#እባካችሁ #ተለመኑን።

 

ቃለ ምልልስ የምትሰጡ አታጋዮች ቢያንስ በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ወገኖቻችሁ ትንሽ እሰቡ። ምን ይሁኑላችሁ? ታስረዋል እኮ? ዕድሜ ልክ ይፈረድባቸውን? ወይንስ የሞት ፍርድ ወይንስ ይሰውሩላችሁ ምን ይሆን ፍላጎታችሁ? ሌላ በስልክ የምታገኟቸውም ቢሆኑ አጋጣሚን ልትቆጣጠሩት ስለማትችሉ ነገ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አታውቁም እና ሥም ከመስጠት ታቀቡ። እባካችሁ ተለመኑን። እባካችሁ።
 
ከታሠሩ፤ ከተሰው በኋላ ማን አስታውሷቸው ያውቃልና? ቀንቷቸው ሲፈቱ ደግሞ እናንተው ቀዳሚ አዛኝ ሆናችሁ ትገኛላችሁ። ጋዜጠኛ ይጠይቃል። መብቱ ነው። ተጠያቂ ጥያቄው ይለፈኝ ማለትም ይችላል። መመለስ ግድ አይደለም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን አይጠቅምም። ከጀማሪ ታጋይ እንኳን አይጠበቅም በሁሉም ዘርፍሁሉም ካለው ሲሆን ያማል። አሁን እኮ እሳት ረመጥ ነው ያለው አገርቤት። በስልክ የሚሰጡ ትዕዛዞችም ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ነው። እግዚአብሄር አምላክ የፈጠረልንን ማስተዋል አብዝቶ በልቦናችን ያስርጽው አሜን።
 
ስለ እስረኞቻችን ትንሽ ርህራሄ ይኑር። ቤተሰብ፤ ትዳር ልጅ ከሁሉምእናት አለች ያቺ መከረኛ። ሌላው ሁሉም በአቅሙ፤ በችሎታው፤ በፀጋው ብቻ ቢሳተፍ መልካም ይመስለኛል።
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ስህተት የለበትም። የሌለበትን፤ ያልነበረበትን አወቃቀር እና ሂደት ለማወቅ ነው ጥረት ያደረገው ከሚያውቀው መረጃ ጋር አቀናጅቶ ለተነሳበት ዓላማ መስመር ውስጥ ለማስገባት። መታሰብ ያለበት ግንጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊም ሆኑ ምክትል ጠቅላይ ሚር ተመስገን ጡሩነህ ሙያቸው ስለላ መሆኑን ነው። ይህ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ ክስተት ነው። ክስተቱ በተለምዶ ዘይቤ ሊታይ አይገባም። እጅግ ጥንቃቄ ይጠይቃል።
 
የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሰው ማትረፍ መስዋዕትነትን መቀነስ በሚመለከት እንዴት ቢደረጉ እንደሚሻል አላውቅም። ሌላው ተጠለፈ የተባለ የስልክ ልውውጥም ከአቤ ቶክቻው ዛሬ አዳምጫለሁኝ። እባካችሁ ጠንቃቃ ሁኑ። ጥንቃቄ ያተርፋልእንጂ አያከስርም።
እኔ በግሌ የተረዳሁት እንዲህ ዘመን ከዘመን ለምንባትል ወገኖች ግን ታላቅ ትምህርት ቤት የተከፈተልን ይመስለኛል። እኛ እንደክማለን ምክሩ፤ ዝክሩ ውሳኔውን ግን አናውቀውም። የሚደርሰን መርዶው ነው። አንጀታችን ስለማይችል ያቺ መከረኛ እናትም ስላለች ለምን? እንዴት? ብለን እንጮኃለን በግራ በቀኝም እንማገዳለን።
 
ለሁሉም ማስተዋሉን፤ ለሁሉም እርጋትን ለሁሉም ስክነትን ከፈጣሪ የሚሰጥ ቢሆንም ድንግል ትርዳን። መነሻዬ አንከር ሚዲያ ከሻለቃ ዳዊት እና ከተረጋጉ ባልደረባቸው ጋር ከጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። የጠቅላይ ሚር አብይ እና የአቶ ተመስገን ጥሩነህ መንግስት በሰፊ ጠቃሚ መረጃ እንደተንበሸበሹ አስባለሁኝ። የሻለቃ ዳዊት ግልጽ፤ ቀጥተኛ እና ሁለንትናዊ መረጃ የሚገርም ነበር። አንከር ላይ ገብታችሁ አዳምጡት። ትዕዛዝ አይደለም ትህትናዊ ማሳሰቢያ እንጂ።
 
ሌላው ለአቶ ወንድም ጋዜጠኛ መሳይ እማሳስበው የእስረኛ ሥም ሆነ ወቅቱን ያልጠበቀ መረጃ ከሆነ ኤዲት ቢያደርገው ህይወት ያተርፋል። ለእናት ልጅ ትርታ ነውና። የሰው ልጅም የጀንበር ዳንቴል አይደለምና። በተለይ የአማራ እናት የዘመንን ግማድ ተሸክማ ሙሉ 50 ዓመታት ለረባ የፖለቲካ ዕውቅና ላልበቃ ተጋድሎ ማህፀኗ ቄራ ሆኗል። ዛሬም። ነገም ይህን ሁሉ ግዙፍ መከራ የተሸከመው የአማራ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደምችል አንድዬ ይወቀው። የሚፈሩ እንዳሉ አውቃለሁ። አሁን ይገበር ሥልጣን የፖለቲካ ውክልናው ግን ያስፈራናል የሚሉ ቲሞች እንዳሉም አውቃለሁኝ። ሚዲያም አላቸው። 
 
በተረፈ አቶ ወንድም ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ያደረገው ቃለ- ምልልስ ለገራገር ነፃ አገልጋዮች ፈዋሽ መድህን ጎዳና ነው። ተባረክልኝ። አሜን። 
 
ውዶቼ እንዴት ናችሁልኝ። መልካም ሰንበት። አሜን። ቸር ያሰማን ቸር እንሁን አወንታዊነትን እንጠጣ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/04/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።