የምናከብርህ ዶር አንባቸው መኮነን ከጎንህ ነን!

እንኳን ደስ አለህ አዴፓ¡
„ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት።“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፵፱ ቁጥር ፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
18.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
                                                                    
  • ·      ፍታ።

የኔዎቹ እንዴት ናችሁ፤ ብዙ ሰው ሹመቱ የራሳቸው ነው እኛን ምን አገባን የሚሉ አሉ አሁን እኮ መንግሥት አለ ብለን ስለምናምን እንጂ እኔ አዲትም ቀን በሹመቶቻቸው ዙሪያ ጽፌም አላውቅም፤ ፓርላማም ጉባኤውን በትጋት እማዳምጠው ከመጋቢት 24 ቀን ጀምሮ ነው። 

ሌአለው ቀርቶ እዚህ ሲዊዘርላንድ ማን አንባሳደር እንደሆነ፤ አንባሲው ቢሮው አድራሻው የት እንደሚገኝ ሁሉ አላውቀውም፤ ምን ይዶለኛል፤ ምንስ ያገበኛል፤ እኔ ዜጋ አይደለሁምና። አሁን አስተያዬት የምንሰጠው የ እኔ ከማለት ነው እንጂ ይህን ራሱን አይተን አይተን እናቆመዋለን።
እኔ በተለይ ወንበሩ ባዶ ሆኖ ስላዬሁት ብቻ ሳይሆን ከስሜን አሜሪካ መልስ ጠ/ ሚሩን የማስወገድ አደጋም ተደርጓል ብዬ አስባለሁኝ፤ ምክንያቱም አብዩን አሜኑን እጅግ አቅርቤ አዬ ስለነበር ፈጣሪ መልዕክት ልኮልኛል ብዬ አምናለሁኝ።

ያ ሳይሳካ ሲቀርም እገዳ ማዕቀብ፤ ቅደመ ሁኔታ ተቀምጧል ብዬ ስለማስብ አሁን እዬሆነ ያለው ነገር ብዙም አልደነገጥበትም። እኛ ነው እየሠራን ያለነው እያለን ነው አቶ ጃዋር መሃመድ፤ ሌላው ቀርቶ የሱማሌ ችግር እኛው ነው የፈተናው፤ ኢትዮጵያ ያለው ስታዲዬም እኔን ደግፎ የሚወጣው ህዝብ ስለማይችለው ለዚህም ነው ከሰው ጋር መገናኘቱን ያቆምኩት እዬተባልን ነው፤ በሌላ በኩል ተበክሮ የሚነገረው እጅግ አስፈላጊ ሰው ስለሆነ ለህይወቱ ጠንቃቃ መሆን እንዳለበት ምክር እንደሚሰጠውም ገልፆልናል። 
  • ·       ውነቱ።  

ባለፈው ሳምንት ስለ ነበረው የጥቅምት ወታደራዊ ግርግር ገፊ ሃይል እንደ ነበረው ኩዴታ ነው ብዬም ነበር። ዛሬ በፓርላማው ሙሉው በዝርዝር ተደምጧል። በሌላ በኩል ሊቀ ሊቃውነቱ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ባቀረቡት ጠንከር ያለ ሃሳብ ተሰንቼ ደግሞ የተቆጣን፤ የተበሳጨን ሠራዊት በትህትና መመለስ አግባብነቱን ጥፌ ነበር። ስለሆነም ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የፈጹሙት አብነት እንዳለው በአጽህኖት ግልጬ፤ እንዲያውም ደርሶ ሰላላዬነው ነው እንጂ ሳያነጋግሯቸው ቢመለሷቸው መከራው ብዙ መሆኑን ጥፌው ነበር ዛሬ ይህው ተደምጧል። በቀደመው ጹሁፌ አንድን ነገር ቢያደርገቿው ኑሮስ እንዲያው አንዱ ተዳፍሮ በጥፊ ቢማታስ ኖሮ ብዬም ነበር። በርከት ያሉ ጹሑፎችን ነበር የጻፍኩት አንዱ ግን ይሕው እና
Ethiopia: ዛሬ የተለቀቀ የዕለቱ አስገራሚ ልዩ ዋና ዋና ዜናዎች

ሌላው ከመጋቢቱ 24.2010 ሹመት ማግስት ከነበረው ሹመት የዲሞክራሲ ግንባታ ሚር ሆነው በተሾሙት ላይ አብይ ሆይ! በሚለው አቤቱታዬን አቅርቤ ነበር ስለ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር ሰብዕና ለቦታው ብቁ አለመሆናቸው፤ በቅርቡ ደግሞ የኢህአዴግ የጽ/ቤት ሃላፊ መሆናቸውን ስሰማ ደግሞ ዴሞክራሲ የሚባለው ጉሮሮው እንደታነቀ በፓርቲውም በመንግስትም የወ/ሮዋ ያን ቦታ መያዙን ተቃውሜ ጥፌ ነበር።

የሳቸው ከዛ የዴሞክራሲ ግንባታ ቦታ መነሳታቸው መልካም ሲሆን ኢህአዴግም ራሱም በምርጫ ተወዳዳሪ ስለሆነ ከፖለቲካ ድርጅቶች ነጻ የሆነ አካል እንዲሆን ፕሮፓዛል አቅርቤ ነበር።

የሥርዓት ሥር ነቀል ለውጥ በሃሳብ ደረጃ ለማምጣት የአስተሳብ ለውጥ ማዕከል እንዲሆን በማሰብ ነበር ያን ጠንከር ያለ ጹሑፍ ያቀረብኩት። ያው ት/ሚር ከሁለት ተከፍሎ ለሁለት የብአዴን ውክል አካላት እንደ ተሰጠው ሁሉ ወ/ሮ ፈትለወርቅ በፓርቲም በመንግሥትም ጠቅለው ይዘውት የነበረውን ለአዴፓ ለሁለት ወኪሎቹ ተሰጥቷል። የኢህአዴግ የጽ/ቤት ሃላፊነት ብዙም ስለማይመለከተን ያን መተው ነው። 

በአሁኑ የወ/ሮ ፈትለወረቅ ገ/ እግዚአብሄር ሹመታቸው የተቃወምኩት ግን የተመረጡበት መስፈርት ዲሪቶ ስለሆነብኝ ነበር። የለውጥ አካል አለመሆናቸው ይታወቃል፤ ሰው ማዕካላቸው እንዳልሆነ ይታወቃል፤ እናት የሚለውን ሰብዕና በሚመለከት ንጥረ ነገሩ የተነነ ስለመሆኑ ይታወቃል። ሹመቱን  በዝምታ ከትሞ መስጠት ሲቻል ሰው የሚውቀውን ሃቅ አታውቁም መባሉ ብቻ እንጂ ሌላው ጠ/ሚሩ ሊቸገሩበት እኛ ምን አገባን? የትምህርቱን ጉዳይ በሚመለከት አባ ጉጉል ጋዜጠኛ አበበ ገላው የእሱ እዬራዊ ሃላፊነት ስለሆነ እሱ እንደሚሆን ያደርገዋል።
  • ·       ጥ ይባል ህመም ይባል እህ! ይባል አላውቀውም።

አብይ / አሜኑ ጠ/ሚር ሆኖ ዶር አንባቸውን ሲክድ ከማዬት በላይ ሌላ ምን ምጥ ይኖራልን? ግን አብዩ እኔ ያጠናሁት አብዩ ነውን?
እህ!
ስንት ጊዜ ይማጥ? ስንት ጊዜ እንሰንጠቅ? ስንት ጊዜስ መረጋጋጫ እንሂን? አቤት ያንት ያለህ የ እኔ ጌታ የህዝብህ እንባ ሆነ ከርታት!
ወደ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ስንመጣ አማራ አልተማነም። ቁልጭ ያለው ሃቅ ይህ ነው። ወይንም አቶ ጃዋር መሃምድ አልፈረሙበትም።

ዶር ለማ መገርሳን ኦዴፓ አለቅም ባይል እሳቸው እንዲይዙት ታስቦ ነበር ውጭ ጉዳያ ሚኒስተርነት ቦታውን። አሁን ግን አማራ አቅመ ቢስ ስለሆነ፤ ስለማይችለው፤ ታማኝም ስላለሆነ፤ ቀን ስላደረሰም ከ እንግዲህ አስፈላጊ ስላልሆነ፤ አቅምም ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቦታን ስለማይመጥን፤ ብቁ ስላልሆነ ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ እንደያዙት ቀጥለዋል። ይህ ህምም ይባል፤ ምጥ ይባል አይታወቅም?

በዚህ ወስጥ ትልቅ ነገር አለ። አመከንዮው አማራ ምን ያህል በርቀት እንደ አደጋ ምልክትነት እንደሚታይ። ይህን አመክንዮ ማንኛውም ሰው በግሉ አቅልሎ ይመለከተው ይሆናል። አይመሰላችሁ እጅግ ትልቅ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው። እስከ ተውልድ የሚዘልቅ፤ ከሆነ ለማ ለማ ካልሆነ ወርቅነህ ይቀትል? ? ?!!!!!!!

ይህ አመክንዮ ሌላ የአማራ ጽዮናዊነት የሚያስነሳ ነው። እጅግም አማራነት ፍልስፋናው እና አሳሩ ያልገባቸው የአማራ ሊሂቃን እና የአማራ ወዳጆች ይህን መሰሉን ጥልቅ ውቅያኖስ የመከራ ቀንበር በማስተዋል ሆነው ሊመረመሩት ይገባል። እኔ አማራ ባልሆንም ይህን ጉዳይ በመደዴ የምተዎው አይደለም። ግን ጉዞው ወደዬት ነው? ጋብቻውስ ከማን ጋር ነው?

አማራ ዜጋ ስለመሆኑ ፈተናዎቹን በዚህ ረቀቅ ባሉ ዘመናይ ውሳኔዎች ውስጥ የእኔ ብሎ መመርምር ይገባዋል። በግልቦሽ፤ በግጥግጦሽ፤ በቅልቅሎሽ እንዲህ ምጻዕተ አማራ ችግር የሚፈታ አይደለም። እራሱ  የአማራ ሊሂቃን በ አንድነት ሃይሉ ውስጥ እራሳቸው ባደራጁት ሳይቀር ሌሎች አዲስ ገቦች የሌላ ብሄረሰብ አባላት  የእነሱ የበላይ እንዲሆኑ ይፈቅዳሉ፤ ይህን ሰሞኑን አቶ ልደቱ አያሌው ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ዘለግ ያለ ታሪክ ቀምስ ውይይት አዳምጫለሁኝ።

ያን ጊዜ አቶ አባ ዱላ ገመዳ ፕ/ በዬነ ጵጥሮስ ሳይቀር ቅንጅትን በ አማራ ፈርጀውት እንደነበር ተገልጧል። አብሶ አቶ አባ ዱላ ገመዳ በ አንድ አፍ ሁለት ምላስ ሆነው ነው ያገኘሆዋቸው በ2010 ጊዜያዊ የጣና ኬኛ ጋብቻ መሰረታችን አማራ መሬት ነው አርማጭሆ፤ በለሳ እና ላሊበላ ለቀን አደረሱን ብለውን ሁሉ ነበር። ለነገሩ ምናቸው ይታመናል ይኸው እያዬን እኮ ነው እንደ ሽንብራ ቂጣ ሲገለባበጡ እነ አቶ በቀለ ገርባ።  

የሚገርመኝ አማራ ያደራጁትን፤ የደከሙበትን ከላይ ለሚመጣ አሳልፈው ስለሚሰጡበት ለምን ሲባሉ ድርጅቱ ነፍጠኛ ትምክህተኛ ስለሚባል እኛ ከፊት ከሆን አደራጅተን የሌላ ብሄረሰብ አባላት እንዲይዙት እንፈቅዳለን ይላሉ። ይህ እንግዲህ ሥነ - ልቦናቸው ተሰልቧል ማለት ነው።

ኢትዮጵያ አገር ከሆነች አማራ ለግርድና እና እቃ ለመለቅለቅ ብቻ የሚፈለግ ከሆነ አማራ በማስተዋል ሆኖ መንፈሱን አንድ በማድረግ የዜግነቱ አድራሻውን ለመፈለግ መቁረጥ ይኖርበታል።

አትፈለግም እዬተባለ ነው ያለው። እሱ ደግሞ ታስፈልጉኛላችሁ እያለ ነው። ይህን አጣምሮ ለማስኬድ አዎን ነፍጠኛ ነኝ! አዎን ትምክህተኛ ነኝ ብሎ ደፍሮ መውጣት ይኖርበታል - አማራ።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር———————–/ አሚር አማን ከአማራ ክልል የተወከሉ ናቸው። በእናታቸውም በአባታቸውም ትግሬ ናቸው። እሳቸውን ሥልጣናቸውን ያጸደቀው አካል ከለውጡ ፍርፋሪ መስዋዕትነት ያልከፈሉ ግለሰብ ሚኒስተርነታቸውን አቶ ንጉሱ ጥላሁን አጸድቀውላቸዋል።

በዛ በለውጥ ወጀብ ፍዳውን ከፍሎ ሌት እና ቀን የባተሉት አንዱ ቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው አስቀድመው ተሸኙ፤ ቀጣዮቹም መሰሉ ቢጠብቃቸውም አሁን ተንሳፋፊ ሆነዋል። ሦስቱም አይፈለጉም። ዶር ገዱ አንዳርጋቸው፤ ዶር አንባቸው መኮነን፤ አቶ ደመቀ መኮነን።

ሦስቱም በህይወት ሰለመቀጣላቸው እርግጠኛ የሚያደርግ ነገር ካለመኖሩ ጋር አሁን ባለው ገሃዳዊ ዓለምም ተንሳፋፊ ሆነዋል። ሳይወደዱ ነው ከቦታው የተቀመጡት ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ሆኑ አቶ ደመቀ መኮነን። ዶር አንባቸው መኮነን ለጊዜው ይፋዊ ተንሳፋፊ ሆነዋል።

ይህ ማለት የአማራ ይህልውና የማንነት ተጋድሎ ድምጽ አልባ ግድያ ነው ማለት ነው። የለውጥ ሐዋርያ የሚባሉት ቄሮ እና ቲም ለማ ብቻ እና ብቻ ይሆናሉ ማለት ነው። የዚህ ሁሉ የራስ ተሰማ ናደው የሴራ አደራጅ እና መሪ ደግሞ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው።

ይህን የአማራ ህዝብ ከልቡ ሆኖ ሊመረምረው የሚገባው ጉዳይ ነው።  ከኤርትራ መንግሥት ጋር ልዩ ግንኙነት እንዲኖራቸው የተፈቀደውም ከዶር አንባቸው መኮነን፤ ከዶር ገዱ አንዳርጋቸው በላይ ታማኙ አርሲኛው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው።
አሁን የሚደመጠው ዶር አንባቸው መኮነን ለህንፃ ጠበቂነት እንደታጩ ነው። መቼም አንቤ ይህን ከተቀበለ 10 ጊዜ መይሳውን ፈቅዶ እንደገደለው መቁጠር ይገባዋል። ቁርጥ ባለ ቋንቋ አልፈልግም ብሎ አቋሙን መግለጽ ይኖርበታል። ታማኝ እኮ አይደለም ለለማ ቲም አማራ። ለዚህም ነው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ቦታ የታጩት ዶር ለማ መገርሳ ሲቀሩ በነበረው እንዲቀጥል የተደረገው።

ይህን አቶ ደመቀ መኮነን ለማግለል ምህንድስናው እንዴት እንደ ተከናወነ እና እንዴትም ውሃ የበላው ቅል ሆኖ ዘጭ ብሎ እንደቀረ ያወቁት የራስ ተሰማ የሴራ ሌጋሲ አስቀጣዮች አሁን ሌላ የብወዛ ሴራ ይዘው ብቅ ብለዋል። ተስብሳቢው የተፈለገውን ነገር መፈጸም ካልተቻለ ረግጦ ስብሰባውን ይውጣ።

ጉባኤው በሙሉ ያጸደቃቸው መሪዎቹ መቀጠል ይኖርባቸዋል፤ ዶር አንባቸው መኮነን ከሆነ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በስተቀር ግን የአባቶቹን፤  የእናቶቹን ሌጋሲ አሻምን በተደሞ መፈጸም ይኖርበታል። ሦስቱም አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው እና ዶር አንባቸው መኮንን እጅግ አማራ ያስፈልጉታል። ለ አማራ ልቡ ህሊናው ትንፋሹ ናቸው።

ከሁሉ በላይ የፈጣሪ ሥራ ሊያደርግ የፈቀደውን ነገር ደግሞ በጸሎት ትጋት የሚታይ ይሆናል። የአሁን ዝምታ የአረጋ ጽንስ ስለሆነ ለውጡን በማገዝ ተግባር ብቻ ማተኮር ተፈልጓል። እንዲህ እዬመረረ ሲሄድ  እዮባዊነትን ሰንቅን በተደሞ እንከታተል አለን። እዬበዛ ሲሄድ ደግሞ የለዬለት ፍልሚያ ይቀጥላል።

ልዑል እግዚአብሄር ብዙ እናቶች ከልጀቻቸው ጋር አንዲገናኙ አደርጓል፤  የትንታጉ ዶር አንባቸው እናትም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ናት፤ የዶር ገዱ አንዳርጋቸው እናትም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ናት፤ የአቶ ደመቀ መኮነን እናትም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ናት። ቢያንስ የተከፋች እናት እንባ እዮርን ያንኳኳል። የቆሞስ እንጂነር ስመኘው፤ የቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ደምም የ አቤል ደም ነው ይጮኻል።
እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም … ልዑል እግዚአብሄር ያዳምጣል የተከፉትን። እኔም ከሦስቱ ጎን ነኝ። አንቤ አይዞህ! አብረንህ ነን! ከጎንህ ነን!

ቲም ለማ አማራን አትጫኑ! ፈጣሪን ፍሩ!
ቲም ለማ አማራን አትጨቁኑ! ኪዳን አትሰንጥቁ!
ቲም ለማ አማራን አታግልሉ! ፍቅርን አታደፍረሱ!ታማኝነትንም አትቆራርሱ!

ፎቶው የዶር አንባቸው መኮነን ከሳተናው ድህረ ገጽ የተወሰደ ነው።
የኔዎቹ ኑሩልኝ
መሸቢያ ጊዜ።




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።