ትንሽ ስለጤናችን። #ግራዋ ለነስር ቀጥ እንደሚያደርግ ስለመሆኑ እኔም #ምስክር ነኝ።

 

#ትንሽ ስለጤናችን።
#ግራዋ ለነስር ቀጥ እንደሚያደርግ ስለመሆኑ እኔም #ምስክር ነኝ። ለሆድም ለመጋኛ ይጠቅማል። ቁርጠቴ ሲነሳ በጣታቸው ለክተው ቤተሰቦቼ ይግቱኝ ነበር። ታዳጊ ወጣት ሳለሁኝ። የስለት ልጅ ስለነበርኩ ጤናው የዚያን ያህል ነበረና።
 
የሆነ ሆኖ እኛ ደሃ ያልሆን ማን ደሃ ይሁነው። ወርቅ አፍሰን ወርቅ ለመሸመት ለመለመንም እንጀግናለን። ስንት ጥበብ በጥበብ የተቃኜች አገርን ፀጋ በረከት ተሰጥኦ፦ ማክበር ተስኖን እንሆ ከድህነት ወለል በታች ሥር። ቢያንስ የቀደምቶችን የጤና በረከቶች እስኪ አክብረን እንጠቀምባቸው። ከዚህ የባህል መዳህኒቶች ቅዱስ ነው የሚባሉት። የተፈጥሮ የሚባሉ ፈርማሲወች፤ ሃኪሞችም አሉ። ኢትዮጵያ እንዳለ አሁን አሁን ባደምጥም ይህን ያክል ዕውቅና ግን ያገኜ አይመስለኝም። 
 
ሥርጉትሻ 13/3/2025
 May be an image of angel's trumpet and text
ፌስቡክ ላይ ያገኜሁትን መረጃ እንሆ።
"ስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀትGeneral knowledge ethiohakim
reotpSnodst01808 2m11ah48f3,ffct9a2f8035021agc98rM3h9t342i3" ·
ግራዋ
«ሳይንሳዊ ስሙ ቨርኖኒያ አሚግዳኒና (Vernonia amygdalina) ይባላል፡፡ ለጽዳት፣ ለምግብነት፣ ለአጥር፣ ለእንስሳት መኖ፣ ለሰው እና ለእንስሳት መድኃኒት እና ለሌሎችም ብዙ ነገሮች ይጠቅማል፡፡ አገራችንን ጨምሮ በብዙ የአፍሪካ አገራት በተለያየ መጠሪያ ይታወቃል፡፡
ለምግብነት በምዕራቡ የምድር ወገበ አካባቢ ያሉ የአፍሪካ አገራት ቀንበጡን ግራዋ ለሾርባ ወይም ለወጥ ይጠቀሙታል፡፡
 
በምዕራብ ታንዛኒያ ውስጥ በታንጋኒካ ሐይቅ ምሥራቃዊ ክፍል ነዋሪ የሆኑት እነ ቶንግዌ (Tongwe) ለመድኃኒትነት በውሃ ዘፍዝፈው በቀዝቃዞው ለወባ፣ ለአንጀት ጥገኛ ተውሳክ፣ ለተቅማጥ እና ለሆድ ህመም ይጠቀሙታል፡፡ በብዙ የአፍሪካ ማህበረሰቦች ዘንድ የሚታዘዝ ማከሚያ የሆነው ለወባ ንደድ፣ ለብለሃርዝያ፣ ለአሜባ ተቅማጥ፣ ለብዙ የአንጀት ተውሳክ እና ለሆድ ህመም ነው፡፡
 
በናይጀሪያ ለጋ ዘንግ እንጨቱን በማኘክ ለጥርስ ጤና ይጠቀማሉ፡፡ በኡጋንዳ ግንዱ እንደ ሳሙና ያገለግላል፡፡ በጋና ከጠንካራ ይልቅ ቀንበጥ ቅጠሎቹ ለፀረ ስኳር በሽታ እና የሰውነትን መነፍረቅ ወይም መቁሰል እንዲሚያክም እውቅና ሰጥተውታል፡፡
 
2ኛ. አበቃቀል በሚያብብ ጊዜ ብን ያሉ ደቃቅ ዘሮች አሉት፡፡ እነዚህኑ መዝራት፣ ሲያድጉ በሚፈልጉት ቦታ መትከል፡፡ ብዙ ጊዜ ችግኙ ቀደም የተክሉ አበባ በተበተነበት ቦታ ሁሉ አድጎ ይገኛል፡፡ ይህን ችግኝ እዚያው መንከባከብ፣ ወይም ቦታ ቀይሮ መትከል፡፡ ዘንጉን ወደ አንድ አቅጣጫ ማጋደም፣ ወደ ላይ ብዙ ዘንጎች እንዲበቅሉ ዕድል ይፈጥራል፡፡
 
ሀ/ ለአፍንጫ ነስር በጣም ለጋ የግራዋ ቅጠል ማጠብ፣ በእጅ ማሸት እና መጭመቅ፣ በመሐረብ ማሰር እና መጭመቅ፡፡ ፊትን ታጥበው ወድያው ወደ ኋላ ጋደም ብሎ ወደ አፍንጫ ማንጠባጠብ፡፡ ትንሽ ተገጋግቶ መቆየት፡፡
 
ለ/ ለእሳት ቃጠሎ ለእሳት ቃጠሎ ቁስል በጣም ተፈላጊው የድግጣ ቅጠል ነው፡፡ ሆኖም ድግጣ በማይገኝበት ጊዜ ግራዋ ያገለግላል፡፡ ቅጠሉን አጥቦ ወቅጦ ጨምቆ ማዘጋጀት፡፡ በቁስሉ ላይ ነጠላ ጨርቅ ሸፍኖ የጭማቂውን ውኃ መጨመር ነው፡፡ ይህም እርጥብ ሆኖ እንዲቆይ ማድረግ፡፡ በየቀኑ እስከሚድን እንደዚሁ ማድረግ፡፡
 
ሐ/ ለእከክ እርጥቡን የግራዋ ቅጠል አጥቦ፣ ወቅጦ፣ በዚሁ እያሹ ማጠብ ነው፡፡ መ/ የግራዋ ጭማቂ መጠጣት ፈጽሞ ነፍሰጡር ሴቶች ግራዋ እንዳትጠጡ፡፡ ግራዋ ለመጠጥ ሲዘጋጅ ምሬት ለመቀነስ ወይም የመድኃኒት ብቃቱን ለመጨመር በሶቢላ ቅጠል አብሮ መጨመር ይቻላል፡፡
 
ለአሜባ እና ለጃርድያ አንድ እፍኝ የግራዋ ቀንበጥ ቅጠል ማጠብ፣ በውቀጥ፣ አንድ ብርጭቆ ውሃ ጨምሮ መጭመቅ እና ማጣራት፣ አንድ ማንኪያ ማር ጋር ጠዋት መጠጣት፡፡ በተከታታይ ለሶስት ቀናት ቢጠጣ የአሜባ እና ጃርድያን ከሆድ ውስጥ ያስወግዳል፡፡
ለቫይቫክስ የወባ ዓይነት አንድ እፍኝ የግራዋ ለጋ ቅጠል ማጠብ፣ መውቀጥ፣ አንድ ብርጭቆ ውሃ ጨምሮ መጭመቅ፣ አንድ ማንኪያ ማር አክሎ መጠጣት፡፡ ለአንድ ሳምንት መጠቀም የወባ በሽታውን ያስወግዳል፡፡
 
ለአንጀት ተስቦ (ታይፎይድ) አንድ እፍኝ የግራዋ ለጋ ቅጠል ማጠብ፣ መውቀጥ፣ አንድ ብርጭቆ ውሃ ጨምሮ መጭመቅ፣ አንድ ማንኪያ ማር አክሎ መጠጣት፡፡ ለአንድ ሳምንት መጠቀም ታይፎይዱ ከአንጀት እንዲወገድ ይረዳል፡፡ እንዳያገረሽም ያግዳል፡፡
 
ለሆድ ውስጥ ጥገኛ ትሎች ከላይ እንደ ተነገረው በተመሳሳይ ዘዴ መጠቀም፡፡ ለሶስት ቀን ቢጠጡት በቂ ነው፡፡ ለችኩንጉንያ በሽታ ቅጠሉን አጥቦ መውቀጥ፣ በፈላ ውሃ ላይ ጨምሮ በሻይ መልክ ይዘጋጃል፡፡ ካስፈለገ ማር አክሎ አንድ ብርጭቆ መጠጣት፡፡»

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?