"በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ "ህመማቸው እንደባሰባቸው" ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ" BBC እኔ ደግሞ ... የዚህ ሥርአት #በቀለኝነት እኮ #የዲያቢሎስ ዓይነት ነው።

 

 

የዚህ ሥርአት #በቀለኝነት እኮ #የዲያቢሎስ ዓይነት ነው።
በእጃቸው ያሉ እስረኞችን እንዲህ እንዲሰቃዩ ማድረግ #አረማዊነት ነው። ሃይማኖት አለኝ የሚል ስርዓት በእነኝህ የአማራ ሊቃናት ላይ የወሰደው፤ በመውሰድ ላይ ያለው በቀላዊ እርምጃ ነገን #ያከስለዋል። ዛሬንም #ቃሬዛ ላይ ያውለዋል። ከዚህ ቀደምም የአማራ ባንክ ትጉህ ሰራተኛ በቁሙ እስር ቤት ገብቶ አስከሬኑን ነው ተረከቡ የተባለው። የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና አሁንም የሚፈለገው ይህ ነው። 
 
በየትኛውም ሁኔታ የሚደረጉ የህልውና ተጋድሎወች በብርቱ ጥንቃቄ ሊያደርጉበት የሚገባውም በዚህ መሰል አመክንዮ ላይ ያስተዋለ የፖለቲካ አቅም መፍጠር ሲቻል ብቻ ነው። በድንገቴ ግጥግጦሽ ስልጣኑን የተረከበው ማህበረ ኦነግ በአዲስ ዘይቤ መምጣቱ አይቀሬ ነው። የአማራ ቅን ህዝብ አቅሙን ቆጥቦ በስርዓት አቅሙን የማስተዳደር ግዴታ አለበት። የአማራ ህዝብ #መታመኑን ከእነ ሙሉ አቅሙ አስረክቦ ነው "ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቁሞ ማውረድ ይቸግራል" እንደሚባለው የሆነው። 
 
የአማራ ህዝብ አመድ አፋሽ ነው። ሙሉ ድምፁን ሰጥቶ በወዘተረፈ የበቀል ዓይነት ሙሉ ስድስት አመት ተቀጠቀጠ። እንዴት ህመም ላይ ባለ ሰብዕና ይጨከናል? አንዴት? ለምንስ???? 
 
ይህ አስተምህሮ ነገንም በማስተዋል ማደራጀት እንደሚገባ ትልቅ ትምህርት ቤት ነው። እየዳሁ ያሉ አመክንዮወችን አያለሁኝ። ብርቱ ጥንቃቄ የሚጠይቁ። በዳግም "በኢትዮጵያ ሱሴ" መደናገር እንዳይኖር ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ማህበረ ኦነግ መንፈሳቸው የሚቀዳው ከአንድ ነውና። አይደለም የይዘት የቅርጽ ልዩነት የላቸውምና። አህቲ ናቸው። እየገዙም የማይጠግቡ። እየገዙም የማይረኩ። ይሉኝታየሚባል ያልሰራላቸው።
 
ፍትህ በህመም ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን።
እንዴት አመሻችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁን?
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/12/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

 

 https://www.bbc.com/amharic/articles/c24n6y9e31qo

 

በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ "ህመማቸው እንደባሰባቸው" ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "ለከፍተኛ ሕመም" መዳረጋቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ቤተሰቦቻቸው እስረኞቹ ቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ "የማያቋርጥ የደም መፍሰስ እንዳጋጠማቸው" ገልጸዋል።

ሁለቱ ፖለቲከኞች "በተደጋጋሚ አቤቱታ" ከሁለት ሳምንት በፊት ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሁለቱ ግለሰቦቹ በሆስፒታል ይቆዩ ቢባልም "ያንን እምቢ ብለው በሰዓታት ልዩነት በማይመች መኪና ጭነው ወደ ማረሚያ ቤት መልሰዋቸዋል" ሲሉ የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ተናግረዋል።

አንድ የአቶ ክርስቲያን የቅርብ ቤተሰብ "ቁስሉም አልደረቀም እና ደግሞ ደም እየፈሰሳቸው ነው። ሐኪሞቹም ተናግረዋል፤ ደም መፍሰስ ሊያጋጥም እንደሚችል እና ይህ ሲያጋጥምም እንድታመጧቸው ብለው ነበር" ብለዋል።

ነገር ግን ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ወደ ሆስፒታል አለመወሰዳቸውን ገልጸዋል።

ሕክምናውን ተከትሎ ለሚከሰተው የደም መፍሰስ ማስታገሻ እንደተሰጣቸው ያስታወሱት የቤተሰብ አባላቱ "የተሰጣቸው የማስታገሻ መድኃኒትም አልቆባቸዋል። ሕመሙን ለማስታገስ ቶሎ ቶሎ እየወሰዱት ስለነበር" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የአቶ ዮሐንስ ቤተሰብ አባል፤ "ትላንት ማስታገሻ ይዘን ስንሄድ መግባት አትችሉም ተባልን፤ ለምንድን ነው ስንል? ሊቀየሩ ነው አሉን። እስከ ትናንት ግን እነሱ አይሄዱም ብለውን ነበር። ትናንት በድንገት ተነስተው ሊወጡ ስለሆነ ምንም ምግብ ማስገባት አትችሉም መድኃኒትም አይገባም ብለው ከለከሉን" ብልዋል።

የአቶ ክርስቲያንም የቤተሰብ አባል በተመሳሳይ "ትላንትና ምግብም ማስታገሻም ይዘን ስንሄድ የሚያስገባን ስለሌለ ተመለስን" ሲሉ ተናግረዋል።

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ሰኞ ታህሳስ 7/ 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፤ "ታራሚዎችን ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ ወደሚጠራው ማረሚያ ቤት እንደሚያዘዋውር አስታውቆ ነበር።

ይህን ተከትሎም "በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ የሚቆይ" መሆኑን ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ በዚሁ መግለጫው ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ የተቋረጠው አገልግሎት ከዛሬ ታህሳስ 14 እንደገና እንደሚጀምር በመግለጫው ገልጾ ነበር።

ነገር ግን የአቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ ቤተሰቦች ዛሬም ምግብ ማስገባት እና እስረኞቹን መጠየቅ እንዳልቻሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ጉዳዩን በተመለከተ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገረመው አያሌው ጋር ያደረገው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ምላሽ ባለማግኘቱ አስተያየታቸውን ማካተት አልቻለም።

ዐቃቤ ህግ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ላይ ክስ የመሰረተው ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ነበር። ከሁለት የምክር ቤት አባላት በተጨማሪ ሌሎች 50 ግለሰቦች እና ፖለቲከኞችም በአቶ ዮሐንስ ቧያሌው ስም በሚጠራው የክስ መዝገብ ተካትተዋል።

ግለሰቦቹ በ2015 ዓ.ም. ማብቂያ ላይ በአማራ ክልል ከተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ክስ ሳይመሠረትባቸው ለስድስት ወር ቆይተው ነበር።

ዐቃቤ ህግ ክሱን የመሰረተው የወንጀል ሕጉን እና የፀረ ሽብር አዋጅን ጠቅሶ ነው።

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በ12 ገጾች የተዘጋጀ የክስ መቃወሚያቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበዋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።