በሰጨኝ ለጠቅላይ ሚ/ር ፈጽሞ አያምርም።

በሰጨኝ ለጠቅላይ ሚ/ር
ፈጽሞ አያምርም።
„እሳት በረድ ረሃብ ቸነፈር ይህ ሁሉ ሊበቀሉበት ተፈጠረ“
መጽሐፈ ሲራክ ፴፱ ቁጥር ፳፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute© Selassie
 24.03.2019
 ከእመ ዝምታ ከሲዊዝ።

/ ዶክተር አብይ አህመድ በአዲስ ወግ ላይ ኢትዮጵያን በተመለከተ ያደረጉት ንግግር

ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት አንድ ንግግር ነበራቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ። አሁን አሁን ሌላ ሰው ሌላ ሰው እዬመሰሉኝ ነው። ምን ነካቸው የምለው እኔ ብቻ አልሆንም ብዬ አስባለሁኝ። ከእኛም አልፎ የመንፈስ ወርቅ ለህሊናቸው ያነጠፈላቸው ሉላዊው ዓለምም በትዝብት ሳይመለከታቸው አይቀርም ብዬ አስባለሁኝ። ለነገሩ አንድ ጠንከር ያለ ጥራዝም ወጥቷለኝ።

እሳቸውን ለመወቅስ ለመተቸት ማሰቡ በራሱ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ቢያውቁት ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር። ዳሩ በእኛ ውስጥ ስለሌሉ ጭንቁና ችግሩን የተረዱት አይመስልም። እጅግ ነው የሚቸግረን አንድ ብሄራዊ መሪ ለመተቸት። በሁለት ምክንያት።

አንደኛው ባህላችን ሲሆን፤ አብሶ እንደ እኔ ወግ አጥባቂ ክፍለ ሀገር ላደገ ሰው ፈተና ነው። ሁለተኛው ደግሞ እኔ በሳቸው አክቲቢዝም ላይ ተግቻለሁኝ። እንዲያውም እንደ እኔ በሳቸው ላይ በ አዎኢንታዊነት የጻፈም አለ ብዬ አላስብም። እኔ ብቻ አይደለሁም የሳተናው ድህረ ገጽም እጅግ ትጋት ነበረው።

በጣም ቅን በሆነ የተስፋ ጥበቃ መልካሙን ሁሉ ተመኝተናል። ተቀናቃኝ ሃሳቦችን ሞግተናል። ቅራኔ ውስጥ ገብተናል። ውጤቱ መልካም ሲሆን ደስታችን አብረን አሳልፈናል። ችግር እዬታዬ ብዙ አደናጋሪ ነገሮች እያሉ እንኳን እሳቸውን ወግነን ብዙ ታግለናል።

የደገፈናቸው ግን ለኦነግ ዓላማ ስኬት አለነበረም። በፍጹም። ቅንጥብጣቢ የኦነግ መንፈስ አለበት ብለን አስበን ቢሆን ኑሮ እንዲህ መትጋት አይኖርብንም ነበር። እኔ በግሌ ቀደም ብዬ እከታታል ስለነበር በዛ ልክ ጠ/ሚር አብይን አገኛቸዋለሁ የሚል ሙሉ ዕምነት ነበረኝ። እድሉን ቢያገኙ ቢያንስ የሴራን ፓለቲካ ይንዱታል የሚል ሙሉ ተስፋ ነበረኝ።

የሆነው ግን ያ አይደለም የማዬው። ይህም ሆኖ መልካሞችን እያበረታትን ደካሞችን እንዲስተካከሉ የበኩላችን ጥረት አድርገናል። እሳቸውንም በሚመለከት ድክመት በምንላቸው ላይ አትኩሮት ያደርጉበት ዘንድ አሳስበናል። ጠ/ሚር አብይ አህመድ የሚሰሙት፤ የሚያዳምጡት ራሳቸውን ብቻ ነው። ከዚህ ሌላ የመወሰን አቅም ስስ ነው። 

አቋምን በሚመለከት በዬለም ደረጃ ነው ያለው። ይህን ራሳቸውን በምልሰት ቢገመግሙት በአስቸኳይ ጊዜ ውሳኔ ላይ እንኳን አልተገኙም ነበር። አንድ የአገር መሪ አቋም ከሌለው እጅግ ከባድ ነው። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ወሳኝ አገር ናት። ለመካከለኛው አፍሪካም ልብ ናት። ለጠቅላላው አፍሪካም ህሊና ናት። ይህን ሃላፊነት ለመወጣት ደግሞ አቋም ወሳኝ ጉዳይ ነው። የመወሰን አቅም ሙሉነትም ወሳኝ ነው።

ባለፈው አንድ ዓመት አቋምን በሚጠይቁ አገራዊ ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ የሚታዬው ልል ነው። በዚህ ልል ሁኔታ ደግሞ ባለቤት የሌላቸው ማህበረሰቦች ተፈጥረዋል። ባለቤት የሌላቸው የህዝብ ጥያቄዎችም አሉ። 

ይህም ሆኖ ባለቤት ለሌላቸው ማህበረሰቦች ባለቤት የሚሆን ዜጋ ሲኖር ሊበረታታ ይገባል። ምክንያቱም ጠ/ሚሩ አቅም እያነሳቸው ስለሆነ። የጎደለን የሚሞላ ጥብቅ የምር ወዳጅ ብቻ ነው። እያዬ የማይሳለቅ ማለት ነው።

አዲስ አባባን በሚመለከት ከሌሎች ክልሎች በተለዬ ሁኔታ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ህዝቡን፤ የአገር ሽማግሌዎችን አላወያዩም። ያ ትልቅ ግድፈት ነው። መጀመሪያ መቀመጫን ማደላደል ይጠይቃል። የሁሉም የፖለቲካ ማዕከል አዲስ አባባ ነው። አዲስ አባባ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነው። እንደ እንጀራ ልጅ ሊገፋ፤ እንደ ባይታዋር ሊታይ አይገባም። ድሬድዋም የሆነው እንዲሁ ነው። በዚህ ውስጥ የተመሰጠረ አጀንዳ እንደነበረበት ልብ አለን።  

አንድ ኢትዮጵያ ማንፌስቶዬ ናት ብሎ ለተነሳ ሙሴ፤ ነብይ፤ ባለቅኔ፤ ጥበበኛ፤ ዳዊት፤ ስጦታ፤ ደግ የዓለሙ ሥም ሁሉ የተሰጠው መሪ ብሄር አልቦሿ ርዕሰ መዲና አብነት፤ አርያ፤ ተምሳሌት አድርጎ የእኛነት ማዕከል ማድረግ ይገባ ነበር። ሁሉን በእኩል ማዬት። ይህን ስል በነገረ አማራ ላይ ያላቸው ምልከታ ጠናና ስለነበር ከውጥኑ ነበር የሞገትኳቸው፤ ግን መከራዋ ለጠና አገር አቻችሎ መሄድ በሚል ትጋቴ ላይ ማዕቀብ አልጣልኩበትም ነበር። ወቀሳውም ቢኖር ... 

ኢትዮጵያ ስትኖር ነው ኦሮምያ የምትኖረው። ኢትዮጵያ ስትኖር ነው ኦዴፓ የሚኖረው። ኢትዮጵያ ስትኖር ነው ጠ/ሚር የሚኖረው። ኢትዮጵያ ስትኖር ነው ክብር የሚኖረው። ኢትዮጵያ ባትኖር እኮ ዶር ቴወድሮስ አድሃኖም የዓለሙ ጤና ጥበቃ ሚ/ር አይሆኑም ነበር።

ማስተዋል ይጋባል። ያ ሁሉ ክብር፤ ያ ሁሉ ሞገስ፤ ያ ሁሉ ልዕለና፤ ያ ሁሉ አጀብ ኢትዮጵያ ማንፌሰቶዬ ናት ስላሉ ብቻ ነው። ሌላው ገመና ይዘርዘር ቢባል እንደ ግንባሩ አባልነተቸው ሆን እንደ ኢትዮጵያ ዜግነታቸው ተጠያቂ የሚያደርጋቸው ነገር የለም፤ አልነበረም ቢባል እንኳን ተወቃሽ የሚያደርጋቸው ነገር ጠፍቶ አልነበረም። 

ግን ያን ያስታወሰ የለም። ሁሉ ነገር የቆጥ የበረከት ይሁን ተብሎ እርግፍ ተደርጎ ቃላቸው ታምኖ፤ እሳቸው ታምነው፤ መንገዳቸው ታምኖ በእልዕልታ አቀባበል ተደረገላቸው።

እኔ ለሳቸው የቤት ሥራ እምሰጠው ሲሾሙ ያደረጉትን ንግግር እንደገና እንዲያዳምጡት ነው። ያ አቅም፤ ያ የእርግጠኝነት ድምጽ፤ ያ የተሰፋ ድምጽ፤ ያ  የአቃፊ ድምጽ፤ ያ የምህረት እና የቸርነት ድምጽ፤ ያ የፍቅር ድምጽ አሁን አለ ወይ ብለው እስኪ ይሰቡት። ብናኝ ብጣቂ ንክኪ የለውም አሁን እያደረጉ ያሉት ነገር። ተቀናቃኞቻችው ወደ ሚፈለጉት ሸጎሬ ሰተት ብለው ነው የገቡላቸው። 

ህሊና አላቸው ብዬ ስለማስብ እሳቸው በራሳቸው ውስጥ እየጠፉ መሆናቸውም አይጠፋቸውም። የቅደም ተከተሉ ሂደት እስከ ሀምሌ ድረስ መልካም ነበር። ከዛ ወደ መሬት ተግባራዊ ሥራ መለወጥ ነበረበት። ዓመት ሙሉ በስብሰባ ይከብዳል። ትጋቱ ለግልጹ ዓላማ እና ፍላጎት ቢሆን ምርቃቱ በጸደቀ፤ በጸናም ነበር። 

የሆነ ሆኖ ልቤ ያለኝን ማለት እሻለሁኝ። አንድ የነፃነት አርበኛ አንድ እሰከ ልጁ፤ እስከ ባለቤቱ የካቴና እራት የነበረ ወንድም ከእስር ሲፈታ እንኳን እግዚእብሄር አስፈታህ ብለው እንኳን ለሌሎች የሰጡትን አትኩሮት ቆራጣ አልሰጡትም።

ህፃን ናፍቆት እስክንድር እኮ አብሮ ታስሯል። ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እኮ የበኽር ልጇን የእርግዝና ወቅት በእስር ቤት ነው ያሳለፈችው። አራስነቷን እንዲሁም።


ይህን ስለምን አንደ ሰው አያስቡትም። ለዚህ ነፃነት እኮ እነሱ በሰላም ልጀቻቸውን ወልደው ሲያሳድጉ ይህ ጀግና እስከ ልጁ፤ እሰከ የመጀመሪያ ባለቤቱ ድረስ በእስር ቤት ነው ያሳለፈው። ልጁን እኮ ሳያውቀው ጠረኑን ቀርቦ ሳያዳምጠው ነው የተወለደው። ሲያድግም እንደዛው።

አንዲት ነፍሰጡር ሴት ስንት ነገር ያስፈልጋታል። ያን ሁሉ እስር ቤት ነው ያለፈው። አንዲት አራስ ስንት ነገር ያስፈልጋታል። ያም በእስር ቤት ነው የተጠናቀቀው። ግን ህሊና ማለት እንዴት ይገለጥ? በምንስ ይለካ?

ሰው እንሁን እንጂ። አሁን እሱን የመታገል ፕሮጀክት እንዲህ ሊኖራቸው ይገባልን ጠ/ሚር አብይ አህመድ? የመጋቢት አንዱ ታምራት እኮ ከዚህ እንዲማሩ ከእዮር የተላከ ነበር። እንደ አንድ ተራ ጎረምሳ እንተያያለን? ምነው የጉለሌለው ንጉሥ ያን ያህል ጦርነት ሲያውጅ ይህን ስለምን አልተናገሩትም? 18 ባንክ ሲዘረፍ ስለምን አልተናገሩትም? 

በሻሸመኔ ላይ ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ ሲሰቃል ስለምን ዝምታን መሩጡ? የቡራዩ ሰቆቃ፤  የአዲስ አበባ ሰቆቃ በማን እንደተፈጸም ጠንቅቀው ያውቃሉ ስለምን ስለዚህ ትንፍሽ አላሉም? ማን ተፈሪ ማን ተዋራጅ ተወቃሽ ሆኖ?

ለምን የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ እንዲህ ከነከናቸው? ስለምን እንዲህ አንገበገባቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድን? ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ኢትዮጵያዊ አይደለምን? ዜጋ አይደለምን? የሲሶ ዜግነት ነውን ያለውን?

የሳቸው ድርጀት ስንት መግለጫ ነው የሚያወጣው ህዝብን ለመሰቃቅ፤ ህዝብን በሰቆቃ በስሥነ - ልቦና ጭንቀት በሽተኛ ለማድረግ? የሳቸው ምክትል ሊቀመንበር እኔያ ታቦት ይቀረጽላቸው የምናላቸው ዶር ለማ መገርሳ ዴሞግራፊን አቅደው ስለመከወናቸው ቁጭ ብለው አድመጣዋል ምነው ይህ አላበሳጫቸውም? ድርጅታቸው ታላቅ አገር ኢትዮጵያን ርዕሰ መዲና አልባ ለማድረግ እዬሠራ ስለመሆኑ ሲነገር ስለምን ዘራፍ አላሉም እንደ አባት አደሩ?

አቶ በቀለ ገርባ ዓለምን የሚንድ ፍልስፍና ሲያመጡ ምነው አልቆጫቸው? አቶ ጃዋር መሃመድ ያን ያህል ሲፎገላ ያን ያህል ሲፏልል ስለምን አልጎረበጣቸው?

የአዲስ አባባ ህዝብ አደባባይ ላይ ሲረሽን ስለምን አልከነከናቸውም? የአዲስ አባባ ወጣቶች ጦላይ ሲላኩ ስለምን አልጎረበጣቸውም? ሰው መሆን መሪ መሆን ማለት ይህን ሚዛናዊ ማድረግ ማለት ነው።

እንደ ሰው ማሰብ ያቸሉበት አይመስለኝም ወይንም ለግመዋል። ሰው ተገድሎ የሚቀጠልበት አገር ላይ ተቀምጠው በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ላለ ብዕር ብቻ ለያዝ ጋዜጠኛ ያን ያህል ሥሙን ለማጠልሽት በአደባባይ ለመክስስ ያውም የሳቸው አንደበት እንዴት ቻለ? ለዛውም ብስጭታቸውን መቆጣጠር እስኪሳናቸው ድረስ? ለምን ተክለ ሰውነታቸውን ያበላሹታል?  ለሚያልፍ ቀን ... ለድንኳን ኑሮ?

ለምን ጠርተው አያወያዩትም? ዜጋ እኮ ነው ለዛውም ለነፃነት ተጋድሎ ግንባር ቀደሙን ፍልሚያ ያደረገ። የማይመጥናቸውን ነገር እያደረጉ ዶር አብይ አህመድ፤ ባልተገባ ሁኔታ ራሳቸውን ወስደው እያላተሙ፤ ደፍረን ወጥተን የሞገትናላቸውን ዜጎች ሁሉ እያሸማቀቁን ነው። አሁን የአዲስ አበባ ህዝብ ከመስከረም 5 ቀን ጀምሮ ኑሮውን እዬኖረ ነውን?

በሥነ - ልቦናው እዬተቀጠቀጠ፤ በሰቀቀን ውስጥ እኮ ነው የሚኖረው። እሳቸው የአገር መሪ ሆነው ሳላ ነጋ መሼ ስለሁለት ክልል ብቻ ነው የሚተርኩት። ትግራይ ኦሮምያ … ይገርማል።

መሪነት እኮ በማለት ሳይሆን በመሆን ውስጥ ያለ ቁምነገር ነው። ሌላው ሚዛን እንዲሆን የሚጠዬቅ ከሆነ ሚዛናዊ አመራር በመስጠትም መሆን ይኖርበታል። የለም። ይህ መርዶ ለእርስዎ አይታዬዎት ይሆናል።

እኛ ግን መርዶውን እዬሰማን፤ እያወቀን ጥቁር ውስጣችን ለብሷል። እኔ መሽቶ እስኪነጋ ቀኑንም ሌሊቱንም አላምነውም። የሆነ አንዳች ነገር የሚፈጠር ይመስለኛል። በዬለችም ውስጥ ያላች አገር እኮ ነው እዬመሩ ያሉት። የቀደመው ስንጥቅ መኖር እንኳን የለም እንኳንስ ሚሊዮን ተስፋ ያደረገው ያ ቅን መንፈስ።

ጠ/ሚር ቢሮ፤ ውጭ ጉዳይ፤ ገቢዎች ሚ/ር፤ አዬር መንገድ፤ ሚዲያ፤ መከላከያ፤ አዬር ሃይል ምን እዬሆነ ነው? አይታወቀዎትንም? ህግም ሞራልም አመክንዮም ተደሞ እዬተጣሰ እኮ ነው። አድሎ ማግለል የእኔ ብቻ እኮ ነው ህጋዊ ሆኖ ቦታውን ተክቶት ያለው፤

… ትናንት መልካም ነገሮች እኮ ለዘለቄታ መኖር ዋስትና ካልሰጡት ቅብ ነው ተገኜ የሚባለው ለውጥ፤ እሰረኛ መፈታቱ ስናስብ አሁን ደግሞ አስራለሁ አዲስ ጫን ያለ ነገር እዬተደመጠ ነው … ዴሞክራሲ እንደፈረደበት ታስሮ ይቀመጥ፤ እሱ ለቅንጦች ይሁን፤ መኖር ላልተፈቀደለት ዋስትና ለለው ሚሊዮን ነፍስ እንደ ገና የመከራ ነጋሪት፤ ህም።

ሺ ሚሊዮን ጊዜ እንዲህ ሆኖ፤ ያ ተፈጽሞ ዛሬን ማስገኝት ካልቻለ፤ ነገን በተስፋ መቀበል ካልቻለ ፋይዳ የለሽ ነው። ዛሬም ህይወት አለና … ህዝብ በወል በተደሞ ጌዲዮ ላይ ሲያለቅስ እኮ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። እነሱም እኮ ዜጎች ናቸው

ቀድሞ ነገር እውነቱን ብናገር እኔ ጠ/ሚር አብይ አህመድን ልንታገለዎት አልጀመርነውም። ገና እያስተማምነዎት ነው ያለነው። ትግሉን ስንጀምረው እኮ እጅግ ይመራል። ምክንያቱም አንደኛው ተስፋ ያደረግን ብቻ ሳይሆን ልባችን ሞልተን የመሰከርንለዎት ስለሆነ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኢትዮጵያ ፖሊሲያዊ ባርባርያን እዬሆነ ስለሆነ። 

ኢትዮጵያ ባልተጻፈም በተጻፈም ህግ ነበር የምትተዳደረው። ዛሬ ሁሉም የለም። መንግሥት ስለሌ በደቦ ህግ ነው አገር እዬተመራች ያለችው። እንደ ቸርነቱ ነው መሽቶም የሚነጋው።

በዬትኛው ዓለም ነው ጉዳት ደርሶ እረዳለሁ ለሚል ግለሰብ፤ ድርጅት ክልከላ የሚፈጸመው? በቡራዩም፤ በጌዲዮንም የታዬው ይኸው ነው። በዬትኛው አገር ነው ፍቅር ተገድቦ የጋብቻ ዕቀባ የሚጣለው?

በአቶ በቀለ ገርባ ቀጣይ የመከራ ፓሊሲ ፍልስፍና ሚሊዮኖች መረዝ እዬተጋቱ ነው ይህን ፓርቲዎት ኦዴፓ ምን ይለዋል? በዬትኛው አገር ነው በቋንቋ የማይናገር ሰብዕ ተገሎ፤ ተረግጦ፤ ተገድሎ ቦታውን እንዲለቅ የሚደረገው? ቡራዩ ላይ ይህ ሆኗል በጋሞ ወገኖቻችን፤ ጌዲኦ ላይ ሆኗል። ከዚህ ይጀምሩ … መሪነት ከራስ መጀመር ነው። አይደለም ትክክል ብሎ ለመቅጣት ለመናገር እንኳን ድፍረት የለም።

የተባበሩት መንግሥታት፤ የአውሮፓ ህብረት፤ የአፍሪካ ህብረት፤ ፓን አፍሪካ፤ አምንሲት ኢንተርናሽናል፤ ቀይ መስቀል ወዘተ የደራጁበት መርህ፤ ሃይማኖት የተዋቀረበት ዶግማ እኮ በአቶ በቀለ ገርባ ፋሽስታዊ ፖሊስ እዬተጣስ ነው። ሰው እና ተፈጥሮን እንዲጠፉ አውጀውበታል። መጠለያው ደግሞ የእኛ ሰዎች መሪ ሆነዋል ነው። እሳቸውን መሰል ሰዎችን ህግ አይጠይቃቸውም እነዚህ ፋሽታዊ ሰብዕናዎች። የፖለቲካ ድርጅታቸው አይታገድም፤ ሚዲያቸው አይከሰሰም አይቀጣም።

የራሰን ሁነኛ መጠለያ ቤት ነውረኝነትን ተሸክሞ ጨዋን ማዋረድ እና ማስገለል አብሶ ከጠ/ሚር አብይ አህመድ የሚጠበቅ አይደለም። ችግሩን ህዝብ አልፈጠረውም። ችግሩን የፈጠረው ሁለት ምክንያት ነው። አንደኛው ድብቅ አጀንዳ። ሁለተኛው ኦቨር ኮንፊደንስ ያመጣው ጣጣ ነው። አቅም ሳይኖር፤ ዝግጅትም ሳይኖር ካለምንም መሰናዶ ሲናቆር የኖረውን የፓለቲካ ድርጀት ናልኝ አላችሁ። ከነጓዙ መጣ። መሰናዶ አልነበረም፤ ይህን ቅጥ አስይዞ የሚመራ መዋቅር የለም። 

አሁን በሁሉም አቅጣጫ ወተቴ እንደያዘው ገላ ሲፈነዳዳ ያን ሥርዓት ባለው ሁኔታ አደራጅቶ ወጥ የሆነ አመራር ለመስጠት አቅም ጠፋ። ምክንያቱም ሱናሜ ነው የነበረው። የሚገርመው ያሉት ፓርቲዎች አልበቃ ብሎ አሁንም አዳዲስ ፓርቲዎች እዬተፈጠሩ ነው።

ብቻ ካለ አቅም የተለጠጠ ቸርነት ልበለው ምን ያን መጥኖ ያልተሰራ ልቅ ነገር መርቶ ከግብ ለማድረስ አሁን ማጣፊያው አጠረ። ሌላው የበደለም የተበደለም አብሮ የሚኖርበትን ሥርአት በእኛ ይጀመራል „በመደመር ፍልስፍና“ ተባለ የነበረው የሸር የተደራጀ ኔት ወርክ እንዳለ ቀጠለ ምን እና ምን ይገናኝ …

እንዲህ ዓይነት መንገድ በቅጡ መደራጀትን ይጠይቃል። እራሱ ከግንባሩ አባላት ጋር እንኳን ምክክር አልተደረገም። እንደ ድርጅት። ወርክሾፖች፤ ሰሚናሮች፤ ተከታታይ የህሊና ዕጠባዎች አልተካሄደም። የጅምላ ጉዞ መሪ እና ተመሪ ጠፍቶ እንዲህ እና እንዲያ ሆነ። ይህም ሆኖ ችግር የለም አቅም አለኝ እኔ እራሴ አሻግራችሁአለሁ፤ እመኑኝ ያለ መንፈስ በትንሹም በትልቁም ተበሳጭቶ አይችለውም። ለነገሩ እኔ ወንበሩ ባዶ ሆኖ በህልሜ ያዬሁት ሐምሌ ወር ላይ ነበር።

መቆሚያ ብትን አፈር እኮ የለም። ዕለት እለት አስፈሪ ነገሮች ናቸው ያሉት። ይህን ደግሞ በብስጭት ሳይሆን በማረጋጋት ነው ሊሆን የሚችለው። የቀረች እንጥፍጣፊ እምታስቀጥል ሁኔታ ከኖረች።  

ሌላው ከዚህም የከፉ የህዝብ አመፆችም መጠበቅ ነው። በሩ ቧ አለ፤ ፊትም ፏ አለ። ሁሉም ተቀላቀለ። ማናቸውም ዓይነት መንፈስ እንዳሻህ ተባለ። በዚህ ሂደት ውስጥ፤ በዚህ በሞቀ የህዝብ ድጋፍ ውስጥ የኦነግን ሙሉ ዓላማ ተረክቤ የራሴን ድርጅት ተልዕኮ ብቻ አስፈጽማለሁ ለሚለውም ቢሆን አሁን በችሎት ነው የተያዘው። እሱ የፈነዳ ዕለት ደግሞ መከራ ነው። ሚዛኑን ያልጠበቀው የጠ/ሚር ቢሮ የወደፊቱ ግማድም ቻለኝ የሚለው ይህን መሰሉ ጉዳይ ነው ... 

አቅሙ ከጠፋ ደግሞ በተከፈተው በር እንደሚሆን አድርጎ የባለ አደራ መንግሥት ፈጥሮ እንደሚሆን ማድረግ ነው። አቅም አለኝ ከሆነ ደግሞ ከተዛባው አስተሳሰብም፤ ተደብቆ ከተያዘው አጀንዳም፤ ከአፈናቃይ መንገድም እራስን ገርቶ ህዝብን በአደባባይ ይቅርታ ጠይቆ ወደ ትክክለኛው መንገድ መምጣት ነው

ተራፊ የለም ይህ ሥርዓት ቢናድ። ሰው ይመስለዋል አትራፊ ያለ … ጦርነት ህግ የለውም። ሰው ተቋስሏል። ስለዚህ ከብስጭት የራቁ እርጋታና ስክነትን የሚጠይቁ ሂደቶችን መከተል ይገባል። መፍትሄ እኔ ብቻ ነኝ ከእንግዲህ የሚያስኬድ አይሆንምእውነቱ አቅም የለም። አቅሙ ራሱ ተሸርሽርሽሮ ሰሎ መንገዱን ስቷል። ተቀባይነቱም በዚህም በዚያም ተብሎ አፈር ድሜ ግጧል። "ሳይቸግር ጤፍ ብድር" ሆና እንዲህ ሆነ።

ኦነግ ሃሳብ ቢኖረው እኮ እንዲህ የኩሬ ውሃ ሆኖ እዛው አይዳክርም ነበር። አሁን አቅም አለኝ ለሚለውም ተፈቅዶለት ነው። ስንቅና ትጥቁ ተፈቅዶለት። መሃል ከተማ ተቀምጦ ጦርነት እያወጀ። በጀት እንዳይቸግረው ያሻውን ያህል ባንክ እዬዘረፈ፤ በዚህ የኢህድግ ላይ ጫና ተፈጥሮ በድርድር ወደ ማህል ለማስመጣት ነበር ትልሙ፤ ኢትዮጵያዊነት በመሆን ውስጥ የሚበላ ፍሬ ነው። ረቂቅ ነው አይታይም አይጨበጥም።  

እስኪ ከፈቀዱ ጠ/ሚር አብይ አህመድ እሳቸው በተመሰገኑበት ዘመን የመንግሥት ሚዲያ ዩቱብ ላይ ያለውን ተመልካች እና ዕይታ እስኪ ይመልከቱት አሁን ላይ ያለውን? አስተያዬቱንም። ሰው መንፈሱ የለም። ፍርሃት ለኖረበት ህዝብ እንደገና ፍርሃት እያወጁ ድጋፍን ተስፋ ማግስት እንዴት ይታሰባል? መስከን ይጠይቃል። ስህተትን መቀበል ይጠይቃል።

ህግ እዬጣሱ ህግ ይከበር አይሆንም አያስኬድምም። ኢንጂነር ታከለ ኡማ ምርጫ ትክክል አይደለም። ከፖለቲካ ድርጅት፤ ከከተመ የምርጫ ህግ ውጭ ነው የተፈጸመው። ይህን ለእኔ መንገር ወይንም ማስረዳት አይቻልም። እኔ አደራጅ ነኝ እና። እኒህ ሰው የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል እንኳን አይደሉም። ኗሪም አልነበሩም። ጭነቱ ተጭኖ። ጭነቱ ከብዶኛል ከዚህ በላይ አልሸከምም ሲባል ደግሞ ማን አባቱ የተገባ አይደለም። ለዛውም እንተያያለን?

አንድ ጠ/ሚር ጠ/ሚር ሆኖ የከተማም ከንቲባ ሆኖም አይሆንም። እኔ አብራችሁ እንደምትሠሩ ስለሚገባኝ ነው። የገቢዎች፤ የሰላም ሚ/ር ጋርም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚከውን „ባናርስ እናጣምድለን“ ይላል የጎንደር ሰው።

ሁሉ ቦታ ተሁኖ አይዘለቅም። ለዚህ ነው አሁን ለያዥም ለገራዥም የሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ኢትዮጵያ የምትገኘው። አንድ የውጭ ጠላት ቢመጣ በሩ ሁሉ ክፍት ነው።
ሻሸመኔ ባሌ አርሲ ትግራይ አዋሳ ወለጋ ላይ ጠ/ሚሩ እራሱ ሄደው ህዝብ ሰብስበው ማነጋገር አይችሉም። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ይህ ብስጭታቸው እሳቸው እንደሚያስቡት አገር ሰላም መስሏቸው ይመስላል። በኪነ ጥበቡ፤ በታምራቱ ነው ያለችው ኢትዮጵያ እንደ ለመደባት።

ስለዚህ ጠ/ሚር አብይ አህመድ እዬተናደ ያለው መንፈስ ትንሽ ጥሪት እንኳን እዲቀር እዬሄዱ መጋጨት አይገባቸውም። አላስፈላጊ ቅራኔ ውስጥ እዬገቡ ነው። ማስፈራሪያው የተገባ አይደለም። ዲያስፖራውንም መናቅ አይገባም። ትልቅ ሃይል አለው።

አሁን ደግሞ እንደ ቀደመው ግለሰቦችን ሳይሆን እራሱን ያመነ እንቅስቃሴ ካደረገ ሞገዱ ችግር ነው … በቀደመው ጊዜ ፓርቲ ነን የሚሉት አፈና መከራ ነበር። አሁን ግን ሁሉም ነፃ ነው። እነሱ ምድር ላይ ነው እዬተፋለሙ ያሉት ለዚህ ይልቅ ይህ ለውጥ የተመሰገነ ይሁን … እቅም አለን ለሚሉ የግል ታጋዮች ሜዳውም ፈረሱም ነው …

የሆነ ሆኖ አሁን ሁሉም ነገር ስስ ነው። ሆድ ብሶታል ህዝቡ። 27 ዓመት የኖረበት መከራ አልበቃ ተብሎ የአሁኑ ደግሞ ህም ነው ጭካኔ። ብርቱ ጥንቃቄ ይጠይቃል። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ስልት ብለው የያዙት የቀደመው አላዋጣም።

ስለዚህ አዲስ ስልት ለመቀዬስ ቢሞከር እንኳን የተበላ ቁብ ነው። ስለምን የኦዴፓ አቋም ስለታወቀ። የአንድ ዕብድ ጉዳይ አይደለም። አገር የመመሥረት ጉዳይ ነው። ስለዚህ ቃ ብሎ በደረቀ ጉዳይ ላይ ማርጠብ ባይቻልም ቢያንስ ንግግር ላይ እንደ አገር መሪ መሆን ይገባል። መሪ ሲኮን ወጣትነት ሆይ! መንገድህን ያሰምርልህ ኮብልል ተብሏልና።

አማኑኤል ያበደውን ይግባ ከተባለ ኦዴፓን ያስገቡት። የአበደው ድርጅታችሁ ነው። ግንባሩንም የናደው ድርጅታችሁ ነው። እከሌ ተከሌ ሳይባል አማኑኤል ማስገባት ነው … አንግዲህ እስካሁን ባለው እኔ አቶ ካሳሁን ጎፌ ምን ሁኔታ ላይ አንዳሉ አላውቅም እንጂ ሁኔታው ወጥ እና ፓለቲካዊ ውሳኔ ከኢትዮጵአዊነት ጋር በተጻራሪነት የቆመ ነው። ይህን በመንግሥት ለማስፈጸም ዕድሉ ይሰጠኝ ነው ጥያቄዎት ሆነ ብስጭተዎት ሆነ ማስፈራራቱም ሆነ … ካዋጣ መብት ነው …

ብሄራዊ ግዴታ ያለባቸው ወገኖች ደግሞ ቆፍጠን ብለው ተጋድሎውን አህዱ ይሉታል። እስካሁን አልጀመርነውም። ስንጀምረው መራራ ነው። ጎምዛዛ ነው የሚሆነው ተስፋ ያደረገ ሃይል ተስፋውን ሲያጣ ከእርስዎ በላይ ብስጩ ነው የሚሆነው።

ያ ግልብጥ ብሎ ደግፎ የወጣው ሃይል ደግሞ መሰሉን ይፈጽማል። ነፃነት በችሮታ የሚገኝ ስላልሆነ … ከኢትዮጵያ በላይ የአብይ ሌጋሲ አይወደደም - አይከበረም  -አይደነቀም፤ ሁሉም ምንጩ እሷው ናት። እንዲከፋት እማንፈልጋት እማማ ኢትዮጵያ … ስለዚህ በዚህ ድርድርም የለም።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሆይ!

እንደ እኔ ወደ ራስዎት፤ ወደ ቀልበዎት፤ ወደ ሰብዕናዎት መመለስ፤ መጸለይ መጸለይ መጸለይ የእግዚአብሄርን የክብር ስጦታም አክብሮ መነሳት ይጠይቃል …

ኢትዮጵያዊነት በገፉት ልክ ተበቃይ አምላክ ያለው ማንነት ነው …. ኢትዮጵያዊነት ሲሶ እና እርቦነት አይደለም ሙሉነት እና መሆንነት ነው ኢትዮጵያዊነት። ቁስል አለብኝ እያሉ ኢትዮጵያዊነትን ማዜም በራሱ ፈተና ይመስለኛል …. ቂም አለበዎት በኢትዮጵያዊነት ላይ  … በአሁኑ ንግግርዎት የተረዳሁት እንደዛ ነው … „ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት“ ይሉታል አባው እና እመው …

ሌላው ከተፈለገ በኦነግ የበላይነት በስተቀር የባሰ ይገጥማል እያሉ በተደጋጋሚ እባከዎትን ስለመዳህኒተዓለም አያስፈራሩን። ኢትዮጵያ አምላክ አላትና … ከጭካኔ፤ ከአረመኔነት የሚጠበቅ ተስፋ ሳይሆን የመኖር ሞት ነው … ቀድሞ ነገር ምን መኖር መቼ አለና … ህዝብ ተከዝኖ በራብ እንዲያልቅ እኮ ተደርጓል።

የ66ቱ አብዮት ምክንያት ያ ነበር … መማር ከኖረ አወዳደቅን መሳመርም ብልህነት ነው። የኦነግ መንገድ ለኢትዮጵያዊነት የጽድቅ አስፓልት አለመሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን። ከተፈጥሮም ከሰብዕም የተጣላ መቼውንም ከራሱ ጋር የማይታረቅ ድርጅት ነው። 

ለነገሩ ለበታችነት ስሜት መፈወሻ መዳህኒቱ ሞት ብቻ ነው። ለዚህ ሁሉ መከራ አዲስ የዳመና ዘመን የዳረጋችሁን እናንተው ናችሁ። እንጂ አንዲት ቅንጣት መንፈስ ከልባሞች ኦነግ አያገኛትም ነበር። በስል ገብቶ ድል አደረገን። ፈነጨም። እግዚአብሄር ይይላችሁ፤ አነደዳችሁን አቃጠላቸሁን። 

በመዲናችም በይፋ አርማውን ተፈቅዶለት አውለበለበ። የሞትነው የዛን ቀን ነው። እንደ ቀደምቶቹ የአዲስ አበባ ወጣቶችም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። አንድ ቀን ቀኑ ሲያልፍ መታሰቢያ ይሰራላቸዋል …

ግን ኢትዮጵያ አምላክ አላት እና ፍርዱን ፍትሁን ከአንድዬ እንጠብቃለን። መታበይ አያበረክትም። ቁጣ በማንኛውም ሁኔታ ይከሰታል። የሆነ ሆኖ ቀሪውን ጊዚያችን ደግሞ ተረግመን የለም፤ አትሳቁ ተብለን የለ እንደለመደብን የበኩላችን እናደርጋለን … ድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ግሪደር ስንቃችሁ ይሁን ተብለዋልና። ስለ እነሱ ዝም አንልም፤ የሁሉም በረድ ተሸካሚዎች እነሱው ናቸውና …  


ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው!

·       ተጨማሪ ጥቂት የማነጻጻሪያ  መረጃ አባሪ። ሞራሉን አምጦ ለመውለድ እነዚህ ገመናዎች ይለፈ ይሚሰጡ አይመስለኝም። ማናቆ ናቸው እና። ህሊናም አለ ፈራጅም … ፈጣሪም አለ አዘቅዝቆ ይመለከታል።

ለማ መገርሳ በልዩ ሃይሉ ታግዞ፣ በጌድዮ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው፣ ዘግናኝ ግድያና ማፈናቀል አልጀዚራ አንደዘገበው።

የኦህዴድ/ኦዴፓ ሜዲያዉን የመቆጣጠር እርምጃ #ናኦሚን በጋሻው
ብአዴን(አዴፓ) ለሌላ ዙር መከራ አሳልፎ እየሰጠን ነው፡፡አዲሶቹ ተረኞች በሁለት እግራቸው ሳይቆሙ በፊት መላ ሊባል ይገባል
March 10, 2019
ብአዴን(አዴፓ) ለሌላ ዙር መከራ አሳልፎ እየሰጠን ነው፡፡አዲሶቹ ተረኞች በሁለት እግራቸው ሳይቆሙ በፊት መላ ሊባል ይገባል
March 10, 2019
ኦዴፓ የዘረጋው አመራር መዋቅር በአዲስ አበባ!
March 23, 2019
የተጀመርከው የብሽሽቅ ፖለቲካ እመነኝ የሚጎዳው ህዝባችንን አንድ ላይ ነው
March 7, 2019
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በሜኖሶታየኢትዮጵያ” (አካ ኦሮሚያ) ቆንፅላ /ቤትን መርቀው ከፈቱ (አያሌው መንበር)March 2, 2019
ለተማሩና ሐሳብ ላላቸው ዜጎች የብድር ሥርዓት ሊዘረጋ ነው

ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ህጋዊ መስመር የማስያዝ ስራ ከመቼም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል” – ወይዘሮ ሎሚ በዶ (የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ)
February 22, 2019
የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ከየካቲት 19 ቀን 2011 . ጀምሮ በሚያደርገው አራተኛ ዓመት ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ወደ ህጋዊ መስመር የማስያዙ ስራ የሚቀጥል እንጂ ወደ ኋላ የሚመለስ ጉዳይ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
/ አብይ /ቤትበኦሮሚያ ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም” – ግርማ ካሳ
የአቶ ለማ /ቤት
አቶ ለማን ማናገር አትችሉም
የኦሮሞ ክልል መሬት አስተዳደር
ቤታችሁ ከመፍረስ አይድንም። ልንተባበራችሁ አንችልም
/ አብይ /ቤት
በኦሮሚያ ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም
ይሄን ጊዜ የኦሮሞ ቡድኖች ቢሆኑ ኖሮ የመጡት ..እናንተው አረፍተነገሩን ጨርሱት
ቢቢሲ ከዘገበው የተወሰደ
ክምታደርገው ይልቅ የምትናረው ብዙ ርቀት ይጓዛል (ይኄይስ አእምሮ)
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94303“
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ላሉት ክፍት ቦታዎች 350 ሠራተኞች ተመልምለው እንዲሰለጥኑና እንዲቀጠሩ የሚመለከተውን ክፍል ያዛል አሉ – ከሁነኛ ምንጮች የሰማሁት ነው፤ በሚዲያም ተገልፆ ከሆነ አላውቅም፡፡ ትዕዛዙ የደረሰው ክፍል በአጭር ጊዜ ውስጥ ምልመላውን አካሂዶ 350 ሰዎችን ስም ዝርዝር ያቀርባል – የሰውነት ደረጃችሁን ያልሳታችሁ ጤናማ ወገኖቼ እንዳትደነግጡ እነዚያ ሰዎች ሁሉም ኦሮሞ ናቸው፡፡ የበላይ ማኔጅመንቱ ውስጥ የሰው ሽታ ያላቸው ጥቂት ርዝራዥ አሳቢ ሰዎች ኖረው መሆን አለበት “አይ፣ በዚህ የለውጥ ጊዜ ይህማ እንዴት ሊሆን ይችላልአየር መንገዱ እኮ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ነው፤ ከሁሉም ዜጎች በአዲስ መልክ ምልመላው ይካሄድና ይምጣ” ተብሎ ይመለሳል፡፡ እንዲያም ሆኖ ተሻሽሎ በቀረበው ዝርዝርም 350 170 በላይ የሚሆኑት ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ የገባንበትን አረንቋ እግዚአብሔር ያሳያችሁ፡፡ ወያኔዎች ጥቁር ውሻ ይውለዱ፡፡ አሜን ብለናል።
የሚኒስትሮች ሹመትሳይድበሰበስ! (ዮፍታሔ)
የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን አዲሱ መዋቅር የሹመት ዝርዝር:-
1. እናትአለም መለስ …ዋና ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
2. ነጻነት አለሙ…………ም/ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
3. ሳሙኤል ከበደ ……..ም/ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
4. ዮሚ ተመሰገን…….……..ም/ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
5. ካሳ ወ/ሰንበት…….. አማካሪ (ኦሮሞ)
6. ውብሸት ወልዱ……..ልዩ ረዳት (ኦሮሞ)

Ethiopia: ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማሳካት ቀን ከሌት እየሰሩ መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በአንደበታቸው አረጋግጠዋል፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=r75NnOoeZZA&t=63s

ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውን ቤንዚን አርክፍክፎ ያቃጠለው የኦዴፓ ጭንቅላት።

https://www.satenaw.com/amharic/archives/65399

ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙአቶ በቀለ ገርባ

 https://www.youtube.com/watch?v=ZYzLOYd_5OI&t=27s

የኦሮሚያና የፌደራሉ መንግስት ሊከሰሱ ይገባል - ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ | Ethiopia


Published on Mar 16, 2019





የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።