መቼ ይሆን ደግሞ አዬር መንገድ ዬንጥር ባህርዳር ጉዞ እንዳያደርግ ዬሚታገተው????

 

መቼ ይሆን ደግሞ አዬር መንገድ ዬንጥር ባህርዳር ጉዞ እንዳያደርግ ዬሚታገተው???? ……
"አቤቱ ፀሎቴንም ስማ ልመናዬንም ቸል አትበል።"
(መዝሙር ፶፬ ቁጥር ፩)
 

 
በጭካኔ በሰለጠኑ፤
• በበቀል በተነከሩ፤
• በቂም በበቀሉ፤
• በጥላቻ በተዘፈዘፉ፥
• በበታችነት ስሜት ወፈፍ ባሉ፥
• በህሊና አቅም ማነስ በሚባትቱ፤
• በአንጃ ግራንጃ ግንዛቤ ዬሚውተረተሩ፤
• በተለጠጠ ፍላጎት አገር ያህል ቁምነገር በከንቱነት ዬሚመሩ ዘመነኞችን ለመታገል _ መበሳጨት _ መጣደፍ _ መንቦጅቦጅ _ ሱሪ በአንገት አያዋጣም።
• ብዙ ነገር ዬተፈጠርንበትን ባዕት፤ ዬዘር ሐረግ፤ ዬአልረገጥም ጽኑ አቋም እና አሻምነት ባይመቻችሁ እንኳን በጣም በርቀት ዬሚታዩ ዕሳቤወችን እህ ----- ብሎ ማድመጥ ይገባ ነበር ቤተ ሰለሞን ላይ ከሊቅ እስከ ደቂቅ አላችሁ። ግን ዓለማችን ዬጆሮ ገብያ አልከፈተች። በስልተ ቢስ እሰጣ ገባ፤ በግርግር ፖለቲካ፤ ወዳጅ እና ተቀናቃኝን ባለዬ ዬዝንቅ ጉዞ ባዶ እጅ እዚህ አደረሰ።
• ዛሬን ለማዬት ተስኖ አዳዲስ አዛይ ዕሳቤወችን እዬፈጠሩ ዬናዷችሁን አክ ብላችሁ ዕውነት - ሃቀኝነት - መርህ እና ዬትግል ታማኝነት ዬት ላይ እንዳለ መዝኖ መወሰን ይጠይቃል። አሁንም ለግብር ዬሚጠራው ማን እንደሆን አስተውላለሁ። በማን መሪነት? ምን አለን? ማን አለን? ነገስ ለማን - ልዕልና ይታሰብበት። ብቻውን ዬቆመው ዬአማራ ህዝብም ይሰብበት።
• ወደ ባህርዳር ጉዞ ዬሚታገትበት ዘመን ሊመጣ እንደሚችል እሰቡት። መታገት ዓይነቱ ብዙ ነው። ሁሉም እስረኛ እንደሆነ ይሰማኛል። ለዚህ ደግሞ መንገዱ ዬእስራኤሎች ጽናት እና ጥበብ ይመስለኛል። መሪ ማውጣትም ይለመድ። ፋክሩ ይቁም። እማዬው ነገር ስላለ።
#የጣቶቼ ፍቅረኛ የጠይሟ ዕንቁዬ ዬባርች። ታላቅ እህቴም እንዲሁ ትወደዋለች።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/03/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።