«አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ማን ናቸው?»
«አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ማን ናቸው?»
6 ሀምሌ 2024
«ሰር ኪር ስታርመር የሌበር ፓርቲን በመምራት በምርጫ አሸናፊ ሆነው የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል።
ሰር ኪር የጠንካራ ግራ ዘመም ፖለቲከኛው ጄሬሚ ኮርቢንን ከአራት ዓመት በፊት በመተካት የሌበር መሪ ሆኑ። ፓርቲውንም ከግራ ዘመም ወደ መሃል ሜዳ በመመለስ ተመራጭ ለማድረግ ሠርተዋል።
የሌበር ፓርቲ ለ14 ዓመታት ከሥልጣን ርቆ ነበር።
ሰር ኪር ጥሩ ስም ከገነበቡት የጠበቃነት ሥራቸው በኋላ ዕድሜያቸው በ50ዎቹ ውስጥ በነበረበት ወቅት ነበር የፓርላማ አባል የሆኑት።
በፊትም ቢሆን ግን ለፖለቲካ ፍላጎት ነበራቸው። ወጣት እያሉ አክራሪ ግራ ዘመም ነበሩ።
ሕይወት ከፖለቲካ በፊት
እአአ በ1962 በለንደን ተወለዱ። ወላጆቻቸው አራት ልጆች ነበሯቸው። ያደጉት ደግሞ ደቡብ ምሥራቅ እንግሊዝ ውስጥ በመትገኘው ሰሪ ነው። ብዙውን ጊዜ ከሠራተኛ መደብ ከሆነ ቤተሰብ እንደተገኙ ይጠቅሳሉ። አባታቸው ፋብሪካ ውስጥ ይሠሩ ነበር። እናታቸው ደግሞ ነርስ ነበሩ።
ቤተሰባቸው ጠንካራ የሌበር ፓርቲ ደጋፊዎች ነበሩ። ሰር ኪር ስማቸውን ያገኙት የፓርቲው የመጀመሪያ መሪ ከነበሩት ስኮትላንዳዊው ኪር ሃርዲ ነው።
የቤተሰብ ሕይወታቸው በብዙ ፈተና የተሞላ ነበር። “ቀዝቃዛ እና ከሰው የማይቀላቀል ዓይነት ሰው ነበር” ይላሉ ሰር ኪር ስለአባታቸው ሲናገሩ።
እናታቸው ለዓመታት ስቲልስ በተባለ በሽታ ተሠቃይተዋል። በሽታው በመጨረሻ ላይ መራመድ እና መናገር እንዳይችሉ አድርጓቸው ነበር። በኋላም እግራቸው እስከመቆረጥ ደርሷል።
ሰር ኪር በ16 ዓመታቸው የሌበር ፓርቲን የወጣቶች ክንፍን ተቀላቀሉ። ለተወሰነ ጊዜ ደግሞ አክራሪው የግራ ዘመም ሶሻሊስት ኦልተርኔቲቭስ መጽሔት አዘጋጅ ሆነው ሠየምስሉ መግለጫ, ሰር ኪር ስታርመር የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳሉ
ሰር ኪር ዩኒቨርሲቲ የገቡ የመጀመሪያው የቤተሰቡ አባል ለመሆን በቅተዋል። በሊድስ እና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ተማሩ። ከዚያም በሰብአዊ መብት ላይ ጠበቃ ሆነው ሠርራተዋል።
በዚህ ወቅት ነበር በካሪቢያን እና በአፍሪካ አገራት የሞት ቅጣት እንዲቀር የሠሩት።
እአአ በ1990ዎቹ በአንድ ታዋቂ የሕግ ጉዳይ ላይ የተሳተፉ ሲሆን፣ ይህም ግዙፉ ማክዶናልድስን በስም ማጥፋት ወንጀል የከሰሱ ሁለት የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾችን ወክለው ቆሙ።
እአአ በ2008 ሰር ኪር የዐቃቤ ሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ። ይህም ማለት በእንግሊዝ እና በዌልስ ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ ሆነዋል ማለት ነው። እስከ 2013 ድረስም በኃላፊነቱ ቆይተው በ2014 ደግሞ ንጉሣዊውን የክብር ማዕረግ አግኝተው ሰር ተባሉ።
የሌበር ፓርቲ መሪ
ሰር ኪር በ2015 ሆልቦርን እና ሴንት ፓንክራስን በመወከል የፓርላማ አባል ለመሆን በቁ።
ሌበር ፓርቲ በአክራሪው ግራ ዘመም ፖለቲከኛ ጄሬሚ ኮርቢ ይመራ ነበር። ሰር ኪር በ‘ሻዶው’ [ትይዩ] ካቢኔ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው በጄሬሚ ኮርቢ ተሾሙ። በዚህ ወቅት ሰር ኪር ኢሚግሬሽን በመሳሰሉ ጉዳዮች የመንግሥትን አፈጻጸም ያብጠለጥሉ ያዙ።
ዩናይትድ ኪንግደም ከአውሮፓ ኅብረት ስትወጣ ደግሞ ሰር ኪር ‘በሻዶው’ ካቢኔ የብሬግዚት ሚንስትር ሆኑ። ቦታውንም ተጠቅመው ሁለተኛው ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ግፊት አድርገዋል።
ሰር ኪር የ2019 ጠቅላላ ምርጫን ተከትሎ የሌበር ፓርቲ መሪ የመሆን ዕድሉን አገኙ። ይህ ለፓርቲው ከባድ ጊዜ ነበር። ከ1935 ወዲህ ከባድ የተባለው የፓርቲው ሽንፈት ጄሬሚ ኮርቢ ከኃላፊነት እንዲለቁ አስገድዷቸዋል።
ሰር ኪር የኢነርጂ እና የውሃ ኩባንያዎችን በመንግሥት ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ለማድርግ እና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከክፍያ ነፃ ምዝገባን በማበረታታት የሌበር መሪነትን አሸንፈዋል።
ጄሬሚ ኮርቢ ሌበር ፓርቲን ግራ ዘመሞች እና ለዘብተኛ በሚል ከፍለውት ነበር።
ሰር ኪር ፓርቲውን አንድ ለማድረግ እንደሚፈልጉ ቢናገሩም የኮርቢንን “አክራሪነት” ማቆየት እንደሚፈልጉም ገልጸዋል። “ወደ መሐል ከመጠን በላይ መሳብንም” ያለውን ችግር በማንሳት አስጠንቅቋል።
በኋላም ኮርቢ መሪ በነበሩበት ወቅት ከፀረ ሴማዊነት ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት ምክንያት ጄሬሚ ኮርቢን ከፓርላማው የሌበር ፓርቲ አባልነት እንዲታገዱ አድርገዋል።
አብዛኞቹ የፓርቲው የግራ ዘመም አባላት ሲር ኪር በፓርቲያቸው ውስጥ የረዥም ጊዜ ዕቅድ በመያዝ ለዘብተኛ አባላት ብቻ የፓርላማ ዕጩ ሆነው እንዲቀርቡ እያደረጉ ነው ሲሉ ከሰዋቸዋል።
የሰር ኪር አቋም ምንድን ነው?
ሰር ኪር በምርጫ ዘመቻ ወቅት ከተናገሩት በተለየ ሁኔታ ፓርቲው የበለጠ ድምጽ እንዲያገኝ ለማድረግ ወደ መሐል ስበውታል።
የዩናይትድ ኪንግደም ደካማ የፋይናንስ ሁኔታን በመጥቀስ ብዙ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስወጡ ውድ ፖሊሲዎችን ወደ ጎን በማለት ጥቂት አክራሪ ዕቅዶችን ይዘዋል።
· በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ማድረግ
ሰር ኪር የኢነርጂ እና የውሃ ኩባንያዎችን በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ለማድረግ ከዚህ ቀደም ያቀረቡትን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል።
ሆኖም በአምስት ዓመታት ውስጥ ግሬት ብሪቲሽ ሬይልዌይስ በተባለው አዲስ ኩባንያ ስር ሁሉንም የመንገደኞች የባቡር አገልግሎቶችን ወደ ሕዝባዊ ባለቤትነት ለመመለስ ቃል ገብተዋል።
· ትምህርት
ሰር ኪር ከዚህ ቀደም የኮሌጅ ተማሪዎች የትምህርት ምዝገባ ክፍያን ለማስቀረት የገቡትን ቃል በመተው መንግሥት ሊከፍል እንደማይችል ተናግረዋል።
ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ “እራሳችንን በከባድ የፋይናንስ ሁኔታ ውስጥ ስላገኘነው በዚህ ውሳኔ አንቀጥልም” ብለዋል።
ሰር ኪር ሌበር የብሪታንያ የግል ትምህርት ቤቶች በሚያስከፍሉት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስከፈል እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።
·
ሌበር ፓርቲ እአአ በ2021 ለአረንጓዴ ኢነርጂ ፕሮጀክቶች በዓመት 35 ቢሊየን ዶላር ለማውጣት የገባውን ቃል አጥፎታል። ለነፋስ የኃይል ማመንጫዎችን እና ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የባትሪ ፋብሪካዎችን የመሳሰሉትን ለመገንባት የባውን ቃል ጠብቋል።
ይህ ደግሞ ከኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ ቁልፍ የሆነውን ፖሊሲ “ለማስወጣት” እየሞከረ ነው የሚል ትችት እንዲሰነዘርበት አድርጓል።
ሰር ኪር በቅርቡ ጂቢ ኢነርጂ በተባለ አዲስ ኩባንያ አማካኝነት 8 ቢሊዮን ፓውንድ ከብክለት ነጻ በሆነ የአረንጓዴ ኃይል ዘርፍ ላይ ለማፍሰስ ቃል ገብተዋል።
እአአ በ2030 እንደ ድንጋይ ከሰል እና ነዳጅ ከመሳሰሉ ዘርፎች ዩኬ የምታመርተውን ኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ቃል ገብተዋል። ብዙ ባለሙያዎች ግን ይህንን ማድረግ አይቻሉም ሲሉ ገልጸዋል።
· እስራኤል እና ጋዛ
መስከረም መጨረሻ ላይ ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ፣ ቴል አቪቭ በጋዛ ላይ የምታካሂደውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና ራስን የመከላከል መብቷን ሰር ኪር ደግፈዋል።
ይህ ደግሞ ከብዙ የፍልስጤም ደጋፊ መራጮችን አስቆጥቷል። ከዚህ ይልቅ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እንዲጠይቁ ከበርካታ የሌበር የፓርላማ አባላት ተጠይቀዋል።
በዚህ ዓመት በየካቲት ወር “ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲደረግ” ጥሪ አቅርበዋል። “አሁን መሆን ያለበት ይህ ነው” ሲሉ አክለዋል።
በመጋቢት ወር ዩጎቭ በሰበሰበው የሕዝብ አስተያየት መሠረት በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 52 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ጉዳዩን በጥሩ ሁኔታ እንዳልያዙት ያስባሉ።
የየመን ሁቲ ታጣቂዎች ከእስራኤል ጋር የተገናኙ በመርከቦች ላይ ለሚያደርሱት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ዩናይትድ ኪንግደም በየመን የሁቲ ይዞታዎችን ማጥቃቷን ሰር ኪር ደግፈዋል።
· የአውሮፓ ኅብረት
ሰር ኪር እአአ በ2019 ብሪታንያ ከአውሮፓ ኅብረት መውጣት አለባት ወይ? በሚለው ጉዳይ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ሕዝበ ውሳኔ እንድታደርግ ግፊት አድርገዋል።
አሁን ወደ ብሬግዚት መመለስ ምንም ጥያቄ እንደሌለው ተናግረዋል። ሆኖም ከአውሮፓ ኅብረት ጋር እንደ ምግብ፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የሥራ ደረጃን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ አዲስ የትብብር ስምምነቶችን በተመለከተ እንደሚወያዩ ተናግረዋል።
“መሸነፍን እጠላለሁ”
ሰር ኪር ስታርመር ብዙ ጊዜ አሰልቺ ተብለው በተቃዋሚዎቻቸው መሳለቂያ ይሆናሉ።
እራሳቸውን እንደ ሕግ አክባሪ አድርገው ማሳየት ይወዳሉ። አንድ የሥራ ባልደረባቸው “ሚስተር ሩልስ” [ደንቦችን የሚያበዛ] የሚል ቅጽል ስም አውጥቶላቸዋል።
አንድ ጊዜ ብቻ ነው ሕግ የጣሱት። ወጣት እያሉ ያለ የንግድ ፍቃድ አይስ ክሬም ሲሸጡ በፖሊስ ተይዘዋል። አይስክሬሙ ከመወሰዱ ውጪ ምንም ተጨማሪ ቅጣት አልገጠማቸውም።
በቃለ-መጠይቆች ውቅት ስለ ግላዊ አነስተኛ መረጃ የመስጠት ልምድ አላቸው።
ለዩናይትድ ኪንግደሙ ጋርዲያን ጋዜጣ “መሸነፍን እጠላለሁ። አንዳንዶች ዋናው መሳተፍ ነው ይላሉ። እኔ ግን በእንደዚያ አላምንም” ብለዋል።
ሰር ኪር በ2007 ለብሔራዊው የጤና አገልግሎት (ኤንኤችኤስ) የሚሠሩትን ቪክቶሪያ አሌክሳንደርን አግብተዋል። ጥንዶቹ ሁለት ልጆች አፍርተዋል።
አምስት ለአምስት ሆነው እግር ኳስ መጫወት የሚያዝናናቸው ሰር ኪር፣ የአርሰናል ደጋፊ ናቸው።»
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ