"አዲሱ የዩኬ ጠ/ሚ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድ ተግባራዊ አይሆንም አሉ"

 

New UK PM declares Rwanda migrant plan 'dead and buried' - CNA

"አዲሱ የዩኬ ጠ/ሚ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድ ተግባራዊ አይሆንም አሉ"
7 ሀምሌ 2024
«አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የወጣው ሕግ “የሞተ እና የተቀበረ ነው” በማለት ዕቅዱ ተግባራዊ እንደማይሆን አረጋገጡ።
 
«የሌበር ፓርቲ መሪ በቀድሞው የዩኬ ወግ አጥባቂ ፓርቲ መንግሥት የቀረበውን ስደተኞችን “በሕገ-ወጥ መንገድ” ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድን እንደሚያስቆሙ ተናግረዋል።
ከጥቂት ቀናት በፊት የተደረገውን ምርጫ ያሸነፈው ሌበር ፓርቲ እስካሁን አገሪቱን 310 ሚሊዮን ፓውንድ ያስወጣውን ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድን እንደሚሰርዝ ሲገልጽ ቆይቷል።
 
ሰር ኪር ከጽህፈት ቤታቸው ፊት ለፊት ሆነው በሰጡት መግለጫቸው “የሩዋንዳው ዕቅድ ገና ሳይጀመር የሞተ እና የተቀበረ” ሲሉ ዕቅዱን ተችተዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕገ-ወጥ ስደተኞችን ፍልሰት የሚገታ የተሻለ ያሉትን ዕቅድ መንግሥታቸው እንደሚያስተዋውቅም ተናግረዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ መንግሥት ተግባራዊ ያደረገው ዕቅድ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዩኬ ከሚገቡ ስደተኞች መካከል 1 በመቶ ብቻ የሚሆኑትን ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ስለነበረ ጨርሶ ውጤታማ የሚሆን አይደለም ብለዋል።
 
አዲሱ የሌበር መንግሥት ይህን ዕቅድ ውድቅ ማድረጉ በአገሪቱ ላይ የሚያደርሰውን የገንዘብ ኪሳራ መጠን እስካሁን ገልጽ አይደለም።
 
ከዚህ በተጨማሪም በቀድሞው አስተዳደር ወደ ሩዋንዳ ለመላክ በዝግጅ ላይ የነበሩ 52 ሺህ ስደተኞች ዕጣ ፈንታ ገልጽ አይደለም።
 
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ ዋነኛ የመንግሥታቸው ትኩረት እንደሚሆን በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ሲገልጹ ቆይተዋል።
ሱናክ መንግሥታቸው ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቱ ስደተኞች በአነስተኛ ጀልባዎች ወደ ዩኬ ከመግባት እንዲቆጠቡ አድርጓል ቢሉም አሃዞች የሚያሳዩት እውነታ ግን ከዚህ የተለየ ነው።
 
ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ ዕቅድ ይፋ የተደገረው በጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የአመራር ዘመን ሲሆን፣ ይህ ዕቅድ ባለፉት ዓመታት በርካታ ሕጋዊ ጥያቄዎች ሲነሱበት ቆይቷል።
 
ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 13 ሺህ 195 የሚሆኑ ስደተኞች በአነስተኛ ጀልባ በኢንግሊዝ ቻናል በኩል ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ገብተዋል።
 
ከእአአ 2018 ወዲህ ደግሞ በዚህ መስመር 120 ሺህ ስደተኞች ዩኬ ገብተዋል።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፉት ወራት በአስተኛ ጀልባዎች ወደ አገራቸው የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ መሆኑን ተናግረው “ስደተኞችን ሊገታ የማይችል ዕቅድን ተግባራዊ አላደርግም” ብለዋል።
 
የሌበር ፓርቲ ሕገ-ወጥ የሰው ዝውውር ላይ የሚሠሩ የተደራጁ ቡድኖች ላይ ትኩረት በማድረግ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር የመቀነስ ዕቅድ እንዳለው ገልጿል።»

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።