አቶ ታገሰ ጫፎ አፈ ጉባኤ ሆኑ።

አቶ ታገሰ ጫፎ አፈ ጉባኤ ሆኑ።
„ሳሙኤልም ወደ አምልኮቱ መለሳቸው፤
የልቦናቸውም ዓይኖች በሩላቸው።“
መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፴፫ ቊጥር ፶፬

ከሥርጉተ©ሥላሴ 
18.102018 
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።




አቶ ታገሰ ጫፎ ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜልን ተክተው አሁን በሙሉ ድምጽ ካለ ሌላ እጬ ተዋዳዳሪ የኢትዮጵያ ፓርላማ እንደመረጣቸው አየሁኝ። በሰሞናቱ ስብሰባ ከፓርላማ ተሳታፊዎቹ በሚቀርበው ጥያቄ ላይም ማብራሪያ ሲሰጡ አዳምጬ ነበር። 

የሆነ ሆኖ ያው ሌላ እጩ የለም፤ ተቃውሞ የለም። ድምጸ ተዕቅቦ የለም። እንግዲህ አቶ ታዳሰ ጫፎ በዘመነ ወያኔ መራሹ ግንባር በኢህአዴግ ከሥር ጀምሮ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች አብሮ የኖሩ፤ በድርጅታዊ ህይወት የበቀሉ፤ በቀለም ትምህርትም የገፉ፤ ስለሆናቸው የህይወት ታሪካቸው ሲገለጥ ሰምቻለሁኝ ቀደም ባሉ ቃለ ምልልሶችም መጠነኛ መረጃ አለኝ። በሙሉ ዕድሜ ላይ ስለሚገኙ የተገባ ነው ባይ ነኝ። ታሪካቸውን ጠለቅ ብዬ አላውቀውም።

የገረመኝ የፓርላማው ጉዳይ ነው። የቀረበለትን ምግብ ሳያማርጥ መዋጥ ብቻ ነው የማህያው ውል። የተሻለው መስሎኝ ነበር ግን ያው ዴሞክራሲያዊ ማዕክላዊነት የሚባለው ፈሊጥ አሁን እዬሠራ ስለመሆኑ በዬስብሰባዎቹ እያስተዋልኩኝ ነው። 100/100 ህም?

መቼም በ2010 የተጀመረው የስብሰባ ዘመን ለ2011 አጋብቶበታል። መደበኛ ስብሰባዎችን ማለቴ ግን አይደለም።
የሆነ ሆኖ ምን ተሰማሽ በአቶ ታገሰ ጫፎ ብባል ጥሩ ስሜት ተሰምቶኛል። 

እኔ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የአቶ ጃዋር አህመድ፤ ብቻ ሳይሆን የኦህዴድም  ቀዳሚ ምርጫ ስለሆነ ያ ሪኮምንዴሽን እና ለሳቸው የሚሰጠው ነጥሎ ከአማራ ክልል የማቅረብ፤ የመንከባከብ እና ወኪላችን፤ ጭንቅላታችን ነው ብሎ ኦዴፓም የማለት ዝንባሌ አይበታለሁኝ።

ልዩ አትኩሮትም በተለዬ ሁኔታ የተሰጠበት፤ ልዕልናቸውን ለማስቀጠል ይህ ይከዋናል የሚል ዕድምታ ነበረኝ። ምክንያቱም ኤርትራ ለነበረው ለአማራ ዶሞክራሲ ታጣቂ ሃይል ከዶ/ር ገዱ አንዳርጋቸው፤ ከዶር አንባቸው መኮነን ተመራጭ እሳቸው ነበሩ። ይህ ፖለቲካዊ ስሌቱ ለፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂም ምቾት የሚሰጥ ወግ ነው።

አሁን የጠ/ ሚር ቢሮ አንደበት የመሆኑ ነገር ገና ቦታው አልተያዘም። የአቶ ጃዋር የቀደመው ሪኮምንዴሽኑ አቶ አዲሱ አረጋን እና አቶ ንጉሡ ጥላሁን ከዶር ለማ መገርሳ ጋር ወደፊት መምጣት አላባቸው የሚል ስለነበር ጠ/ ሚሩ ከኦዴፓ ስለሆነ አሁን የቤተ መንግሥት ልሳን አቶ ንጉሱ ጥላሁንን የሚቀጥለው የሥልጣን ቁልፍ ቸንከረኝ ቦታ ይሆናል ብዬ እስባለሁኝ።

ይህን ቦታ ለአቶ ንጉሡ ጥላሁን ቢሰጥ ለአማራ ተብሎ መሰላት ያለበት አይመስለኝም። አርሲያውያን ዘመን የመተካት ፈሊጥ ከመሆን አያልፍም።

በዛ ላይ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በመደዴ ሊተረጎሙ የሚችሉ አይደሉም ልክ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂን በመደዴ መተርጎም እንደማይቻለው ሁሉ። በዛ ላይ ድፈረታቸው እና ኮስታራነታቸው ደግሞ አለ። ባመኑበት ነገር ወደ ኋላ እና ወደ ፊት የሚሉ አይመስሉም። በራስ የመተማመን አቅማቸውን ብወደውም የራስ ተሰማ ናደው ሌጋሲ ጭንቅላት መሆናቸውን ግን አልወደውም። ለኢትዮጵያም የሚበጅ አይደለም። የራስ ተሰማ ናደው ፍልስፍና መነቀል ያለበት ሌጋሲ ነው። ጠንቅ ነው።

አቶ ንጉሱ ጥላሁን አንደበተ መንግሥት ከሆኑ ለአቶ ጃዋር መሃመድም የጠ/ ሚሩን ዕለታዊ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ቶፕ መረጃ  ከእጁ ለማስገባት ጥሩ መስመር ይከፈታል ብዬ አስባለሁኝ፤ እራሱ እንደተመደበበትም ይቆጠራል። ልክ ኦደፓ ኦቢኤን ለኦኤም ኤን እንደሰጠው አይነት። አቶ ንጉሱ ጃዋርውያን ናቸውና። 

እሳቸውም ትንሽ ተሸውደዋል። ጃዋርውያን ማለት ኦነጋውያን ብቻ ሊመስላቸው ይችላል። ጃዋርውያን ማለት ለእኔ ቦኮሃራማውያን ማለትም ነው።

ኦዴፓም በአማራ መሬት አለኝ የሚለው ፍጹም ታማኝ ሰው ቢኖሩ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ናቸው፤ ያው ሳጅን በረከት ስምዖን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ህሊና እንደ ነበሩት ሁሉ። እርግጥ ነው ያን አማራ መሬት ላይ ከሥሩ መንቀል ኦዴፓ ካልፈልገ ላያደረገው ቢችልም፤ የመፍንቀለ መንፈስ ማህበርተኞች ግን ሙሉውን መቆጣጠር የሚፈልጉት በራሳቸው መንፈስ ነው።

አብሶ የጠ/ ሚሩ ውሎ እና አዳርን ውስጡን ማግኘት የሚችል ታማኝ ሰው ቢኖሩ ለግራ ቀኙ ለኦዴፓም ይሁን ለጃዋርውያን አቶ ንጉሡ ጥላሁን ተመረጭ እና ተፈላጊም ናቸው። ኦነግውያንም ጥምር መረጃ ያገኛሉ። ውይ አንድ ነገር ዘንግቼ አቶ አርከበ ዕቁባም አሉ ለካ፤

ለእኔ ግን አቶ ካሳሁን ጎፌ ለዶር አብይ አህመድ መንፈስ ቅርብ ስለመሆናቸው ባለፈውም ጽፌው ነበር፤ ብቃታቸውም አቶ ካሳሁን ጎፌ ቢሆኑ የተሻለ ስሜት ይሰጠኛል። ምን ያህል ከኦነጋውያን ጋር የተለዬ አቋም አንዳላቸው የመንግሥት መግለጫውን ሲሰጡ ስሜታቸው ግብረ ምላሹ ከአዲስ አባባው የፖሊስ ኮሚሽነር በእጅጉ የተለዬ ነው።

አቅም እና ታማኝነት እንዲሁም ሰብዕና ከሆነ መለኪያው አቶ ካሳሁን ጎዴ በያዙት ቦታ ከፍ ብለውም ቢቀጥሉ ምርጫዬ ነው። ወይንም ሌላ አዲስ ሰው ሙያውን የተካነ የተማረ በኮታ ሳይሆን በክህሎት አብሶ ሰውን ማዕክል   ርህርህና ያለው ቢሆን ምርጫዬ ነው።

ከዚህም በላይ አቶ ካሳሁን ጎፌ እና ዶር አንባቸው መኮነን በጃውራውያን  ዘንድ የማይፈለጉ ስለሆነ እዬመራ ያለው የጃዋርውያን መንፈስ ከሆነ ብቻ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ወደዚህ ቦታ ይመጣሉ ብዬ አስባለሁኝ። ያ ለኦነግውያን አብሶ ለጃዋርውያን ሠርግ እና መልስ ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ።

የሆነ ሆኖ የአቶ ታገሰ ጫፎ አፈ ጉባኤነት ግን ለእኔ መንፈስ ጤነኛ ስሜት ፈጥሮልኛል። እሳቸውም ደስ ብሏቸው ፍልቅልቅ ብለው ተቀብለውታል። የጤና የውጤት ያድርግላቸውም እላለሁኝ። 

ከእንግዲህ በሚያደርጉት ተግባር መለካቱ ነው የሚበጀው። አጠፉም ሰሃም አክልም አለባቸው ቢባል እንኳን ስንቱ ተከሶ ስንቱ ተወቅሶ ይቻላል እና? 

አቅም ያለው አብዛኞቻችን የሚያስማማ የሚተካ የፖለቲካ ፓርቲስ ሲባልም በእጃችን ምን አለን?አብሶ ለአማራ ያዬነው እና የምናውቀው ነው። አማራ ይህን ያህል የተደራጀ ሴራ በግራ በቀኝ በቀዝቃዛው ጦርነት ላይ ሆኖ ወስጣችን ለመረዳት የፈቀደ እንኳን ይገባቸዋል ያለ እንኳን እኔ አላዬሁኝም። 

 ·     ለተጨማሪ መረጃ።
‹‹የተደበላለቀውን የአመራር ጎራ መለየት ያስፈልጋል››

ሰላምን ፈጣሪ ይስጠን! አሜን!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።