#ኦኦ! "እኛ BRICS ነን።" #በለው! #ፌንጣዊ የዴፕሎማሲ አያያዝ ለኢትዮጵያ አይጠቅምም።

 

#ኦኦ! "እኛ BRICS ነን።" #በለው! #ፌንጣዊ የዴፕሎማሲ አያያዝ ለኢትዮጵያ አይጠቅምም።
 

ወዳጅወነት ፓርክ የሠራ" መደመር" መርሄ፤ ርዕዮቴ ብሎ ሠርክ መጽሐፍ ሲያትም ውሎ የሚያድር አገዛዝ ደጋፊ ስሎጋን "እኛ ብሪክስ ነን" አትፎግሩን ዓይነት ጨዋታ አምጥተዋል። ። ግን አብይዝም አንስት ዩቱበር የለውምን??? ለጨዋታ ያህል።
ለወዳጅነት ልክ ያስፈልገው ይሆን? ግን የወዳጅነትስ - ከወገብ በላይ እና በታችስ ያሰኜው ይሆን?? ኦ! መዳህኒዓለም አባቴ ደግሞ ልደግመው ነው ለርግማን "መደመር" ልበለው ይሆን? እሱስ ምን እንበለው። ሦስት መጸሐፍ ነው መሰል የታተመው። ዛሬ ዛሬ እንደ "ኢትዮጵያ ሱሴ" #አድራሻ ቢስ ሆኗል። +|ጥሎብህ። የሆነ ሆኖ ኮንፊደንስ ከልክ በላይ ሲሆን #ዕብጠትን፤ ኮንፊደንስ ከልኩ በታች ሲሆን #መኮስመንን ያመጣል። ኮንፊደንስ ጤናውን የሚያገኜው በልኩ ለልኩ ሲሆን። የተንቧለለም፤ የተጣበቀ ወይንም የተኮረኮደ ወይንም ጥብቆ አያስፈልገም። ለልኩ ልክ።
"የዛሬ ዓመት ረጂወቻችንንም በእናመሰግናለን እናስናብታለን። በምግብ እራሳችን እንችላለን" ዓይነትም ጣዕም ያላት የፋንታዚ ወግ ጠሚ አብይ አህመድ ገልጠዋል። እንደ አፈወት ብያለሁ። የሆነ ሆኖ "ብርክሲም" ብትሆኑ ወዳጅነት ከሌላው ጋርም ያስፈልጋል። አላያችሁም የቻይናው መሪ በአገረ አሜሪካ ሲንቦላኩ፤ እዛም እንደተማሩ አዳምጫለሁኝ። የአሜሪካ ወዝም አለባቸው ማለት ነው። ለጠቅላዩም ቤተሰቦቻቸውን አስጠልሎ ነበር የአብርኃሙ ዕልፍኝ አሜሪካ።
ብቻ ……… የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ ወዘተ ፖሊሲው አሳቻ የሆነ አገዛዝ መሪውም አሳቻ ናቸው። የልብ አያደርስም። በአባይ ጉዳይ #ተዘነቋቁሎ አፋፍ ላይ ደርሶ ኢትዮ 360 ሚዲያ ቀድሞ ነቅቶ በቅድመ ማስጠንቀቂያ ደወል በስንት ርብርብ ከእጅ ሳያመልጥ ቀርቷል።
የኤርትራ፤ የሱማሌ እና የኢትዮጵያ ግንኙነትም ልዝ ሽንብራ ወይንም ልዝ እንጨት ሆኖ ቀርቷል። የሱማሌ ላንዱም እግዚኦ የሚያሰኝ ማት አምጥቶ ዳንሱ ተገትቶ ሌላ ጨዋታ መጥቷል። አሁን ደግሞ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ካላት ከእናት አሜሪካ ጋር ፋክክሩ፤ ትርፍ ነገሩ አይበጅም። ጎንደሮች ባለ ቅኔ ናቸው። "ሸማ በዬዘርፋ ይለበሳል" ይላሉ። አክለውም "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይላሉ። ሁሉ ቀርቶ አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵውያን የወላጆቻቸውን ጉሮሮ ሸፍነው ማደራቸው በራሱ ልዩ ስጦታ ነው። እሚልኩትም ቀላል አይደለም። "የነቀዘ ስንዴ" በማስተዋል ሆነን ለምናስተውል ጦስ አስከትሏል። የልተገራ ንግግር አይገባም። ባለፈው ጄኔባ ላይ የነበረው ፈንድራይዚንግስ እንዴት ይታያል? ብሪክሶች ያዘጋጁት ነበርን?? ዓለም የተጨነቀበት ስውር እራህብ እና ማግስት???
ሌላው #ራሽያ
ራሺያ እኮ ስለኦርቶዶክ ጠሚር አብይ አህመድ ስለሚያደርጉት ድምጽ አልባ ምንጠራ፤ ብወዛ ባለፈም ዲስክርምኔሽን እና አስምሌሽን ዕውነቱን በአግባቡ እንድታውቅ ቢደረግ ብዙ የኦህዴድ ኦነግ የተስፋ መረቦችን ማርገብ ይቻላል። ንጉሳዊ ሥርዓት ለመሆኑ ለኦነግ ምኑ ይሆን? ይህን ይገነዘባሉን አረብ ኢምሬት፤ ሳውዲወች፤ ኖርዊያን????
ዝምታው ሥርዓቱን ለመታገል #ኢትዮጵያ #እናታችን ደግሞ እንዳትከፋ ጥንቃቄው በአደብ፤ በፀሎት፤ በአቅል ስለሚከወን ነው። ሌላ በደልን በበደል፤ መከፋትን በቂመኝነት እና በበቀል ማወራረድ ስለማይገባም ነው። ህዝባችን ህይወታችን ነው። ሊቃናቱ ሊሂቃኑ በሚፈጥሩት መከራ ስቃዩ ቢያንስም ቢበዛ ለህዝባችን ፍዳ ነው።
በህወሃት እና በአብይዝም አገዛዝ ጦርነት እና ውጤቱን አስመልክቶ በአማራ ህዝብ ላይ የነበረው ያልተመጣጠነ ዕይታ፤ በጣም #አጥንት #የሚሰነጥቁ ገለፃወች እኮ ሙሉ ለሙሉ እንዲቆሙ የተደረገው #በታይታ #አታሞ አይደለም። #በተደሞ #ስክነት በተከወኑ #ብልህ ተግባራት ነው።
#ምራቁን የወጣ ሙያ ምራቁን የዋጠ አመራርን ይሻል።
ዲፕሎማሲ በሙያቸው ብቻ ሳይሆን በተፈጥሯቸውም ጥንቁቅ፤ አደብ የገዙ ብቁወች የሚከውኑት ተግባር ነው። ስታዮዋቸው እራሱ መንፈሳቸው የተረጋጋ አቅም እና አቅል ያላቸው በሰብዕናቸው አንቱ የተባሉ ጥቂት ምርጦች የሚመረጡበት ዘርፍ ነው። ዲፕሎማሲ እኮ አገር ነው። ዲፕሎማሲ ሉዓላዊነት ነው። ሉዓላዊነት ደግሞ ሩጫ አይመስለኝም። #ዲፕሎማሲ #የካድሬ ተግባር ከሆነ ነገር አለሙ ውሃ የበላው ቅል ይሆናል። ለኢትዮጵያ ክብር እና ልዕልና ሲባል #ካድሬወች አንደበታቸው በዲፕሎማሲ ጉዳይ እንዲታቀቡ ሊደረግ ይገባል። የሌላ ሙያ አማካሪወችም። በስንት ዓይነት ፈንጣጣ እናት ትቀጣ።
ወዳጅነት ገደብ አይሰራለትም። ለዕውነተኛ የፍቅር ተፈጥሮ ዳር ደንበር፤ ወሰን ሊበጅለት አይገባም። ሁሉም አገር፤ ሁሉም የሰው ልጅ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋታል። ኮንፒተርን ማን ሠራው? ስልክንስ? አውሮፕላንስ? አውቶብስንስ? ጉግልንስ?? አንድ ሰው ብቻውን የሠራው ብቻውን የፈጠረው ምንም ነገር የለም። ይህንን መፃህፍቶቼ ላይ በስፋት ጽፌዋለሁ። አንዱ ለሁሉ፤ ሁሉም ለአንዱ፤ ይህ ዓለም ብትመራበት ደስ ይለኛል። የግሎባላይዜሽን መንፈስ ይህን የሚያካትም ይመስለኛል። እና ወዳጅነቱ ሳንክ ሲገጥመው የአንድ አገር ሥልጣኔ ይኮረኮዳል። ጋብቻም አለ እኮ? ውህድ ማንነት ላላቸው ልጆችም ይታሰብ እንደማለት።
#እርግብግቢቱ #ያረገረገው የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ይገርመኛል። #ፌንጣዊም ይመስለኛል።
1) ኢትዮጵያ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሚር እንዴት ተቀበለች? በወቅቱ አዝኜ ጽፌበታለሁ።
2) ኢትዮጵያ የጀርመን ካንስለርን (መሪ) እንዴት ተቀበለች? በወቅቱ በመከፋት ጽፌበታለሁ። ለኦነግ ቤተ - መንግሥት መፈረሽ ጀርመን ለኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ስትል አንከር ሚና ተጫውተዋል?
3) ኢትዮጵያ የአረብ ኢምሬትን መሪ እንዴት ተቀበለች?
4) ኢትዮጵያ የኤርትራን መሪ እንዴት ተቀበለች?
5) ኢትዮጵያ የጣሊያንን መሪ እንዴት ተቀበለች?
6) ኢትዮጵያ የኦስትሪያን ካንስለር (መሪ) እንዴት ተቀበለች? ወዘተ ……
ሁሉንም መዝኑት። የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲያዊ አያያዝ ወጣ ገብነት፦ የፕሮቶኮል ዕውቀት #አናሳነት ለኩት። ኦኦ! ለመሆኑ #ገዳ #ፕሮቶኮል አለውን??? ለመሆኑስ ገዳን ርዕዮት ያደረጉት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የፕሮቶኮል #ሹም አላቸውን? ማን ይባላሉ? ለመሆኑ ፕሮቶኮል በአብይዚም ፖሊሲ ሙያ ነውን? አካል አለውን? ዕውቅና አለውን?????? ቢሮ አለውን??? ምጥ እና ዳጥ።
ወገኖቼ ከቅንጣቱ እስከ ገዘፈው አመክንዮ ድረስ ሥርዓት ያስፈልጋል። በስተቀር አናርኪዝም ይሰፍናል። የበላይ እና የበታች ይከስማል። ልቅነት ይንዳል እርሾ አልባ። ኢትዮጵያ ሃራም የማህበረ ኦነግ አመራር፤ አፍሪካም ስለ ክብሯ ግድ ስለሚላት ሃራም የማህበረ ኦነግ አመራር ልትል ትችላለች። ዓለማችንም። ምልክቱም እዬታዬ ነው።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጥሩ የፖለቲካ ዋናተኛ አይደሉም። ሲወጥኑ አፍርሰው ነው። ዕድሉ ከተደፋ በኋላ ደግም እሳቸውን ነፃ አድርገው እሳቸው አስማሚ አስታራቂ ችግሩን ፈጣሪ ሌላ ሰው አድርገው ይስላሉ። ካድሬወቻቸውም ይህኑ ወደ ቀኝ ሲጓዙ ያን ያግለበልቡ እና ወደ ደቡብ ሲመጡ ደግሞ ያን ይከበክባሉ። ያው ትልቅ ባንባ ንፋስን በሚያስተናግድበት መልኩ። የባንባ ተክል ንቅናቄ ይናፍቀኛል። ባንባ እሸቱም፤ ባንባ ቋንጣውም ናፍቆኛል። ጠረኑም እንዲሁ። ራሱ ዛፋ የባንባ፤ ይናፍቀኛል። የሙጌራ ዳቦ ጉዝጓዝ የቁንዶበርበሬ ለምለምም ሽው ይለኛል።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ይከወን።
"ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል።" በዚህ ይከወናል።
ክብሮቼ እግዜር ይስጥልኝ። አሜን። የወጣትነት ፎቶ ነው የተለጠፈው። በዚህ ዕድሜ ስንት ተባተለ???
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/05/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።