ውሃም የሜንጫ ቤተኛ ….
እንኳን ደህና መጡልኝ
ውሃም የሜንጫ
ቤተኛ ….
„ጥበብ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች“
መጽሐፍ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
24.03.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
እንዴት ናችሁ ውዶቼ ጥቂት ነገር አንድ ማሰተዋል ባለብን ጉዳይ የበለጠ ብልህነት መሰነቅ እንዳለብን
ትንሽ ማለትን ፈልግሁ …
· ቁጥር አንድ አሮማራ እና ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ …
ኦሮማራ ውስጥ በንቃት ከተሳተፉት ጦማርያን ውስጥ አቶ ስዩም ተሾመ አንዱ ናቸው። በኦሮማራ ጥምረት
ምን ትርፍ ምን ኪሳራ ተገኜ የዛሬ አጀንዳዬ አይደለም። ብቻ የዛ ቀዳሚ አቀንቃኝ የነበሩት አሁንም የሆኑት ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ
ማን ናቸው? የሚለውን የቤት ሥራ ልሰጣችሁ ነው … ለቅኖቹ ለውድ አንባቢዎቼ …
Ethiopia: [ነፃ ውይይት] የአዲስ አበባ ባለቤትነት እና የኦሮማራ ጥምረት
Published on Feb 27,
2019
ከዚህ ውይይት በሆዋላ ጠ/ሚር አብይ
አህመድ የዶር ገዱ አንዳርጋቸውን ሽኘታ ተገኝተው ጠቅላይ አዲሱ ርዕሰ መስተዳደር ዶር አንባቸው መኮነን
ወደ አንቦ ጎራ ብለው ያ የተጀመረውን የአስተኛኝ ኦሮማራን መንፈስ እንዲያድሱ ጥሪ አቅርበዋል።
ቀኑን ተመልከቱት ጦማሪ አቶ
ስዩም ተሾመ በየካቲት 27 ቀን 2019 ያደረጉትን ቃለ ምልልስ እሳቸው በመጋቢት 8 ቀን 2019 አጸደቁት ማለት ነው። አሁን
ትናንት ሳደማጥ ደግሞ ከትህትናም ወርዶ ይቅርታ እንዲጠዬቅ የሚል ዕድምታ አለበት …
Published on Mar 8, 2019
· ቁጥር ሁለት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ
ኦህዴድን በተመለከተ በአወንታዊነት ሲጽፉ ሲተነትኑ ነፍስ ያለው መልዕክት ሲያስተላለፉ ነበር ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደግሞ አቶ በቀለ ገርባ እና ፕ/ መራራ ጉዲና አስቸኳይ ጊዜውን ጥሰው ነቀምት ህዝብ ስብሰባ ሲሄዱ እሳቸው
ደግሞ መጠሞራቸውን ቀጠሉ።
እነ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ሲፈቱ ዜና ያላደረጉት ሚዲያዎች ሳይቀር ሲታገቱ ዜና አደርገው አራገቡት።
የለውጡን ጫና ይፈጥራል በመሃል አሽልከን እምናስገባው ሃይል አለ በሚል ይመስላል። ህግ ህግ ነው ተቀበልነውም አልተቀበልነውም። መኖራችን
እዛ ካደረግን ህግ ተላላፊነት ያሰቀጣል።
ዛሬ ነጋ ጠባ ጠ/ሚር አብይ አህመድ የሚያስበረግጋቸው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ጓዶቹ ወሎም፤
ጎንደርም፤ ጎጃምም ሄደው ነበር ያን ጊዜ። ግን ህዝብ አልሰበሰቡም። ካስተነገዷቸው ሰዎች ውጪ ጋጋታ፤ ኳኳታ፤ ሿሿታ አልታዬም። ቤተሰቦቻቸውን
ሄደው አዩ፤ ልጆቻቸው ያጡትን አጽናኑ። በቃ።
እስር ቤትም ተገኘተው አቶ ታዬ ደንዳኣን ጠይቀዋል። ይህ እንደ ማህበራዊ ኑሮ የሚታይ እንጂ
ህግ ተላላፊነት አልነበረም … ያን ጊዜ ህግ የጣሱት ዛሬ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ልዩ አማካሪዎች ናቸው … ያን ጊዜ ህግን ያልተላለፉት
ደግሞ መተንፈስም እዬታገዱ ነው።
አንድ ግዙፍ ብሄራዊ የሚደያ እና የፖለቲካ ድርጅቶችን ያሳተፈ ጉባኤ ቤተ መንግሥት ያካሄደው
ከእስክንድር እንቅስቃሴ ተፈርቶ ነው። ግን … አነቃነቀው … ያመዋል የኢትዮጵያ መንግሥት በጫና ከሚያጣድፈው ማህበረሰብ አንዲት ነፍስ
ብቅ ስትል … ሌላውም እንዲሁ።
ትናንት ደግሞ ይኽንኑ መርበተበትን በጠበንጃ ለማስከበር ፉከራ ቢጤ አዳምጫለሁኝ … ከዛለቀ ጥሩ ነው … ለዚህ ግብዕታ
ደግሞ ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች አሉ ልክ እንደ ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ ዓይነት … እና የኤል ቲቢዋ ልዕልት ቤትሻ።
በግራ ቀኝ የሚጣደፈው መንፈስ ማን እንደሆነ ልብ ላለን እናውቀዋለን። ይህን ብአዴንም ለሽ ብሎ
እንደማይመለከተው አስባለሁኝ። በአሮጌ በሬ አርሶ የተጠቀመ የለም እና። „ ለአማራ ባሬያ እንሆናለን“ ሞቶው ተመችቶናል እንደማለት።
ብቅ በሚሉ ሊሂቃን የሚደረገው የመብት ጥሰትንም ብአዴን አትኩሮት ሊሰጠው ይገባል፤ ባለሜንጫ መግለጫ ሰጪ ሲሆን እንደማለት
… የጠ/ሚር ቢሮ ባባለቤትነት ተቆርቋሪ እንደሚሆነው ሁሉ የ አማራ ልጆች ትጋታቸው ማዕቀብ ሲጣልበትም አሉላችሁ ማለት አለበት። ኢትዮጵያ የሁሉም ናት። የ ዓለምን ተክለ ቁመና የወንጌልን፤ የቁራን ተልዕኮ የደረመሰ መንፈስ ተሸክሞ ባለቤት ላጡ ነፍሶች ባለቤት ለሚሆን ብርጌድ ማሰለፍ የሞራልም ጥያቄ ነው>>
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ የአቶ በቀለ ገርባ እና የፕ/ መራራ ጉዲና እና የጦማሪ አቶ ስዩም
መስፍን አካሄድ ግን ያን አስቸኳይ ጊዜ የሚጣረር ነበር። እሳቸው የሚጽፉትን እኛ ሰላም አገር ያለነው ልናደርገው ስንችል እሳቸው
ገብተው ተቀረቀሩ። ያው አቤቱታችን ተሰምቶ ተፈቱ … ያ ግን አሁን አሁን ሳስበው ታልሞ የተከወነ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ፤፡ ሌላው
ቀርቶ ሱማሌ ላይ የነበረው ቀውስን አክሎ …
· ቁጥር ሦስት የአብይ ካቢኔ እና የጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ ቀልብ።
ከእስር እንደተፈቱ በቀጥታ የብዕር ጥቃት ያደረጉት በሙሉ መንፈስ ይደግፉት የነበረውን ኦህዴድን ተቃውመው ወጡ እሳቸው አቶ ስዩም ተሾመ። እሳቸው ያሰቡት ያን ጊዜ እስር
ቤት ሲገቡ ወደ ጠ/ሚር አልመጣም መሰል „ሰው ሰው የሚሸት መሪ ናፈቀኝ“ የሚል እድምታ ያለው ጹሑፍ አወጡ። በቀድሞው ፕ/ ባራክ
ኦባማ ፎቶ ታግዞ ህፃን ልጅ እያጫወጡ ነበር ፎቶው፤ ያን ጊዜ እንግዲህ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሰውኛ ጉዳይ ተጠምደው
የነበረበት ወቅት ነበር፤
ቀጥለው የእስራኤል አገር ታላቅ የፖለቲካ መሪ በመደበኛ የህዝብ መጓጓዣ ስለሄዱ እስኪ ለአገር
የሚያስቡ ከሆነ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በህዝብ መጓጓዣ ከህዝብ ጋር ተሳፍረው ሲሄዱ እንይ ብለው ሌላ ጹሑፍም አውጡ … እኔም ግርም
ብሎኝ ጻፍኩኝ … ፍላጎታቸው አልገባኝ ስላል። ወቅታዊም ሚዛን ደፊም አልነበረም ...
· ቁጥር አራት ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ እና የሰኔ 16ቱ ዕድምታ።
በዚህ ጉዳይ መኢህአድ እና ሌሎችም ወገኖች ለጠ/ሚሩ የምስጋና ቀን እናሰናዳ ብለው ሲዘጋጁ ጣልቃ
ይግቡ፤ ሃሳቡን እሳቸው ያንሱት የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ስላልሆንኩኝ ፍርዱን ለህዝብ ሰጥቼ ብቻ አባወራ ሆነው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጪ ሆኑ
… የተፈጠረው አደጋ እና ሁኔታውን ያው ህሊና ይፍረደው … እራሱ ሰልፉ ሲዛጋጅም የቀደመውን ተቃርኗቸውን ስለማውቅ ወዮልሽ አዲስ አባባ በዚህ ግብአተዊ ስልፍ ከታደምደምሽ ብዬ ጹሑፍ አወጣሁ።
ያም አሁን አሁን ሳስበው የበለጠ ተቀባይነትን ለማጉላት ይሁን ወይንስ
ሌላ ወፊቱ ትጠዬቅ … ወይ አጭር ኮርስ ተሰጥቷቸው ከሆነ ጦማሪ አቶ
ስዩም ተሾመ አቅጣጫውን ቢያመላክቱን መልካም ነው … ገል ይዛው እሳት ከጫሩ በኋላ ነዲዱን እያዬን ስለሆነ…
· ቁጥር አምስት ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ እና የኢነጂነር ስመኛው የነፍስ ፍጻሜ።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከህዝብ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ስለ አባይ ተጠይቀው „ ነገረ አባይ እስከ
10 ዓመትም አያልቅም „ብለው አሉ በሚል ደግሞ ሌላ የፌስ ቡክ ወጀብ ፈጠሩ … እናም ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ስሜን አሜሪካ
ሲያቀኑ ቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ደመከልብ ሆኑ፤ ጠ/ሚሩ ሲመጡ ደግሞ ጭጭ ብሎ ተዳፍኖ ቀረ።
… በመሃል አንድ ሰው ያለስተዋለው ነገር ስላለ እሱን ከድኜ አልፈዋለሁኝ … በዋዜማው የተፈጸመ
ጉዳይ ነበር ከጦማሪ ስዩም ተሾመ ጋር የሚይያያዝ ግን ቤተ መንግሥት ብቻ የሚያውቀው ስለሆነ ይከደን።
ስለምን ያ ሆነ ብዬ ሳስበው
ተደሞን ይጠይቃል፤ የእድምታ ባለሙያዎችንም ይማጸናል። መቸኮልም አያስፈልግም … በሁሉም ነገር ፈጣሪ አለበት እና የፈቀደው የወደደው
… ይሁን ያስቀረው …
· ቁጥር ስድስት ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ እና የምክትል ከንቲባ መኖሪያ ቤት ኪራይ
… ጣራነት
ይህ ደግሞ ሌላው ግራጫማ ተውኔት ነው። የምክትል ከንቲባው መኖሪያ ቤት ኪራይ ጣሪያነት አስመልክቶ
ተችተው ሲወጡ ሌላ ወጀብ ተነሳ … ኢንጂነር ታከለ ኡማ ደግሞ መልስ ሰጡ በዚህ ውስጥ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጉዳይም አለበት
… ከውለታ ይቆጠርልን ዓይነት… ለምን ይህ እንዲታወቀው ተፈለገ
…? ይመርምር …
· ቁጥር ሰባት ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ እና የ ባልደራስ እንቅስቃሴ ….
ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር የተደረገ ውይይት በተመሳሳይ ሁኔታ ጫሪ ሃሳቦችን በማነሳሳት
የመደመር ፖለቲካን የማጥራት ሂደት የተፈጸመበት ነበር። እሳቸው ያነሱት የአዲስ አባባ ውሃ ከ ሮምያ ስለሚመጣ ለዚህስ ልዩ ጥቅም
አያስፈልግም ወይ የሚል ነበር .. ጹሁፉን ጽፌው እርማት ስለቀረው ነው እንጂ ግርም ብሎኝ ጽፌ ነበር።
ይህም ሆኖ እዛው ላይ ሰፊ
ሀተታ አቅርቤያለሁኝ … ምክንያቱም ትግራይ ከጣና ነው መብራት እምታገኘው እና ትግራይ ለአማራ ክልል ቀረጥ መክፈል ይኖርበታል
ነው ዕድምታው። በዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሲታሰብ የተቃጠለ ነው።
በሌላ በኩልም የጉሮሮ ነገር ከተነሳ ትግራይ ከአማራ ክልል
ነው አብዛኛው ፍጆታ እምታገኘው፤ ስለዚህም የትግራይ ክልል ቀረጥ ትከፍል ዓይነት ነው … ብዙ ነገር ነው ያለበት በዬትኛወም ደረጃ እና ሁኔታ ያሉ ሊሂቃኑ እንዴት
እንደሚያስቡ ደግ ጊዜ ስለሆነ እየተፈታተሽን ነው …
Ethiopia:
[ነፃ ውይይት] “ልዩ ጥቅም ብሔር ማፅዳት እንጂ የመብት ጥያቄ አይደለም" እስክንድር ነጋ
Published on Mar 14, 2019
አሁን አዲስ አባባ በከፊል ውሃ እስከ ሦስት ቀን የላትም።
ምክንያት ለገዳዲ መስመር ስለተሰበረ። ከዚህ ጋር ሌሎች ማዕቀቦች እና ቀውሶችን እንጠብቃለን ማለት ነው …
ቀውስ መፍጠር ተልዕኮ ያላቸው ሆነው ነው እኔ ያገኘሆዋቸው።
እና ለመሆኑ ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ ማን ናቸው? ተልዕኳቸው ምንድን ነው? በተቃርኖ ውስጥ ያለ ሃሳብን በማንሳት እና
በማመሳቀል፤ በማሳቀልም፤ በመኮርኮር፤ በመጎርጎኢርም ማን እንዲያተርፍ ማን እንዲከስር እዬሰሩ ነው … ? ? ?
የዚህ ጹሑፍ ዓላማ እንወቃቸው ነው። ሥልጣን የተሰጣቸው
የሥልጣናቸው መሰመር ደግሞ በተሰውረ ሁኔታ የሚከውን፤ አቅም በማወጣት የደገፉበትን መሰሶ ተጠቅመው ሊኮስስ የሚጋባውን በማኮንሰስ
ሊጎላ የሚገባውን በማጉላት ግን በመሆን እና በማስመስመሰል ያለ የመሃል ሚና እዬተጫወቱ እንዳሉ ይሰማኛል …
· የኦሮምኛ ቋንቋ አገልግሎት እና የጦማሪ ስዩም ተሾመ ቅላጼ
·
Ethiopia: [ነፃ ውይይት] “ልዩ ጥቅም ብሔር ማፅዳት እንጂ የመብት ጥያቄ አይደለም" እስክንድር ነጋ
·
Published on Mar 14, 2019
በዚኸው ቃለ ምልልስ ያነሱት ዋናው ነገር የጳውሎስ ሆስፒታል አገልግሎት በኦሮምኛ ቋንቋ አገልግሎት
መሰጠት እና ኮሳሳ ዕድምታው ከልቤ ያሳቀኝ ጉዳይ ነበር። እንዴት እንደተበጁ ሁሉ ያስተዋልኩበት ነበር።
ቀድሞ ነገር ከአጀንዳም የሚገባ አልነበረም። የሆነ ሆኖ ከዚህ ቃለ ምልልስ በሆዋላ ደግሞ የነጠረ
ከናዚዝም በላይ የሆነ ገመና ዓለምን ሊያፋልስ የሚችል፤ የተባበሩት መንግሥታትን፤ የአፍሪካን ህብረት፤ የአውሮፓን ህብረት፤ አምኒስተ
ኢንተርናሽናልን፤ ቀይ መስቀልን፤ ለሰብዕዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑ ድርጅትን የሚያፍረስ አልፎ ተርፎ ቁራእንና ቅዱስ ወንጌልን የተዳፈረ
የአቶ በቀለ ገርባ የቋንቋ ደመነፈስ ፍልስፋና ደግሞ ዓይኑን አፍጥጦ ወጣ።
ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙ – አቶ በቀለ ገርባ
March 23, 2019
ክቡር ጠ/ሚር አብይ አህመድም ይህን እናስታምም ዘንድ፤ ይህን እንሸከም ዘንድ ቆፍጠን ያለ ትዕዛዝ
ሰጥተዋል። እቦታው ሄደንም ተጎድታችሁዋል ብለን ድንጋይ ተሸከምን እንለምን ዘንድ መመሪያ ሰጥተዋል። ለማሰተዛዘኛም ትግራይንም
አክለዋል።
ግራ ቀኛችን ተገፍተን የኖርን ነን፤ ብሶተኛ
ነን፤ ከፍቶናል ይሉና ወዮላችሁም አለበት፤ ዋና ኢላማቸው ያው የእስክንድር ንቅናቄ ነው ሥልጣኑ ከበረከተላቸው … እኔ የዓለም
ጦርነት ያስነሱ ሳቢያዎችን እንደገና በምልሰት አብሶ የፈረንሳይን አብዮት ቢመረምሩት መልካም ይመስለኛል … እርግጥ ነው በዚህ ጉዳይ እመለሰበታለሁኝ።
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በአዲስ ወግ ማጠቃለያ ላይ ያደረጉት ንግግር
March 23,
2019
ውዶቼ ይህን እንድታዩልኝ እምፈልገው የግራ ቀኙን ሊንክ የሚያይዘው ይህ መንፈስ ሆኖ ነው እኔ
ያገኘሁት። ሰባራ ገል ይዞ እሳት ለመጫር ይሄድና መንፈሱ … እሳቱን ፍሙን ይረጫዋል ከዛ አይዋ ወጀብ ይመጣ እና ይነጠዋል … አገር ምድሩን ያዳርሰዋል? ግራጫማ ሰብዕና ቤተኛነት። ወይንም ሲቃዊነት ...
· ማያያዣ ወይንም ማጣፈጫ።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሚያድነቋቸው፤ ከሚያከብሯቸው ሰዎች ውስጥ አንድም የአማራ ሊሂቅ፤ ጋዜጠኛ፤
ታዋቂ ግለሰብ፤ ጦማሪ፤ ተሟጋች የለም። ሚደያቸው OBN አንድም አማራ አክቲቢስት፤ ጋዜጠኛ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጎ አያውቅም፤
የኢትዮጵያን ብሮድ ካስት ጨምሮ። የአማራ ማስ ሚዲያ ግን ሁሉን ተሸከም ተብሏል። በጃዋርውያኑ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አማካኝነት ስለሚመራ ...
አንድ አፍታ ሚዲያ ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ ወደ ሚዲያው ብቅ ከማለታቸው በፊት ከጋዜጠኛ፤ እና
ከጸሐፊ እንዲሁም ከአክቲቢስት ሙሉቀን ተስፋው ጋር ቃለ ምልልስ ማድረጉን አዳምጫለሁኝ። እርግጥ ከዛ ላይ አንድ ብልህ ነገር ተነስቶ ለብ ባለ ሁኔታ ምለስ ሲሰጥ፤ አሃ አሰኝቶኛል።
የሆነ ሆኖ እሳቸው ሚዲያውን ከተቀላቀሉ በኋላ ግን አይታሰብም።
እንዲያውም አፋቸውን ሞልተው ጽንፈኛ ሲሉ ነው እማዳምጣቸው። „ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ“ እንዲሉ …
· ግን ማናቸው ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ …
ከሳቸው ቁስቆሳ በኋዋላ የሚሆኑ ሁነቶችን በጥሞና በማዬት እናም የሃይል አሰላለፍ ማስተካከል
የሚገባ ይመስለኛል። አሁን ኤል ቲቢ ልዕልት ቤቲ ያለችበትን ደረጃ አወቅን፤ እሳቸውንም እንወቅ ነው መሰረታዊ ጉዳይ …
የሚገርመው
እንደ ጦር የሚፈሩት ነገር አለባቸው ያ ያስስባቸዋል … የበታችንት ስሜትን ማስለቀቅ የሚቻለው በምን ይሆን? አንድ የምርምር ማዕከል የሚያስፈልግ ይመሰለኛል … ቤተ መንግሥቱንም ይዘው ነው እንዲህ ብል እንደበላው ጨርቅ ብትክት የሚሉት …
ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ የቲም ለማ መንግሥት ጸንቶ እንዲቀጥል ይፈልጋሉ፤ ሲፈልጉ ግን የኢትዮጵያ
ህዝብን የእንቅልፍ መርፌ በመስጠት ነው … አብሶ ኦሮማራ በተቀለደበት ልክ እንዲቀጠል ህልማቸው ነው። እሱ ኦነግን ለሥልጣን አብቅቶ
እንደ ኢሠፓ፤ እንደ ቅንጅት መራራ ስንብት አድርጓል … ኦሮማራ?
ጠቅላላ ቀወሶችን በመኮርኮር እና በመቦርቦር ልዩ ሚና ያላቸው ይመስለኛል። እንዲህ ዓይነት ሰብዕና
ደግሞ አደጋው ሰፊ ነው። ሲገድለን የኖረ ነውና። በመታመን እና መታመንን በመቀበል እረገድ በመሆን ብሌን እንጭጭ ነው ፖለቲካችን ሲፈተሽ አደጋው ትወልድ እዬነቀለ መጓዙ ነው ...
እኔ እራሱ በሳቸው
መታሰር ጠንከር ያለ ጹሑፍ ጽፌ ነበር … ህግ መጣሳቸውን ሳላነሳ … ያን ይቅር ብዬ ማለት ነው … እንዲህ ባለጣምራ ሜዳሊያ ባለቤት
መሆናቸውን ፈጽሞ አልተጠራጠሩክትም ነበር። ቅን ሰው የፊቱን እንጂ የጥርጣሬ አድማስን ሲያሳክክ አይገኝም።
አሁን እኔ እማያቸው ልክ እንደ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ነው … የዚያ ቡድን አባል ሆነው
ነው እኔ እያዬሆዋቸው ያለው። መረጃም ያገኛሉ፤ መረጃውን ደግሞ አንዘርዝሮ አደጋ ያልተደመረውን ወገን አጋልጦ የመስጠት ሂደት ነው እኔ እያስተዋልኩኝ ያለሁት።
በዚህ ስሌት ስሄድ የለጋዳዲው ውሃ መታገድ ከዚህ ጋር ሳያው፤ ይህን ተቃውሞ ለሚወጣው ደግሞ
በቅድሚያ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የቆሞስ ስመኘው መበቀለ ዕጣ ፈንታ እንዳይመጠ ስጋቴ ሰፊ ነው፤ በሌላ በኩል የአዲስ አባባ ህዝብን ለሌላ ሰቆቃ የሚሸልም
ቀውስ አማራችም ነው። ይህን ጉዳይ የ አዲስ አባባ ህዝብ በዝምታ አያዬውም። ብልህ ህዝብ ነው። ህብር ቀላማም ህዝብ ነው። አስኳልም ነው ለ ማናቸውም አገራዊ ሆነ ሉላዊ ጉዳይ።
እንዲህ ሲሉ ይጀምራሉ ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ „የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ከገፈርሳ እና ከለገዳዲ አዲስ 350 ሺህ ኪዩብክ
ታገኛለች … እነዚህን ውሃ የምታገኘው የገፈርሳ ውሃ ግድብ አለ ከሌገዳዲ አለ ሌላው ደግሞ ከኦሮምያ ክልል አካባቡ ዙሪያ …“
በሞቴ ውዶቼ ጨርሻችሁ አዳምጡት … እና ምስላቸውን ተመልከቱት። ከውስጣች የሚንተከተክ ጉዳይ አለበት። መንፈሳቸው እርጋታ ነሳው ...
„ከዚህም የአገልግሎት ክፍያ አዲስ አባበ ያገኛል“ ወዘተ ወዘተ … እኔ የለገዳዲን ውሃ ቧንቧ መሰመር ተበላሽ የተባለው ከዚህ አንጻር ነው የማዬው
… ያታቀዱ ነገሮችን እሳቸው አፍታቶ አስታኮ ያቀርባሉ፤ በሚያገኘው ግብረ ምላሽ እርምጃ ይወሰዳል።
ስለሆነም እኒህ ሰው ማነ ናቸው? ምንስ ነው ፍላጎተቻው? ተልዕኮው ምንድ ነው? የየትኛው የመንግሥት አካል ባልደረባ ናቸው የሌሊቱ ቢሯቸው የት ይሆን የቀኑን እያዬን ስለሆነ? ምን ስውር ተልዕኮ ተሰጣቸው? መደበኛ ሥራቸው ይህ ብቻ ነው ወይ? ከመደበኛ ሥራቸው እንደለቀቁ አዳምጫለሁኝ።
ሁሉን አደብ ገዝቶ መመርምር ያስፈልጋል። ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ
አዲስ ባለሥልጣን እንደሆኑ ነው የሚሰማኝ … ግን ያለተገለጠ፤ ያልተነገረ እንዲህ ዓይነት ባለሙያዎች አሉ … የዘመን ፈተናዎች ...
በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነፍስ አንዲት ነገር ቢከሰት ከዚህ ሰው እራስ መውረድ አይቻልም …
የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ጉዳይ በማስተዋል እንመርምረው …
ቅኖቹ ከልባችሁ ሆናችሁ ቃለ ምልልሱን አዳምጡት … የለገዳዲ ውሃ እና ጥማት የታወጀበት መሰንስኤው። ደግሜ ዳጋግሜ እምለጥፈው የቤተ መነግሥቱ ተከታታይ ጉባኤ የኦነግ ፍላጎት ደንቀራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ነው። ለዚህ ደግሞ የፊት ለፊቱ ኢላማ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ጓዶቹ ናቸው።
የለገዳዲ የውሃ መስመር ላይ ስብራት ደረሰ
„አዲስ አበባ መጋቢት 14/2011 ከለገዳዲ አዲስ አበባ ከተዘረጉ ሁለት የውሃ መስመሮች አንደኛው ትናንት ምሽት መሰበሩን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ።“
Ethiopia:
[ነፃ ውይይት] “ልዩ ጥቅም ብሔር ማፅዳት እንጂ የመብት ጥያቄ አይደለም" እስክንድር ነጋ
Published on Mar 14, 2019
ከዚህ ቃለ ምልልስ በኋዋላ ነው የለገዳዲ ውሃ መተላለፊያ ተሰበረ የተባለው … ወደ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው የተገነባው ግድቡ … ለመሆኑ የኢትዮጵውያን ሃብት ጠጠር ነውን? ከመሬት የታፈስ ወይንም ከጓሮ የተሸመጠጠ የጌሾ ቅጠል … ነውን?
· ማጠቃለያ።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጉዞ ላይ ሲሆኑ ቃጠሎ፤ ግድያ ይፈጸማል። ከጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ መንፈስ ቃል ሲወጣ ደግሞ ቀውስ ይቀጥላል … ትርፍና ኪሳራው ይመዘን። እኒህን ሰውም እንመርምር እዬተሸከምን ላይ እያወጣን ነው ራሳችን እያጠፋን ያለው … ልክ በዘመነ ወያኔ ሪፖርትር ሲከውን የነበረውን ነው በፌስ ቡካቸው
ሲከውኑ የባጁት፤ አሁን ደግሞ አንድ አፍታ ሚዲያ ላይ ናቸው ያሉት።
አንድአፍታን እንጠርጥረው እያልኩኝ አይደለም ለመጀመሪያ ጊዜ ሳብስክራይብ ያደረግኩት ሚዲያ ነው። ግን የሚያሳትፋቸው ሰዎችን ተክለ ፍላጎት ከመሰረቱ መመርምር ይገባል። ስንት ጊዜ እንጠቃ?
· እኔ እንግዚአብሄርን ከመቼውም በላይ አመሰግነዋለሁኝ።
አላዛሯ ኢትዮጵያ ተሸክማው የኖረችው መከራ ምን እንደ ነበር አደባባይ ላይ አሁን ተዘርግቷል። ጠፍጣፋውም፤ ሞላላውም፤ ዝንቁም፤ ቅይጡም፤ ድንብላሉም፤ ዝቃቅቤውም፤ ኮረሪማውም፤ እንክርዳዱም፤ አርቲውም፤ ስንዴውም፤ ድንብልብሉም፤ ቀስቱም፤ ሸክላውም ሁሉም አንድ ላይ ነበር
እስተ ዛሬ።
አሁን ግን ጊዜደጉ በአንድ ማዕዶት ማንዘርዘሪያ ሰጥቶ እያዬን ነው። ብዙ ፕሮፖጋንዲስት አስፈለጊ አይመሰለኝም። ሁሉም
መሬት
ላይ
እዬተፈታተሸ
እዬተፈተሸም
ስለሆነ።
የሚገርመው ባለ ከረባት እና ገበርዲኑ ሁሉ ፈሪ መሆኑን ነው።
ዛፍ በተንኮሻኮሸ ቁጥር ሲባትቱ ውለው የሚያድሩት አገር እንመራለን ብለው ሲያታክቱን የባጁት ሁሉ አዬናቸው። ዓይን አያይም፤ ጆሮ አይሰማም አይባልም። ያልተለካ፤ የላተሰፈረ፤ ያልተመዘነ አንዳችም ሊሂቅ የለም። ይህን
ደግፎ የወጣውም፤ ይህን ተቃውሞ የወጣውም እውነት መስሎት አብሮ የነጎደውም፤ ሁሉም ሜዳ ላይ ተገናኝቷል።
ለዚህ ትልቅ ምሳሌ የሚሆኑት
የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አካል የሆኑት አቶ ነአምን ዘለቀ ናቸው። ፈተሹ ብዙ አቅም ካፈሰሱ ከደከሙ በኋዋላ ደግሞ በቃኝ አሉ። ሌላም ከ አገር ገቢ ወደ ውጭ ተመላሽም ይኖራል .. እናያለን ... ዓይናችን እስኪታክተው ድረስ።
የሆነው ሁሉ የሚሆነው ሁሉ ለመልካም እና ለበጎ ነው። ይህ መልካም እና በጎ ነገር የሚያመለክተን ደግሞ አላዛሯ ኢትዮጵያ እግዚአብሄር ያላት ስለመሆኑ ነው። ባቡሩ ይሄዳል ስንክሳሩ ተንጠባጥቦ ይቀራል፤ ከመከራ ጀርባ ሁልጊዜም ክብር አለ። ያለዬነውን አዬን። በምኞት ተስክሮ ስንቀጣቀጥ
የባጀንበትንም አውራ ጉዳይ አዬን። ዕውነት ራሷ ታድን ዘንድ ንቅናቄ ላይ ናት …
ዕውነት ያሸንፋል!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ