡ ሐዋርያት ዕድሜ እዬለመን፤ ይህን ሳያዩ ያለፉነትን ነፍስ ይማርልን እያልን፤ በእኛ መንፈስ ዙሪያ አብርው የደከሙ የውጭ ዜጎችን ልብ ይመርቅ ብለን ፍስሃን ሰናይን ተስፋን ሰንቀን ነገን በጉጉት እንጠብቃለን። ተመስገን!
ሙሉ በሙሉ ለውጡ ከታለመለት ግብ ይደርሳል! የታላቋ ትግራይ ህልም ተረት ሆኖ ደቆ ብን ትን ብሎ አሮ እና ከስሎም ይቀራል! ወንጀለኞችም ምድራዊው ሳይሆን ሰማያዊ አምላክ ፍርድ እና ዳኝነቱን ይሰጥበታል! ይህ ሁሉ የሚሆነው በሰዎች ብቃት ክህሎት አይደለም በእዮራዊ ጥበቃ እና አይዟችሁ ባይነት እንጂ። ወጀቡ ሁሉ ረብ ብሎ ኢትዮጵያ ቀኗ ቧ ፏ ፍንትው ብሎ ይፈካል …
· ልዕልት ትግራይ እና ሙሉ መብቷ።
በመጨረሻ በልዕልተይ ትግራይ በተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ ስልፍ ተካሂዷል። ማንም ያሰናዳው ህዝብ ይህ መብቱ እንዳይነፈግ ነው መራራው ትግሉ። ስለዚሀ ለነፃነት የሚታገል ሰው ይህን ሰልፍ በአሉታ ሊያው አይገባም።
አቃቂር ሊያወጣለት ሆነ ሊያጣጥለው አይገባውም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጫካ በነበረበት ጊዜ ህዝብ ባያቀፈው ኖሮ ለዚህ ድል አይበቃም ነበር። አሁንም የትግራይ ህዝብ በቀህኝ ቢለው ከስህተቱ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ይማር ነበር። በስህተቱ እንዲቀጥል የሚያደርጉት መረጃው ያላቸው ሊሂቃኑ ናቸው እነ አቶ አስራት አብርሃም፤ እነ አቶ አብርሃም ደስታ ዓይነቶች።
የሆነ ሆኖ ማንም አሰናዳው ሰላማዊ ሰልፉ በአጀንዳ ይዤ ያልጻፍኩት መብታቸው ነው ብዬ ስለማምን ነው። ጥቅሙን የሚጻራር ተጠቃሚ አይኖርም፤ አይፈጠረም ካለ ወለጋ ነዋሪዎች በስተቀር። ስለሆነም የትግራይ ህዝብ በመብታቸው መጠቀም መብታቸው ነው። አጥቁረን እንመልከተው። ዴሞክራሲ ማለት የሚመችን ለመቀበል ህሊናን ማሰናዳት ማለት ሳይሆን፤ ይልቁንም የማይመቸውን ለማስተናገድ መድፈር መፍቀድም ማለት ነው።
ትጥቅን በሚመለከት የስሜን ኢትዮጵያ ንጹህ ባህል ነው። ጎንደር የአማራ ተጋድሎ አብዮት ሲቀጣጠል በሩምታ ተኩስ ነበር፤ የሰምዕቱ አርበኛ አቤ ጎቤ ሙት ዓመት ሲከበር በሩምታ ተኩስ ነበር። በሰርግ፤ በልጅ መውለድ፤ በዬምሥራች ጊዜ በሞት በስንብት ተኩስ አለ የጠበንጃ ሰልፍ ትዕይንትም።
ስለዚህ ከሌላ ነገር ጋር ማያያዙ ባህላችን ትውፊታችን አለማወቅ እና እኛ ሁልጊዜ ሁሉንም ነገር በአሉታ ስለመንመለከተው እንጂ ምንም የከፋ ነገር የለበትም። ለ አንዱ ሲሆን ትክክል ለሌላው ሲሆን ጥርጣሬ ሊሆን አይገባም። ከጎንደር የተነሱ ታጠቂዎች ወደ ራያ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ሄደዋል። ያው ለስሜን ሰው መሳሪያ በትሩ ዱላው ማጫው የወንድነቱ መግለጫ ነው።
ስለዚህ በትግራይ ከተሞች የተደረጉ ሰልፎች የጠበንጃ ትርኢት መታዬታቸው ባህላችን የእኛነት መግለጫችን አካላችን ስለመሆን ከልብ ልንቀበለው ይገባል።
ጀግንነትን በሚመለከት የአንድ ብሄር ወይንም የአንድ ብሄረሰብ መለያ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የወል የመለያ ዕሴት ቢባል ጀግንነት፤ አትንኩኝ ባይነት፤ ወኔ፤ አክብሮት፤ አልደፈርም ባይነት፤ ተፈሪነት፤ እንግዳ ወዳድነት፤ አብሮነት፤ መቻቻል መለያችን ነው። ይህ የእኛ ብቻ አይደለም የኤርትራም ጭምር ነው።
ምክንያቱም ሰዎች ከሰዎች ፈቅደው ወይንም ተገደው ሊለያዩ ይችላሉ። ነገር ግን እግዚአብሄር አንድ አድርጎ የሰጠን ስጦታ ግን መለያዬት አይቻለውም ማንም አቅም የለውምና።
ኢትዮጵያዊ ዜጋ ኤርትራዊ ዜጋ ምን ያቆረኛዋል ቢባል የአድዮ አባባ አዕማደ ሚስጢር ነው። ያ የአድዮ አበባ ኪናዊ ሊንክነት ነው ደግሞ የጀግንነቱ ሚስጢር።
በሥጋ የተለዩን ቅድመ አያቶቻችን መቃብርን ፈንቅለው ቢወጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ማህተማቸው ይገኛል። አሁን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አያት የተቀበሩት ጎንደር አባጃሌ ተ/ሃይማኖት ነው። ከሙታን መንደር ቢነሱ ያ ሰንደቅ ከግንባራቸው ተለጥፎ ይገኛል።
ያ ሰንደቅ ደግሞ የደማችን መግለጫ ጀግንነታችን ነው። ከዚህ አንጻር ነው እውነት እውነትነቷ ለትውልድ በልጽጋ መታዬት ያለባት። ስለዚህ ትግራይ ላይ የታዬው የጀግንነት መንፈስ የእኛም ነው፤ ትውፊታችን ነው፤ ትሩፋታችን ነው ብሎ ከድንግል መንፈስ በአዎንታዊነት መቀበል፤ በቅንነት ማዬት ይገባል።
ብዙውን ነገ ማዬት የሚገባው በሃሳብ ዓውደ ምህረት እንጂ የፍላጎት ልዩነቶችን የባሩድ ቀጠና አቅጣጫ ማስያዝ አይገባም። እኔ ጦርነት የሚባል ነገር ማዬትም መስማትም አልሻም። በቃት ኢትዮጵያ። በቃቸው የኢትዮጵያ እናቶችም። እኛም ደክሞናል። አይበቃም ወይ?
ዋሽቶ ማስታረቅ ነው አዳኙ መንገድ፤ እንዲህ ከስሜት ጋር ማያያዝ አይገባም፤ እንኳንስ ለትግራይ ህዝብ ባህሉ የሆነውን የጠበንጃ ትርኢት ማሳዬት ቀርቶ። እኔ እኮ የዘንድሮ መስቀል ደመራ ላይ ርችት ሲተኮስ ኡኡ ነው ያልኩት። ስለምን? ትውፊታችን ትሩፋታችን ስላልሆነ ዶግማም ቅኖናም ስለተጣሰ።
መሳሪያ ለስሜን ኢትዮጵያ የነባቢቱ ዶግማ ነው። ኢላማ መተኮስ ሁላችንም ተምረናል። እኔ ተምሬያለሁኝ። አሳምሬ አነጣጥሬ መተኮስን ተለማምጃለሁኝ። ወታደር አይደለሁም። ሲቢል ነኝ። ግን ትውፊቴን ባገኘሁት አጋጣሚ ለመማር፤ ለማወቅ ግን ስንዱ ስለሆንኩኝ ተምሬያለሁኝ አነጣጥሮ መተኮስን።
በእግር መሄድ አንድ ትውፊታችን ነው። አቀበት ዳገት ቁልቁለት መውጣት እና መውረድም ባህላችን ነው፤ ጥበብም ነው። የባህላዊ ስፖርት አካልም ነው። ለዚህም እኔ የጎንደር ከተማ ልጅ ነኝ፤ ይህንም ፈቅጄ እና ወድጄ እንደ ሙያ ተምሬዋለሁኝ - ፈረስ ግልቢያ ሳይቀር አሁን ካልጠፋኝ በስተቀር። ትውፊቴ ነውና።
ዓራት ዓይናማው መንገዳችን የአብይ ሌጋሲ ብቻ ነው!
አብይ ኬኛ!
ኢትዮጵያ በክብር ታሸነፋለች!
ውዴቼ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ