#እንፈላለግ። #እንጠያዬቅ። አቶ ኦባንግ ሜቶ ምልክታችን የት ነው ያለው?

 

#እንፈላለግ#እንጠያዬቅ። አቶ ኦባንግ ሜቶ ምልክታችን የት ነው ያለው? 
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 

 
 
Obang Metho🇪🇹🇨🇦🇺🇸ሰውነኝ Humanity First (@ObangMetho) / X
 
 
ዛሬ ሲነጋ ደስ አለኝ። ውዱ ወዳጄን በህልሜ አቶ #ኦባንግ ሜቶን አዬሁት። ከስቷል። ዝነጣው ግን እንደ ዱሮው #ፕስ ሆኖ ነው ያዬሁት። ወጣት ሆኖ ነው የተመለከትኩት። ስልክ እዬተጠባበቀ ነበር። ስልክ ሲደወል ተነስቶ ወደ መናገሪያው ሲቀርብ ነቃሁኝ። 
 
ስልክ በሙሉ ሁኔታ ሳይ #መኖር ነው። እና ውስጤ ተጽናና። የሆነ #ማዕቀብ እንደተጣለበት ግን ይሰማኛል። ቢያንስ ፈጣሪዬ እስከዚህ ድረስ መረጃውን ከሰጠኝ ተመስገን ነው። አዘውትሬ አስበዋለሁኝ። ኢትዮጵያ ውስጡ ናት። የኢትዮጵያ ቀለሟ ነው። 
 
ቀጣይ ህይወቱንም አማኑኤል ይጠብቅልኝ አሜን። ሁልጊዜ ግን ፍርኃት አለብኝ። አቶ ኦባንግ ሜቶ #ምልክታችን ነው። የእኛነታችን #ማሾ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ደፍሮ "ጠቅላይ ሚኒስቲሬ" ያለ ፍፁም ቅን ሰው ነው። እኔ በጣም ነው የገረመኝ የቅንነቱ ንጽህና። ቃሉን ደፍሮ ሲናገረው። ለዛውም ጠሚር አብይ የኢንሳ መሥራች ስለመሆናቸው መረጃው ከነበራቸው ወገኖቹ አንዱ እንደ ነበር አቶ ኤርምያስ ለገሰ ሲናገር ሰምቻለሁኝ። 
 
መረጃው ስሰማ ደነገጥኩኝ። በተለይ ኦባንግሻ ኢትዮጵያ ውስጥ እዬኖረ፤ አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) እስር ቤት እያለ፤ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ኢትዮጵያ እያለ ስለነበር ብሎጌ ላይም እንተዛዘን፤ እንጠባበቅ ብዬ ጽፌያለሁኝ። ጥንቃቄ በእጅጉ ያስፈልግ ስለነበር። አንዳንድ አመክንዮወች ስሜታዊ ያደርጋሉ። አንዳንድ መሪወች #ስስ ሊሆኑ ይችላሉ። ስሜታቸው ሳይረጋጋ፤ ወይንም ዘግይተው እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ።
የሆነ ሆኖ የአቶ ኦባንግሻ የበዛ ጥግ ድረስ የተጓዘ መታመን #የአውሮፓ ህብረት ባለሙሉ #አንባሳደር ሊሆን የሚገባ ታላቅ ሰው ነበር። ኢትዮጵያም ታተርፍ ነበር። ኦባንግሻ ሰዋዊ እና ተፈጥሯዊነት ነው አጀንዳው። ለተወሰነ ጊዜ የተቋሙን ርዕሰ አንቀጽ በፀጋዬ ራዲዮ አቀርብም ነበር። ቲሙ የሚደንቅ ነበር። ለሴቶች ተሳትፎ የነበረው ክብር ደንበር አልነበረውም። 
 
ሲዊዝ ሲመጣ ደግሞ ኦባንግሻ ከተቀመጥኩበት ድረስ መጥቶ ምሳውን ሲመገብ እኔ ከነበርኩበት ቦታ ላይ ስለነበር እና ሥርጉተ ሥላሴ ማለት እኮ እኔ ነኝ አልኩት። እግዚአብሄር ነው ያገናኜን። ስብሰባ ሲኖር ስሄድ ለዘገባ እንጂ ከእንግዳው ጋር ለቀጣይ ግንኙነት ስላልሆነ በራሱ እግር ባይመጣ ሄጄ ካለበት አላነጋግረውም ነበር። ይህን መሰል አቋሜ ዘላለማዊ ነው። #ስለማያስፈልገኝ። ባይሆን እዛ በአካል ባንገናኝ ኦባንግሻ ጋር በጣም የቀደመ የስልክ ግንኙነት ስለነበረ ባላገኜው ኑሮ ከሲዊዝ ሲመለስ እደውልለት ነበር። በፈቃዱ እግዚአብሄር ግን በአካል አገናኜን። ቅብዓ ያለው። #ግርማ ሞገሱ ሙሉዑ። ሰው - ወዳጅ። ሰው - አቅራቢ። ተጠራጣሪ ያልሆነ ቅን ሰው ነው አቶ ኦባንግ ሜቶ።
 
ዛሬ #አንደበቱን መስማት እንኳን አልቻልኩም። ወደ አገር ከመግባቱ በፊት ነሐሴ ወር ላይ ስለ ተስፋችን የሆነው የለውጡ ጉዳይ #እንደተቀለበሰ በ2010 ላይ ነበር ያሳሰብኩት። እሱ ግን ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ተጓዘ። የእናት አገር ፍቅርም ናፍቆት #አቻኮለው። ጥሩ እዬሠራም ነበር። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ወሬው ጠፋ። ግን ኦባንግሻ የት ነው ያለው ዶር አብይ አህመድ? በምን ሁኔታ ይሆን የሚኖረው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ? አቶ ኦባንግ ሜቶ ኦኮ ዋርካ ነው።
 
ክብሮቼ የአገሬ ልጆች --- #እንፈላለግ
 
#እንጠያዬቅ። ፖለቲካ የሳሙና አረፋ ነውና የተፈጥሮ ጸጋችን ለፖለቲካ ዕይታ ተብሎ ማህበራዊ ግንኙነታችን ሊጓጉልም፤ ሊተጓጎልም አይገባም ብሄራዊ ጥሪ ነው የባተሌዋ የሥርጉትሻ።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። 
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
13/03/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?