#ክስተት #ለዘመን #ለራዕይም። #በተደሞ #ይመርመር። የመዳኛም #የፊደል #ገበታ ሊሆን ይችላል። ሰክኖ መመርመር። ይህ አዲስ ውሃ ያልነካው የተጋድሎ #ካሪክለም ነው። በአደብ ይመርመር።

 

#ክስተት #ለዘመን #ለራዕይም#በተደሞ #ይመርመር። የመዳኛም #የፊደል #ገበታ ሊሆን ይችላል። ሰክኖ መመርመር።
ይህ አዲስ ውሃ ያልነካው የተጋድሎ #ካሪክለም ነው። በአደብ ይመርመር። 
 
 
"የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።"
(ምሳሌ ፳ ቁጥር ፲፭)
 May be an image of 1 person, beard and text
 
ወጣትነቱን፤ መኖሩን፦ ዜግነቱን፦ ርዕሰ መዲናውን፦ ተስፋውን፤ ራዕዩን፤ ሐሴቱን፤ ምኞቱን፤ ትውፊት ትሩፋቱን፤ ወግና ባህሉን በሥርዓት እንዳይፈጽም፤ በባዕቱ በባድማውም መቀመጫ ያጣ ትውልድ እንዲህ ይቆርጣል። በእኔ የወጣትነት ዘመን የት ይደርሳሉ የተባልን ወጣቶች እንዲህና እንዲያ ሆነን ቀረን። ገና በጥዋቱ ነበር ቀዬወን ሰላም እንዳያሳጡ በ100 ቀናት ተግባራቸው ውስጥ ለጠሚር አብይህ አህመድ አሊ የገለጽኩት፤ ሂደት ላይም እያሉ በስፋት ዘርዝሬ ጽፌላቸው ነበር። ተማላ ሳሉ።
እሳቸው አምቀው በያዙት የአስምሌሽን፤ የስውር ዲስክርምኔሽን የወረራ እና የመስፋፋት አብዝቶ የመጫን እና አማራነትን የመጠዬፍ ተግባራቸው ተጉ። ጆኖሳይድን አንቅረው በተፋው አገር ራውንዳ ሂዶ ከማስመሰል እሳቸው የጀመሩትን የትውልድ ምንጠራ ማስቆም ቀዳሚው ተግባር ነበር። ግን አልሆነም። የቆረጠ ትውልድ፤ መኖሩን የናቀ ትውልድ እንዲህ ሰማዕትነትን ፈቅዶ በሐሴት ያልፋል። ያውም በመንበረ መንግሥቱ መቀመጫ በአፍሪካ መዲና በአዲስ አበባ።
የሚገርም ሰፊ የምርምር ተግባር የሚጠይቅ በጥሞና እና በተደሞ ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ ፊደል ያስቆጠረ፤ አናባቢም ተነባቢም ክስተት እንሆ በምድራችን ተፈፀመ። አስፈሪም አጽናኝም፤ ፈታሽም አራሚም፤ ጎባጣ ሃሳብን አቃንቶ በሰከነ፡ በተረጋጋ መንፈስ ምንሽን ነው እማ ብሎ በማስተዋል ሊመረመር የሚገባው ክስተት።
ይህ የጀግንነት ተግባር ተብሎ ሊታለፍ አይገባም። ለበቀል ብርንዶነትም ኦነጋዊው ኦህዲድ ሊጠቀምበት የሚገባ ክስተት አይደለም። ይህ በማናህሎኝነት አሳዬነው እንጠርገዋለን፤ ፀጥ እረጭ እናደርገዋለን ተብሎ የሚያንጓጥጡበት ክስተት ሊሆን አይገባም። በሥነ ሃይማኖት፤ በሥነ ኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍና፤ በሥነ ህዝብ አሰፋፈር እና መዋቅራዊ ትሩፋት፤ በሥነ ቋንቋ ሥልጣኔ እና የነፃነት አዋጭነት፤ በሥነ ሰነድቅ ዓላማ ተከባሪነት፤ አስከባሪነት እና ተወራራሽነት ከተፈሪነት ጋር፤ በሥነ ቀደምትነት ትሩፋት እና የታሪክ ድርሳን ነፃነት ላይ ያለው ውጥንቅጥ ሁሉ ተግ ብሎ አደብ በልቶ በጥሞና ሊቃናቱን፤ ሊሂቃኑን በአርምሞ አንድ ላይ አስቀምጦ ሊመከርበት፤ ሊዘከርበት የሚገባ ቋሚ አሻራ ሊሆን ይገባል። ትርጉም አትግደሉን ልትገድሉን ከባድማዬ ከመጣችሁ አልሞት ባይ ተጋዳይነታችን ይቀጥላል። እኛን ጠልታችሁ፤ እኛን አሳዳችሁ፤ እኛን አዋርዳችሁ የሚቀጥል በትረ መንግሥት እና ህልውና የለም ነው አዋጁ።
ዓዋጁ የጥላቻ፤ የመገለል፤ የመመንጠር፤ የመነቀል የመፍረስ ዕጣ ፈንታ ሊታወጅብን አይገባም። የትኛውም ሥርዓት መንበሩን ሲይዝ አማራን ተንተርሶ በኋላ ግን አማራን መንጥሮ ሊሆን አይገባም። ሰላማችን ስትነጥቁ ሰላማችሁንም እኛም እነጥቃለን ነው ዓዋጁ። በዚህ መሃል የሚሰጉ ማናቸውም አገራዊ እውነቶች ሁሉ በአደብ ማሰብ ይገባቸዋል። ይህ አዲስ የተጋድሎ ካሪክለም ነው።
ትናንት ዬEMS ውይይት ላይ አቶ ግዛው የነሳው ሃሳብ ነበር። ገርሞኛል። "ሁሉ የጠላው አማራ ከሁሉም ተለይቶ የራሱን ግዛት ለተወሰነ ጊዜ ይዞ ቢቀመጥስ" የሚል እድምታ። ይህ ከአቶ ግዛው የወጣ ሃሳብ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ የፀናው ሰብዕና ያፈለቀው ሃሳብ ብዙ በጣም ብዙ ይነግረናል። አማራ ከኢትዮጵያ ከተነጠለ አፍሪካም ብዙ ያልተለመዱ ክስተቶች እንድታስተናግድ ትገደዳለች። ከዛ በፊት ግን ባለው እንጥፍጣፊ ጊዜ ማሰብ፤ ማሰብ፤ አሁንም ደግሞ ማሰብ ይገባል። አገር የሚመራው የሚተዳደረውም በአንድ ሰው ራዕይ እና ፋንታዚ ሊሆን አይገባም። ከሁሉም ጭካኔው። ከሁሉም መስቃው እና መታበዩ። መራራ ነው። ከርቤ።
በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ለዋሉት፤ በገፍ ከእንግዲህም ወደ ካቴና ለሚወረወሩት፤ በዚህ ምክንያት ማናቸውንም በቀል የሚቀበሉት ንዑዳንን ፈጣሪ ብርታት እና ጥንካሬውን ይስጣቸው። አሜን። ይህን ክስተት በጥሞና መርምሮ ዘላቂ መፍትሄ መስጠቱ እንጂ በቀሉ አይበጅም። በቀል እና ጭካኔ ትርፋ ኪሳራ ነው። ልቡ የሸፈተ ህዝብን መምራት ብቻ ሳይሆን ማሰቃዬት ለሰማይም ለምድርም ህግ ተላላፊነት ነው። ማድመጥ ይገባል ማንኛውንም ክስተት። ግፋ በዝቷልና። ግፋ ተትረፍርፏል እና። ነፃነት አልባ ብልጭልጭ ለእኛ የሚሆን አይደለም። ነፃነት ሲቀማ ነፃነቱን የሚያስከብር ህዝብ መፈጠሩ ቀመር አይሻም።
ህዝብን በማስደንገጥ፤ ህዝብን በማሸበር መንግሥታዊ ሥልጣን አይረጋገም። አሁንም ተግ በሉ። አሁንም አደብ ግዙ። ወጣቶች ለምን ተቆጦ???? በአደብ ይመርመር።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ማስተዋሉን ይስጥ ኢትዮጵያ በእጃቸው ላይ ለምትገኜው መሪወች። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
13/04/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።