ልጥፎች

እኮሳ!

ምስል
እኮሳ ! ወደ ዬት ? „ከሱም የተነሳ ባንደበቴ ነገር ተነገረ፤ ምድርም ጠፋች ብዬም እጮኽ ነበር።“   መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፳፱ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ © ሥላሴ 17.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ የራስ ተሰማ ናደው ቅኝተኛ ቀኝ ጌታዎቻችን። ·        እኮሳ!  ወደ ዬት ጥሩ ጥያቄ ነው። አሁን በምናዬቸው ምስቅልቅሎች አንዳንድ ጊዜ ድንጋጤ እንዳንድ ጊዜ ብስጨት፤ አንዳንድ ጊዜ ሀዘን ይሰማናል። ስለምን ቢባል አዲስ ሥርዓት ለመፍጠር ያለን ተስፋ እና ጭብጡ የሚነግረን ድብልቅልቅ፤ ውልቅልለቅ ያለ ድንገቴ መረጃ መላ ከማጣቱ የተነሳ ነው። ብዙ ነገሮች ዝንቅ ናቸው። የእነኝህ ቀውሶች መነሻ ያው የራስ ተሰማ ናደው የሴራ ምህዋር ሲሆን ነጠል አድርገን ለማዬት ግን እኔን በሚገባኝ ልክ ትንሽ ልፈትሽው። ለነገሩ እኔ ከሰሜን አሜሪካ ጉዞ መልስ የሆነው በአባ ዝምታ የሐምሌ ዕድምታ ብዙ ኮልሚያለሁኝ። አማራን በተመለከት ምንግዜም ያው ነው። ብዙም አልጠበቀነም ባልጠበቀነው ልክ የሆነውን ከዕለቱ ጀመርነን ታዝበናል። አንቦ ይናገር! ግን ዛሬም ትንሽ በተያያዘ መልኩ ልበል፤ ቀውሰኞች በጅረታቸው እስኪ ይፈተሽ … ·        ቀድሞውንም የወያኔን ዓላማ ሲያራምዱ የነበሩ ግን ተጋሩ ያልሆኑ በፍጹም ሁኔታ የአብይን መንፈስ የማይፈቅዱ አሉ። እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አይነት እነኝህ ከአኩራፊው ማህበር መዶል እንችላለን።   ·        በፍጹም ሁኔታ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ውጪ መሽቶ የማይነጋ የሚመስላቸው አሉ ማህበረ ተጋሩ ብቻ ሳይሆን የማህበረ ተጋሩን ስሜት የሚጋሩ። እንደ ሳጅን በረከት ስምዖን አይነት። ·        በዛ በሽግግር ዘመን አብረው ሆነው

ለንጉሥ ታከለ ኡማ ሲባል ግለት በአደባባይ።

ምስል
ያቅለሽልሻል። „በታካች ሰው እርሻ   እምሮ በጎደለው ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፴ ከሥርጉተ©ሥላሴ  16.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።  ለነገሩ እኔ ብዙም አይደንቀኝም ወንበሩ ባዶ ሆኖ ነው ያዬሁት። የዛሬ ሹመት ስንት ቀናት እንደሚሰነበት ደግሞ ወጀብ ይጠዬቅበት። መፈንቅለ መንፈሱ በጉልህ ዛሬ ማዬት ያስችላል። ጉለበታሙ አርሲኛው እና ጉልበታሙ አደዋኛ ጋብቻው የደራ ይመስላል።  ሌላው ሴቶች እኩል በኩል ቁጥር መሆኑ እናትነት አህትነት እርህርህና ሲሉን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጫካ እንዴት እርህርህና፤ ፋቲክ እንዴት ርህርህና፤ ምላጭ እንዴት እናትንት፤ ጭካኔ እንዴት ደግነት፤ ጋዳይነት እንዴት ጽድቅ ስለመሆኑ ፊት ለፊት በቀዳማይነት  ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄርን ሮል ሞዴል አደርገውልን ነው። ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜልም ቢሆን ሥራ በዝቶባቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ ነው የተባለው። እንደ እኛ በፖለቲካ ድርጅት ለሰራ ሰው እቃ እቃ ጨዋታ ነው። ለጠ/ ሚር ቦታ የሚያሰጉ ሴት እዬሆኑ መጡ፤ አሁን በቅርብ በወሰዱት እርምጃ የለውጡ ኮከብ አንስት መሆናቸው፤ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው አስፈራን፤ የለውጡን ታሪክ እኛው እንጠቀልለዋለን ቢባል በስንት ጣሙ። አሁንም ድርብርብ ያለ ሃላፊነት ነው ያተሰጣቸው በዛ ላይ ሥሙ "የሰላም"እና ምግባሩ የማይገናኝ ነው።  ለእኔ እንደ ዕንባ ጠባቂ፤ እንደ ሴቶች እና ህጻነት፤ እንደ ሰብዕዊ መብት ኮሚሽን ነው የማዬው። ለውጥ በምለው ወስጥ ያለወን የሴራ ገመድ ምዕራባውያን እንዳያዩት ለመሸበብ ነው። እሳቸው እንዲሙሩት የተፈለገው ተቋማት  የኦሾቲዝ ታሪክ ነው ያላቸው። በሌላ በኩል  እኔ ይህ ዲሞሽን ነው። ዶር አብይ ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር ወደ ኦ

ጠ/ ሚር ዶር አብይ ለልዩ ሃይሉ ትህትና መቀለባቸውን እደግፈዋለሁ።

ምስል
መጋጋል ። „እግዚአብሄር የእውነት ዳኛ ነው፤ ሃይለኛም ታጋሽም ነው። ሁልጊዜ አይቆጣም“ ከሥርጉተ© ሥላሴ  13.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። በሰሞናቱ የልዩ ሃይል አመጥ ጉዳይ የሁለገብ ሊቀ ሊቃውነቱ ሻለቃ ዳዊት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት። ያው ሙያዊ ነው። እሳቸው ሉላዊ ዕውቀትም፤ ልዩ ተመክሮም ያላቸው ሊሂቅ እጬጌም ናቸው። በሌላ በኩል መጀመሪያ ላይ ከምንም ያልቆጠሩት ሁሉ አሁን ውይይቱ ሦስት ቀን ነበር ሲባል ማጋጋሉን ተያይዘውታል። መጀመሪያ ላይ ነው ጠረኑ ትክክል አለመሆኑን በርቀት ማዬት፤ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ለመንግስት መስጠት። ቀደም ብሎ ጉዳዩን ማጥናት፤ መተንተን እና መረጃውን ከተለያዬ አቅጣጫ የመገምገም ምህንድስና ሊደረግበት ነበር የሚጋባው። ቀድሞ ነገር እንደዚህ ያለ ነገር ሲደመጥም ወዲያው ማብራሪያ መስጠትም የተገባ አይደለም። ችኮላ አያስፈልገውም። ተደሞ ያስፈልገዋል። ርጋታ እና ስክነትም ይጠይቃል። አሳድሮ አገላብጦ አይቶ ከስሜት ጋር ሳይስጠጉ፤ በራስ ፍላጎት ሳይቸነክሩ የጭብጡን ማንነት ብቻ በራሱ ማንነት ራሱን አስችሎ መመርመር ነበር የሚገባው። የሆነ ሆኖ እኔ አስተያዬቴን ዛሬ ልሰጥ የፈልግኩበት ምክንያት ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮወርጊስ ዕይታ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የወሰዱት እርምጃ ትክክል አይደለም የሚሉትን ነው። እሳቸው ዘመን ጠገብ ባለሙያ ስለሆኑ እሳቸውን አሻቅቤ መተቸት አልችልም። ክህሎቱም ተመክሮውም ብልጹግ ነው በሲቢሉም ሆነ በወታደራዊ። መሬት ላይም ሰርተውበታል። ነገር ግን እኔ እንደ ሰው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የወሰዱት እርምጃ ትክክል ነው ብዬ ነው እማስበው ። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ እያስተማሩ ያሉት የሃሳብ አቅም ከባዱን ተራራ ንዶ፤ ደልድሎ፤ ሸካራውን ለግ