ለንጉሥ ታከለ ኡማ ሲባል ግለት በአደባባይ።

ያቅለሽልሻል።
„በታካች ሰው እርሻ   እምሮ በጎደለው ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፴
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 16.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


 ለነገሩ እኔ ብዙም አይደንቀኝም ወንበሩ ባዶ ሆኖ ነው ያዬሁት። የዛሬ ሹመት ስንት ቀናት እንደሚሰነበት ደግሞ ወጀብ ይጠዬቅበት። መፈንቅለ መንፈሱ በጉልህ ዛሬ ማዬት ያስችላል። ጉለበታሙ አርሲኛው እና ጉልበታሙ አደዋኛ ጋብቻው የደራ ይመስላል። 

ሌላው ሴቶች እኩል በኩል ቁጥር መሆኑ እናትነት አህትነት እርህርህና ሲሉን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጫካ እንዴት እርህርህና፤ ፋቲክ እንዴት ርህርህና፤ ምላጭ እንዴት እናትንት፤ ጭካኔ እንዴት ደግነት፤ ጋዳይነት እንዴት ጽድቅ ስለመሆኑ ፊት ለፊት በቀዳማይነት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄርን ሮል ሞዴል አደርገውልን ነው።

ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜልም ቢሆን ሥራ በዝቶባቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ ነው የተባለው። እንደ እኛ በፖለቲካ ድርጅት ለሰራ ሰው እቃ እቃ ጨዋታ ነው። ለጠ/ ሚር ቦታ የሚያሰጉ ሴት እዬሆኑ መጡ፤ አሁን በቅርብ በወሰዱት እርምጃ የለውጡ ኮከብ አንስት መሆናቸው፤ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው አስፈራን፤ የለውጡን ታሪክ እኛው እንጠቀልለዋለን ቢባል በስንት ጣሙ። አሁንም ድርብርብ ያለ ሃላፊነት ነው ያተሰጣቸው በዛ ላይ ሥሙ "የሰላም"እና ምግባሩ የማይገናኝ ነው። 

ለእኔ እንደ ዕንባ ጠባቂ፤ እንደ ሴቶች እና ህጻነት፤ እንደ ሰብዕዊ መብት ኮሚሽን ነው የማዬው። ለውጥ በምለው ወስጥ ያለወን የሴራ ገመድ ምዕራባውያን እንዳያዩት ለመሸበብ ነው። እሳቸው እንዲሙሩት የተፈለገው ተቋማት  የኦሾቲዝ ታሪክ ነው ያላቸው። በሌላ በኩል  እኔ ይህ ዲሞሽን ነው። ዶር አብይ ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር ወደ ኦሮምያ እንደተወረወሩት ማለት ነው። 

ሌሎቹ አዳዲስ ሴት ሚ/ርች እዬታዩ ይለኩ፤ የመጀመሪያ የመከላከያ ሚ/ር ሴት መሆን ሳይሆን ቁም ነገሩ እንደ ጀርመኗ ሴት የመከላከያ ሚ/ር በመሆን መገኘት ሲሆን ያኔ ጎሽ እንላለን። ያው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ጨላማዊ መህን እንዲያስቀጥሉ ስለሆነ ጥናት መቀነቱን ብለናል ...  

  • ግለት በአደባባይ። 

ወደ ጉዳዬ ስመጣ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ዛሬ የትራንስፖርት ሚ/ር ሆነው መሾማቸው እያዘን ሰማን። የመጀመሪያው ሃዘን ሂጅ እና ብአዴን ጉባኤ ተሳታፊ የተባለ ቀን ነው ደም አልቅሰናል። 

ልክ አቶ ታማኝ በዬነ አንተ ስለ ኢትዮጵያዊነት እንድትዘምር እምንሻው ለእኛ የቃል ጉዝጓዝ እንጂ አንተማ አማራ ነህ እዛ ተገኝ ተብሎ በብአዴን/ አዴፓ ጉባኤ እንዲገኝ ተደረገ። እሱም እሺ ብሎ መቀበሉ ይገርም እስከ ወዲኛው ነው። ባይሆን በኢህአዴግ ጉባኤ ተገኝ ቢባል እኮ በተሻለ። 

የሆነ ሆኖ ልብ ካለው ብዙ መልዕክት ተልኮለታል በሽምቅ ውጊያ። አቶ ጃዋር መሃመድ ማለት እንዲህ ነው። ካላሸነፈ የማይተኛ። የጠ/ ሚር ቢሮን ሚመራውም የሱ መንፈስ ነው። መፈንቀለ መንፈሱን መዳፉ ላይ ያደረገው ተገለባብጦ አሳካቶታል። ከዚህ በላይ ምን ስልጣን ያስፈልጋል ብሏል እኮ እራሱ። አሁን ከጉባኤ ማግስት አዴፓም አዲስ ብወዛ ላይ እንዳለ እዬተደመጠ ነው ምን ይሰራሉ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ታላቁ የጃውርዋያን አርሲውያን አካል ናቸው እኮ ሰሚ ጠፋ እንጂ።   

የሆነ ሆኖ አዲስ አበቤዋ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የአንድ የፖለቲካ ድርጅትን መርህ ሳይከተል በቀጥታ ትእዛዝ የብአዴን/ የአዴፓ ጉባኤ አባልተኛ መሆናቸው ሲገርምን አሁን እምንሰማው የትራንስፖርት ሚኒስተር ሚኒስተር ሆናው መሾማቸውን ነው። ይገርም እስከ ወዲኛው ነው። ቲም ለማ ማለት ቲም ፑቲን እዬሆነ ነው። ለነገሩ አታውቋቸውም እዬልኩ ስቸከችክ ነበር። ግን እኔ በ አሉታዊ ሳይሆን በአውንታዊ ነበር። እኔ አሁንም አብይን ፍለጋ ነኝ ...  

ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን ይህ የሆነበት ምክንያት ጸሐፊ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ብቁ እንደሆኑ፤ ሲነሪትም እንዳላቸው፤ ሰለ አዲስ አባባ የበቃ መረጃ እንዳላቸው፤ አዲስ አባባ ተወልደው ማደጋቸውን አክሎ፤ ክህሎታቸውን የሥራ፤ ልምዳቸውን በሚገባ በዝርዝር ጽፎት ከንቲባ መሆን እንዳለባቸው በአጽህኖት ጽፎ ነበር።

የአሁኑ ሹመት ይህ የሆነበት ምክንያት የአዲስ አበባን ማንነት ለመጨፍለቅ የተወሰደ እርምጃ ነው። ለንጉሥ¡ አቶ ታከለ ኡማ ይደላ ዘንድ ነው። ምክንያቱም ይህቺ ብቁ ሊሂቅ ሁሉንም መስፈረት ስለሚያሟሉ ቀጣይ ምርጫን ሳይጠብቅ ተቀባይነታቸው፤ ዕውቅናቸው ጎልቶ ንጉሡን¡ እንዳይገለብጡ ተብሎ የተሠራ ድራማ ነው። አዲስ አባቤን መንፈሱ ትንፋሹን ነው የተቀማው። እሳቸው እኮ ዞግ የላቸውም። ብሄር አልቦሽ ናቸው። አዲስ አባቤ ዞግ ኑሮት አያውቅም። አሁን ይልቅ በትልቁ ጭነውታል። አቤት መከራው አዲስ አበቤ!
የአዲስ አባባ ወጣቶችም የታሠሩበት ምክንያት ለንጉሥ ታከለ ኡማ ተልዕኮ ኦነግውያን ስኬት ሲባል ነው። ሹመት ያደበር ዕድሜውን ከሰጠ¡

ዛሬ በነበረው የፓርላማ ጉባኤ ላይ አዲስ አባባ የአፍሪካ መዲና ስለመሆኗ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አውስተዋል። ማንነት የሌላት ከተማ 1204 ወጣቶቿ ጦላይ በበቀል በሰከሩ ጸላዬ ሰናዮች ክብራቸው ሲገፈፍ፤ ከ5 ሚሊዮን በላይ አብይን ደግፌያለሁ ብሎ በራሱ ወጪ ቲሸር አሰርቶ ላከበረ አዲስ አባቤ በአደባባይ ሲረሸን አዲስ አበባ የማን ስለማን ስለመሆኗ እዬተነገረው ነው ለዓለም ህበረሰብ ሁሉ።

ይባስ ብሎ የዛሬ ሹመት የአዲስ አባባን ተስፋ እንቆቆ ያስቆረጠመ ጥቁር ቀን ነው። ለአዲስ አባባ ድቅድቅ ጨለማ ነው። ያሳደጋት ልጁ ተገፍታ በሌላ ሹምት ስም እንድተገለል ሲደረግ ቲም ለማ ዕውነትም „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውን¡“ እዬተረጉመልን ስለመሆኑ መርዶውን ልኮልናል። 

ለመሆኑ ከአዲስ አባባ የተወከሉ የፓርላም አባላት እንዴት አብረው ይህን ውሳኔ ያጸድቃሉ? የወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እኮ ትልቁ ልክ ቦታቸው የአዲስ አባባ የዛሬ ም/ከንቲባነት ቀጥሎም ከንቲባነት ነበር።  ለኢትዮጵያ ታሪክም እጅግ ብልጹግ ይሆን ነበር። ለነገሩ አብዩ እኮ ከስሜን አሜሪካ መልስ በቅድመ ሁኔታ የታገተ ነፍስ ነው ያለችው። ሰው አይደክመው እንዲህ እንዲያ ያደርግ ይላል እንጂ ... እዛ አገር የገቡተም ትይንቱ ውጧቸው ውሉ እንደጠፋቸው ይሰማኛል። እኔ አንድ ሊሂቅ ከመሄዱ በፊት ሽፍኑን ነገር ይገልጥ ዘንድ ሳሳበው ለካንስ እሱ ትኬት ቆርጦ ኗሯል። "አክ" መባላችን ቀን ይፈታዋል። 

ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከማዕቀፈ አዲስ አባባ እንዲገለሉ ነው ይህ ሹመት የተሰጠው። አልታወጀም እንጂ አዲስ አባባን ለኦሮምያ አስረክቧል የለውጥ ሃይል የሚባለው። ሀቁ ቢመርም፤ ኮሶ ቢሆንም ይህው ነው። ቀጣዩ ተመራጭ ንጉሥ¡ ታከለ ኡማ ይሆናሉ። ለነገሩ ነግራችሁናል እኮ ህገ መንግሥታዊ ኢህአዴጋዊ ውሳኔያችሁን።

ሌላው ዶር አንባቸው መኮነን ለውጭ ጉዳይ ሚ/ር የማይመጥኑ ሆነው ይሆን ወደ መጣህበት ተወርወር የተባሉት ነው ወይንስ የ አቶ ንጉሱ ጥላሁንን አፕሮባል ስላላገኙ? ይህ አመክንዮ የለውጡ አካላት አብሶ የአማራ ኮከቦች እዬተገፉ ስለመሆኑ ያሳያል። ምን አለ ያን ጭንቅ አሳልፎ ዛሬ ለ176 ድምጽ አድርሷል። ቀን ካወጣ እንዳ አካፋ እና ደሞ መወርወር አማራ ለምዶበታል።  

ለነገሩ ዶር ገዱ አንዳርጋቸውንም ወደ አንባሳደርነት ገፋ ለማድረግ እንደታሰብም እዬተደመጠ ነው ወደ አሜሪካ ነው መሰል የሰማሁት፤ … ስለምን ለውጡ የኦህዴድ ብቻ፤ ተጋድሎው የቄሮ ብቻ ታሪክ እንዲሆን ስለሚታስብ ነው። ለዚህ ነው ለረጅም ጊዜ የአማራ ይህልውና ተጋድሎ ዕውቅና እንዳይሰጠው የተደረገበት ምክንያት ግልጽ እዬሆነ ነው። እኔ ስሞግት ነበር የባጀሁት። 

እኔ ለረጅም ጊዜ ጮሄላሁኝ። አሁን የለውጥ ሃይል አካላትም እዬተገፈተሩ ነው የትናንቶች የመከራ ቀናት ቀን ያደረሱት ተረስተው ግጥም ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋራ ተሁኗል። ለነገሩ ቀደም ብሎ  በአቶ ደመቀ መኮነን ስለምን ራሴን አገላለሁ እንዳሉ በስፋት ጽፌበታለሁኝ። አሁን ኮተት እያለ ወደ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፤ ወደ ዶር አንባቸው መኮነን እዬመጣ ነው። ለነገሩ ነፍስ ይዞ መውጣትም አንድ ነገር ነው። አይ ግንቦቴዎች አሁንም እዛው ላይ ትሆኑን? 

ቆመስ ተስፋዬ ጌታቸው በጊዜ ተሸኝተዋል። በዚህ ሹመት ዶር አሚር አማን ጨምሮ ስንት እጁን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሹመኞች ተንበሸበሹበት? ይበል ብለናል¡የሐምሌ ዝምታ ማን እና ማን እንደ ከወኑት አሁን ግልጽ እዬሆነ ነው። ጃዋርውያን እና አደዋውያን ይሆኑን?

 ውይ የገረመኝ ደግሞ ባለቤት አልባዎቹ የአዲስ አባቤዎች ምንዱባን ከሰሞናቱ ከእስር እንደሚለቀቁ  እንደሚፈቱ ሲሰሙ ግሎባል አላይንስ መግለጫ እንዳወጣ ሳተናው ላይ አገኘሁኝ። የት ነበር እስከ ዛሬ፤ እንዲያውም እኮ ሄዶ ማዬት ነበረበት ጦላይ ድረስ ሄዶ? ከእነሱ መግለጫ በፊት ቀደም ብሎ መረጃውን ተደምጧል። እውነት ብንሆን ምን አለበት? ስንት ዘመን ልንኖርበት? ይደክማል እያቅለሸለሸ።  

ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ አብይ አህመድ (ግሎባል አሊያንስ)
October 16, 201

ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም ይፈሳል።
ዕውነት የት ትገኝ ይሆን? 
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።