"ኒው ዮርክ ባቡር ጣቢያ ውስጥ አንዲት ሴት በእሣት ተቃጥላ መገደሏ ተሰማ" BBC እኔ የሚያስፈራኝ ይህ ነው።

 

 እኔ የሚያስፈራኝ ይህ ነው። ክፋ ሃሳብን ያነገቡ ሰብእናወች ዓለማችን የጥፋት እና የመከራ በማድረግ ፈሪ ትውልድ ይሻሉ። የጭካኔው ዓይነት ይዘገንናል። ይህን ጭካኔ የሚገታ ወይንም የሚመክት ተቋም አለማችን ምን አላት? የሚያስፈራኝም ይሄ ነው።

https://www.bbc.com/amharic/articles/c23vezjzgzdo

 

"ኒው ዮርክ ባቡር ጣቢያ ውስጥ አንዲት ሴት በእሣት ተቃጥላ መገደሏ ተሰማ"

 

"በኒው ዮርክ አንዲት ሴት ባቡር ጣቢያ ውስጥ በእሣት ተቃጥላ መገደሏን ተከትሎ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል።

የፖሊስ ኮሚሽነር ጄሲካ ቲስክ እሑድ ዕለት የተፈፀመውን ጥቃት "አንድ ሰው ሌላ ሰው ላይ ከሚፈፅማቸው እጅግ ዘግናኝ ወንጀለኞች መካከል አንዱ" ሲሉ ገልፀውታል።

ኮሚሽነሯ እንደገለፁት የተገደለችው ግለሰብ 'ስቴሺነሪ ኤፍ' ከተባለው ጣቢያ ወደ ብሩክሊን እያቀናች ሳለ ነው አንድ ሰው መጥቶ በእሣት መለኮሻ (ላይተር) ልብሷን ያቀጣጠለው።

ግለሰቧ እዚያው ባቡር ጣቢያ ውስጥ ስትሞት ተጠርጣሪው በተማሪዎች ጥቆማ መሠረት ሌላ ባቡር ሲሳፈር በቁጥጥር ሥር ውሏል።

ፖሊስ እንዳለው ስሟ ያልተጠቀሰው ሴት እሑድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ጥዋት 1፡30 ገደማ ነው ባቡር ስትሳፈር አንድ ሰው የተጠጋት።

ከጥቃቱ በፊት በሁለቱ መካከል ምንም ዓይነት ንግግር አልነበረም ያለው ፖሊስ ሁለቱ ሰዎች ይተዋወቃሉ ብሎ እንደማያምን አስታውቋል።

በባቡር ጣቢያ ያሉ የፖሊስ መኮንኖች እሣቱን ለማጥፋት ሲረባረቡ ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው ግለሰብ ከሥፍራው ሮጦ ማምለጡ ተሰምቷል።

"በባቡር ጣቢያው በላይኛው ክፍል ላይ የነበሩት ፖሊሶች በሽታ እና በጭስ አማካይነት እሣት መነሳቱን ተመልክተው ለመመርመር ወደ ሥፍራው አቅንተዋል" ብለዋል ኮሚሽነሯ።

"ወደ ሥፍራው ሲደርሱ ግን አንዲት ግለሰብ ሙሉ በመሉ እሣት ተያይዛ ነው ያገኟት።"

ፖሊስ አሁንም የሟችን ማንነት ለማጣራት ሙከራ እያደረጉ እንዲሁም የጥቃቱን መንስዔ ለማጣራት ሙከራ እያደረገ ይገኛል።

ኮሚሽነር ጄሲካ እንደሚሉት "ተጠርጣሪው ጥቃቱን ካደረሰ በኋላ ባቡር ጣቢያው ውስጥ በሚገኝ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ነበር። ለምን ይህን እንዳደረገ አላወቅንም።"

የኒው ዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት የግለሰቡን ፊት የሚያሳይ ፎቶ ማሰራጨቱን ተከትሎ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ነው በቁጥጥር ሥር የዋለው።

ማንሀታን በሚገኘው ኢምፓየር ስቴት በተሰኘው ሕንፃ አካባቢ ባለው ባቡር ጣቢያ ውስጥ ነው የተያዘው።

የፖሊስ ኮሚሽነሯ እንደገለፁት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሲውል ኪሱ ውስጥ ላይተር ተገኝቷል።

"ታዳጊዎቹን ማመስገን እፈልጋለሁ። ያዩት አይተው ዝም አላሉም። 911 ደውለው ጥቆማ ሰጥተዋል" ብለዋል።

ስሙ በይፋ ያልተጠቀሰው ተጠርጣሪ በአውሮፓውያኑ 2018 ከጉዋቲማላ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተሰዶ የመጣ መሆኑን የኒው ዮርክ ከተማ ፖሊስ ጆሴፍ ጉሎታ ተናግረዋል።

አክለው ግለሰቧ ጥቃቱ ሲደርስባት እንቅልፍ ተኝታ ነበር ወይስ አልተኛችም የሚለውን ለማጣራት ሙከራ እያደረጉ እንደሆነ አስታውቀዋል።"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።