እራሱ „ተጋድሎ“ ዬሚለው ሥያሜ ቃለ ወንጌል ነው። ዛሬን የሰጠን ትናንት ነው።
ዬስጋት ቋት - ጦሮ!
„አቤቱ፦ ምህረትም የአንተ ነው፤
አንተ እንደ ሥራው ለእያንዳዱ
ፍዳውን ትሰጣለህ።“
(መዝ. ምዕራፍ
፷፩ ቁጥር ፩፫)
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
04.12.2016 (
ዙሪክ - ሲዊዘርላንድ።)
v ጠብታ።
ውዶቼ
ይህም የአማራ የህልውና የመንነት ተጋድሎ ወጀብ በበዛበት ወቅት የጻፍኩት ነው። ሳተናው/ ኢትዮ ሪጅስተር አትሞልኝ ነበር። መርቁት።
ጀግና እሱ እንጂ ሌላ አልነበረም። ጀግንነት በገንዘብ ሳይሆን በድርጊት ነው የሚቀልመው። የቃላት ግድፈትን ብቻ ነው እማርመው እና
የሚገርሙኝ አገላለፆችን አቀልማቸዋለሁኝ። የእኔ የእኔ የማይመስሉኝ ግን የቀደሙ አገላለፆች አሉበት። እኔን እራሴ እዬገረመኝ ነው
ሳነበው …
ጹሑፉ
በዛን ዘመን መንፈስ እና በተነሳሁበት የአማራነት ማንነት ቃለ ምልልስ ውስጥ ነው መታዬት የሚገባው እሺ ውዶቼ። ግን ታሪክም ስለሆነ
ቀንበጥሻ አርኬቧ ላይ ልታስቀምጠው ወዳለች። እንዲህ ነበር የተጀመረው
…
v እንዲህ
…
ዓለም እራሷን ፈጣሪ አደራጅቶ ነው ዬፈጠራት። በአህጉር - በአገር - በዬብስ፤ በውቅያኖስ፤
በሰማይ አሳምሮ ነው ዬሠራት። ዬሰው ልጅ ደግሞ ሥጦታውን፤ ዘመኑ በፈቀደለት እውነት፤ ለእሱ በሚያመች መልኩ ስልት ቀይሶ፤ ህግ
ሰርቶ፤ ዬአፈጻጸም መመሪያ አሰናድቶ ተጠቃሚ ሲሆን ቆይቷል።
በዓለም ከድርጅት ውጪ
ዬሆነ ነገር ዬለም። ስለሆነም ዓላማና ግብ ያለው ዬሰው ልጅ ዬኑሮው ላዕላይና ታህታይ መዋቅር ድርጅት ነው ማለት ያስችላል።
v መደራጀት ማለት ምን ማለት ነው? ግባእቱስ?
በቀላል አገላለጽ ብቻ ነው ዛሬ እምገልጸው። ምክንያቱም ዬተነሳሁበትን አጀንዳ እንዳይጫንብኝ ስለምሻ። መደራጀት ማለት በሚያግባባ ፍላጎት አቅዶ መሰባሰብ - አልሞ ዬወል ማህበር መፍጠር ማለት ነው።
ዬጋርዮሽ ዕሳቤ ማስፈጸሚያ ቋት - ዬዓላማ
ማህደር እንደ ማለት።
መደራጀት ዬስብስቡን ሂደት፤
የሚያቅፋቸውን አካላትና አባላት ሲገልጽ፤ ድርጅት ደግሞ ዬአወቃቀሩን ባህሪ፤ ዓይነት፤ ቅርጽና ይዘቱን፤ ዬተቋሙን ተፈጥሮ አቋም
ይገልጣል። ለተሰባሰበው አቅም፤ በነቃ ህሊና ዬሚከወን ወይንም ለሚታሰበው ዬአቅም ማማከያው ማዕከል ድርጅት ነው።
ድርጅት ሙሉ አቅም ያለው የሙያ
ዘርፍ ነው። ትልቅ ዬዕውቀት ማዕከልም
ነው። መደራጀት ሲባልም የሰዎች ብቻ አድርገን ማዬት ያለብን አይመስለኝም።
እንሰሳትም፤ ነፍሳትም በተቀደ መልኩም ባይሆን ኑሯቸው በመደራጀት ማዕቀፍ ዉስጥ ስለሆነ።
የዱር እንሰሳት በዬዘራቸው የተደራጁ ናቸው፤ በቤተሰብ ደረጃ ዬመኖር ልማድ አላቸው። „መንጋ“ የሚለው ስያሜም ከዚህ ከመደራጀት ጽንሰ ሃሳብ ጋር የተጋባ ነው።
በዬብስ፣ በሰማይ፤ በውሃ ያሉት ሁሉ የተደራጀ ሥነ - ህይወት አላቸው፤ አሣ፤ ዶልፊን፤
ዋል፤ ፒንጉይ፤ ዝብራ፥ ቀጭኔ፤ አንበሳ፥ ንብ፤ ጉንዳን፤ ቅምጫጭሪት፤
ፍላሚንጎ፤ ጭልፊት፤ እርግብ ኑሯቸውን ስትመረምሩት ደመ-ነፍሳዊ ቢሆኑም ዬጋራ ዬአኗኗር ዘይቤ አላቸው። በጋራ ይጓዛሉ፣ በጋራ ይበራሉ።
በጋራ ይተማሉ። በጋራ አጥቂዎቻቸውን ይቋቋማሉ። እንደ ወገናቸው ተራብተው በውልዮሽ ይኖራሉ።
የሰው ልጅም ከትዳር ጀምሮ ያለው የኑሮ መስመሩ ሁሉ ድርጅት ነው። ለእኔ የመጀመሪያው ድርጅት በፈጣሪ ቃል ለአዳም ከአካሉ ህይዋን ስትፈጠርለት ፈጣሪ በፈቃዱ ድርጅትንንም መደራጀትንም እራሱ በቃሉ ፈጥሮታል ብዬ አምናለሁ። ዓላማው ለምስጋና ግቡ ዬሰው ዘርን ለማበራከት ትውልድን፣
ህብረተሰብን ዬመፍጠር።
ይህም ዬተቃራኒ ፆታዎች የአኃቲነት ኑሮ። ጋብቻ። ትዳር። ዬማህበረሰቡ መሰረትነቱም
ከተደራጀ ዬስሜት ውህድነት መገኘቱ ነው።
ሁለተኛው የድርጅት የፈጣሪ ቃል የተመሰረተው
የኖህ መርከብ የሥነ - ፍጥረት ሁሉ መሰባሰቢያ ድርጅት ነበር - ለእኔ። በሁለቱ ዘመናት መካከል ከህይዋን ፍጥረት እስከ ኖኸ በነበረው
ጊዜ ውስጥም ቢሆን ሁሉም በዬወገኑ የተደራጀበት ሁኔታ እንደ ነበር አካል ዬሌለው አገልጋይ ቅዱስ ወንጌል ያሰተምረናል።
ከኖኽ የጥፋት ዘመን ድህነት በኋላ የአደረጃጀት ሁኔታዎች በተለያዬ መልኩ እንደዬዘመኑ
ተስተውለዋል፤ ሃያማኖታዊ ቢመስሉም፤ አስተዳደራዊ መልክ ያላቸው ጥቃትን መቋቋም የሚያስችሉ፤ ዓላማና ግብ ዬነበራቸው፤ ወቅቱ የጠዬቀውን
ፍላጎት ለማስፈጸም የአቅም አደረጃጀትና ስምሪት ከአመራር ክህሎት ጋር ተዋደው አሮጌውን ዘመን እዬሸኙ፤ ለአዲሱ ዘመን መቀበያ መጣኝ
ስልቶችን በመቀዬስ ዛሬን - ለዛሬዎቹ ድልድዮን ዘርግተው አቆይተውናል።
v መደራጀት በባህሪው፤
መደራጀት በባህሪው ወጥ አቅምን ማመንጨት፤ ማስተዳደር፤ መምራትና ማከፋፈል ይታይበታል፤
መደራጀት ዬመኖር ግንብ ነው። ዬመደራጀት አዳጊ ሁነት፤ ወይንም መቀጨጭ ዬሚወስነው ድርጅቱ
ወቅትን በማድመጥ አቅሙን ዬመመርመርና ወቅቱን ያደመጠ ስልት ዬመንደፍ ችሎታው ይወስነዋል። ይህን ካልቻለ ዬአድማጩ መንፈስ ቀስ-በቀስ እዬሸሸው ራቁቱን
መቅረቱ ሳይታወቀው፤ ቀጣይነቱን ጊዜ ይነጥቀዋል።
አብሶ እውነትን እዬራቀ በመጣ
ቁጥር ታላቁን ኃብቱን ዬህዝብ አመኔታን ጊዜ ይዘርፈዋል። በቃልና በቃላት ያሸበረቁ ዬዓላማና ግብ ማስፈጸሚያ ሰነዶችም
ዕጣቸው ሞት እንዲሆን ዬጊዜ ሰበር ችሎት ይወስናል። ዬጊዜ ትዕግስት ሲያልቅ ዬጊዜ ፍቅርም ይሰደዳል። ጊዜ አደብ ዬገዛ
ተግባር ካላዬ ዬስንብት ወረቀቱን ይግባኝ አልቦሽ ይሸልማል።
አንድ ድርጅት እቅሙን
መጥኖ መነሳትን ዋቢው ማድረግ ይኖርበታል። ህልሙን ለማሳካት
ዬስልትና ዬታክቲክ አቅሙ ለፈለገው እርከን ዬሚያደርሱት መሆኑን ምንም
ከማበከኑ በፊት ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል።
… ማለት ዬህልሙ አቅም በእጁ መኖሩን ማረጋገጥ ይኖርበታል። አጋዢ ገጠመኞችን ብቻ ተጠላይ ወይንም ተጠማኝ ከሆነ ጉዞው ትንፋሽ ያጠረው ይሆናል። በራሱ
አቅም ጎልቶ ለመውጣትም ሆነ፤ ህልውናውን ቀጣይ ዬሚያደርገው ድልድይ ዬዕክል ቤተኛም ይሆናል። ዬግቡ ሹልከተም አይቀሬ ነው።
· ይህን መቼም አሊ የማይባለው ድርጅቶችን ሁሉ ከመንበር
አውርዶ እኩል አደርጎ ይህ የለውጥ ዘመን አሳይቶናል። እና ሥርጉትሻ በዛን ጊዜ ይህ እንዳይመጣ ለሁሉም አማክራለች፤ ሳይከፈላት
በነጣ።
v ድርጅትን ማን? - እንዴት?
የሰው ልጅ አቅሙን ከአቅሙ አጋብቶ ፍላጎቱን፤ ምኞቱን፤ ራዕዩን፤ ለማሳካት አማኙ በእምነቱ
ዶግማ - ቅኖና፤ ፖለቲከኛው በዓላማው ራዕይ ዙሪያ፤ ሴቶች በፆታቸው፤ ወጣቶች በዕድሚያቸው፤ የጥበብ ሰዎች በጸጋቸው፤ ሙያተኞች
በክህሎታቸው፤ ጎሳዎች በዞጋቸው፤ ዲታዎች በኢኮኖሚ ተቋማት ይደራጃሉ።
የሁሉም ዬሰው ልጅ ዬሚፈጥራቸው ድርጅት የወል መግለጫ አላቸው፤ ይህም ሁሉም ድርጅት ዓላማና ግብ አላቸው። ነፍሳት፤
እንሰሳት ግን ዓላማና ግብ የላቸውም፤ እርግጥ እራሳቸውን ለመከላከል ቢራዳቸውም ኑራቸውን ለማሻሻል፤ ለማሳደግና ለማበልጸግ የሚያስችል
ጸጋ ስላልተሰጣቸው።
ስለሆነም በለውጥ ውስጥ በራሳቸው አቅም ጎልተው ለመውጣት አልተፈቀደላቸውም። የተፈጠሩት
ተፈጥሮን ለማስዋብ ብቻ ነው። እርግጥ ለሰው ኑሮ ደጋፊ፣ አገልጋይ፣ ደስታ ሰጪም ናቸው። ትጉህም ናቸው።
በሬ ንብን እንደ አብነት መውሰድ ይቻላል፤ ድርጅትን ሁለትና
ከዚያ በላይ ዬሆኑ ሰዎች በሚያግባባቸው መስመር ይፈጥሩታል።
ማንኛውም ድርጅት ኑሮው
የሚገነባው ዓላማውና ግቡን
ባመኑና ወደውና ፈቅደው አዎንታዊነታቸውን ባበረከቱ ሰዎች ይመሠረታል።
እሺታን በመፍቀድ። መርሁ
አባልነት በፈቃደኝነት ነው።
v እርካብ።
መደራጀት ሁለገብና ዘረፈ ብዙ ጥቅም ያለው የአመራር ሥነ - ጥበብ ልዩ ማዕደ - ዬአብሮነት ገበታ ነው። መደራጀትን አስፈላጊ የሚያደርጉት ገፊ ሁኔታዎችን
በቅን ልቦናና ከቂመኝነት በጸዳ መልኩ ከሆነ፤ „ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሞ ለሃምሣ ሰው ግን ጌጡ“ „ድር ቢያብር
አንበሳ ያስር“ „ከአንድ ብርቱ ሁለት መዳህኒቱ“ „ዬሺህ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ (አሰባስቦ ዬሚይዘው)“ ለማለት እንዲሉ ይሆናል።
መደራጀትን ዬጽናት አንኳር፤ ዬኃይል ማመንጫ ሞተርም ነው። ድርጅት መጠነ ሰፊ ጥቅም
አለው። በአመሠራረቱ ላይ ግልጽነት እንዲገዛው ከተፈቀደ
ዬስኬት አድባር ነው።
በመደራጀት መኖር ውስጥ አደብ ህልውናው ነው። በመደራጀት ህይወት
ውስጥ ረጅም የማስተዋል ጊዜ መፍቀድ ዬግብ
እርካብ ነው። መደራጀት ቁጭ ብሎ
ማጥናትን - መመራመርን፣ ይጠይቃል። ርጉ መንፈስን አብዝቶ ይሻል። መደራጀት አውራ ሥነ- ምግባሩ ከፍላጎት ጋር መደማመጥን በአጽህኖት
ይናፍቃል። የመደራጀት የአቅም ምንጭ ሕዝብ ስለሆነ የህዝብን ልብ - ልቤ ነው ብሎ መቀበልን በተደሞ ይሻል።
መደራጀት የቱግታ ቋት
ክፍሉ አይደለም፤ ይልቁንም ስክነት የአውራ መንገድ ጠራጊ መሀንዲሱ ነው። በመደራጀት ብቻ ግብ አይገኝም። መደራጀት ነገን መተንበይ ችሎ፤ የህሊና መሰናዶ ቀድሞ
ካላደረገ ሞገድ በተነሳ ቁጥር ባታቻ ይሆናል።
ስለሆነም የፈተና ገጠመኞቹ በመባተት ስለሚመሩና ስለሚወጠሩ የግጭት ዓውድ ከመሆን አያመልጥም፤ በግጭቶች ስበት ውስጥም የአቅም መራቆትና፤ ተስፋ ማጣትን፤
እንዲሁም የጠላት መብዛት ከዋናው ዓላማው ውጪ እንዲወጣ ስለሚያደርጉት፤ ምርጫው ተጫኝ ኃይል ይሆናል፣ አፈናም መተንፈሻ ቧንቧው።
ታሪኩም ምስቅልቅል
ያለ ህልፈት፤ እውነቱን እዬዘለለ በጋለበ ቁጥር ከባህር የወጣ አሳ እንዲሆንም ይገደዳል። ድፍረት ያንሰዋል፤ ቆሜበታለሁ ያለው አቅም
ንደት ስንቁ ይሆናል። ታዕማኒነቱም ለድርቅ ይጋለጣል።
ስለሆነም በአዲሶቹ ድርጅቶች ውስጥ መርህን በጠራ መስመር መወጠን ለቀጠሮ የሚተው አይደለም።
የአማራ ተጋድሎ ወጨፎው የበዛበት ዕንቡጥ ዬነገ ዬተስፋ ማህደር ነው። እራሱ „ተጋድሎ“ ዬሚለው ሥያሜ
ቃለ ወንጌል ነው። በመዳህኒታችን በእዬሱስ ክርስቶስ
ከሰባት ሥርአቶች ውስጥ አህዱ አብ ነው። የጌታዬ ቃል እንዲህ ይላል ….
„ መጀመሪያቱ ሥርአት እንዲህ ናት ዛሬ በህይወታቸው
ሳሉ
በኃጢያታቸው እንዳያስታቸው ይነሱ ዘንድ በብዙ
ድካም ተጋድለዋልና በብዙ ድካም ተጋደላችሁ ይሏቸዋል።“
(መጸሐፈ ዕዝራ ሱታኤል ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፳፪)
የወደዳችሁ ቀሪዎችን ፮ ሥርዓታት ቀጥላችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።
ይህ ሥያሜ እንደ ህይወት ቃልነቱ ቢያንስ መገለሉ ቢቃለልለት ምኞቴ ነው። ስለሆነም ዬአማራ ተጋድሎ ዬህልውና መሠረት
አቅሙን ከግብታዊነት በጸዳ ሁኔታ መገንባት
የመጀመሪያው ሲሆን፤ ዬአባልነት መቀበያ መስፈርቱ ግን የተልዕኮው
ጭንቅላት ፥ አንጎልም ነው።
ከምለጥፍላችሁ አውድዮ እንደምትረዱት ግን ዓላማውን - መንገዱን እንዲደራጀ የገፋውን
ህዝባዊ አብዮት በአረም ዬሚያስበላ ነው። ዬቂም ተርቲም ወበራ ለመልካም ነገሮች ቃሬዛ ነው። ዬተዛባ ዬዓላማ መንገድም ከመፈጠሩ
በፊት ሞት ጠሪ ጉጉቱ ዬሆናል። አንዲት ስንዝር ወደፊት ዬመራመድ አቅም አይኖረውም። ዕጣውም - ቹቻ።
ዬፖለቲካ ድርጅት ዬቅልሞሽ
ጨዋታ አይደለም። ዬቁም ነገር ማዕከል ዬድርጊት ዓውደምህረት ዬራዕይ ዬጽድቅ ጉዞ ነው። ዬቅራኔ አያያዙም
አትራፊ መንገዶችን ብቻ እንዲከተል ግድ ይለዋል። ዬቁመናው አገነባብ በመቻቸል ማዕቀፍ ውስጥ መኖር አለበት።
ይህ ውጪያዊውንም ውስጣዊውንም ችግሮችን ዬመቋቋም አቅም እንዲኖረው ይረዳዋል። ዬመንፈሱ
መሪ ሰብዕዊነት እንዲሆን መፍቀድም አለበት። እንዲከበር
ሌሎችንም ማክበር፤ ስህተትን ፈቅዶ መቀበል ዬውስጥ ሰላሙን ይጠብቅለታል።
v ለሌላው ሚዛናዊ ፍትህንና ዕውነተኛ ነጻነት እሰጣለሁ፤
ለዛ አታግላለሁ ብሎ ከማወጁ በፊት እራሱን በእነዚህ መርሆች ሥር ለማስተዳደር መቁረጥና መወስን አለበት። ነፃነት በራሱ በድርጅቱ ቤት ውስጥ መጀመር አለበት። በተለይ በአመሰራረቱ ላይ ድርጅቱ እንዲመሰረት
ላደረጉት ገፊ ጭብጦች ዬበቃ ነፃነት ዬመስጠት አቅም መኖር አዲሱን ቡቃያ ሃሳብ ዬሰብል ባለቤት ያደርጉታል።
በጠንካራ መሠረት ላይ ዬተገነባ ድርጅት ህልውና ዘላቂ ነው።
/ይህንን ሰሞኑን ጠ/ሚር አብይ አህመድ በ አጽህኖት ሲናገሩት ሰምቻለሁኝ። ዴሞክራሲን
ከራስ ስለመጀመር።/ የለጠፍኩት ሊንክ ዛሬ ላይ የለም። ግን ጭብጡን ጽፌው ስለነበረ መነሻ
ይሆናል።
v ዬማከብራችሁ ዬሐገሬ
ልጆች።
ዬለጠፍኩትን ሊንክ ሙሉውን ማድመጡ እጅግ
አስፈላጊ ነው። ሲሆን
ሲሆን ደግማችሁ አዳምጡት። ዬዕሳቤው
ፍሬ ነገር ኮሶም - ኮስኳሽም ነውና። እንዲህ
ይሉናል ዬድል አጥቢያ
አርበኞቻችን። ሙሁራኑ „አማረነት በደም አይደለም።“ „አማርኛ ቋንቋ መናገር ብቻ በቂ ነው።“
አቶ ወንድም አማራ አይደሉም ማለት ነው። „ዬትግሉ አቅጣጫ ተለዋዋጭ ሊሆን ይችላል።“ ይህ እንደሚሆን ይታወቃል። ዬአማራ ተጋድሎ ቅዱስ መንፈስ እንዲህ በጠራራ ጸሐይ እንደሚዘረፍ ተንባይ አያስፈልገውም።
„አያያዙን አይቶ ሸክሙን ይቀሙታል“።
ዬአደረጃጀት መስመሩ
„አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው ሁሉ በአባልነት ዬሚያደራጅ ነው።“ ገንዘብ ዬከፈለ ሁሉ ዬአማራነት መታወቂያ ዬሚታደልበት ዬገብያ ማዕከል። ቀጠሉ
… ዓለም አቀፋ ብቸኛ ጋዜጠኛ „ከስያትሉ ጉባኤ እኔ ነበርኩ። ስምምነቱና ዝንባሌው ይህ መንፈስ እንደ ነበረው ጉባኤው ላይ ተረድቻለሁ። ( ጋዜጠኛ አቶ ደምስ በለጠ።“)
ሞቅ ካለው ድንኳን ሰበረ አቶ ግርማ ካሳ ደግሞ „እኔ ኢትዮዽያዊ ነኝ። ዋው! ማለፊያ። „እራሴን አማራ
ነኝ ብዬ መናገር አልችልም። አሃ! „አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነኝ።“
ስለዚህ አማራ አይደሉም ማለት ነው።
ታዲያ ምን ዶለዎትና „ያገኘነው
መረጃ አላረጋገጠልንም“ ምን አመጣው? ባለቤት ሆነው እኮ
ቁጭ አሉ። እንደ ወሳኝ አካልም እያደረገዎት ነው። ህም! „ዬአማራ
ድርጅት መልቲ ኤትኒክን (Multi Ethnic) መሆን አለበት።
ይህ ጉዳይ በቀጥታ ዬሚመለከተው ዬአማራ ደም ያለበትን ብቻ ነው። ስሜት አይሸመት ነገር። ዬስሜት እኮ ገብያ አልተፈጠረለትም። ስሜት ደም ነው። እሚገዛ ቢሆን ሰሞኑን እናንተን ያዬ … በወረፋ
ነበር።
ከቶ ይሄ ዬደም ባንክ ዬሚባለው ይህችን ዬግብይት ዘይቤ አልደረሰባት ይሆን?! ሽልንጓን
በደራ ገብያ ይቸበችብባት በነበረ።
… ደሙ ከሌለ እንደ አማራ መፈጠርም፣ ማሰብም፣ መኖርም አይቻልም። ዬአጥንት ጉዳይ ነው። ዬትም ቦታ ሲታይ ዬተኖረው በዚህ ልጣጭ ጅምላዊ
አስተሳሰብ ነው። ከእንግዲህ መታለል አይኖርም። እኔ በግሌ ዬጉድጓድ ኑሮ ሰልችቶኛል። ዬተከድኖ ይብሰልም ጨቋኝ ትዕግስትም አንገሽግሾኛል። እኔም ሰለባ ነኝና።
ጥቁር ሲኖር ነጭ መኖሩ ይታወቃል። ቀን ሲኖር ጨለማ መኖሩን እናውቃለን። ዬአማራ ተጋድሎ መፈጠር ዓይነጥላውን ገፎታል፥ ዓይነት
አውጥቶለታል። በሌለንበት ማዕቀፍ
ውስጥ በግርዶሽ ታምቆ በጭቆና መኖር ዬለም ከእንግዲህ። ስለዚህ አታጭበርብሩን። ቦታችነን አውቀናል፤ መሰረዛችን ገብቶናል፤ እንደ አካፋና ዶማ ለመገልገያነት
ብቻ እንደምንፈለግ አረጋግጠናል፤ ልብ ሳንላቸው ሲስረከረኩ ዬቆዩት ዬሥነ - ልቦና ጫና ምክንያታዊ ዬነበሩ መሆናቸውን በመራር ሃዘን
ተገንዝበነዋል። ከጭንቅላቱ እኛን ባገለለ መንፈስ ውስጥ መኖራችነን አስተውለንበታል።
አቶ ግርማ ካሳ ለመሆኑ … ያቺ ግንቦት ሰባትን ላብጠለጠሉባት ጹሁፈወት ዬአልማዝ ቀለበት
አሰሩላትን? ለዚህ መተንፈሻ ቮንቯ ስላበቃቸዎት ስጦታዋን እንዳይንቁ እንጂ እሶዎንማ አገር ያውቀወታል ዬጥገናዊ ለውጥ አርበኛ። ፍሰኃዎት ዬአንድነት ኃይሉ ሲናድ ማዬት ነው።
በሰሞኑ „እኔ በግሌ ዬአማራን
በማህበር መደራጀት አላምንበትም“ ሲሉን አልነበርን -ም? ከቶ ማን ያበደ ይሆን ለጦሮ ይለፍ ዬሰጠዎት?! „ምን አደረገ
ትግራይ አትድረሱበት ሌላውስ መቼ ተነሳ“ ሲሉ ወርቅ ይነጠፍልህ ዬሚባሉ መስሎዎት ነበር።
ዬዕውነት ጹሁፎዎትን ሳነብ ቋቅ እያለኝ ነበር። ዬብዕር አለቅላቂነት አቅለሽልሾኝ ነበር።
አሁን ደግሞ አማራ ያልሆነ ከአናትሽ ወጥቶ ይዝፈንብሽ እዬተባልኩ ነው። እምምምምምምም! ያነን አማሽ
ጃኬት እንደዘለበ ይሄው እያዬን
ነው። ይገርም ነው ነገሩ …
„መልቲ ኤትኒክን (Multi Ethnic)“ እውኃ ያልነካው መንጠላጠያ ቆጥ ነገር ተፈለገ። ከቅንጅት እስከ አንድነት (ሰማያዊም አልቀረለትም) ጃኬት እዬቀያዬሩ
አለሁ - ለትርምስ። ጉድ በል ጎንደር!
„ወደ አንድ መጠቃለል
አለበት!“ ትርትር።
አቶ ግርማ ካሳ ያው እንደተለመደው - በቁርሾ ቀንበር ለማረስ ታጥቀው ተነስተዋል። „ዬአማራ ድርጅቶች
አንድ ሺህ ናቸው።“ ግን ዬዕውነት አንድ ሺህ ናቸውን? ዬሆነ ሆኖ ይህም መብቱ ዬአማራ ነው። እኔ ዬምለዎት አቶ ግርማ ካሳ ያ ዬጥገና ለውጥ ቁምጥ ይሉለት ዬነበረው ቁራኛዎት ዬት ተሸኝቶ
ይሆን? መቼ ይሆን በቃኝን ዬሚያውቁት? እንደ አንድ ኢትዮዽያዊ አስተያዬት መስጠት ሲቻል ቀጭን ትእዛዙን ምን አመጣው? ይህን መባተት
አተራምሰው፤ እረፍት ነስተው ላፈረሱት ዬድርጅት ሙት መንፈስ …
ዬኛ ዬአማራ ልጆች ህብረ ብሄር ያሰኛቸው በአባልነት ድርሻቸውን እዬተወጡ ነው። እኔ ለእነሱም ክብር አለኝ። ነገር ግን ዬመብት ጭነት በደማቸው ላይ እንዳይኖር መትጋት አለባቸው ባይም ነኝ። ዬግድ ከእነሱ እሲኪደርስ ድረስ መጠበቅ አይኖርባቸውም። በተገኙበት ቦታ ሁሉ ዬዕውነት አርበኛ መሆን አለባቸው።
በተረፈ ለመንፈሳቸው ለቀረበው አቋም ለማድር ዬማንም ፈቃድ አያስፈልጋቸውም። እናም እሶዎም
መልቲ ኤትኒክም (Multi
Ethnic) ዬማረከዎት
ከሆነ ዬፈቀዱትን መቀላቀል ይችላሉ።
ዬሚቀበል ከተገኜ። ስለምን?
በአንድም ጹሁፍ ላይ
ዬፀና አቋም ሳይሆን ዋላይ፤ ወላዋይ
አቋም ነው ሳነብ ዬኖርኩት፤ ሰማያዊ ሲፈጠር
ብዕረዎት ጨርቋን ጥላ
አብዳ ነበር።
በአንድ ወቅት
ወጣት ፓለቲከኛው ይድነቃቸውን ዘልፈዎት
ስለነበር ቢታሰር ፎቶውን
ይዘው ይወጣሉ ብዬዎዎት ነበር።
ሰሞኑን ደግሞ በእኔ
ምክንያት ታሰረ ምንትሶ
ቅብጥርሶ ሲሉን ነበር።
እኔ ዕውነቱን ብናገር ለምንም
ኃላፊነት ዬሚያበቃ ቋሚ አቋም ዬለዎትም። አቋሙዎት ዬተልባ ስፍር ነው፤ ወይንም
ግልብጥብጥ ዬሚያሰኘው ዬሽንብራ ቂጣ።
የአማራ ማንነት ዩተጋድሎ
አብዮት አስኳል አማራነት ደም ብቻ
ነው። ደሙ አማራ ዬሆነ ብቻ። ከአማራ ወገብ ዬወጣ። ደፍሮ
አማራነቱን መናገር ዬሚችል።
ብሄሩን ሲገልጽ ዬማይደናበር።
በጽናትና በኩራት አማራነቴ ማዕረጌ፤ ኩራቴ ዬሚል። እርግጠኝነትና በራስ ዬመተማመን ስሜቱ አስገኝ ኃይሉ
ዬአማራነቱ ደም ነውና። ለደሙ ፍጹም ታማኝ መሆንን ይጠይቃል። ደሙ ነው አማራነት። አጥንቱ ነው አማራነት።
በአውራ ማንነቱ በኢትዮጵያዊነቱ እንዳይደራደር ዬሚያደርገው ትልቁ ሚስጥር ዬአማራነቱ ደም ነው። ልግጫውን በተለመደው ቦታ።
ስለሆነም የተጋድሎው መንፈስ
ዬአማራነት ብሄርተኝነት ደም እንጂ አማርኛ ቋንቋ መናገር መስፈርት ሊሆን አይገባም። መልቲ ኤትኒክም (Multi
Ethnic) አይሆንም። እስከወዲኛው ድረስ።
ቁልፋን አሳልፎ መስጠት ዬለበትም። መስመሩን ያገኜ ተጋድሎ። ከመስመሩ ንቅንቅ ማለት
ዬለበትም። በቤተ - ኦሮሞ፣ በቤተ -ትግራይ በዚህ ቀልድ ዬለም። ዬዝጉ ስብሰባ ሚስጢር ይሄው ነው። በጠራ ደም ደባልና ዝንቅን
ዕሳቤ ተስፋውን ጅው ባለ ገደል ይለቀዋል።
ዬማከብራችሁ …. ዬቋንቋ
Ethnicism ህውሃት ወልቃይትንና ጠገዴን ዬወረረበት አስኳሉ ጉዳይ ነው። በእጃ
አዙር መጥቶ ቁጭ አለላችሁ፤ ነገ ደግሞ
ጀግና ኮ/ ደመቀ ዘውዴ መደራደር አለበት - ዬለበትም፤
ምህረት መጠዬ አለበት
ዬለበትም። ከሁለት ከሦስት
ጎራ ተከፍሎ ጉግሱ ይቀጥላል።
ስለሆነም ዬተጋድሎው ቀጥተኛ
ባለቤቶች ይህን ጉዳይ
ብለው መስመር ካላስያዙት ዬጎንደሩ አብዮት ምክንያታዊ አመክንዮም ይናዳል።
ይሄን መንገድ ዬአማራ ተጋድሎ ከሳተ ዬገድሉን ታሪክ ገደለው ማለት ነው። ፋሲል ግንብን ዬማቃጠል ያህል ነው። ስለሆነም ይሄንን ውርዴ ሃሳብ ልትጸዬፋት ይገባል።
አይበቃም ወይ ይህ ዬድብብቆሽ ኑሮ? ከገልባጣ ዕሳቤ ገልባጣ
ሰፌድ ይሻላል። ከዘርዛራ ዕይታ ዘርዛራ ወንፊት ይሻላል፤ ከልግመኛ ምልከታ ሞገደኛ መደቆሻ ይሻላል።
ይህ ዬጋዜጠኛ ደምስና ዬአቶ ግርማ ካሳ ንድፈ ሃሳብ ዬአማራ ደም ያለባቸውን፤ ግን
አማርኛ ቋንቋ መናገር ዬማይችሉትን ልጆችን በፍጹም ሁኔታ ያገለለ ነው።
ሌላው ቀርቶ ዛሬ በወገራ፤ በስሜን አውራጃዎች፤ በራያና ዘቦ
ህውሃት በወረራ በያዛቸው ዬሚወለዱ ልጆች ዬሚማሩት በትግረኛ ነው፤ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲሆን ዬተደረገው ትግረኛ ቋንቋ ነው።
ስለዚህ እነኝህ ደማቸው አማራ ዬሆነ ልጆች ግለት እንዲፈጸምባቸው፤
26 ዓመት ዬተሸከሙት መከራ አልበቃ ብሎ ነገም ጥቁር ለብሶ እንዲመጣባቸው ታጣፊ መንገድ እዬተዘጋጀ ነው። ዬአማራ ትውልድ ምክነት
ተደግሶለታል።
v ዬተጠዬቅ - እንብርት።
· ዬዘር ደም ልዋጭ ዬለውም። ቋንቋ
ግን መለዋወጫ አለው። ዬቤተሰብ
ዘር ሐረጋዊ ደም ሲኖር
በምድር - ሲያልፍም በስጋ
በቋሚነት ነው። ሥረ
- ግንዱ
ዬተፈጠረበት ደሙ እንጂ ቋንቋ አይደለም። ቋንቋን ዬሰው ልጅ ከተፈጠረ በኋላ ዬሚማረው ሲሆን ደሙ ግን ጽንሱ በእናቱ ማህጸን ከተቋጠረበት ቅጽበት ጀምሮ ሰው መሆኑን ዬገነባው ዬማንነቱ ልዩ መለያውና ዬህልውናውም ሚስጢር ነው።
· እናትን ቅኔ ዬሚያደርጋትም የዚህ ሰማያዊ ሚስጢር ኃላፊ በመሆኗ ነው። ሴት ዬተሰጣት ኃላፊነት ሊቅ ነው። በዚህ ድርድር
ዬለም። አምክናዮዎ አዕማድ ነው። ጉልላት። ስለሆነም …
· „ሁለቱም ያነሱት አመክንዮ መከራ አመንጭነቱ …“
1. አማራ ዬሆኑ ዬኦሮምኛ
ቋንቋ በሚነገርበት የተወለዱ ልጆች
ቋንቋውን ላይናገሩ ይችላሉ።
ግን ዬቤተሰቦቻቸው ደም አማራ ሊሆኑ
ይችላሉ።
2. አማራ ዬሆኑ ውጪ
ሐገር ተወልደው ዬሚያድጉ ልጆች
አማርኛ ቋንቋ ላይናገሩ
ይችላሉ። ግን ዬቤተሰቦቻቸው ደም አማራ
ሊሆኑ ይችላሉ።
3. አማራ ዬሆኑ ከውጭ
ሀገር ዜጋ ጋር በጋብቻም ሆነ በሌላ
ሁኔታ ዬሚወለዱ ልጆች አማርኛ
ቋንቋ ላይችሉ ይችላሉ። ግን ዬቤተሰቦቻቸው ደም
አማራ ሊሆኑ ይችላሉ።
4. አማራ ዬሆኑ ለውጭ
ሀገር ዜጎች በማደጎነት ዬተሰጡ ልጆች
አማርኛ ቋንቋ ስለመፈጠሩ
ሳያውቁ ሊያድጉ ይችላሉ።
ግን ቤተሰቦቻቸው ደም አማራ ሊሆኑ ይችላሉ።
5. አማራ ዬሆኑ በጉድፍቻ
ማደጎነት ስለተሰጡ አማርኛ ቋንቋ
ዬሥራ ቋንቋ ሆኖ በማይነገርባቸው (ክልሎች) የሚያድጉ
ልጆችም አማርኛ ቋንቋን
ጨርሰው ሳይሰሙ ያድጋሉ። ግን
ዬቤተሰቦቻቸው ደም አማራ ሊሆኑ
ይችላሉ።
6. አማርኛ
ቋንቋ ዬሥራ ቋንቋ ሆኖ በማይነገርባቸው ክልሎች ዬሚወለዱ
ልጆች ዬቤተሰባቸው ዞግ ደም አማራነት
ሆኖ ነገር ግን ወላጆቻቸው ቤት ውስጥ
ካልተጉ፤ በተጨማሪም በአማራ
መሆን ባለው ዬሥነ - ልቦና ጫና ምክንያትም አማርኛን ቋንቋን
እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው ላያውቁት
ይችላሉ።
7. ከሌላ
ብሄርና ተጨማሪ ብሄረሰብ
ዬሚወለዱ ዬአማራ ደም
ያላቸው ልጆች ፤
ዬአማራን ደም ዬሚጫኑ
ቤተሰብ ከገጠማቸው ልጆቹ
በአንዱ ቋንቋ ብቻ
ያድጉና ዬአማራው ደማቸው ዓይን አፋር እንዲሆን ሊደረግባቸው ይችላል። አማርኛን
ቋንቋንም ሳያውቁት ሊያድጉት
ይችላሉ።
8. ዬዘር
ሐረጋቸው ኤርትራዊ ወይንም
ኢትዮዽያዊ ሆነው ዬሌላ
ብሄረሰብ አባላት አማርኛ
ቋንቋ ተናጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ።
ከዚህ ላይ አንድ ተጨባጭ ዕውነት ላንሳ …
ዬእማማ ብሬ እና
ዬአባ ገ/ህይወት ልጅ አቶ
በረከት ስምኦን ጎንደር
አንባጅኔ ነው ዬተወለዱት። አማርኛን ቋንቋ
እንደአስፈለጋቸው ዬሚያደርጉት ቋንቋ
ነው። ባባታቸውም በእናታቸውም በዘር ሐረጋቸው
ኤርትራዊ ናቸው።
የአማራ ዬዘር እልቂት ለሳቸው ምናቸው ነው? ምንም ነው። ጎንደር በእሳት ብትጋይ ምናቸው ነው? ምንም።
„የወልቃይትና ዬጠገዴ ዬአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ ምናቸው ነው“ ምንም።
የብር ሸለቆ የወጣቶች ዬጣር ጩኸት ምናቸው ነው? ምንም።
ዬአማራ ባለ ታሪና ቁንጮ ልጅ እግሮች እንዲመክኑ ቢደረግ ምናቸው ነው? ምንም መፈናቀሉ መታረዙ ለሳቸው ምንም ነው። ስሜታቸው ድርቅ ዬመታው ነው። ወያኔ የአማራን ገበሬ በአዬር ቢደበድብ ለሳቸው ምናቸው ነው? ምንም። ስለምን?
ዬጠብታ ዬአማራ ደም ዬለባቸውምና። ይሄ እኮ ዬስሜት ጉዳይ ብቻ አይደለም የአጥንት፣ የደም፣ ዬስጋ ጉዳይ ነው። አንዲት
እናት ልጇ ቢሞት ዬልጇ ዬሀዘን መጠን ለእሷ ግዙፍ ነው። ለሌላው
በሁለተኛ ደረጃ ነው
ዬሚታዬው።
9. እጄ
ላይ ዬመኪና አዳጋ ቢደርስብኝ
ለእኔ ዬሚሰማኝ ህመምና ሊጠይቁኝ
ዬሚመጡት የቅን ወገኖቼ
ሃዘኔታ እኩል አይደለም።
ውስጣቸው አዝኗል ስቃዩ ግን ዬብቻዬ ነው።
የውስጥን ስቃይ በተለምዶ
ከምንታደምባቸው ሁነቶች በቅርጹ
ሳይሆን በይዘቱ ዬተለዬ ነው።
· ሌላው
ዬተነሳው ነጥብ ዬአማራ
ደም ሳይኖርባቸው አማርኛ ቋንቋ
በመናገራቸው ብቻ ጥቃት
ዬደረሰባቸውን ወገኖቻችን በተመለከተ
በሰባዊነት፤ በዜግነት ማዕከል
ፍትህ ሊያገኝ ዬሚገባው የሁሉም
ኢትዮዽያዊ ጉዳይ ነው።
በተጨማሪም ዬሁሉም ዬሲቢክስ ድርጅቶችና
ዬፖለቲካ ድርጅቶች ጉዳይ ነው።
አማርኛ ቋንቋ እኮ
ዬዘመናት ብሄራዊ የሥራ ቋንቋ
ነው። አሁንም ነው። ስለዚህ
ይሄ ሌላ መሰሪ ተልዕኮ እስከሌለው ድረስ
ቁልጭ ያለ ጉዳይ ነው። በአማራነት ለመደራጀት መስፈሪያ
ሚዛን ሊሆን አይችልም። አከራካሪ ም
አይደለም። ይህ አስተዳደራዊ ፍትሃዊነት እንጂ በብሄርተኝነት ዬመደራጀት ፖለቲካዊ መብትን
አይሰጠም። ደም ዬውስጥ ማንነት ማፍለቂያ ነው።
ዬአማራ ደም ያለበት ሲባል
ደሙ ነው ዬሚደራጀው እንጂ ቋንቋው አይደለም።
አማራው በአማራነቱ መደራጀት ይዘታዊ እንጂ ቅርጻዊ አይደለም። ደም ቅርጽ ሊሆን አይችልም። ከሌሎች እንደ አንድ ዜጋ ዬሚጋራው ወላዊ ገጸ ባህሪያት ቢኖሩትም፤ ወይንም ከተወለደበት አካባቢ ልሙድ ዬሆኑ ከሌሎች
ጋር ዬሚጋራው ዕሴቶች ቢኖርም፤ ዬተላለፋቸው በሰው እጅ ያልተጠፈጠፉ ተፈጥሯዊ ውስጣዊ ክህሎት፤ መክሊት፥ ሥርዓትና ህግጋት አሉት።
ዬውስጥ ደሙን ሲያስተዳድሩ ዬኖሩ።
በአማራ ደምነት ብቻ
ዬሚገኙ ዬእኔ ዬሚላቸው ዬውስጥ መገለጫዎች አሉት። በተለይ አማራው ዬእሱነቱ መግለጫ ሆነው ግን ቁብ
ሳይሰጣቸው ዬቆዩ። አማራ
ሲኮን መንፈሱ በአማራ ዕሴቶች
ውስጥ ይፈጠራል።
አማራ መሆኑን ዬሚገለጠው በውስጣዊ ማንነቱ ንጥረ ነገር በደሙ ብቻ ነው። አማራነት በገፀ በረከት አይገኝም። ወይንም ገብያ ተሂዶ አይሸመትም። ወይንም በተለዬ ቀረቤታ ለሽልማት ዬሚቀርብ ዬመደራደሪያ መክሊት ሊሆን አይችልም። አማራነት ቀለሙ ዉስጣዊ እንጂ ውጪያዊ አይደለም። ዬአማረነት ውስጥነት አናባቢው ምላስ ሳይሆን ደም ብቻ ነው። በደም ድርድር ዬለም።
አሁን የአማራ
ዬኮምኒኬሽን ሚ/ር ሰሞኑን
በቀረበላቸው ድንቅ ጥያቄ ሆድ
እቃቸውን አሳይተዋል። የአማራ ተጋድሎ
ቤተኛ መስፈርቱ „አማራነት በደም አይደለም“
በማለት አስረግጠው ተናግረዋል። ተደግሞ ተደጋግሞ ነው ዬተነገረን። „አማርኛ ቋንቋ መናገር ብቻ በቂ ነው“ ብለው
ማህተሙን ገጭ አድርገውታል።
ይሄ የበደነ፣ ዬነፈሰበት የሦስተኛ መንገድ
ቲወሪ ነው- ለእኔ። ቅልብጭ ያለ ቅድመ መሰናዶ ነው።
ይህ ከሆነ ስለምን አማራው ራሱን
ችሎ መደራጀት አስፈለገው? ስለምንስ
ከህብረ ብሄር ዬአደረጃጀት
መርህ ጋር ግብ - ግብ ይገጠማል? ነገ በቋንቋ
ላይ ብቻ ዬታለመ ራዕይ ከኖረ
ስለምን የወያኔ ትንፋሽ
ዬሆነውን ዬባህርዳሩን እንኮሸሽሌ እናወግዛለን?
ሌላ ዬቀረበ አሳቻ መንገድ ደግሞ አለ ….. ለመሆኑ አዲስ አበባስ ዬሚወለድ ልጅስ
ዬዞጉ ዘር ዬለውምን??? እንኳን ኢትዮጵያ መሬት ላይ ዬሚወለድ
በአፍሪካ፤ በአውሮፖ፤ በአሜሪካ፤ በአውስትራልያ፤ በላቲን አሜሪክ ዬሚወለድ ኢትዮዽያዊ ልጅ ቤተሰቦቹ ዞግ አላቸው፤ ይህ ምልከታ ከፋክት ያፈነገጠ
ዬጭብጥ ደሃ ዬሆነ ዕሳቤ ነው፤ እውሃ ሲሄድበት ዬከረመ አለት
ዬሚመስል።
በዚህ ስሌት ጸሐፊና ፖለቲከኛ አቶ
ያሬድ ጥበቡ ዬሸለሙንን አቶ አዲሱ
ለገሰን ለጥ ብለን
እጅ ነስተን አንቀበልም¡
ይህ
ዬተበረዘ ራስ መርዝን
ካልተስተካከለ በሁለት ቢላዎ
ለእርድ ዬሚቀርብ ወጣት
ሊኖር አይችልም። አማራ እንደ አማራነቱ ለሚደርስበት በደል ቅርቡ ዬአማራ ደም ያለበት ብቻ ነው። እርግጥ ነው ሰውን ማዕከላቸው ያደረጉ፣ ቅኖች፤ ሩህሩህ ፓርቲዎች፤ ዬስቢክስ ድርጅቶች፤ ነፃ ሚዲያዎች እገዛቸው ላይለዬው ይችላል። በደጋፊነትና በተባባሪነት፣ በተለይ ወደፊት ዕውቅናው እዬጎለበተ ሲሂድ።
ዋናውን ሚና ግን
እራሱ ደሙን እዬገበረበት ስለሆነ ይህን
ተጋድሎ ከእርከኑ ለማድረስ
ውጪ ያለው ኃይል ግልጽና ዬማያሻማ አቋም
መያዝ አለበት። በወያኔ „የአማራ
መቃብር ማኒፌስቶ፤“ በቀጥታም
ይሁን በተዘዋዋሪ የብዙ ሰው
ህሊና ተጠቂ ሁኗል። ዬአማራ ጥላቻ „አማራን
በሩቁ“ ተመስጥሮ ዬተያዘ
አመክንዮ ነው። ከዚህ
ዘመን በላይ ማረጋገጫ ዬለም።
ሰሞናቱ ዕድሜውን ሙሉ
ለሽ ብሎ ዬኖረው መረጋገጫነት ቁልፋን
አስረክቦታል። ከማዬት በላይ
ምን ፊርማ አለና?! መደራጀት ሲያንሰው
ነው አማራ በፖለቲካና በሲቢክስ ድርጅት። ያባከናቸው ጊዜዎቹ ሊከነክኑት ይገባል። ይህ ነው ቀበቶውንም መቀነቱንም ድርብ ዬሚያደርገው።
ጊዜ መስታውት ነው፤ ጊዜ እንደኛም ይሉኝታ ዬለውም። እንደ አማራ ይሉኝተኛ ተኝተህ በለኝ ዬሚል ማህበረሰብ
ዬለም። አማራ ፍጹም ታጋሽ ነው። ለሀገሩ ሲል። ይህ ግን አስገፋው እንጂ ያተረፈለት ምንም ነገር፤ ዬተናቀው ከዜሮ በታች ነው።
ዬአማራን ዬማንነት ጥያቄ
ተጋድሎን አንድ የቲፒ.ኤል.ኤፍ
አምላኪ አማርኛ ቋንቋ
ስለተናገረ ብቻ በአማራነት
መደራጀት ይችላል ሲባል
ለአዲስ ሰይፈ ነበልባል
መከራ ዬነገን ዬአማራን ትውልድ
ለእርድ እናዘጋጃለን ማለት
ነው።
Ø ይህ ለአማራው ብቻ ሳይሆን ለኦሮሞም ፕሮቴስትም አዲስ የተዘጋጀለት ዲዲቲ ስለሆነ ከነጭልፊት መጠንቀቅ ይኖርበታል። እጅግ
መርዛማ መንገድ ነው።
· ቁንጥንጥ።
አደብ ጋር ግብግብ ዬገጠመው ዬአቶ ግርማ ካሳ ቁንጥንጥ ዕይታ „አሁኑኑ! ውህደት“
ጠይቋል። ዬሻይ ማህበርም እንኳን ቀን ይሻል። እማናውቅ መሰለወት? በወራት ዬፓርቲ ምስረታ ሂደት ሳይጠናቀቅ ተዋህዱ፤ ተቀላቀሉ
በማለት ወጣቶች ግንባራቸውን ከሰጡ በኋላ አጋ ለይታችሁ ለመሰነጣጠቅ
ነው። አሁን እንኳን በቃኝን በማያውቀው ዬማፍለስ ተልዕኮ ይሄው ተጠምዳችሁ ለተስፋ ቀንበር ልታሽክሙ ቁንጣን ላይ ናችሁ።
ቅንጅት፤ መድረክ፤ አንድነት ተልእኮዉን እንደቅርጫ ስጋ ስትቀራመቱት። ፍርስርሱን አውጥታችሁ
እናንተ በተድላ ጀግና አንዱአለም አራጌ ቀራኒዮ። አሁንም አሁንኑ ውህደት ብላችሁ በተካናችሁበት ግሪደር መደራጀቱ በቅጡ ሳያጣጣም
፤ ህልፈቱን ሰምቶ ተስፋ ያደረገው ህዝብም መቅኖ አጥቶ እንደ ዋተተ እንዲቀር ነው።
መደራጀት እኮ ገበርዲን
ለብሶ መንጎራደድ አይደለም ወይንም ከረባት ለብሶ መሽቀርቀር ወይንም በሦስት ቀን ሊጥ እንጀራ ዬሚሆን አይደለም። አቁነጠነጣችሁ ዬቻፕተር ቁንጮ ለመሆን። ፈረሰ
ሲባል ደግሞ ተድላ ነው። ድርጅት ስለሚባለው ጽንሰ ሃሳብ ጋር እኮ እሩቅ - ለሩቅ ናችሁ።
ድርጅት ሻንጣ መሰላችሁ? ካኒትራ፤ ኮት - ቲሸርት ተቀላቅሎ ዬሚታሸግበት። ምንድን
ነው በላይ በላይ ለእነዚህ ቀንበጦች ኃላፊነት እምትጭኗቸው? ስለምን አዕምሯቸውን ትወጥሩት አላችሁ? ለነገሩ ምን ይደረግ ሰው ጠፍቶ
ታላቁ ተልዕኮ እንዲህና እንዲያ ….
እምትፈልጉትን ዓይነት ዬፖለቲካ ድርጅት ዬራሳችሁን መገንባት
ትችላላችሁ። እንዲህ ዬሙቀት ቴርሞ ሜትር ተከታይ ከምትሆኑ።
ለመሆኑ አቶ ግርማ ካሳ አማራ ካልሆኑ ምን አገባዎት? ሺ ቢሆኑስ ይሸከሙኝ አላልዎት።
ያን ዬተስፋ ሀገር አንድነት ፓርቲን ምድማዱ ሲጠፋ አሁን ደግሞ ከዚህ ግባ በማይባል አፍራሽ፤ አዘናጊ አምክንዮ ዬአማራን ተጋድሎ
ጅምር ያምሱታል። ለመሆኑ መቼ ነው ከማቡካት ዬሚታቀቡት??!!! አይበቃም??!
· ጥሞና።
ልብ ያላችሁ አሁን ዬሚያስፈልገው ወጥ ሃሳብ እንጂ በአንድ
እግር ብረት መታሰር አይደለም። እራሱ መጀመሪያ ይጥና። በጠነከረ መሰረት፣ ፈተናን ባሸነፈ ተግባር አህታዊነት በራሱ ጊዜ ይመጣል፤
ጥድፊያ አያስፈልግም። ስክነት ነው ስኬት።
አንድ ሆን ብላችሁ ከምትፈርሱ፤ መንፈሳችሁን ማሰባሰቡን አስቀድሙ። ድርጅት ዬረጅም
ጊዜ ሂደት እንጂ ዬነጠላ ቁጭት አይደለም። ድርጅት
በበሰለ ቁመና፤ በጸና አቋም ሥር ይዞ መብቀል አለበት። አሁን ገና ችግኝ ነው። ግልፅነትን በተጎነጨ አቅም ሰከን ብሎ
ይደረስበታል። „ዬእነ ቶሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ“ እንዳይሆን።
አሁንም እኔ አብክሬ ማስገንዘብ እምፈልገው፤ በእውቀት ላይ ዬተመሰረተ ጥበባዊ ጉዞ
ከጀመረው ዬኦሮሞ ፕሮቴስት ልምዱን አዳምጡት። አጣጥሙት። ዬውስጡም ሆነ ዬውጩን ወጀብ መቋቋም የሚቻለው በጸና መተማመን
ዬሚገነባ ቤት እንጂ በስሜት ዬሚጋልብ በቅሎዊ ስሜት ሊሆን አይገባም።
መደጋገፋ፣ መመካከሩ፤ መረጃ መለዋወጡ፤ ውስጥን በጥራት ማደራጀቱ ነው ሊጠቅም ዬሚችለው።
ዛሬ ተዋህዶ ነገ እውሃ በቀጠነ ከሚፈረካከስ
ዕጣ። ዬደም አደራ፤ ዬዕንባ ውል አለባችሁ። ውህደት ወይንም ጥምረት አላምጦ መዋጥን ይጠይቃል።
· ህሊና።
ይህ ዬተጋድሎ መንፈስ እንመራለን ዬሚሉ ኃይሎች ሌላ ማኒፌስቶ ማርቀቅ አያስፈልጋቸውም።
ማንፌስቷቸው ህዝቡ በትናንሽ ከተሞች፤ ቀበሌ
ገበሬ ማህበሮች ሳይቀር ያነሳቸው መርህ - ገብ፦ ህሊና - ገብ፦ ህልውና - ገብ፦ ርትህ - ገብ፦ አብሮነት - ገብ፦ መሪ ሃሳቦችን
አማክሎ ዬአብራሃሙን ቤት መገንባት ይኖርባቸዋል።
እንዲሁም የሚያኮስሱ ህጸፆችን እዬነቀሱ በማውጣት፦ ተጋድሎውን ከማንኛውም አዳጋ መጠበቅ
ያስፈልጋል። ወያኔ መሳሪያ እጀታ አዘጋጅቷል። ሦስተኛ መንገደኞችን። ባለ ሦስተኛ መንገዶች „አማርኛ ቋንቋን ዬሚናገር“ ሲሉ ጀምረውታል። ነገ ደግሞ ዬእኔ ፓርቲ ዓላማና ግብ ተብሎ አዲስ ማኒፌስቶ
ምዕራፍ - ሁለት ዘመቻ ይጀምራል።
ህዝብ በአደባባይ ያነሳቸውን ለማስፈጸም በሚል አዲስ ባርኔጣ ተለብሶ በአማራ ሥም ሊሆን
ይችላል። ይህ የሦስተኛ መንገድ ህልመኞች ንድፍ አገላብጬ እንዳዬሁት ዬበታችነት ዬፈጠረው ስሜት ነው። ዬበታችነት ስሜት ማደሪያው
ቂምና በቀል ነው። ቂምና በቀል መባቻውም - መሰናበቻውም አሳቻዊነት
ነው። ስለሆነም በዬአቅጣጫው ጠረኖችን ማጣጣም ያስፈልጋል። ለእርምጃም አለመዘግዬት አሸናፊነትንና ተስፋን ይወልዳል።
v
አንድ ሰው ዬአንድ ዬፓለቲካ ድርጅት አባል ሆኖ ከተመዘገበ በኋላ፤ ሌላ ከአሰኘው መሰረዝ
ነው ጠቃሚው መንገድ፤ በስተቀር አዳጋው ሰፊ ነው። ስለሆነም አባልነትን ስትቀበሉ በጥራት መሆን ይገባዋል። ለቆረጠ ግብ ዬቆረጡ ጥቂት ጀግኖች ብዙ ማድረግ ይችላሉ።
ዬገብያውን ሰው ሁሉ እንቀበላለን ካላችሁ መሰንጠቅን፣ ዓላማ መሳትን፤ ለጠላት መመቸትን ዬፈቀዳችሁ ትሆናላችሁ። ከሁሉ በላይ ዬዕንባ አደራ በላ ትሆናላችሁ። ረጋ ብላችሁ ተራመዱ። ሰከን ብላችሁ ያለባችሁን ኃላፊነት አዳምጡት።
ጠላት ከማብዛት አጋር መሸመትን ለመንፈሳችሁ ሸልሙ። እስራዔሎች መሳሪያቸው ዬጠራ ዬፍላጎት መስመርና ዬበዛ ትእግስት ነበራቸው።
ስለሆነም ከህልማቸው ጋር ተገናኙ። አሰር ሃስብን እንደ አሰርነቱ፤ ምርጥ ዘርን እንደ ተጣራ ምርትነቱ ይሁን አቀባበሉ።
v
ትችትን አትፍሩ፤ ወቀሳን
ደስ ብሏችሁ ተቀበሉት። አዳዲስ
ሃሣቦች ዬአቅም ብጡል
ናቸውን በራችሁን ቧ
አድርጋችሁ ክፈቱለት። ፊት ለፊት ለወጡ ዬአማራ ሴቶች አክቲቢስቶችን እንዳይናችሁ ብሌን ጠብቋቸው። ሴቶች ደፋሮች ናቸው። ሴቶች ዬአቅም ዲታዎች ናቸው። ሴቶች ዬተግባር እመቤቶች
ናቸው። ሴቶች ዬዘዴ ማህንዲስ ናቸው። ሴቶች በልምድ፤ በቀለም ዕውቀት ከሚያገኙት ብልህነት በላይ ፈጣሪ ካለተቀናቃኝ ዬቸራቸውን በረከት ንብረታችሁ አድርጉት። ሴት ቅኔ ናት።
· ሁነኛ።
ምንም እንኳን „አባልነት በፈቃደኝነት“
ቢሆን ተጋድሎው ጥራትን አስኳሉ
ማድረግ ይኖርበታል። ሌላው
ግብረ - ዬትኩረት አቅጣጫ
ከሌላ ዬፖለቲካ ድርጅት አባል
ዬሆነ ማንኛውም ዬአማራ ልጅ
አንዱን መምረጥ ይኖርበታል።
መንፈስ አንድ አዛዥ
ብቻ ነው ሊኖረው ይገባል። በስተቀር
ከነጃኬቱ ከተረከባችሁት ከአላማችሁ
ጋር ፍችን ፈቅዳችሁ እንደ ፈጸማችሁ እወቁት።
ዬህውከት ቤት መሆኑ
ብቻ ሳይሆን፤ ዬአባላት ዘረፋም አይቀሬ
ነው።
ቦርቡረው፤ ሰርስረው ዉስጡን
ወና ያደርጉታል።
ድካሙ - ብክነቱ ሁሉም
መና። ከሁሉ በላይ ዬደም ዋጋ ለተከፈለለት ለዚህ ተጋድሎ እያንዳንዷ ዬጥንቃቄ እርምጃ ዬወሳኝ ምዕራፍ አካል መሆኑን ለአፍታ ልትዘናጉ አይገባም።
መጠቃቀም በሌላ መስመር
ይህ ግን አቅማችሁን ከታሪካዊ ዬህዝብ
ኃላፊነት ጋር በውል
ልታጋቡት ይገባል። ከኦሮሞ
ፕሮቴስት በልምድ፤ በጥንቃቄ
ዬበለጸገ ተመክሮ ለመማር
ፍቀዱ። በእነሱ ቤት
እንዲህ መፈንጨት ዬለም።
በመንፈስ ላቀረባቸው ወገን
ሁሉ ጥንቃቄያቸው መድህን ነው።
እጅግ ኮርቸባቸዋለሁ። ዬእኔ ተስፋዎች
- ወጣቶች ጥንቃቄ ያተርፋል
እንጂ አያከስርም። ከአኗኗራችሁ ዘይቤ
ጀምሮ ጠንቃቆች ሁኑ - አደራ። በጋብቻ፤ በጓደኝነት፤ በግብዣ ሊመጡ ዬሚችሉትን ጥቃቶች ሁሉ ዬእኔ ብላችሁ ሁነኛ መንፈስ ሸልሟቸው። መታቀብ ዓላማንም እራስንም ይታደጋል። መኖራችሁ ነው የተስፋ
ማደሪያ …
· መዝበጥ።
ቤት ሲሰራ መሰረቱ ካልጠበቀ ዕድሜው
አጭር ነው። ዬፖለቲካ ፓርቲዎች ሲመሰረቱ
ያላቸው ዬጠራ ራዕይ፤
ዬራዕዩ ማስፈጸሚያ ስልትና
መንገድ። የመዋቅሩ መሠረት
መጣያ ደልዳነት፤ ዕባጭ ዬሌለው
መሆን፤ ዬሚያቅፋቸው ዬአባላት
ጥራት ብዛት ተኮር አለመሆን፣ ዬጥንካሬው
ብርቱ ዳኛ ነው።
ዬፖለቲካ ፓርቲ በተፈጥሮው የፈተና ቤት በመሆኑ፣ ዬፈለገ ወጀብ ቢመጣ ንቅንቅ አያደርገውም። ነገር ግን እነዚህን በኲራት ጉዳይ ከሳተ፤ በፈተና በተናጠ ቁጥር ቀዳዳ ይበዛበታል፤ ቀዳዳውን ለመወታተፍ በሚያደርገው ዬችግር መፍቻ ተጋድሎ፤ ከአንዱ ችግር ሽሽት
ወደ ሌላው እዬባዛ ነዳላው ሲሄድ ቁጡና ተጋጭ ባህሪ እጣው እንዲሆን ይገደዳል።
ስለሆነም መርከቡ ያረገረገ፤
ሃዲዱም ዬዘበጠ ይሆናል፤
መካተቻውም ቀዝቃዛ ተስፋ
ቆራጭነት ይሆናል። ስለዚህ
ጥንቃቄ ማቀድ ቢቻልም፤
በእጅ ላይ በገባ ጭብጥ አቋምን በውሳኔ ማቆም
ዛሬን ያሳድራል። ነገንም ያዋውላል።
„ውል ያዋውላል ታንኳ ያሻግራል“
ይላል ዬጎንደር ሰው። „ዬሚያድግ
ጥጃ ከገመዱ“ ሲልም ያስጠነቅቃል።
· ነባቢት።
ትግረኛ ቋንቋ በመናገር ትግራዊነት ወይንም ኤርትራዊነት እንደሌለው ሁሉ፤ ትግረኛ ቋንቋ በመናገርም አማራነት ዬለም። መሪያችሁን ተከተሉ፤ ኮ /ደመቀ ዘውዱ ትግረኛ በመናገሩ ትግሬ ነኝ አላለም።
አማራ ነኝ በማለቱ ነው ይህ ገድለኛ አብዮት ዬፈነዳው።
ጎጃም ጤፍ፤ ወይንም
ማር፤ ወይንም ለስታ ቅቤ አይደለም ያዋጣው። ዬተስፋ መሰረቱን ልጁን፤ ዬትዳር አጋሩን ነው ዬገበረበት። ልጆቹ ሺዎች ዬሰውን ልጅ
መከራ ሁሉ ነው ዬተቀበሉበት፤ በአንድ ቀን ሃምሳ ልጆቹን ሲቀብር ዬደም ግብር ነው ዬከፈለው። ለልጅ ሳይሳሳ፤ ለትዳሩ ሳይጓጓ፤
ለኑሮው ሳይራራ እሳትና ረመጥን ደፍሮ ዬረገጠው „እኔ ደመቀ ነኝ“ በማለት ደረቱን ለፉሺስት በድፍረት ሰጥቶ ነው።
„አሸባሪ“ ካላችሁትም
እኔም „አሸባሪ ነኝ“ ብሎ ነው ነፍሱን ዬገበረው። ዬዚህ አብዮት ትንግርት እኮ ተነግሮ አያልቅም። ይህ ዬደም ዋጋ ዬአደራ ዕዳ
አለባችሁ። ከ19,000 ሺህ በላይ እስር ቤት ዬሚማቅቀው ወገናችሁ ለላንቲካ አይደለም። በቆረጠ ውሳኔ ውስጥ ለመኖር መወሰን አለባችሁ።
አማራነት ዬቋንቋ ዬገበጣ መጫዎቻ አይደለም። „ዬሚያብረቀርቅ
ሁሉ ወርቅ አይደለም።“ ይህ መሪ ቃልን ማተብህ አድርገው። ህሊናህ አድርገው። ሩሕህ አድርገው።
አማራነት በአማራነት ማንነት ዬሚገኝ ዬደም ነባቢተ - ነፍስ እንጂ እንጂ ዬስጦ ሜዳ አይደለም። አማራነት ውስጥ ነው። አማራነት ግማድ ነው። አማራነት
ለዘመኑ ቀራኒዎ ጎለጎታ ነው።
ዬጓጎሉ ሃሳቦች ትውር እንዳይሉ ዬመተንፈሻን አውራ በርህን ዝጋ፤ ትጥቅ አስፈች፤ አዳላጭ፤
ጋሬጣ ዕሳቤዎችን ነቅተህ ጠብቅ። ለምንስ ጥገኛ ትሆናለህ? አንተ ምን አጥተህ? ዘንጋዳ - ዘንጋዳ ነው፤ ስንዴም - ስንዴ። „ልብ ያለው ሸብ።“
አሁንም ከነመይሳው ሥህነ -
ትውፊት። ዬግብ መሰረቱም
ታማኝነት ነው፨ ለጀግኖቹ ውሎ ታማኝነት ሽሽት እንዳያሰኘው፤ ለአደራ ቃል ታማኝ ሁኑ! ጥራት ዬድል መባቻ ነው።
· ዕርገት።
ዬእሳር እህላዊ ዘሮች…
ጠመጅ፥ ሰነፍ፥ ስንዴ፥ አጃ፥ ገብስ፥ ዘንጋዳ፥ ጤፍ፥ ዳጉሳ፥ ቡሌ፤ ወዳከር፥ ወደአርባ፥ ደበር፥ ዱራኛ ወዘተ …
ጥራጥሬ …. ጓያ፥ ግብጦ፥ ምሥር፥ አተር፥ ሽንብራ፥ ባቄላ፥ ወዘተ ….
ቅመማ ቅመም … አብሽ፥ ነጭ አዝሙድ፥ ዝቃቅቤ፥ ጤና አዳም፥ እርድ፥ ኮረሪማ፥ ድንብላል፣
ሰናፍጪ፥ ጎመን ዘር፥ ቁንዶ በርበሬ ወዘተ …
ዬእንሰሳት ውጤት ወተት (ዬከብት - ዬግመል - ዬፍዬል - ዬበግ) ዬከብት ፥ እርጎ፥
ግረን፥ አጓት፥ ወገሚት፥ አይብ፥ ቅቤ ወዘተ እነኝህ ሁሉ ዬምግብ አይነቶች ሲሆኑ ጠቀሜታቸውን መለዬት ዬሚቻለው ግን በውስጣዊ ንጥረ
ነገራቸው ብቻ ነው። ሽንብራ ያለው ንጥረ ነገር ከምስር ይለያል።
ገብስም ያለው ንጥረ ነገር ከጤፍ ይለያል። አብሽ ያለው ንጥረ
ነገር ከጥቁር አዝሙድ ይለያል ዬአማራነት ንጥረ ነገር ደምም እንዲሁ። አማራነት ቋንቋ ሳይሆን ዬደም
ትርጉም ነው።
ትርጉም ተርጓሚው ሆነ አመሳጣሪው ደግሞ አንደበተ እርትዑ ዬአማራነት ደም ሥህነ - ህይወት ህልውና ብቻ ነው። ከዝች ፈቅ ያላችሁ እለት ዬግርዶሹን ጥልማሞት ኑሮ ወስናችሁለታል ማለት ነው። ለቀጣይ መደቆስ
እጅ ሰጥታችኋልም ማለት ነው። የዕንባ
ትርጓሜ ፍሰት እንዳይገጥመው ዬደም
መርህ ይጠበቅ - በጥብቅ! … ብለናል እኔና መንፈሴ።
የመሆን ቁም
ነገሩ መደማመጥና መዋዋጥ ነው፨
መፍቻ።
· ጦሮ --- ለህግ ዬማይገዛ ድንገተኛ ሲሆን አቧራን ወታደሩ አድርጎ ርህራሄ ባልሠራለት አንጀቱ በፈጣን ሩጫውና ፋጨቱ ያገኘውን ሁሉ በጭካኔ ዬሚደመስስ ቁጡ ዬንፋስ ዓይነት።
· ቋት ---- መሠብሰቢያ፤ ማጠራቀሚያ ማለት ነው። ባንክም ማለት እንችላልን። ገጠር በእያንዳዱ ቤት ወፍጮ አለ። ዬቁም ወይንም ዬእንብርክክ ሊሆን ይችላል፤ ለእንብርክኩ ሰፌድ ወይንም አነስ ያለች ወራንታ ይዘጋጅለታል። ለቁሙ ግን ከወፍጮው አፍ ጋር ዬተያያዘ ጎድጎድ ብሎ ከጭቃ ዬሚሰራ ማጠራቀሚያ ይበጅለታል። ባለሙያዎችም አሉት። ከጭቃ ዬተሰራው ጎድጓዳ ማጠራቀሚያ ነው ቋት ዬሚባለው። ቃሉም ተግባሩም ዬእኛነታችን መግለጫ ሥህነ ትውፊታችን ነው። ይሄው ነው። መሸብያ ጊዜ፤ ቸር
ሁኑልኝ።
አምላኬ ሆይ! እርዳን።
ድንግልም አትርሽን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ